uz
Feedback
አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም

አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም

Kanalga Telegram’da o‘tish

ያፈቀረን ማሳቅ ለኛ ኖርማል ነው አያሳስብም😉 #Join ያርጉና የትም ባልተሰሙ ቀልዶቻችን ፈታ እያሉ በውብ የፍቅር ቃላቶች ይደመሙ😍 ዘፈን ግጥም ጠቃሚ ምክሮች... ከቻልክ❤️ ፍቅርን ተናገር፣ኑር! ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን 👉 @just_811 👉 @get_Mu Please😊Don't Leave ችግር ካለ አናግሩን

Ko'proq ko'rsatish
9 631
Obunachilar
-524 soatlar
-357 kun
-8630 kun
Obunachilarni jalb qilish
Okt '26
Oktabr '26
+3
0 kanalda
Sentabr '26
+160
0 kanalda
Get PRO
Avgust '26
+211
1 kanalda
Get PRO
Iyul '26
+232
2 kanalda
Get PRO
Iyun '26
+235
0 kanalda
Get PRO
May '26
+225
1 kanalda
Get PRO
Aprel '26
+200
0 kanalda
Get PRO
Mart '26
+241
0 kanalda
Get PRO
Fevral '26
+244
1 kanalda
Get PRO
Yanvar '26
+264
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '25
+252
2 kanalda
Get PRO
Noyabr '25
+286
1 kanalda
Get PRO
Oktabr '25
+171
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '25
+275
1 kanalda
Get PRO
Avgust '25
+296
1 kanalda
Get PRO
Iyul '25
+319
0 kanalda
Get PRO
Iyun '25
+281
0 kanalda
Get PRO
May '25
+368
2 kanalda
Get PRO
Aprel '25
+264
1 kanalda
Get PRO
Mart '25
+288
0 kanalda
Get PRO
Fevral '25
+256
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '25
+306
2 kanalda
Get PRO
Dekabr '24
+275
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '24
+275
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '24
+194
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '24
+168
1 kanalda
Get PRO
Avgust '24
+135
0 kanalda
Get PRO
Iyul '24
+218
0 kanalda
Get PRO
Iyun '24
+215
0 kanalda
Get PRO
May '24
+188
0 kanalda
Get PRO
Aprel '24
+288
0 kanalda
Get PRO
Mart '24
+301
2 kanalda
Get PRO
Fevral '24
+359
1 kanalda
Get PRO
Yanvar '24
+284
2 kanalda
Get PRO
Dekabr '23
+213
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '23
+253
1 kanalda
Get PRO
Oktabr '23
+218
2 kanalda
Get PRO
Sentabr '23
+250
0 kanalda
Get PRO
Avgust '23
+286
0 kanalda
Get PRO
Iyul '23
+493
0 kanalda
Get PRO
Iyun '23
+445
0 kanalda
Get PRO
May '23
+428
0 kanalda
Get PRO
Aprel '23
+337
0 kanalda
Get PRO
Mart '23
+348
0 kanalda
Get PRO
Fevral '23
+335
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '23
+468
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '22
+532
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '22
+545
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '22
+326
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '22
+291
0 kanalda
Get PRO
Avgust '22
+263
0 kanalda
Get PRO
Iyul '22
+297
0 kanalda
Get PRO
Iyun '22
+217
0 kanalda
Get PRO
May '22
+201
0 kanalda
Get PRO
Aprel '22
+188
0 kanalda
Get PRO
Mart '22
+230
0 kanalda
Get PRO
Fevral '22
+141
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '22
+138
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '21
+82
0 kanalda
Get PRO
Noyabr '21
+118
0 kanalda
Get PRO
Oktabr '21
+203
0 kanalda
Get PRO
Sentabr '21
+166
0 kanalda
Get PRO
Avgust '21
+207
0 kanalda
Get PRO
Iyul '21
+277
0 kanalda
Get PRO
Iyun '21
+253
0 kanalda
Get PRO
May '21
+141
0 kanalda
Get PRO
Aprel '21
+233
0 kanalda
Get PRO
Mart '21
+241
0 kanalda
Get PRO
Fevral '21
+241
0 kanalda
Get PRO
Yanvar '21
+252
0 kanalda
Get PRO
Dekabr '20
+3 407
0 kanalda
Sana
Obunachilarni jalb qilish
Esdaliklar
Kanallar
01 Oktabr+3
Kanal postlari
 ♥️ ፅናት ♥️...!!!      .      . 🥀..ክፍል 24..🥀 . . . ከዛ በቃ በቃ በል ና ፅናትን ተሸክመክ መኪና ውስጥ አስገባት በፀሎትዬ በይ ነይ አንቺም ብላቸው መኪና ውስጥ ካስገባቻቸው በኋላ መጣው ብላ ፎጣ እና ለፅናት ልብስ ይዛ ተመለሰች። ሹፌሩም መኪናውን እየጋለበ ሀኪም ቤት በሩ ላይ አደረሳቸው። ሊባኖስ ከመኪናው ወርዳ ቶሎ በሉ ቃሪዛ አምጡ ፍጠኑ በሉ በሉ ቶሎ በሉ አለች።ነርሶች ተሯሩጠው ፅናትን ቃሪዛ ላይ አረገው ወደመታከሚያ ክፍል ወሰዷት ሊባኖስ እስከተወሰነ መንገድ ተከተለቻቸው።ከዛ ግን መታከሚያ ክፍሉ ጋር ስትደር እንድትገባ አልተፈቀደላትም "ምክያቱም ምንም ነገር ላይ ገደብ አለው። መሄድ እማንችለበት ነገር ወይም ጉዳዮች አልያም መስመሮች አሉ። ሊላው ሰው ሊድን ሊሎቹ ደሞ ሊያድንኑ አንድ ቦታ ሲሆኑ ታማሚው እንዲድን ደሞ ከአዳኖቹ ይበልጥ የሚፈልጉ ሰዎች እዛ ስብስብ መሀል መገኘት የማይችሉበት ነገሮች ይፈጠራሉ። ይገርማል!" አለች ሊባኖስ ፊት ለፊቷ የተዘጋባትን በር እያየች። ወዲያው በፀሎት እና ሹፌሩ ወጡ። ሊባኖስ ኮቴያቸውን ሰምታ ዞረች። ከዛም ወደ በፀሎት ተጠግታ አቀፈቻት። በፀሎት እና ሊባኖስ ተቃቅፈው ደቂቃዎች አለፉ።ያለ ምንም ንግግር ያለ ምንም ትንፋሽ።ከቆዩ በኋላ ሊባኖስ "በቃ በቃ ይበቃል ፈጣሪ ይህንን አይወደውም የኔ ሚጢጢ ጠንካራ ናት ምንም አትሆንም በቃ ነይ በፀሎትዬ ነይ አንተም ና አለች ሹፌሩንም ከዛ ወደ ሀኪም ቤቱ በረንዳ ላይ ሆነው ብዙ ሰአታት አስቆጠሩ በፀሎት እህቷን ልታያት ፈልጋ ነበር ግን ሊባኖስ ሀኪሞቹ ያሉትን መስማት እንዳለባቸው ነግራት ከለከለቻት። ሹፌሩ መኪና ውስጥ ቁጭ ብሎ ነበር።