cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

EBS TV

worldwide news🌍

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 776
Obunachilar
+424 soatlar
+127 kunlar
-130 kunlar
Post vaqtlarining boĘťlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
#Ethiopia " አምባሳደሩ ንግግራቸው ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለብን ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " - መንግሥት የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ አምባሳደር የተንጸባረቀው ሀሳብ " ሀሰተኛ እና ተቀባይነት የሌለው ነው " ብሎታል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ትላንት አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በንግግር ማሰማታቸው ይታወሳል። ይህን በተመለከተ ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ በኩል መግለጫ አውጥቷል። በዚህም የአምባሳደሩ ንግግር " በተረጋገጠ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው " ብሎታል። " በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣን መንግስት እንጥላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ፣ ንጹሃንን ከሚያግቱና ከሚያሸብሩ አካላት ጋር መንግስትን መጥቀሳቸውም ተገቢ አይደለም " ብሏል። ንግግራቸው " የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " በማለት ገልጾታል። " ከሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ወዳጅነት ላይ ከተመሰረተው ግንኙነት የተቃረነ ነው " ሲልም አክሏል። መንግሥት በመግለጫው ላይ ፤ " የተፈጸመው ዲፕለማሲያዊ ስህተት ነው " ያለ ሲሆን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመስራት የተፈጠረውን ስህተት እንዲታረም እንደሚደርግ ገልጿል። ኢትዮጵያ የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮችን ጨምሮ ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ያላትን ዝግጁነትም ገልጿል። @tikvahethiopia
170Loading...
02
" የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለንም " - የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሙያዎች " መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው " - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ6 ጤና ጣቢያዎች የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው፣ እንዲከፈላቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ጤና ባለሙያዎቹ በሰጡት ቃል፣ " እንዲከፈለን ጠይቀን ነበር። ‘#ገንዘብ የለንም እንከፍላለን’ እያሉ ነው የተበጀተ በጀት እያለ ገንዘቡን ለሌላ ጉዳይ እየተጠቀሙ ያቆዩት " ብለዋል። - ጪጩ - አንድዳ - ስሶታ - ወቸማ - ኡዶ - ቱምትቻ በተሰኙ የወረዳው 6 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከ01/06/2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/09/2016 ዓ/ም ለ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለም ነው ያሉት። ያልተከፈላቸውን ገንዘብ መጠን ሲገልጹም አንዷ ቅሬታ አቅራቢ፣ " የእኔ ከ80,000 ብር በላይ ነው። ከእኔ በላይ ደመወዝ እርከን ላላቸው ደግሞ ይጨምራል። የአንድ ሰው ከዚህ በላይ ሲሆን፣ የ6ቱ ጤና ተቋም ብዙ ገንዘብ ነው " ሲሉ አስረድተዋል። ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ የጠየቅናቸው የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ፣ " ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው " ብለዋል። ባለሙያዎቹ፣ 'የተበጀተ በጀት አለ ግን ለሌላ ጥቅም እያዋሉት ነው ያዘገዩብን' ላሉት ቅሬታ በሰጡት ምላሽ ኃላፊው፣ " እንደዛ አይደለም። በጀቱ ተይዟል እውነት ነው። ነገር ግን የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንጂ ወረዳውም ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል። የዞኑ የብልጽግና ጽ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አይደፈር ሽፈራው በበኩላቸው ፤ ችግሩ የጥሬ ገንዘብ እጥረት መሆኑን ገልጸው፣ ለ3 ዓመታት የዱቲ ክፍያ 6.4 ሚሊዮን ብር እንደተበጀተ፣ ገንዘቡን ለማፈላግለግ እየተሰራ እንደሆነና ዱቲ የሚከፈላቸው የባለሙያዎች ብዛት መረጃም እየተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
250Loading...