እና ለሊባኖስ እና ለበፀሎት ሊባኖስ ካዘጋጀችው ፎጣ አምጥቶ ሰጣቸው ሊባኖስ እና በፀሎት ለሁለት ለብሰው ቁጭ አሉ።ከዛም ፅናትን ሊያክሟት ከገቡት ዶክተሮች መሀል አንደኛው መጣ። ሊባኖስ ዶክተሩን እንዳየችው ወደ እሱ እሮጠች። ዶክተሩም አይቷት ቆመ። ሊባኖስ የዶክተሩን አይን አይን እያየች "ዶክተር ቅድም የገባችው ታካሚ እንዴት ናት? " አለችው።ዶክተሩም "አሁን ላይ ምንም ማለት አንችልም ነገ የምርመራ ውጤቱ ሲደረስ ነው የምናውቀው እናንተ ግን ተረጋጉ ይህ ለእሷም ለእኛንተም  አይጠቅማችሁም"አለና ጀርባዋን መታ መታ አረጓት ሄደ። ሊባኖስ ለትንሽ ሰከንድ ባለችበት ቆማ ቀረችና ወደ በፀሎት እና ሹፌሩ ጋር ተመለሰች። በፀሎት "ሊቦቲ ምን ምን ሆነሽ ነው የት ሄደሽ ነው? " አለቻት።ሊባኖስም ጋቢውን ከበፀሎት ጋር ለመጋራት እየለበሰች "አይ በሚጢጢዬን ሊያክሟት ከገብት ዶክተሮች አንደኛውን አይቼው ስላለችበት ሁኔታ ልጠይቀው ነበር የሄድኩት" አለች። በፀሎት የሊባኖስን እጅ አጥብቃ ይዛ ሙሉ ለሙሉ ወደ እሷ ዞራ "እና ምን አለሽ ሊቦቲዬ ንገሬኝ እባክሽ ጭንቅላቴ ሊፈየዳ ነው"አለች።በለቅሶ በተዘጋው ድምጿ። ሊባኖስም "ደና ናት ነው ያለኝ አትጨነቂ እሺ" አለቻትና ወደ ደረቷ አስጠግታ አቀፈቻት።በፀሎትም ሊባኖስ ደረት ላይ ልጥፍ አለች።ሊባኖስም ወደ ሹፊሩዋ ቀና ብና እንዲሄድ ምልክት ሰጠችውና ሄደ። ሊባኖስም በፀሎትን ነይ በቃ ወደ ውስጥ እንግባ ብላ ወደ ሀኪም ቤቱ ገቡ።ፅናት ወደ ተኛችበት ክፍል ሄዱና። ከክፍሉ ትይዩ ካለው ወንበር ላይ ተቀመጡ። የሆነ ሰአት ላይ እንደተቃቀፉ ከ ለሊቱ 9 ሰአት አከባቢ እንቅልፈ ወሰዳቸው። ንጋት ላይ ተቃቅፈው ከተኙበት እንቅልፍ ላይ ያባነናቸው የትናትናው ዶክተር የጎረነነ ድምፅ ነው "ደና አደራቹ " ሲል ነው። በፀሎት "ደና ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን " አለች። ሊባኖስም "እንዴት አደርክ ዶክተር" አለች። ዶክተሩም "ደና ደና ስለ ታካሚ ፅናት ለማውራት ፈልጌ ነበር ከ 2 ሰአት በኋላ ቢሮ ኑ እና እናወራለን አሁን ፅናትን ወደ ማገገሚያ ክፍል ልትወሰድ ነው አሁን በሰፊው እሷን ማግኘት ትችላላቹ።" ብሏቸው ፅናት ወዳለችበት ክፍል ገባ።  ትንሽ ቆይተው ነርሶች ፅናትን ደግፈው ለሊት  ላይ ከገባችበት ክፍል ደገፈዋት ወጡ። ሊባኖስ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ወደ ፅናት 1 እረምጃ እያለች ቀርባ ፅናት ጋር ደረሰች "የኔ ሚጢጢዬ የኔ ልእልት ደና ነሽ" አለች። ፅናትም "ደና ነኝ ደና ነኝ አታሰቢ ሊቦዬ " አለችና እህቷ ጋር ደርሳ "እህቴ" አለቻት። በፀሎት ከተቀመጠችበት ተነስታ "የኔ ውድ እህት የእኔ ልዩ" ብላ እጆቿን ዘረጋችላት። ፅናትም ከ ክንዶቿ ላይ የነርሶችን እጅ አስለቀቃ እህቷ እቅፈ ውስጥ ገባች። በፀሎት እህቷን በደንብ እቅፍ እያረገቻት "አስደነገጥሽኝ እኮ እህቴ አሁን ደና ነሽ?"  አለቻት። ፅናትም "አታስቢ የእኔ ልዩ እህት አሁን ደና ነኝ እሺ" አለቻት ሳመቻት። አንደኛዋ ነርስ "በቃ አሁን ማረፍ አለባት" ብላ ይዛት ሄደች። ሊላኛዋ ነርስም በፀሎትን "በቃ ተረጋጊ እህትሽ ደና ናት" አለችና ወደ ፅናት እና አንደኛዋ ነርስ እሮጥ ብላ ደርሳባቸው የፅናትን ሊላኛውን ክንዷን ያዘቻት ደግፋም ወደ ማረፊያ ክፍሏ ወሰዷት። ማረፊያ ክፍሉ ውስጥ አስገብተዋት አልጋው ላይ በጀረባዋ አንጋለው አስተኝዋት። ሊባኖስ እና በፀሎትም ፅናት ከተኛች በኋላ መጡ። ነርሷም "በቃ  አሁን እዚህ ብትሆኑም ታካሚዋን ማድከም ነው።አሁን ዶክተሯ ስለሚመጣ አታስቡ። ቁርሳችሁን በልታቹ ሻይ ቡና ብላቹ ትመለሳላችሁ " አለች። አልተቃወሟትም ሊባኖስ ከ ሀኪም ቤቱ ወደ ሹፌሩዋ በፀሎትን ደግፋ ከሄደች በኋላ ወደ ሹፌሩ ሄደች። ሹፌሩ መኪና ውስጥ ተኝቷል።ሊባኖስ አንኳኩታ ጠራችው።እሱም ተነሳና የኋላ በሩን ከፈተላቸውና በቅንድቡ ሰላምታ ሰጣቸው። ሊባኖስም "ደና አደረክ ጎረምሳው በል እዚ አከባቢ ጥሩ ምግብ ቤት ውሰደን" አለች። እሱም እሺታውን ሰጥቶ ወሰዳቸው። ሊባኖስም 2ቋንጣ ፍርፍር እና 3ሻይ አዛ ቁርሳቸውን በሉ። አሁን ዶክተሩ የቀጠራቸው ሰአት ደርሷል ከምግብ ቤቱ ወጥተው። አሁን ዶክተሩ ቢሮ ለመግባት በሩ ላይ ናቸው። ሊባኖስ አንኳኳች። ዶክተሩም ይግቡ አለ። ሊባኖስ እና በፀሎት ሲገብ ሹፌሩ ሄደ። ዶክተሩ ደሞ "ኦኦኦ እንኳን ደና መጣቹ በሉ ግቡ " አላቸው። ሊባኖስም "እሺ" ብላ ከዶክተሩ ፊት ለፊት ያለው አንደኛው ላይ በፀሎትን አስቀምጣ ሊላኛው ላይ ደሞ እሷ ተቀመጠች። ዶክተሩ  ንግግሩን ቀጠለ። ለመናገር የጨነቀው ይመስላል። "እየውላቹ ፅናት እንክብካቤ የሚያስፈልጋት ልጅ ነች ከእዚህ በኋላ ትንሽ ነገር ተፈጥሮ ከተበሳጨች ንዴትን የሚፈጥሩ ነገሮች ካጋጠሟት እሰሰከዘላለሙ ልታጥዋት ትችላላችሁ " ሲል ሊባኖስ እና በፀሎት እኩል "ምን?" አሉ። ይቀጥላል like ትታችሁታል ኧረ ደስ አይልም ለጓደኞችዎ ያጋሩ 🙏

2
 ♥️ ፅናት ♥️...!!!      .      . 🥀..ክፍል 23..🥀 . . . እናቴ አትሙችብኝ እባክሽ እያልኩ ለመንኳት ያ እናቴ ጋር ሽጉጥ የደቀነውን ሰውዬ እባክህ እናቴን እርዳት አልኩት እሱ ግን ምንም ሳይተነፍስ ፊቱን ወደ አባቴ አዙሮ እያየ እናቴ ሆድ ላይ ተኮሰባት። እኔ ህልም ህልም መሰለኝ አልፈዘዝኩም እና ደርቄም አልቀረውም የሆነ አይነት ስሜት ውስጥ ነበርኩኝ። ምን አይነት ስሜት ውስጥ ካላችሁኝ ደሞ እኔ አላውቅም የአያቴን ሞት ሳላምን ሊላኛው አያቴን እየጎተተ ያመጣት ሰውዬ አባቴ ላይ ያለ ማቋረጥ ተኮሰበት መሳሪያው ድምፅ አልባ መሳሪያ ነበር።ስዎቹ ጫማቸው ላይ ፌስታል አስረው ነበር። አሁን ሲገባኝ አሻራቸው እንዳይታወቅ እንደሆነ ነው የተረዳውት እነዛ ሰዎች እኔን እና የቤተሰቦቼን እሬሳ ሳሎን ቤታችን ትይዮ ካለው ሻውር ቤት አስገቡን አባቴ ሞታል እናቴ ግን እያጣጣረች ነበር።ከትንሽ ቆይታ በኋላ የሻውር ቤቱ በር ተከፈቶ ሰራተኛችንን ይዘዋት መጡ። እያቴን ከስር አባቴን ከመሀል አናቴን ከላይ አርገው ገንዳው ውጥ ከተቷቸው።እኔ ዝም ብዬ ማየት ጀመርኩኝ ዝም ዝም ብዬ። ሰራተኛችን ግን እኔን አቅፋ በጩከት እያለቀሰች ነበር። ከዛ ሰራተኛችንን የሆነ ነገር በጨርቅ አፍንጫዋ ላይ አርገው እራስዋን አሳቷት። በሩን ዘግተውብን ወጡ። ሲነጋ ወገግታው ታየኝ። ያም ቀን መሸና ነጋ እናቴ አያቴ እና አባቴ መሽተት ጀመሩ። በጣም መሽተት ስራተኛችን ደሞ በ2ተኛው ቀን ማታ ላይ ነቃች  ደክሞኛል የአስክሬኑ ሽታም ውስጤ ገብቶ እረብሾኛል።" አለችና የቀዘቀዘውን ሻይ በአንድ ትንፍሽዋ ጨለጠችው። በፀሎት እና ፅናት አይናቸው በእንባ ተሞልቷል ሊባኖስ ወሬዋን ለመቀጠል "እንደዛ ከሆነ በኋላ " ስትል ፅናት ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ በቀኝ እና በግራ እጇ ጭንቅላቷን ያዘች። እና ወደ መውጫ በሩ ሄደች። ማንም አላያትም በፀሎትም ማየት አትችልም ሊባኖስም አንገቷን ደፈታለች። ፅናት እራስዋን ሳተች ዷ የሚል ድምፅ ተሰማ ሊባኖስ ቀና ብላ ዞር ስትል ፅናት ወድቃለች።በፀሎት ደንግጣ "ምን ምንድነው" አለች።ሊባኖስ በፍጥነት ፅናት ጋር ሄዳ ፅናትን ከአንገቷ ቀና አረገቻት እና "የኔ ሚጢጢ ደና ነሽ?" አለቻት። ፅናት ግን እራስዋን አታውቅም ነበር።"በፀሎት የተፈጠረውን ነገር ማወቅ ተሳናት። "ሊቦቲዬ እህቴ ምን ሆና ነው?" አለች።