03
" ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈተ ህይወት ጋር በተያያዘ ምርመራ እያደረገ ነው " - አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ህይወቷ አልፏል። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን ሞት 'ድንገተኛ ህልፈት'  በማለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ የሀዘን መልዕክት አሰራጭቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዋ ' #በጩቤ_ተወግታ ህይወቷ እንዳለፈ ' የሚገልፁ መረጃዎችን ተመልክቷል። ይህን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን አነጋግሯል። በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አመራር፤ " ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈት ጋር በተያያዘ የጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያደረገ ይገኛል " ብለዋል። " በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተሰራጨው መረጃ ጉዳዩ ገና በፖሊስ የተያዘ በመሆኑን ነው " ሲሉ አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን አስክሬን ወደቤተሰቦቿ አሸኛኘት ማድረጉንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። Via @tikvahuniversity
200Loading...
04
" ችግሩ በሚባለዉ ደረጃ የተጋነነ ባይሆንም ጊዜያዊ እርምጃ ለመዉሰድ እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባሉ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህራን ሁሉም በሚባል መልኩ ትምህርታቸዉን በፋይናንስ እጥረት እየተማሩ አለመሆኑን የደቡብ ኢትዬጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል። ወንዶች ትምህርት መማር ሲገባቸው የቀን ስራ እየሰሩ እንደሆነና ሴቶችም ላልተፈለገ ችግር መጋለጣቸውን ጠቁሞ ነበር። ተማሪዎቹ በ2015 ዓ/ም ወደ ኮሌጆች ሲገቡ ከመንግስት የሚሰጣቸዉ 450 ብር በቂ እንዳልሆነ እየታወቀ ቢጀመርም እስካሁን አለመስተካከሉንና ለዚህም በተከታታይ ደብዳቤ መጠየቁን ማህበሩ መግለጹ አይዘነጋም። ጉዳዩን በተመለከተ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስተያየቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቷል። የቢሮው ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ታምራት ይገዙ ፤ " ጉዳዩ በተባለዉ ልክ የተጋነነ ባይሆንም የተወሰነ ችግር መኖሩን አውቀን እየሰራንበት ነው " ብለዋል። " ለችግሩ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ለመስጠት እንቅስቃሴ ጀምረናል " ያሉት ሀላፊው " አሁን ላይ ተማሪዎቹ ያለባቸዉን የቤት ኪራይ ችግር ለማቅለል ከዲላ እና ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መነጋገር ጀምረናል " ብለዋል። ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጥሩ መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት ዶ/ር ታምራት ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋርም ሂደቱ ጥሩ መሆኑን አመልክተዋል። " በቋሚነት ችግሩን ለማስተካከል እየሰራን ነው። ምናልባትም ለሚቀጥለዉ አመት ሲመጡ የሚከፈላቸዉ ገንዘብም ይጨምራል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ገልጸዋል። #TikvahEthiopiaFamilyHawassa @tikvahethiopia
210Loading...
05
#ቡሬ ➡️ “ 15 ተፈናቃዮች ናቸው በሚሊሻ የተወሰዱት ” - በአማራ ክልል የሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች ➡️“ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” - አቶ ኃይሉ አዱኛ በ2013 ዓ/ም ከኦሮማያ ክልል #ተፈናቅለው በአማራ ክልል ቡሬ ፣ ቻግኒ ፣ ፍኖተ ሰላም ፣ ባሕር ዳር የነበሩ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ወደ ወለጋ ለመመለስ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ሰንቶም ቀበሌና ጣቦ የገጠር ከተማ ላይ ድንገተኛ ችግር እንደገጠማቸው አሳውቀዋል። ተፈናቃዮቹ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፣ “ እየሄድን እያለ ሶንቶምና ጣቦ ላይ አደጋ አጋጠመን። የሕዝብ ማዕበል መጣብን። ኬላ ላይ ተይዘን በ1ዐ ተሽከርካሪዎች የተሳፈርን ተፈናቃዮች አወረዱን እና ተሰቃየን በጣም ” ብለዋል። “ ወጣቶች ድንጋይ፣ መሳሪያ ይዘው (ያልያዙት መሳሪያ የለም) ወጡ፣ ልክ አሸባሪ እንደሄደ እንጂ ተፈናቃይ አልመሰልናቸውም። ‘ከዚህ ቀደም በጦርነት ሲሳተፉ የነበሩ ናቸው’ እየተባለ ተፈናቃዮቹ እየተመረጡ ተያዙ ” ነው ያሉት። “ 15 ተፈናቃዮች በሚሊሻ ተወስደዋል ፤ ሊገድሏቸው ሲሉ መከላከያ ወደ ካምፕ ወስዷቸዋል። ቀሪዎቹ ጫካ አድረን ወደ #ቡሬ_ተመልሰናል። በድንጋይ የተመቱ አሉ። ሰዎቹ ' እንደምትመጡ ማወቅ ነበረብን ጠብ እንዳንፈጥር ' ነው ያሉት ” ሲሉ ተናግረዋል። ተፈናቃዮቹን ወደ ምሥራቅ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገር መከላከያ አጅቦ ሊመልሳቸው ፣ የወለጋ ኃላፊዎች ደግሞ ሊቀበሏቸው ቅድሚያ ቢነገራቸውም የሸኟቸው ሚሊሻዎች መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ አስረድተዋል። ሚሊሻዎቹ ከዓባይ ወደዛ ለመሻገር ስላልቻሉ፣ የወለጋ ዞኖች ኃላፊዎችም ‘ ትዕዛዝ አልተሰጠንም ’ በማለት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከሞት አምልጠው ወደ ቡሬ ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል። የአማራ ክልል ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ለምን ጥበቃ እንዳልተደረገላቸው ጥያቄ የቀረበላቸው የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛም፣ “ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” ነው ያሉት። “ ደብረ ብርሃን፣ ወሎ ካምፕ ያሉትን ቅድሚያ ተሰጥቶ በ1ኛው ዙር 1,600፣ በ2ኛው ከ400 በላይ ሰዎች ተመልሰዋል” ሲሉ አስታውሰው ፣ “ በሶስተኛው ዙር ለመመለስ ደግሞ ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ” ብለዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
550Loading...
06
#የአሜሪካ_አቋም! " ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ? - በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው። - የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል። - ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል። - የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል። - ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ። - በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም። - ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው። - ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው። - የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ። - በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው። - በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።   - ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት። - የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል። - ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች። - የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል። - ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል። - ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው። - የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል። - ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል። - ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል። #USEmbassyAddisAbaba #VOA #EthiopiaInsider @tikvahethiopia
550Loading...
07
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም ' ማለታቸው ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " ብለዋል። ከመንግስት ጋር በታንዛንያ የሰላም ንግግር ሲያደርጉ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) ተዋጊዎችን " በድርድር ተስፋ ሳትቆርጡ ፤ መተማመንን ለመገንባት ጥረት አድርጉ " ብለዋቸዋል። አሜሪካ ይህን ያለችው ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ በአምባሳደሯ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት ነው። በአዲስ አበባ ፤ መርካቶ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የአሜሪካን ግቢ በነበረ መርሀ ግብር የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር። Video Credit : US Embassy Addis Ababa / Ethiopia Insider @tikvahethiopia
1570Loading...
08
#SouthEthiopiaRegion በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል። በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም። ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመመገብም ሆነ ልጆቻቸዉን ለማስተማር መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል። የገዢዉ ፓርቲና የክልሉ ባለሥልጣናት ሠራተኞቹን " በትዕግሥት ጠብቁን " የሚል ምላሽ ቢሰጡም ሠራተኞቹ ግን " ረሐብ እንዴት ቀን ይሰጣል ? " በማለት ጠይቀዋል። ሠራተኞቹ በወረዳው በተለያዩ ጽ/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሠራተኞቹ ተወካዮች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። @tikvahethiopia
1280Loading...
09
#ProsperityParty #TPLF ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል። ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል። ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል። ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል። " ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል። ከዚህ ባለፈ ፦ - " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። - ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል። - የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል። - ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል። - የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ #ProsperityParty #TPLF @tikvahethiopia
1160Loading...