ሊባኖስም "ያው እራስዋን ስታ ነው ቆይ አባ በሬሳ የሰጧትን መዳኒት ላምጣና ልስጣት ከዛ ደና ትሆናለች በፀሎትዬ አደንግጪ" ብላ ፅናትን ተሸክማ ወደ መኝታ ቤት ሄደች። በፀሎት ገባት።ሊባኖስ ፅናትን መኝታ ቤት አልጋ ላይ አስተኛቻት። እና ወደ በፀሎት ሄዳ በፀሎትን ወደ መኝታ ቤት ይዛት ገባችና አልጋው ላይ እንድትቀመጥ እየመራቻት "በይ በፀሎትዬ አይዞሽ አትደንግጪ ምንም አትሆንም በቃ አብረሻት ሁኚ እሺ እኔ መዳኒቱን ልፈልገው" አለችና ከመኝታ ቤት ወጣች። በፀሎትም እጇን በዳበሳ ሰዳ ፅናት እጅ  ላይ ደረሰች አጥብቃ ያዘቻች። እና ማልቀስ ጀመረች። ሊባኖስም የፅናትን መዳኒት ከቲቪው ኋላ አግኝታው ወደ መኝታ ቤት ስትሄድ በፀሎት እያለቀሰች ነበር። ሊባኖስ ወደ በፀሎት ተጠግታ አቀፈቻት በፀሎትም አቀፈቻት። ለቅሶዋን እስክታቆም ጠብቃ አስጨረሰቻት። ከዛ ወደ በፀሎት ሄዳ አባ በሬሳ የሰጧትን መዳኔት መሀል ጭንቅላቷ ላይ አረገችላትና ጭንቅላቷን በሻሽ ጠቀለለችው። ከዛ ፎጣ አምጥታ አልብሳት ስታበቃ በፀሎት አጠገብ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች። ሊባኖስ እና በፀሎት የፅናትን መንቃት እየተጠባበቁ ነው። በፀሎት አንገቷን አንጋጣ "ወይ ፈጣሪ ፤ ወይ አምላኬ በቃ በቃ ህይወታችን እንዲ ሆነ ብዙ ሰቀቀን ፣ጭንቀት ፣ ለቅሶ ፣ሀዘን ፣መደናገጥ፣ እና ደሞ ትንሽ ደስታ ፣ሳቅ፣መዝናናት ምን አርገንክ ነው አልልክም ምክያቱም የሚወደውን ሰው አምላክ ይፈትናል ነው የሚባለው" አለችና ስቅስቅ ብላ ማልቀሰ ጀመረች። ሊባኖስም "ነይ ነይ ወደ እዚህ" ብላ ወደ ደረቷ አስጠግታ አቀፈቻትና "ፈተናው የበዛ ሰውም ሆነ ሌላው  ፍጥረት  በፈጣሪ ዘንድ የተወደደ ነው።" አለቻት በፀሎት እሪ እያለች እያለቀሰች ነው። ቀና አለችና ከሊባኖስ  ደረት ተነስታ ሊባኖስ አንገት ስር ገብታ ማልቀስ ጀመረች።      የሊባኖስ አንገት በበፀሎት እንባ ራሰ ሊባኖስ ደሞ አንገቷ ስር የገባችውን ገብታም ያለ ማቋረጥ የምታለቅሰውን በፀሎት ፀጉሯን(እራሷን) እያሻሸቻት ለቅሶዋን ቀነስ ማረግ ቻለች። ሊባኖስም እያለቀሰች ነበር የሊባኖስ እንባ ፅናት ጭንቅላት ላይ እያረፈ ፀጉሯን አርጥቦታል የበፀሎት እንባም የሊባኖስን አንገት አርጥቦታል። የሚያለቅሱት ከልባቸው ነው። ግን ድምፅ አልባ እንባ ነበር። ሰዎች ከልባቸው ያለቅሳሉ በብዙ መንገድም ያለቅሳሉ ነገር ግን ሀዘናቸው በጣም ሲበዛ እንባ ከአይናቸው እንጂ ከአንደበታቸው ቃል አይወጣም ሊባኖስ እና በፀሎትም የየራሳቸው ነገር  ውስጣቸው ገብቶ  አንኮትኩቷቸዋል።እና የሰው ልጆች ደሞ እነ ፅናት ካሉበት የሀዘኔታ ደረጃ ከፍፍፍ ካሉ በሀዘናቸው ጊዜ መሳቅ ይጀምራሉ። እያነቡ እስክስታ የሚባለው ነገር። ከዛም ከፍ ካለ ግን ሀዘኔታው ሀዘን ላይ ሆነው ሊላ ሀዘን ሲጨምረባቸው ከበፊት ስሜታቸው በጭራሽ አይቀየርም ግን ፀጥጥ ይላሉ። ለብዙ ደቂቃዎች ያክል በዝምታ ካነቡ በኋላ በፀሎት ከሊባኖስ አንገት ስር ሳትወጣ "ሊባቲዬ" አለቻት።"ወዬ" አለች በፀሎት ሁለቱም በቀዘቀዘ ድምፅ ነበር ሲያወሩ የነበሩት በፀሎትም "የእህቴ እንዲ በተደጋጋሚ መውደቅ በጣም እያሳሰበኝ ነው በጣም ምን እንደሚሻለኝ አላውቅም ብቻ አንድ ነገር እንዳትሆንብኝ እየፈራው ነው " አለችና በጉንጮቿ እንባዋ ወረደ። ፅናት ነቅታ እህቷ ምትለውን እየሰማች ነበር።እና በጣም አዝና ከአይኖቿ እንባዋ ፈሶ በጆሮዋ መግባት ጀምሯል። እነ ፅናት በውስጥ ጉዳታቸው የተነሳ በድምፅ አልባ ሂደት ነው የሚያለቅሱት። ሊባኖስ "አታስቢ ምንም አትሆንም ይህ የህይወታቹ ፈተና እንጂ ችግር አደለም እሺ " አለች።ፅናት በወሬያቸው መሀል ገብታ። "እወዳችዋለሁ" አለች። ሁለቱም ትኩረታቸውን ወደ ፅናት አረጉ። ፅናት ተዳክማለች በፀሎት"እህቴ የእኔ ውድ ነቃሽልኝ " አለች።  ሊባኖስም "ፈገግ ብላ አዎ አዎ ነቅታለች" አለች። ፅናት ግን እንደሊላው ቀን ነቅታ አልቀረችም። በድጋሜ የሊባኖስን አይን እያየች ነበር እራስዋን የሳተችው። ይህ ነገር  ሊባኖስ አዲስ ሰለሆነ ደንግጣ "የኔ ሚጢጢ ሚጢጢዬ ደና ነሽ ንገሬኝ ደና ነሽ" አለች በሁለት እጆቿ ጉንጯቿን ይዛ እያወዛወዘቻት። ፅናት ዝላለች መልስም አልሰጠቻትም። እራስዋን ስለሳተች በፀሎት ደንገጠች ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ  "ሊቦቲዬ እህቴ እህቴ ደና ናት ንገሪኝ እባክሽ " አለች። ሊባኖስ ረዥምምም ትንፋሽ ከተነፈሰች በኋላ "አይ  አይ እራስዋን በድጋሜ ስታለች " አለቻት በፀሎት "ሊቦቲ ሊቧቲዬ እባክሽ ቶሎ ቶሎ ብለሽ ለሹፊርሽ ደውይ ጋሽ በሬሳን ይዘዋቸው ይምጡ " አለች። ሊባኖስም ስልኳን በፍጥነት ከሳሎን አምጥታ ደወለች። ሊባኖስ ፅናት እራሷ ላይ እርጥብ ፎጣ እያረገችላት ቆየች ምክንያቱም በጣም ትኩሳት ነበራት በፀሎት ፈዛ ቁጭ ብላለች።ሊባኖስ ሻርፕ አመጣችላት እና ፊቷ ላይ ጠመጠመችላት የፅናትንም ፊት በሻርፕ ተጠንቅቃ ጠመጠመችው።ትንሽ ቆይታ በኋላ ሹፊሩ ያለ ጋሽ በሬሳ መጣ። "ጋሽ በሬሳስ ቆይ " አለች ሊባኖስ። ሹፊሩም ከኪሱ ወረቀት አውጥቶ "ሊታደጉ ሂደዋል" የሚል ፁሁፍ ፅፎ ሰጣት። ኧረ ወገን ላይክ አርጉ አይከፈልበትም 😳
91
3
 ♥️ ፅናት ♥️...!!!  . 🥀..ክፍል 22..🥀  . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!! . ሊባኖስም "እሺ የእኔ ሚጢጢ ግን ስለምን እና ምንን በተመለከተ ነው?" ስትላት ፅናት የሊባኖስን እቅፍ አርጋት "ስትመጪ ይደረሳል ሊቦዬ በይ እንገነመኛለን" ብላ ተጣድፋ በሩን ዘጋችው።በር አዘጋግዋ ሌላ ጥያቄ ላለማስተናገድ ይመስላል።ሊባኖስ የፅናት በፍጥነት በር መዝጋት እና ሁኔታዋ ግራ እያጋባት እራቅ ብላ ቆማ ወደምጠብቃት ደመቁ "ደምዬ አስጠበኩሽ አደል እያለች" ሄደችና የሚያስረክቡትን እቃ ተከፋፍለው ይዘውት ሄዱ። ፅናት ወደ ቤት ገባች። ፅናት ሊባኖስን እንዲ በጥድፊያ ተከትላት የመውጣትዋ ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ የጓጓችው በፀሎት።"እህቴ ቆይ ሊባኖስን ለምንድነው ተከትለሻት የወጣሽው ችግር አለ እንዴ?" አለቻት።ፅናትም ከቆመችበት መግቢያ በር ወደ በፀሎት ሄዳ። በፀሎት አጠገብ ቁጭ አለችና የበፀሎትን እጅ ጥብቅ አርጋ ያዘቻት። በፀሎት "ምን ሆነሻል እህቴ ንገሪኝ አታስጨንቂኝ" ስትላት ፅናት ወደ እህቷ ተጠግታ ደረቷ ላይ ተኛችና "ዛሬ እህቴ " አለችና ዝም አለች በፀሎት ትግስት አጣች።"ዛሬ ምን በይ ንገሪኝ ያንን እብድ አገኘሽው? አለቻት። ፅናትም ፈገግ ብላ "አይ እህቴ አለች" በፀሎት አሁን ቁጣ እና ንዴት በተቀላቀለበት ድምፅ "እና ምንድነው ጉዱ ንገሪኛ " አለች። ፅናትም "እሺ እሺ አትቆጪ ዛሬ ሊቦን ቤት እንድትመጣ ጠየኳት" አለችና "ኡፍፍፍ" አለች። በፀሎት ፊቷን ኮስተር ፈገግ እያረገችው  "ለምን? " አለች። ፅናትም ከ አንገቷ ቀና ብላ በፀሎትን እያየቻት "ዛሬ ሊቦን ስለ ህይወት ታሪኳ ለመጠየቅ ነው የቀጠረኳት እንደምትነግረን ተሰፋ አረጋለው  ያለበለዚያ ጭንቅላቴ በጭራሽ አያርፋም" ስትል በፀሎት "እህቴ ይቅርብሽ ታሪኳን መናገር አትፈልግም " አለቻት ፅናት ግን ልጠይቃት ቆርጣለች። " አይ እህቴ  ታሪኳ ምንም ሊመስል ይችላል እኔ ግን እጠይቃታለው" አለች። በፀሎት እና ፅናት የሊባኖስን ሙያ እያደነቁ የሰራችውን ሽሮ በሉና ሬዲዮ ማዳመጥ ጀመሩ። ፅናት ግን ሊባኖስን በጉጉት እየጠበቀቻት ነው። ሰአቱ ወደ 12:45 አከባቢ ሆኗል። ፅናት እና ሊባኖስ ሶፋው ላይ ተቃቅፈው ተኝተዋል። ሊባኖስ የውጩን  ከዛ የሳሎኑን በር ከፍታ ገባች። ማንም አልስማትም ሊባኖስ የሳሎኑን በር ላይ ቆማ ሁለቱንም ማየት ጀመረች። ፅናትን አይቻት በፀሎትን አየቻት። "በስማም ውበት አይናቸውን ሲጨፍኑ ደሞ ባሰበት የፈጣሪ ያለ " አለች ሊባኖስ። ሊባኖስ እውነቷን ነው የበፀሎት እና የፅናት ውበት በቃላት የሚገለፅ አደለም  ልዩነታቸው የፅናት ፀጉር ከወገቧ በታች ነው፤የበፀሎት ደሞ ከጆሮዋ በታች ነው።