10
#Tigray ከማረት ከተስረቁት 2 መኪኖች አንደኛዋ መገኘቷን ፓሊስ አስታወቀ። ማሕበር ረድኤት ማሕበር (ማረት) በመጋቢት እና በያዝነው ግንቦት ወር አንድ ላንድክሩዘር V8 እና ላንድክሩዘር ማርክ 2 መኪናዎችን ተዘርፏል። የድርጅቱ ንብረት የሆነች በሰሌዳ ቁጥር 35 - 2723 የተመዘገበችው V8 መኪና መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተሰርቃ ሳትገኝ የውሃ ሽታ ሆና ቀርታ ነበር። ይህች መኪና ሳትገኘ ከቀናት በፊት ላንድ ክሮዘር ማርክ 2 መኪና ተዘርፋለች።  ፓሊስ የድርጅቱ መኪኖች ያየና ያገኘ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ በያዝነው ሳምንት የተሰረቀችው ላንድክሩዘር ማርክ2 መኪና ከመቐለ በ250 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አክሱም ከተማ በፓሊስ ተይዛለች። የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ መኪናዋ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 በፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋልዋን አሳውቋል። ፖሊስ መኪናዋን ያገኘው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ክትትል ነው። በሰዓቱ መኪናዋን የያዛት ሹፌር ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ማክሸፉን አሳውቋል። ከነሹፌሩ በተጨማሪ " የኔ ንብረት ናት " የሚል አመልካችም በፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል። የአክሱም ከተማ ፖሊስ " መሰል ስርቆት ከጦርነቱ በኋላ መታየት የጀመረና በትግራይ ያልተለመደ ነው " ያለ ሲሆን " ማንኛውም ወንጀለኛ ከህዝብ አይንና ጀሮ መደበቅ አይችልም ብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ስለ መኪኖቹ ስርቆት ከማሕበር ረድኤት ትግራይ (ማረትረት) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።                                             @tikvahethiopia            
1200Loading...
11
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን እኮ ከኢህአዴግ መጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ 30 ዓመታት ስንጠይቅ ቆይተናል። አሁንም ቢሆን መልክ አልይዝ እያለ ያስቸገረው / ለያዥና ለገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው። ስልጣንን በMonopoly መያዝ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እንደ ባህል ተይዟል። አሁንም ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መሪዎች ከዛ አልወጣ አሉ። ውጤቱ ደግሞ የታወቀ ነው።  ደርግ ወጣቶችን ጨፍልቆ ነው የሄደው ፤ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት አገሪቱን ቀላል ያልሆነ ቀውስ ውስጥ ከቷት ነው ጡረታ የወጣው ፤ ብልጽግናም በባሰ መንገድ ይህንኑ ሁኔታ እየተከተለ ነው። የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ' ከድጡ ወደ ማጡ ' ተብሎ የሚገለጽበት ደረጃ ላይ ነው።  መፍትሄው ቁጭ ብሎ መወያዬት ነው። ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን #ከመገዳደል ፓለቲካ ወደ #መደራደር ፓለቲካ ማምጣት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። " Q. በየጊዜው የንጹሐን ሕይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነው። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም የሞት ጊዜን እንደማፋጠን ሆኖ ይስተዋላል።  መፍትሄ እንዲመጣ ምን እየሰራችሁ ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና፦ " ለ30 ይሁን ለ6ቱ ዓመታት በዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን እንዲያሰፉ ደጋግመን ስንጠይቅ ነበር። አሁንም ያን መጠየቅ ቀጥለናል። ሜዳው / ምህዳሩ ግን በተቃራኒው እየጠበበ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በአገሪቷ ላይ እየተንሰራፉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው። ምህዳሩ ካልሰፋ፣ ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል መልክ ካልያዘ፣ ወጣቱንም ወደ ጫካ እየተገፋ የትም አያደርሰንም። " Q. ከመንግስት የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ጫና ያለበት የእኛ ፓርቲ ነው። ለምሳሌ የዛሬ 4 ዓመት ከ200 በላይ ቢሮዎች ነበሩን፤ አሁን ያሉን 3 ብቻ ናቸው። አባሎቻችን #ግድያ እና #እስራት ይፈጸምባቸዋል።  