ግን ጥቁረቱ ያዉ አንድ ነው። እና ሊላው ልዩነታቸው በፀሎት ቸኮሌት ከለር ስትሆን፤ ፅናት ግን እጅግ በጣም የሚያምር ቅላት አላት። የሁለቱም የፊት ከለር በጣም ያምራል። ጣቶቻቸው አንድ አይነት ነው ሰልካካ ጣቶች፣ረዥም፤ የሰውነት ቅርፃቸው ውብ የሆነ ብቻ በጣምም ውቦዎች ናቸው። ሊባኖስ ሁለቱን ቆነጃጂት እህትማማቾች ማየቷን አቁማ ብርድ ስለሆነ  ኩሽና ገብታ ሻይ አፈላች። በሶፋዎቹ መሀከል ባለው ጠረጴዛ ላይ በሰርቢስ ትሪ ሶስት  ብርጭቆ የስኳር  እቃ ከነ ስኳሩ አቀረበች። በሻይ እንዲበሉት በማሰብ ፓስቲ ለፅናት ለእሷና ለበፀሎት እንፖቲቶ አቀረበች።በፀሎት የሻዩ(በቅመም የተፈላሻይ)  ፣የፓስቲው እንዲሁም ደሞ የእንፖቴቶ ሽታ ቀሰቀሳት ፅናት ከአጠገቧ ናት ቀሰቀሰቻት "ፅናቴ እህቴ" ፅናት እየተንጠራራች "ምንድነው እህቴ አአ ምን እየሸተተኝ ነው ቆይ" አለችና ወደ ጠረጴዛው ዞር ስትል። ሊባኖስን አየቻት ሊባኖስም "አይ እናተ እንቅልፋሞች በቃ ሰው ከሊለ መጋደም ነው አደል ስራቹ በሉ በሉ ተነሱ" አለች።  ሁለቱም ተነሱ ፅናትም ወደ ሊባኖስ ሄዳ "ሊቦዬ የእኔ መልካም በጣም እንወድሻለን " ስትላት ሊባኖስ ፈገግ ብላ " በሉ በሉ ወደ መሟሟቁ እኔም እወዳቸዋለሁ ሽምገላ መሆኑ ነው" አለች በፀሎትም "እንዴ ሊቦቲዬ ኧር አደለም " ስትላት ሊባኖስ "ስቀልድ ነው በቃ በሉ ኑ ብሉ ጠጡ ብርዱ ከባሰ ቡና አፈላለው ዛሬ እዚህ ነው  እማድረው " አለች በፀሎት እና ፅናት "ደስ ይለኛል"አሉ  ሶስቱ ቁጭ ብለው መመገብ ጀመሩ። ፅናት ሻይዋን እየጠጣች ፊት ለፊቷ  ያለችውን ሊባኖስን ታያታለች። ደጋግማ ታያታለች ይህንን አስተያየቷን የተረዳችው ሊባኖስ "የኔ ሚጢጢ ምነው ልጠይቂኝ የምትፈልጊው ነገር አለ?" አለቻት።  በፀሎት አጠገቧ የተቀመጠችውን ፅናት እጇን ወደሷ ሰዳ አቁሚ የሚል ምልክት ሰጠቻት። ፅናት ግን " ታፋዋ ላይ ያለውን ፡የእህቷን እጅ አንስታ "እእእእ አዎ አለ ሊቦዬ አለ እምጠይቅሽ ጥያቄ አለ" አለች።ሊባኖስም "እሺ በያ ጠይቂኝ የኔ ሚጢጢ በይ" አለቻት።ፅናት ወደ በፀሎት እጇን ልካ የበፀሎትን እጅ ጥብቅ አርጋ ያዘችው ፤ በፀሎትም የፅናትን እጅ ሊላኛውን እጇን በመደረብ ይበልጥ አጥብቃ ያዘቻት። ሊባኖስ ግራ በተጋባ አመለካከት እያየቻቸው "እህ ገባኝ ስለዚህ ጥያቄው የሁለታችሁም ነው ማለት ነው በሉ ጠይቁኝ ወይም የሚነገር ነገር ካለም ንገሩኝ" አለች። በፀሎትም እየተርበተበተች ትናት ከእህቷ ጋር የተወያዩበትን አንድም ሳይቀር ነገርቻት። ሊባኖስ ፅናት እየተርበተበተች እጇን ከእህቷ እጅ ጋር እያሻሸች ስታወራ። ሊባኖስ ደሞ አንገቷን ደፍታ በሰሀን የያዘችውን እንፓቲቶ በሀይል እየቆራረጠችው ነበር። ሊባኖስ ፅናት አውርታ ስትጨርስ ቀና አለች። ፅናት የሊባኖስን ፊት ስታይ ደነገጠች። ሊባኖስ በእንባ ፊቷ ታጥቦ አይኖቿ ደሞ ቀልተው ነበር። ቤቱ ፅናት ካወራች በኋላ ፀጥ እረጭ ብሏል። በፀሎት ግራ ገባት። ከዛማ በፀሎት ዝምታውን ለመስበር በማሰብ  " ምን ምነው ዝም አላቹ ሊባቲዬ ፅናቴ ምን ተፈጠረ" አለች። ማንም መልስ አልሰጣትም አሁንም ዝምም አሁንም ጭጭ አሁንም ወሬ የለም። ከብዙ ዝምታዎች በኋላ ሊባኖስ ለቅሶ በዘጋው ድምፆ ማውራት ጀመረች።"የኔ ህይወት ብነግራቹሁም አይገባችሁም ምን ብዬ ልንገራቹ የምኖረው ብቻዬን ነው። ቤተሰቦቼን አጥቻለሁ አባቴ በጣም ባለሀብት ነበር። እና እናቴን አግብቶ እኔን ወለዱ። በጣም ደስተኖች ነበሩ በጣም ደስተኖች አንድ ቀን ቁጭ ብለን እራት እየበላን ነበር።  ተኩስ ተጀመረ። አባቴ በፍጥነት መጋረጃውን ከፍቶ አየ። በድንጋጤም ፈዞ ቀረ። እኔ ያን ጊዜ 15 አመቴ ነበር። እኔ እና እናቴ ስለ ተኩሱ እና ስለ አባቴ ድንጋጤ ለማወቅ ወደ መጋረጃው ተጠጋን ፊታቸው የተሸፋፈኑ ሰዎች ነበሩ። የአባቴ እናትን ገለዋት ነበር። ከዛ ከዛማ እኛ ወዳለንበት ቤትም መጡ በሩን ከፈተው ገቡ። ሁላችንም ባለንበት ደርቀን ቀረን።አንደኛው ከገባ በኋላ ሌላኛው  ደሞ አያቴን እየጎተተ አመጣት አያቴ በደም ተነክራ አይኗ ፈጦ ነበር። በጣም ታስፈራ ነበር። እናቴ ያኔ የ 8 ወር እርጉዝ ነበርች። በድንጋጤ ከቆመችበት ወደቀች ማንም ሊደግፋት አለቻለም። ምክንያቱም ደሞ እኔም ሆነ አባቴ ደርቀን ቀርተን ነበር። አያቴን እየጎተተ ይዞት ያልመጣው ሰውዬ በቀጥታ እራስዋን ስታ የተዘረረችው እናቴ ጋር አመራ እናቴ ደም እየፈሰሳት ነበር።አባቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ።እኔ ከፍዘቴ ነቅቼ እናቴ ጋር ጎንበስ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። እናቴ እያቃሰተች ነበር።ሰውየው እናቴ ሆድ ላይ ሽጉጡን ደቀነው አንገቷ ስር ሆኜ እያለቀስኩ ነበር። የእናቴ ትንፋሽ እየተቆራርጠ መጣ። እናቴ አትሙችብኝ እባክሽ እያልኩ ለመንኳት ያ እናቴ ጋር ሽጉጥ የደቀነውን ሰውዬ .. ይቀጥላል ..
636
4
 ♥️ ፅናት ♥️...!!!          .          .          . 🥀..ክፍል 21..🥀           .           .           ሊባኖስም እህ አደረኩኝ "በሉ በሉ ዛሬ ቁርስ አብረን ነው ምንበላው" አለችና ከተቀመጠችበት ሶፋ ተነስታ ወደ ውጪ ወጣች። በፀሎት እና ፅናትም አብረዋት ወጥተው ፊታቸውን ታጠቡ ሊባኖስም ቡታጋዙን እና ክረቢቱን ከእቃ ቤት አምጥታ አያይዛ ሻይ ጣደችበት። ፅናት ፊቷን ታጥባ እንደጨረሰች "እህቴ በቃ አልጋችንን ላንጥፋ አንቺ ፀሀይ ሙቂ እስከዛ" ብላ ገባች። በፀሎት ፀሀይ እየሞቀች በረንዳው ላይ ካለችው ሊባኖስ ጋር መዝሙር እየዘመሩ ነው። እውነት ነው አዎ እውነት ነው መንገድ ነው በእርግጥ መንገድ ነው እየሱስ የጌቷች ጊታ ነውውውውው.. አሁን የቁርስ ሰአት ነው ፅናትም አልጋዋን አንጥፋ ለብሳ፤ ሊባኖስም ቁርስ አዘጋጅታ፤ በፀሎትም ፀሀይ ሙቃ ልብስ ቀይራ ጨርሰው ቁርስ እየበሉ ነው።ፓስቲ በሻይ በልተው ሲጨርሱ ፅናት በቃ እኔ ልሂድ 1:45 ሆኖል።  ደና ዋሉ ብላ ቦርሳዋን አርጋ ሻርፗን ጠምጥማ  ሁለቱንም ግንባር ግንባራቸውን ስማቸው ሄደች። ሊባኖስም በፀሎትን "በፀሎቴ ከመሄድሽ በፊት ጋሽ በሬሳ ስለሚመጡ ትንሽ ጠብቂያቸው" ከማለትዋ በሩ ተንኳኳ። "ውይ በቃ እሳቸው መሆን አለባቸው መጣው በር ልክፈት" ብላ ሄደች። የውጩን በር ስትከፈተው ጋሽ በሬሳ እና ለሚሸጡት ፓሰቲ ሊጥ የምታቦካላቸው ሴት ነበሩ። "ግቡ ግቡ ብላ ካሰገባቻቸው በኋላ  "ጋሽ በሬሳ በሉ እርሶ ይግቡ በፀሎቴ አለች " አለችና ሊጥ አቡኪዋን ሴት "ነይ ደምዬ" ብላ ወደ ኩሽና ወሰደቻት።እና "ይህው ሁሉም ነገር ተዘጋጅቷል የሚያስፈልግሽ ነገር ካለ ጥሪኝ" ብላት ወደ ሳሎን ስትገባ ጋሽ በሬሳ እና በፀሎት እያወሩ ነው። ጋሽ በሬሳ "ያቺ  እሳት እህትሽን እኮ ወደ እዚህ ስመጣ አግኝቻት እረፍዶብኛል ብላ ተጣድፋ ሄደች " አሉዋት። በፀሎትም "አይደል አዎ ሰአቱ ሄዶባታል" አለች። ሊባኖስም ከበር እየገባች "ቡና ላፍላ?" ስትል "አይ በጭራሽ እቸኩላለው የበፀሎትን የእግሯን ሁኔታ አይቼ እሄዳለው መዳኒትም ይዤ መጥቻለው። በይ በጎንሽ ጋደም በይ ትልቁ ሶፋ ላይ ሄደሽ አሉዋት"በፀሎትን  እሷም "እሺ" ብላ። ብድግ ስትል ሊባኖስ "ቆይ ቆይ ብላ ደግፋ ሶፋው ላይ እንድትሆን ረዳቻት። ጋሽ በሬሳ ከያዙት ፊስታል ብዙ ፈሳሸ እና ዱቄት ነገሮች በብልቃጥ  አውጥተው ቀመሙት። ሊባኖስም ወደ ውጪ ወጣች። ከዛ ያን የቀላቀሉትን ነገር በፀሎት እግር ላይ እያረጉላት "በይ ለ 8 ሰአት ያክል እንዳትንቀሳቀሽ" ብለው። ከእግሯ ስር ፊስታል አንጥፈው ቀቧዋት የቀቧት ነገር ጭስ ማውጣት ጀመረ። በፀሎትም አቅም እያጠራት መጣና እራስዋን ሳተች። ጋሽ በሬሳም ሊባኖስን ጠርተው "በይ ልጅ ሊባኖስ ለ8ሰአት ያክል በጭራሽ ከእዚህ እንዳትነቃነቅ ለነገሩ እራስዋንም አታውቅም" ብለው ሊባኖስን ተሰናብተው ሄዱ። ሊባኖስም እስከ በር ሸኝታቸው ወደ ደመቁ ሄዳ "ደምዬ እንዴት ሆነሽ" አለቻት ደመቁም "ጨረሻለው አሁን የሚድበለበለው ተድበልብሎ የሚጠፈጠፈው ይጠፈጠፍ" ስትላት "እሺ በቃ ቤቱን እስከማፀዳ አንቺ ስሪ ስጨረስ መጥቼ አግዝሻለው"ብላት ወደ ሳሎን ሄደች። በፀሎትን አየቻት አይኗን ስጨፍን ውበቷ ይጎላል የአይኖቿ ቆቦች ታይተው አይጠገቡም በፀሎት በጣም ውብ ናት። ጋሽ በሬሳ የቀቧት መድሀኒት ሰውነቷን በላብ አጥምቆታል አይኗቿ እና የከንፈሮቿ ጫፈ ላይ  ላብዋ በይበልጥ ችፍፍፍ ብሏል። ሊባኖስ አይኗን መለስ አርጋ "ከአይን ያውጣሽ ቱቱቱቱቱ" ብላ ወደ ቤት ፅዳቱ ተመለሰች። ቤቱን አፅድታ ስትጨረስ ደመቁ ጋር ሄዳ ስታያት ደመቁ አብዛኛውን ስራ ሰርታ ጨርሳለች። ሊባኖስ "ውይ ደምዬ ሳላግዝሽ በቃ ከጨረሽማ እኔ ወጥ ልስራ ከዛ ከመጥበሳችን በፊት እንበላለን" አለቻትና ወደ ኩሽና ሄዳ ሽሮን ለፈላው ውሀ ላይ መታ ወደ ደመቁ ሄደች። አሁን ደመቁ ስራዋን አጠናቃለች። ሰአቱ 7:30 አከባቢ ሆኗል። ሊባኖስ እና ደመቁ ኩሽና ቡና እየጠጡ ነው። ከሳሎን ለቅሶ ያጀበው "እህቴቴቴቴ የሚል ጩከት ተሰማ ደመቁ እና ሊባኖስ ተንጋግተው በሩጫ ሳሎን ቤት ሄዱ። ፅናት ቦርሳዋን እንደተሸከመች ሶፋው  ላይ ተቀመጣ  እራስዋን ማታውቀው እህቷ ላይ ተደፍታ እያለቀሰች ነው። ሊባኖስ ቶሎ ብላ ወደ ፅናት ሄዳ ከተደፋችበት ቀና አረገቻት ፅናት እያለቀሰች ነው። ግን ፊቷ በሻርፕ ስለተሸፈነ ፊቷን ማየት አለቻለችም። "ምን ምን ሆነሽ ነው የኔ ሚጢጢ አለቻት"ሊባኖስ ግራ ተጋብታ። ፅናትም እያለቀሰች "ሊቦ ሊቦዬ እህቴ እህቴ ምን ሆናብኝ ነው ስጠራት ዝም ያለችኝ እንደ አባባ እና እማማ ጥላኝ ሄዳለች። ብዙ ጊዜ ጠራዋት ግን አሰማም ቆይ ጠዋት ደና አልነበረች እንዴ" ስትላት ሊባኖስ ጮክ ብላ ክትክት ብላ ሳቀች ፅናት የሊባኖስ ሳቅ አስፈራት የዛ ሰውዬ  ድምፅ አቃጨለባት ሊባኖስ በሰው ስቃይ የምትደሰት ሴት ናት ያላት። ፅናት ፈራች ሊባኖስም ሳቋን የግዷን ካቆመች በኋላ "የኔ ሚጢጢ እህትሽ እኮ ምንም ሆና አደለም አንቺ ፈሪ" ብላ ሁኔታውን አስረዳቻት። ፅናት ልቧ ተረጋጋ ግን ብዙ አደለም። ሊባኖሰ ከደመቁ ጋር ወደ ኩሽና ተመለሰች።ፅናት ደሞ ከእህቷ ትይዩ ሶፋ ላይ ሆና የእህቷን መንቃት መጠባበቅ ጀመረች። 9 ፡45  አከባቢ ሊባኖስ ወደ ሳሎን መጣችና ፅናትን"አንቺ ልጅ ኧረ ባይሆን ልብስ ቀይረሽ ይህን ሻርፕሽን ወደዛ ጣይው" አለቻት። በፀሎት ግን ፈዛ ሊባኖስ ያለቻትንም አልሰማችም። ሊባኖስ ንዴት እና መበሳጨት በተሞላበት ድምፅ "አንቺ ልጅ አሁንስ በጣም አበዛሽው ተነሽ ዩኒፎርምሽን እና ይህን የፊት ሻርፕሽን አውልቀሽ ልብስሽን ልበሺ "ስትላት ፅናት ደንግጣ ብድግ አለች። የሊባኖስ ቁጣ ያስፈራል ልክ ሳቋ እና ፈገግታዋ ሁሉን እንደሚያስረሳው ሁሉ ማለት ነው። ፅናት ብድግ ብላ በንፋስ ፍጥነት መኝታ ቤት ገባች ምንም ቃል አልተነፈሰችም። የሊባኖስ ቁጣ ኩም አድርጓታል። አፍታ ሳትቆይ ቀያይራ መጣች ሻርፖንም አውልቀዋለች። አይኗ አብጦ ነበር ሊባኖስ ስታያት ደነገጠች።ምክንያቱም ከሚባለው በላይ አይኗ አብጦ ስለነበር። ሊባኖስ ለፅናት ነይ ብላ ለማቀፈ እጇን ዘረጋችላት ፅናትም ተንደርድራ ሄዳ አቀፈቻት። ተቃቅፈው ብዙ ቆዩ። "እንዴ ዛሬ ደሞ አስተቃቀፋቹ ይለያል ባካቹ እስቲ እኔንም እቀፉኝ" አለች በፀሎት። ፅናት የበፀሎትን መንቃት ስታይ ፊቷ በርቶ ነበር በደስታ ልትሞት ደረሰች። የሆነ ነገር በጣምም ፈልገነው እና ጠብቀነው የማግኘት አይነት ስሜት። በጥድፊያ ሊባኖስን ለቃ እህቷ እቅፍ ውስጥ ገባች። ሊባኖስም "ወይ አልቀረብሽም በቃ ካድሽኝ ለማንኛውም ዛሬ ለምግብ ቤቶቹ እንፖቲቶ እና ፓስቲ ለማስረከብ እኔና ደምዬ ልንሄድ ነው በሉ ደና ሁኑ በዛውም ምሄድበት አለ ከተመቸኝ ወደ ማታ ብቅ ብዬ አያችዋለው"ብላ ልትሄድ ስትል ፅናት እንዴ ሊቦ እህቴን ተሻለሽ ወይ አትያትም እንዴ" አለቻት። ሊባኖስም "ስለተሻላት ነው የነቃችው መዳኒቱ ስራውን ባይጨረስ አትነቃም ነበር በሉ በሉ ቻው እወዳቹሀለው "ብላ ወጣች። ፅናት ሊባኖስን ተከትላት ወጥታ በሩን አሰወጣቻት ሊባኖስም"በይ የኔ ሚጢጢ ቆንጆ ሻርፕ ሳለብሽ ነው የወጣሽው በይ ጊቢ"ስትላት ፅናት የሊባኖስን ግንባር፣ ሁለቱን አይኖቿን፣ አንገቷን ስማት  "እሺ ሊቦዬ ነይ ዛሬ መምጣት አለብሽ የምጠይቅሽ ጥያቄዎች አሉኝ እንደምትመልሽልኝ ተስፋ አረጋለው"አለቻት።
1 104
5
እንኳን አደረሳችሁ! መልካም በዓል!!
1 223
6
#መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። #መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። #መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። #መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው። #መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው። #መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው። #መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። #መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው። #መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው። #መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው። #መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው። #መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። #መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው። (ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
1 240
7
የዛሬዋን ብሩህ ቀኔን የምጀምረው ሳላውቅም ሆነ አውቄ ያስቀየምኳችሁን ይቅርታ በመጠየቅ ነውና #ይቅርታ !🙏 ቀኑ ከአስመሳዮች፣ ከሸረኞች፣  ከምቀኞች፣ ከሟርተኞች፣ ከሀሜተኞች የፀዳ ይሁንልን መልካም አሳቢዎች እና የፍቅር ሰዎች ያብዛልን!        #ሰ_ላ_ም___ዋ_ሉ_ል_ኝ
1 118
8
#Like👍 በጣም ከመቀነሱ የተነሳ የሆነ ሰው Like ሲያደርግልኝ በinbox📩 እየገባሁ እግዜር ይስጥልኝ ውለታ መላሽ ያድርገኝ ማለት ጀምሪያለው😉
1 113
9
ለሰዎች #ጥሩ_መስራት ባንችል #መጥፎ_ነገር ተናግረን ባለመጉዳት ቀናችንን ውብ እናድርገው
1 049
10
ሴት ልጅ የወር አበባ ስታይ ለአቅመ ሔዋን ደርሳለች ይባላል ወንድ ልጅስ ምን ሲያይ ነው ለአቅመ አዳም ደረሰ የሚባለው ሲላት... #ያው_አንገቱ_እስኪ_ቀጭ_የሴት_መቀመጫ ሲያይ ነዋ 😳😳😜
1 119
11
በቃ በTg እናወራለን ስላት Tg አልጠቀምም ከፈለክ በTelegram እናወራለን ብላኝ ቀኔን አሳመረችው😜😂
1 112
12
አንዱ የኔ ቢጤ የእርግዝና መቆጣጠሪያ (Post pill) ይዞ እባካቹ አሞኝ ነው እያለ ይለምናል ይህ ምስኪን ህዝብ እ/ር ይማርህ እያለ ይመፀውታል🤔