ለምሳሌ ፦ የምሥራቅ ወለጋ የቢሮ ኃላፊ ከተወሰደ የት እንደገባ አላወቅንም 2 ዓመታት ሊሆነው ነው። የምሥራቅ ሸዋ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላችን ለዚያውም የዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ታስሯል። አምቦ 4 ወጣቶች ታስረው 2 ሳምንታት ሆኗቸዋል። " Q. #ብልሹ_አሰራርና #ሙስናን በተመለከተ ኢትዮጵያ በምን ደረጃ ትገኛለች ? መፍትሄውስ ? ፕ/ር መራራ ጉዲና ፦ " በኢትዮጵያ ታሪክ የተለዬ/የከፋ የሙስና ደረጃ ነው ያለው። መንግስትና ተቋማቱ የአንድ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲዋቀሩ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ። አሁንም መንግስት ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንደገና ካልተዋቀረ በስተቀር፣ ከዚህ በሽታ የምንወጣበት መንገድ ያለ አይመስለኝም። Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ አማሮታል። ፓርቲያችሁ ለመንግስት ያላችሁ ግምገማን ቢያጋሩ ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ዜጎች እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ደርሰዋል። መንግስት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ ተይቀናል። መንግስት ግን ጆሮ ያለው አይመስልም። ችግሩ ግን እጅግ በጣም ፈታኝ ነው። " Q. በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " የፓለቲካ ምህዳር ለማግኘት የመገዳደል ፓለቲካው እንዲቆም እየጠየቅን ነው። ምርጫ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው። ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስቻይ የሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም። ትልልቆቹ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነት ውስጥ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄ የምናየው ነው። መደራጀቱን ቀጥለናል። " #TikvahEthiopiaFamilyAA #ቲክቫህኢትዮጵያ #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ? @tikvahethiopia
930Loading...
12
" ሞተዋል !! " - ዓለም አቀፉ ፍ/ቤት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይፈለጉ የነበሩ የመጨረሻው ሁለት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተከሳሾች መሞታቸውን ማረጋገጡን በጉዳዩ ላይ የተቋቋመው ችሎት አስታውቋል። ርያንዱካዮ በሚል ስም ብቻ የሚጠራው እና ቻርለስ ሲኩብዋቦ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ጉዳይ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ችሎት ሲፈለጉ የነበሩ የመጨረሻዎቹ ተከሳሾች ናቸው። በብሔራዊ ደረጃ ግን አሁንም ድረስ ከ1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በመፈለግ ላይ ናቸው። 2ቱ ግለሰቦች ከ30 ዓመት በፊት 800 ሺ ቱትሲዎችን እና ለዘብተኛ ሁትዎችን በጨረሰው የዘር ፍጅት ላይ ተሳትፎ አላቸው በሚል ለሩዋንዳ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በእ.አ.አ 1995 ክስ ቀርቦባቸው ነበር። ሲኩብዋቦ በእ.አ.አ 1998 በቻድ መሞቱን እና በዛው መቀበሩን እንዲሁም ርያንዱካዮ ደግሞ ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከሸሸ በኋላ ከዛም ወደ ዛየር ተሻግሮ ኪንሻሳ ላይ በ1998 ሕይወቱ ማለፉን ፍ/ቤቱ አስታውቋል። በሩዋንዳው የዘር ፍጅት ጉዳይ በዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ሲፈለጉ የነበሩ ተከሳሾች ሁሉ መለየታቸውንም ችሎቱ አስታውቋል። #ቪኦኤ #RwandaGenocide @tikvahethiopia
1300Loading...
13
#Ethiopia የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። አዲሱ አዋጅ የግል ፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰው ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል። ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች አሻሽሏል የተባለ ሲሆን የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል ተብሏል። አዋጁ ምን ይዟል ? - ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ ይችላል። NB. በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት " መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው "። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው " ለመንግስት እና ለህዝብ " ነው። - የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልበታል። - የወል ወይም የመንግስት ይዞታ ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር ይቀጣል። - ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል። - ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል። - ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል። ምንጭ፦ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @tikvahethiopia
1460Loading...