1 047
13
#ቺኬ_በጣም_አጭር_ከመሆኗ_የተነሳ ልስማት💋 ጎንበስ ስል ቤት ደርሳ ውጪ እንደምታድር ተናግራ ጃኬት ደርባ ከቦርሳዋ ውስጥ Lipstick 💄 አውጥታ ከንፈሯን ተቀብታ ሁላ አልደርስም😂
929
14
ለቂጡ ሱሬ መግዣ የሌለው ወንድ ሁላ እየተነሳ ትብላው ብሬን እያለ ይዘፍናል ኧረ bro አያስኬድም ስትለው... አርቴፊሻል ጡትና ቂጥ ያላት እኮ ናት ነካካው ገላዬን አካሌን ደባብሰው እያለች የምትዘፍነው ኧረ sis አያስኬድም😜 #መልስ_ምት_ያስጠላሃል 🤣😂
842
15
#እርጉዝ_መስላኝ🤰 ወንበር ቀይሬ ባከብረው ይጮሀል😳 እንዴ🤷‍♂ ፂም የለውም በዛ ላይ ቦርጫም ነው😂 #እንሂድ_ሹፌር 🚌
791
16
ከእያንዳንዷ Online ተጥዳ ከምትውል ሴት ጀርባ ብዙ ያልታጠቡ ሳህኖች አሉ... #My_Sister_ሄደሽ_አጥበሽ_ነይ 🚶‍♀
794
17
በአለም ላይ የዛሬዋን ቀን ያላዩ በርካቶች አሉና በሰላም አውሎ በሰላም ያሳደረንን ፈጣሪ እናመስግን!!🙏🙏
785
18
  ♥️ ፅናት ♥️...!!!            .            .            . 🥀..ክፍል 20..🥀           .           .           . ፅናት ወደ እህቷ የተቀመጠችበት ሶፋ በመሄድ "ተስተካክለሽ ተመጭ ፀጉርሽን ልስራሽ" አለች እና ከኋላዋ ቆመች። በፀሎትም ጋደም ካለችበት ትልቅ ሶፋ ላይ ፈቀቅ ብላ ደገፈ አለቻላት። ፅናት የበፀሎትን ፀጉር ለመስራት እያበጠረቻት ለስለስ ባለ ድምፅ  "ፀጉርሽ በጣም አድጓል"አለችና መሀል ጭንቅላቷን ሳም እያረገች ። እየውልሽ የኔ ቆንጅዬ እህት እድሜ ለአባ በሬሳ እና ለሊቦ ይሁን አሁን ያለ ምንም ደጋፊ ትንቀሳቀሻለሽ እኮ ይህ ደሞ ደስስ የሚል ነገር ነው እኔም ህልሜን ላሳካ ነው። ደሞ እዚህው አዲስ አበባ ነው ለዶክትሬት ለማመለክተው አንቺ ደሞ ጥሩ ውጤት እንዳመጣ ፀልይና ከጎንሽ እሆነለው።" አለችቻት።ሊባኖስ "ውይይ እንዴት ነው ምታስቀኑት የኔ ቆንጅዬዎች" አለችና በሁለት እጆቿ  ቡና ይዛ መጣችና አንዱን ጠረጼዛ ላይ አስቀምጣ ሊላኛውን ለበፀሎት ያዢ በጸሎቴ ብላ ሰጠጥታት ወደ ቡናዋ እየተመለሰች " በፀሎቴ በይ ደሞ ነገ አቶ በሬሳ እግረሽን ለማየት ይመጣሉ ደውለውልኝ ትንሽ የሚያስነክሳትን ነገር እንዲስተካክልላት መጥቼ አክማታው ብለዋል" ስትላት ፅናት "እንዴ አክማታለው ነው ያሉት ወይስ  እፈውሳታለው ነው ያሉት እፈውሳታለው  ቢሉ አይቀልም  በዊልቸር የሚሄድን  ሰው በ1አመት ከ7 ወር ውስጥ በቅጠላ ቅጠል ሸብስቦ ማስኬድ ቀላል ነው?" አለች። ሊባኖስም ፈገግ እያለች "ስሚ አንቺ ልጅ ፈዋሽ ፈጣሪ ነው ሀጢያት አትግቢ ደሞ ብር ታጣ እንጂ ሀኪሙስ ወደ ጤናዋ ሊመልሳት አልነበር " ስትላት ፅናት አይ ከፈጣሪ በታች ማለቴ ነው ደሞ ዶክተሮች እራሳቸው አይቀምሙት የጋሽ በሬሳ እኮ ስራቸው ድንቅ ነው እኔም እዚህ ክልል ውስጥ አመልቼ ከዛ ጎን ለጎን ከእሳቸው ጋር ነው የምሰራው" አለች። በፀሎትም "ያርግልሽ እህቴ በቃ እኔም እኮ የጨርቃጨርቅ ስራ ላይ እንዳንቺ ምርጥ ሰሪ የለም ብሎኛል አሰልጣኙ ምናለ የሰራውትን በአይኔ ማየት ብችል ጥሩ ነበር" አለች። ፅናትም "ታይዋለሽ እህቴ  የአንቺ ህክምና እኮ ሊላ ብሌን አያስፈልገውም የሚያስፈልገው ውጪ  ሀገር ሄደሽ የምትታከሚበት ብር ማግኘት ነው እሱን ደሞ እኔ ዶክተር ስሆን ብዙ ስለሚከፈለኝ አሳክምሻለው ወይ ከአባ በሬሳ ጋር መድሀኒት ይፈለጋል ብቻ አትጨነቂ አሁን ወደፊታችን እያማረ ነው"አለች።እሱስ ልክ ነሽ አለች።ሊባኖስም "እውነት ነው አባ በሬሳን እዚህ እየተመላለሱ እንዲያክሙሽ ስጠይቃቸው የተስማሙት እኮ ስለ ህልምና አላማቹ በደንብ ስለነገረኳቸው ነው"።አለች። ፅናት የእህቷን ፀጉር እየሰራች ሊባኖስ ያፈላችውን ቡና ጠጡ እና ጨረሱ።ሊባኖስም ቡናውን አፍልታ ሰጨርስ "በሉ በቃ ወደ ቤቴ ልሂድ" አለችና ወደ በሩ አመራች። ፅናትም "እሺ ቆይ ልሸኝሽ" ስትላት ሊባኖስ "አይ ሹፌሬ ይመጣል "በቃ" ልሂድ አለችና"ደና እደሩ የእኔ ሚጢጢዬ በይ አንቺም የእህትሽን ፀጉር ጨርሻት በፀሎትዬ በይ ደና እደሬ በሩን ከውጪ ቆልፌው እሄዳለው" ብላ ወጣች። ሊባኖስ እንደወጣች ፅናት "እኔ እምልሽ እህቴ ስለ ሊባኖስ በጣም ማወቅ ፈልጌ ልጠይቃት ነበር ግን ፈራዋት ሹፌር አላት፤ጠባቂ አላት ሀብታም ናት እንዳልል ደሞ አለባበስዋም ሆነ ሁኔታዋ አይመስልም ነገ ግን እጠይቃታለው በቃ እህቴ ፀጉርሽን ጨርሼልሻው ቆንጆ አርጌ ነው የሰራውሽ" እንደውም ነገ አቃሸ ሲያይሽ ልቡ ትርክክ  እንዲል ሻርፕሽን ሳታረጊ ሂጂ" አለችና ሳቀች።በፀሎት "ወይ አንቺ ልጅ ፅናትዬ ግን አይገረምም ከ2 አመት  ብዙ ነገሮች ግልፅ ጥሩ አልነበሩም አሁን ግን ጥሩ ሆነውልናል በቃ ምን አለፋሽ ሁሉም ነገር ደስ ይላል አሁን አንድ ነገር ነው የሚያሳስበኝ"ስትል። ፅናት "ምን? ምንድነው የሚያሳስብሽ?" አለች። ያ የሚያስፈራራሽ የእብዱ አባት ከኋላዬ ኮቴ ስምቼ ስዞር የለም ያልሽው፤ልጁ ያ የሰውየው ልጅ መሆኑ ቆይ ቢወጋሽስ ብቻ አላውቅም ፈርቻለው" አለች። ፅናትም "አትፍሪ እህቴ አትፍሪ"አለች አትፈሪ ስትል ፅናት እራሱ ከፊቷ ፍርሀት ይነበባል። በፀሎትም "እኔ እኮ ግራ የገባኝ እንዴት ይህኛውን ቤታችንን እንዳወቀው ነው" አለች።በፀሎት እሱን ተይው እህቴ እኔ ደሞ ያኔ ከ2 አመት በፊት ታመን ሊቦ ወደዛ አስፈሪ ቤት ይዛን ሄዳ አቶ በሬሳ ያከሙን እለት። ማታ የሰማነው ሙታን የታሉ የሚለው እና የእንጉረጉሮ ድምፅ ከዛ ደሞ የሊባኖስ ለሊት ላይ መሰወረ እና ጠዋት መከሰቷ እና ደሞ ሊቦ አጠገቤ ስትሆን ይህንን ሁለ መርሳቴ በድንገት ሳስታውስ መደንገጤ ውይይይ ይጨቃን የምር ይጨንቀን" ብላ ከእህቷ ኋላ ዞር ብላ ከበፀሎት ትይዩ ሶፋ ላይ ዘፋ ብላ ተቀመች። ፅናት እና በፀሎት እንቅልፋቸው መጥቷል። በፀሎት ከተቀመጠችበት ሶፋ ብድግ ብላ ቆመችና በዳበሳ ወደ መኝታ ቤት እየሄደች "ፅናቴ ነይ ነይ እንተኛ በቃ " አለች።ፅናትም "እሺ እህቴ መጣው አንቺ ተኚ" አለችና ተደግፋ የተቀመጠችበት ሶፋ ላይ በደረቷ ተጋድማ ስለ ሊባኖስ ከዛ ደሞ ስለ እብዱ እያሰላሰለች እኩለ ለሊት ሆነ። እንቅልፏም ስለመጣ ሄዳ ከእህቷ ጎን ጋደም ብላ ፊቷን ወደ እህቷ አዙራ እቅፍ አረገቻት በፀሎትም በሰመመን ላይ ሆና እቅፍ አረገቻት በቃ ተቃቅፈው ተኙ። ከእኩለ ለሊት በኋላ ያለውን ሰአት እስከ ንጋቱ 1 ሰአት ሿ ያለ እንቅልፍ ተኙ። ከዛን ሰአት በኋላ ግን ሊባኖስ መጥታ የውጩን በር በራስዋ ቁልፍ ከፈታ ገብታ የቤቱን እየከፈተች ሳለ ፅናት ሰምታ ተነሳች።በፀሎት እንደተኛች ናት። ፅናት ወደ ሳሎን ሄዳ "ሊቦዬ መጣሽ" አለች የሳሎኑን በር በጥቂቱ ከፍታ ለመግባት ጫማዋን እያወለቀች ያለችውን ሊባኖስም "እንዴት አደረሽ የኔ ውድ ሚጢጢ በፀሎት አልተነሳችም እንዴ?" አለቻት የመኝታ ቤቱን በር ተደግፋ ለምታያት ፅናት። እሷም አይ "እኔም ለእራሱ አሁን መነሳቴ ነው እህቴ ተኝታነች አለች። ሊባኖስም ተኝታነች ብላ ሳቀችና ሶፋው ላይ ተቀመጠችና "አይ የኔ ሚጢጢ እስቲ ተኝታለች በይ ተኝታነች አይባልም፤ እኔ ለእሱ ሳይሆን እኔ እራሱ ነው የሚባለው" ስትል በፀሎት ውይ ሊባዬ እንግዲ ጀመረሽ አለችና ፈገግ አለች። በፀሎት አንኗን እያሻሸች እና እያፏሸከች። መንጠራራት ባጀበው ድምፅ ተነስቻለው "እንዴት አደርሽ የኔ ውድ እህት" አለች።ከአልጋዋ ተነስታ በዳበሳ በር ላይ ደርሳ ፅናትን እቅፍ አርጋት።ፅናትም ይበልጥ እያቀፈቻት "ደና አድሬልሻለው" አለቻት። ሊባኖስም "እህ አንቺ ቆንጆ እንዴት አደረሽ ባክሽ ዋው ፀጉርሽ ደሞ አምሮበት አሳምሮሻል" ስትል በፀሎት "ያው ከልጅቷ ነው" አለች። ፅናት እህቷን ወደ ሶፋው ይዛት እየሄደች "ኧረ ከሰሪዋ ነውው" አለች። በፀሎት "እሺ እሺ ይሁና ሊቦቲዬ ደና አደርሽልኝ አ" አለች። . . ..ክፍል 21 ከ 15 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል.. . . 🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀          
892
19
 ♥️ ፅናት ♥️...!!!            .            .            . 🥀..ክፍል 19..🥀        ሊባኖስ አይኗን ወደ በፀሎት መልሳ "ምን ምንድነው ያልሽው?" አለች። ፅናትም" እ! እህቴ?" አለች። በፀሎትም ለቅሶ በዘጋው አንደበቷ "እየውላቹ ምን መሰላቹ እነዚህ ሰዎች የእኛን ህይወት መልሰው ሰጥተውናል የእኛን ትዝታ፤ የእኛን ልጅነት ያለ ምንም ክፍፈያ ሰጥተውናል ዛሬ ደስ ብሎኝ በደስታ ያለቀስኩበት የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው ማለቴ በቃ እባካቹ እናንተ ያላቹሁኝን ለእህቴ ድገሙላት ሊቦቲዬም ደስታችን ደስታዋ ነውና ለሁለቱም ንገሯቸው። አለች።ፅናት የሆነ ነገር የገባት ትመስላለች ፈገግ ብላ አይንዋ በእንባ ሞላ። ባልየው መናገር ጀመረ። "እእ እየውላቹ ምን መሰላቹ ዛሬ እኔና ባለቤቴ እዚህ የመጣነው ስለ ቤቱ ጉዳይ ለመነጋገር ነው። ይህን ውሳኔ የወሰነው ተማክረንበት ነው ስለ በፀሎት እና ፅናት ቤት ጉዳይ  ነው ያው እንደሚታወቀው በፀሎት እሷ እና እህቷ ችግር ውስጥ በነበሩበት ጊዜያት ቤታቸውን ሽጣልን ነበር"። ሊባኖስ ትግስት አጣች። "በል ተናገራ የምናውቀውን ነገር ትተክ ለምን ወደገደለው አትገባም" አለች።ሰውየው "እሺ እሺ በቃ አሁን እኔም ባለቤቴም በጭራሽ ቤቱንም ሆነ ለበፀሎት የሰጠናትን ብር አንፈልገውም ስለዚህ  በቃ ከ3 ቀን በኋላ ወደ አሜሪካ ጠቅልለን ልንገባ ስለሆነ ጥሩነትም ለእራስ ስለሆነ በቃ" አለና ከደረት ኪሱ ወረቀት አውጣና ተመልከቱ ይህ ወረቀት ከ5 አመት በፊት በፀሎት እና እኛ በቤቱ  ጉዳይ የተፈራረምንበት ወረቀት ነው" ብሎ ሁሉንም በፈገግታ ፊት ካያቸው በኋላ ወረቀቱን ሁለት ቦታ ቀደደው የፅናት ልብ በደስታ ሊወጣ ደረሰ ሰውየው በድጋሜ ወረቀቱን ለአራት አረገው  ሊባኖስም የሰማችውን ማመን በጭራሽ አልቻለም።ፊቷ ላይ ያስታውቅባታል። ፅናት በፍጥነት ሄዳ አጠገብ ለአጠገብ  የተቀመጡትን ባልና ሚስት አቀፈቻቸው። ሚስትየው "በቃ አታልቅሱ ይበቃል። በቃ እኛ አሁን መሄድ አለብን" ሲሉ ፅናት እጇን ከእነሱ አንስታ ሊባኖስ ጋር ተጠምጥማ ማልቀስ ጀመረች። እነሱም ተነስተው  "ደና ሁኑ ዛሬ የምናረጋቸው ነገሮች  አሉብን  ቤቱን አድሰነዋል ጊቢውንም አሳምረነዋል ልዩ በጣም ልዩ ቤት ነው ያረግንላቹ ይህንን ያረግነው ለህሊናችን እረፈት ነው ቤቱን ከእነ ሙሉ እቃው ትወሰዱታለቹ አታመስግኑን መሆን ያለበት ነው የሆነው " አለና ተከታትለው ወጡ። ሊባኖስ የተጠመጠመችባትን ፅናት ጉንጯን ስማ ካላቀቀቻት በኋላ ልትሸኛቸው ወጣች። ፅናት እሰከ አሁን ድረስ ለቅሶዋን ካላቆመችው እህቷ በፀሎት እግር ስር ቁጢጥ ብላ ማልቀስ  ጀመረች። የአንዳቸው ለቅሶ የሊላኛቸውን እያባባሰ አይናቸው ቀልቶ እራሳቸውን እስኪያማቸው አለቀሱ ተላቀሱ ምንም ሳያወሩ በዝምታ እንባቸውን አዘሩት። ከእዚህ ለቅሶ ሊባኖስ መጥታ "ልጅ በፀሎት ሚጢጢዋ በቃ ይበቃቸዋል ዛሬ የደስታ ቀናቹ ነው ተደሰቱ መደሰትም ይገባችዋል"። አለች ፊት ለፊታቸው ቆማ ሁለቱም እንባቸውን እየጠራረጉ ፈገግ አሉ። ሊባኖስም "አዎ ፈገግ በሉ የእናንተ ህይወት በስማቹ ነው የተሰየመው ያላችሁበትን ችግር ያለፋችሁት በፀሎት እና በፅናት ነው ፀሎታቹ እና ፅናታቹ ለእዚህ አብቅቷችዋል።ልጅ ሆናቹ የትልቅ ሰው ያውም የአስተዋይ ሰው ጭንቅላት ነው ያላቹ  በፀሎቴ" አለች።ሊባኖስ ወደ በፀሎት ይበልጡኑ እያየች  በፀሎት "ወዬ ሊቦቲዬ" ስትላት "ዛሬ የደስታ ቀን ነው እህትሽ ዛሬ እስትሬት ኤ አምጥታ አልፋልሻለች"።ስትል በፀሎት እግሯ ስር ፈገግ ብላ የተቀመጠችውን ፅናት ጭንቅላቷን እየደባበሰች "ፅናቴ ሊቦቲዬ ልክ ናት እኔን መንከባከብን ፤ ለምንበላው መሯሯጥሽን ጭንቀትሽን ችለሽ በምን ፅናትሽ ነው ለእዚህ የበቃሽው?" አለች። ፅናትም "በአንቺ ፀሎት ነዋ በፀሎቴ የእኔ ልዩ እህቴ" አለችት። ሊባኖስም "ውይይ በጣምም ታስቀናላቹ" አለችና መጀመሪያ በፀሎትን ከዛ ፅናትን በተራ ግንባር ግንባራቸውን ሳመቻቸው ፅናትም ወደ ሊባኖስ እያየች "ሊቦ አንቺም የህይወቴ ብረታት ነሽ ብዙ ነገር አግዘሽኛን ስትል በፀሎት "አዎ እውነት ነው ሊቦቲዬ በጣም እንወድሻለን በጣም እናመስግንሻለን" አለች። ዛሬ በአሁኑ ሰአት ይህቺ በእዚህ ያማረ ሶፋ ላይ ደልቀቅ ብላ ጋደም ያለችው ቆንጅየዋ እህቴ በፀሎት ናት ውበቷ ከየት እንደዘነበ ለእኔ ለእራሱ ግራ ግብት ብሎኛል። ግን ችግሩ ከእኔ አትበልጥም።" አለች ፅናት እነዛ ፈጣሪ የባረካቸው ባለትዳሮች በሰጧቸው በራሳቸው ቤት ውስጥ ሳሎን እየተንጎራደደች።ፈገግ ብላ ደሞ በፈገግታ ወደ ሊላኛው አቅጣጫ ዞር ብላ "ቡና እያፈላች እጣኑን እምታጋፍጠው  ሊባኖስ ዞር ብላ ይህቺ የምታይዋት እንቁ ሴት ደሞ የእኔና የቆንጅዬ እህቴ ደጋፊ እና የህይወታችን ፋና ናት እና ደሞ ጥንካሬያችንም ናት።በነገራችን ላይ ሊቦዬ አለችና በፀሎትን አየት አርጋ ማለቴ ሊቦቴዬ" ስትል ሁለቱም "እእ" አሉ። ፅናት ፈገግ በማለት "ቀስ የምን ለወሬ መኖጥ ነው ባካቹ ምንም የምነግራቹ ነገር የለም" አለች።እህቴ ነበር ቤቱ በሶስቱ ሳቅ ድምቅቅቅ ያለው። በፀሎት ሳቋን ረገብ አረጋ "ተመስገን ተመስገን ነው የሚባለው" ስትል እጇን ወደ ላይ ዘርግታ  ሊባኖስ እና ፅናትም ሳቃቸውን አቋርጠው በእኩል ድምፅ "ተመስገንን" አሉ። በፀሎት ከት ብላ መሳቅ ጀመረች። ከዛ በፀሎት ሳቋን ስትጨረስ "ስሚኝ የእኔ ልእልት ቆንጅዬ እህት እባክሽ ፀጉሬን ልትሰሪኝ ትችያለሽ ይህንን ሳቅሽን አቁመሽ" አለች።"አዎዎ ይቻላን በደብ ነዋ ቆይ ማበጠሪያ ይዤ እመጣለው" አለችና ወደ ውጪ ወጣች። በፀሎትም ሊባኖስን "ሊቦዬ ከፅናት ጋር የጀመራችሁትን ስራ ከምን አደረሳችውት አለች። ጥሩ ነው በፀሎትእዬ ያው በር ላይ ምግብ አለ ብለን መለጠፋችን ጥሩ ነው እድሜ ለፅናቴ እሷ እንደሆነ ብሩህ ጭንቅላት ነው ያላት ዛሬ እራሱ እስከ አመሻሹ 12:30 ድረስ 30 እንፖቲቶ እና 40 ፓስቲ ነው የሸጥነው ያው ስራውን ለመጀመረ ብር የሰጡንን ባልና ሚስት  እናመስግን እንጂ የቀጠርናት ሊጥ አቡኪያችንም ምርጥ ናት  አይገረምም ግን በፀሎትእዬ ቤታችሁን በነፃ ሰጥተዋቹ እንደገና ደሞ ያለባችሁን ችግር አይተው ብር መሰጠታቸው አይ የአንዳድ ሰው ጥሩነት ግን በሰማምበስማም የሚገርም ነው"። ስትል ፅናት የሳሎኑን በር እየከፈተች "እንዴ በጣም ነዋ" አለች። በፀሎት እንዴ እህቴ ቁመሽ ስታዳምጪ ነበር እንዴ?" ስትላት "ኧረ እኔ አይገረምም ወይ የሚለውን ብቻ ነው የሰማውት" አለች። ሊባኖስም ፈገግ እያለች "ኧረ ባክሽ እና እስካሁን የት ነበርሽ?" ሰትላት አይ ጓደኛዬ መጥታ እኮ የኢንተርናሽናል ሞዴል  ፈተና ቀጣይ ወር ነው የሚል ወሬ ሰምታ ነዋ በእዚህ ሳልፍ ልንገረሽ ብዬ ነው ብላ መጣች"።ስትል በፀሎት "አይ መከራዬዬ በቃ አሁንማ ዩንቨርስቲ ስትገቢ ናፍቆቱን አልችለውም ምናለ አዲስ አበባ ቢደረሰሰሽ እና ባራቅሽኝ" አለች። ፅናት ወደ እህቷ የተቀመጠችበት ሶፋ በመሄድ "ተስተካክለሽ ተመጭ ፀጉርሽን ልስራሽ" አለች እና ከኋላዋ ቆመች። በፀሎትም ጋደም ካለችበት ትልቅ ሶፋ ላይ ፈቀቅ ብላ ደገፈ አለቻላት። ፅናት የበፀሎትን ፀጉር ለመስራት እያበጠረቻት ለስለስ ባለ ድምፅ  "ፀጉርሽ በጣም አድጓል"አለችና መሀል ጭንቅላቷን ሳም እያረገች ። .
890
20
. . ..... 𝐋𝐈𝐊𝐄 𝐒𝐇A𝐑E እያረጋቹቹቹቹ🙏 . .  ♥️ ፅናት ♥️...!!!            .            .            . 🥀..ክፍል 18..🥀           .           .           . #Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!! . . . . ሊባኖስም የቤቱን መፅዳት አይታ ኦኦኦኦ ቤቱን ፏ አርገሽዋል የእኔ ሚጢጢዬ አለችና ፍራሹ ላይ ተቀመጠች በፀሎት እንዴት አደርሽ ሊቦትዬ አለች። ፅናት ከት ብላ ስቃ ውይይይ እህቴ ሊቦን እኮ ሊባቲዬ ስትያት ሳቄነው የሚመጣው አለቻት። ፅናትም ፈገግ ብላ "ኧረ እህቴ ይህን ያክል " አለችና ፈገግ አለች።ሊባኖስም በይ ፅናቴ ቁርስሽን ቶሎ ብይና ውጤትሽን ሄደን እንየው አለቻት። ፅናትም እየተፍለቀለቀች ከሊባኖስ እቅፍ እየወጣች "እሺ ሊቦዬ አንቺ አትበይም?" አለቻት የጠቀለለችውን ጉርሻ ወደ ሊባኖስ እየወሰደች ሊባኖስ "አይ አይ ይቅርብኝ  በልቼ ነው የመጣውት" ስትላት "እሺ ኢቺን ጉረሽና አንድ ስለሚያጣላ እደግምሻለው" ስትል ሊባኖስ "አይ አይ ፅናቴ አንጣላም ግን ስለጣመኝ ድገሚኝ" አለቻት እህቴ በፀሎት በይ በይ ሊቦ ደሞ 3ተኛ ድገሚኝ ብለሽ እዳትደባደቡ " ብላ ሳቀች። ሊባኖስ "አይ  አንቺ ልጅ  በሉ ቶሎ ብሉ እና ሚጢጢዬ እንሂድ አለች።ፅናት ለሁለተኛ ጊዜ ያጎረሰቻትን ምግብ እያኘከች። ቁርስ በልተው እንደጨረሱ ፅናት ፊቷ ላይ ሻርፕ ጠምጥማ "በቃ ሊቦዬ እንሄድ" አለች።ከዛ ወደ በፀሎት ሄዳ ጉንጮቹዋን ከሳመቻት በኋላ ሻርፕ ፊቷ ላይ እየጠመጠመችላት "እህቴ በቃ እነዛ የቤታችን ገዢዎች ሊያናግሩሽ ይመጣሉ ምን አልባት ካልደረስንባቸው ምን እንዳሉሸ ትነግሪናለሽ" ብላ ከሊባኖስ ጋር ተያይዘው ወጡ።ልክ ፅናት እና ሊባኖስ በር ላይ ሲደርሱ። "ሚስትየው ወዴት ነው?" አለች። ሊባኖስም "መጣን ቅርብ ነን ግቡ በፀሎት አለች" ብላቸው ከፅናት ጋር በጋራ ተያይዘው ወጡ። የቤቱ ገዢዎች ባልና ሚስትየው "ሰላም ለእዚህ ቤት" ብለው ገቡ። በፀሎትም "ሰላም ኑ ግቡ እንኳን ደህና መጣቹ" አለች።በፀሎት ምን ሊሉኝ ነው ብላ ፈርታለች።ውስጧ ብዙ ነገር ይመላለሳል "ቆይ ቤታችሁን አንፈልግም ብሩን አምጡ ሊሉን ነው እንዴ ብላ አሰበችና ቆይ እንደዛ ቢሉኝ ብር ከየት ላመጣ ነው አይ ጣጣዬ በቃ የራሳቸው ጉዳይ በቃ የፈለጉትን ይበሉ" አለች በውስጧ ካለችበት ሀሳብ የቤቱ ገዢ አባውራ "በፀሎት በፀሎት" እያለ ደጋግሞ ሲጠራት ነው የነቃችው።አአአአቤት አለች። ሰውየው ንግግሩን ቀጠለ እየውልሽ በፀሎት እኛ የእናንተን ቤት ስንገዛ ቤቱ በጣም ያስፈልገን ነበር። አሁን ግን" መልሰው ዝም አለ። በፀሎት ጩከት በተሞላው መልኩ "አሁን ግን ምን አሁን ግን ቤቱ ሰለማያስፈልገን የኖረንበትን አስልተሸ ብሩን ስጭኝ እና ቤታችሁን ውሰዱ ልትሉኝ ነው?እ በሉዋ ተናገሩ" አለች። ሰውየው ፈገግ ብሎ ባለቤቱን አያት ባለቤቱም ፈገግ አለች። በፀሎት ዝምታቸው አስፈራት። ፅናት እና ሊባኖስ የፅናትን ውጤት ለማየት ኢንተርኔት ቤት ፍለጋ ላይ ናቸው። በመከራ እና በስንት ፍለጋ የሚሰራ ኢንተርኔት ቤት አገኙ። ሁሉም ኢንተርኔት ቤቶች መስራት አልቻሉም ነበር። ሁለቱም  በጣም ጓጉተዋል በጣም ሊባኖስ ወደ ኢንተርኔት ቤቱገብታ "ሰላም የ10ርኛ ክፍል ፈተና ውጤት ለማየት ፈልገን ነበር" አለች።ባለ ኢንተርኔት ቤቱም "እሺ ኑ ቁጭ በሉ"አላቸው። ሊባኖስ ወንበሩን ስባ ተቀመጠችና "በይ የእኔ ሚጢጢ ኮድሽን ንገሪኝ" አለቻት። በፀሎት ግራ ተጋብታ እንዴ ሊቦዬ ስለ ኮንፒውተር ታውቂያለሽ" አለቻት።ሊባኖስም መጠርጠሩስ "በያ ስጭኝ" አለቻት። በፀሎት  ፈገግ ብላ ሰጠቻት። ሊባኖስም ኮዱን አስገብታ መጠባበቅ ጀመረች ውጤቱ ተዘረገፈ።  ሊባኖስ የፅናትን ውጤት ስታይ ደነገጠች። ወደ በፅናት ስትዞር ፅናት የኢንተርኔት ቤቱ በር ላይ ቆሞ እጆቿን በአፍዋ ጭብጥ አርጋ ሊባኖስን በጭንቀት እና በጉጉት እያየቻት ነው። ፅናት የሊባኖስ የፊት ሁኔታ አስፈራት ሊባኖስ ብድግ ብላ ወደ ፅናት ተጠጋች የሊባኖስ አይኖች በእንባ ተሞልተው ደፍርሰዋል። ፅናት ልቧ በሀያሉ መምታት ጀምረዋል። ሊባኖስ በነፋስ ፍጥነት ፅናትን አቅፋ  "የእኔ ቆንጆ፤ የእኔ ጠንካራ፤ የኔ ጀግና" አለቻት። ፅናት ግራ ገባት ሊባኖስ የፅናትን እጅ ጨብጣ ከለጠፈችው አፍዋ አላቃ እየጎተተች ወደ ኮምፒውተሩ ወስዳ "ተመልከች ተመልከች ውጤትሽን"  ብላ ወደ ፅናት ስትዞር ፅናት አይኗን ጨፍናላች ሊባኖሰ "እይ የኔ ሚጢጢ" አለቻት ። ፅናት የጨፈነችውን አይኗን ገልጣ ውጤቷን አየችው ፈገግ ብላ የደስታ እንባ እያፈሰሰች  "እ እ እ እ እስስስትሬት ኤ" አለች። ሊባኖስም "አዎ አዎ እስትሬት ኤ ነው ያመጣሽው" አለች አይኗን ከ ኮምፒውተሩ ሳትነቅል ሊባኖስ ወደ ፅናት ጠጋ ብላ ፅናትን አቅፋ "የኔ የሚጢጢ የኔጀግና ጎበዝ እውነት ለመናገር እንደምታልፊም ተስፋ አላረኩም ነበር ማለቴ አለ አደል ባለብሽ ጭንቀቶች በዛ ላይ ሰርተፍኬትሽን እንድወስድልሽ ፈተናዎችሽን እንዳይልሽ ስላልፈቀድሽልኝ አሁን በጣም ጠንካራ እንደሆንሽ አውቄያለው በይ አሁን ወደ እህትሽ እንሂድ እና የምስራቹን እንገራት" አለች። ፅናትም " እሺ ሊቦዬ በቃ እንሄድ" አለች። ሊባኖስ ኮምፒውተሩ ኪቦርድ ላይ የተቀመጠውን የፅናትን አይዲ ይዛ ለባለ ኮንፒውተሩ ብር ከፈላው  ወደ ቤት መሄዳቸውን ቀጠሉ መንገዱ ረዘመባቸው  በጣም ረዘመባቸው ፅናት እህቷ ፊት ላይ ፈገግታ ማየት ያውም በእራሷ ምክንያት ማየት በጣም  ያስደስታታል ሊባኖስም እንደ ነብሷ የምትወዳቸውን የፅናት እና የበፀሎትን ፈገግታ ከፊታቸው ማየት አለምዋ ነው። በስንት ጉጉት እና ጥድፊያ ቤት ደረሱ ፅናት ሊባኖስን ጥላት  የግቢውን በረ በርግዳ በፍጥነት  ገባች  ከዛም እሮጥ ብላ ጓ ብሎ ከተከፈተው ቤታቸው ስትገባ  ፊት ለፊት ዊልቸር ላይ ተቀምጣ እየተንሰቀሰች የምታለቅስውን እህቷን አየቻት።ደነገጠች ሊባኖስም ደንግጣ ከቆመችው ፅናት እና የፅናት አይን ካረፉባት በፀሎት ፊት  ደረሰች።ሊባኖስ " በፀሎቴ ብላ ከፅናት ኋላ ስትመጣ በፀሎትን ስታይ" ደነገጠች። የቤቱ ገዢዎችም ነበሩ።ሚስትየው ፅናትን በዝምታ እያየቻት ነው። ባለቤቷ ደሞ መሬት መሬቱ አቀረቅሮ እያየ ነው። በፀሎት ዘላ እህቷ ላይ ተጠምጥማ  ወደ ቤቱ ገዢዎች እያፈጠጠች "እህቴን ምን ብላችዋት ነው?"።አለች ዝም አሉዋት ከዛ ሊባኖስም ተደርባ "በሉ መልሱላት እንጂ"እና አፈጠጠችባቸው ። የሊባኖሰሰ ድምፅ አስበርግጓቸው የባልና ሚስት ትኩረት ሙሉ ለሙሉ ወደ ሊባኖስ ሆነ። በፀሎት "ተይ ተይ ሊባቲዬ አትጩሂባቸው እኔ እማለቅሰው በደስታ  ነው" አለች። ፅናትም አይ አይ እህቴ አትዋሽኝ" አለች። ሊባኖስ ቁጣዋ ሳይበርድ "እየውልሽ አንቺ ልጅ እውነቱን ተናገሪ ብዬሻለው" አለች እና ወደ ሰዎቹ ዙራ "ቆይ ምን ብላቹሀት ነው አትናገሩም እንዴ ቆይ አፋችሁን ምን ያዛቹ" አለች።በጸሎትም "በቃ ሊቦዬ ቤቱን ሰጥተውን ነው በነፃ" አለች። . ..ክፍል 19 ከ 15 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል.. . . 🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀                  
1 248