14
#Ethiopia ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡ ከተመሩት ረቂቅ አዋጆች መካከል አንዱ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ነው። የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አዋጁ በስራ ላይ ከዋለ 6 አመት ያስቆጠረ መሆኑንና አሁን ካሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር ማጣጣም ማስፈለጉን ገልጸዋል። የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሀይል ምልመላና መረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሁሉንም ባካተተና ብዝሀነትን በጠበቀ መልኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ፦ ➡ የደሞዝ ጭማሪ፣ ➡ የደሞዝ እርከን፣ ➡ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ማትጊያና ማበረታቻ ስርአት፣ ➡ የሰራተኞች ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስልጠና አሰጣጥ ስራ ስምሪት እና ነጻ ገለልተኛ ስርአት መገንባት፣ ➡ የመንግስት ሰራተኛነት ውል ማቋረጥና ማራዘም የሚሉና ሌሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 13/2016 ሆኖ በሙሉ ደምጽ ለሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡ ሌሎች ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመሩ ረቂቅ አዋጆች ምንድናቸው ? በዚህ ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Ethiopia-05-14-8 @tikvahethiopia
1621Loading...
15
በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ገንዘብ ? በየዩኒቨርሲቲዎች " ለሥራ ኃላፊዎች የሚከፈል ክፍያ " በሚል የሚመዘበረው ገንዘብ  ከፍ ያለ ነው። ሰዎቹ ከመንግሥት በጀት / አካል ውጭ ተጻጽፈን በሚመጣልን ድጋፍ ፕሮጀክት እየሰራን ብር ይከፈለናል ነው የሚሉት። ክፍያው ግን እጅግ የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ ግልጽነት የጎደለው፣ ብዙ ጥርጣሬንም የሚያጭር ነው። መንግሥት ደመወዛቸውን እየከፈላቸው እያለ " ላስተባበሩበት " በሚል እዛው ግቢያቸው ውስጥ ለሚሰራ ስራ የሚከፈላቸው ብር ብዛት የሚገርም ነው። ለአብነት፦ ሰሞኑን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚፈጸም አይን ያፈጠጠ የለየለት የህዝብ ሀብት ምዝበራን በተመለከተ በተሰራጨው የፋና ምርመራ ዘገባ ላይ ዶ/ር ተመስገን ቶማስ በሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ብቻ የተከፈላቸው ገንዘብ በርከት ያለ ነው። ዶክተሩ ምንም እንኳን " ቁጥሩም እኮ ሳይገለጽ መነጋገር እንችላለን " ቢሉም አይገለጽ ያሉት ቁጥር ግን ይህንን ይመስላል። ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 1) ➡ 11,700 ብር (ሰንድ 2) ➡ 23,212 ብር (ሰንድ 3) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 4) ➡ 7,800 ብር (ሰንድ 5) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 6) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 7) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 8) ➡ 15,600 ብር (ሰንድ 9) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 10) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 11) ➡ 22,000 ብር (ሰንድ 12) ➡ 17,500 ብር (ሰንድ 13) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 14) ➡ 39,000 ብር (ሰንድ 15) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 16) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 17) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 18) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 19) ➡ 21,450 ብር (ሰንድ 20) እኚህ ሁሉ በሰኔ ወር 2013 የተከፈሉ ናቸው። ዶክተሩ ግን እስቲ ልየው 😳 በሰኔ ወር ነው የተከፈለው ? ብለው ይጠይቃሉ ዶክመቱም ይሰጣቸዋል፤ በኃላም ዶክመንቱን ያገላብጡና " እስቲ 2013 የሚለው የታለ ? " ሲሉ ድጋሜ ይጠይቃሉ " ይኸው ! " ይባላሉ ፤ በዝምታ ከተዋጡ በኃላ " እ ! " ብለው ዶክመንቱን መልሰዋል። ዶ/ር ተመስገን በተለያየ ጊዜ የተባከ ክፍያ የፋይናንስ ባጀት ስለሌለ በአመቱ መጨረሻ ባጀት ሲያገኝ ገብቶ ነው እንጂ በአንዴ የተላከ አይደለም ብለው ተከራርክረዋል። ሌላው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሐንስ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ሲሆን " እኔ ብዙ ፕሮጀክት ስለምሰራ ነው። ቀንም ማታም ቅዳሜና እሁድም በፕሮጀክት  ላይ ሰራው ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ ለዛ ነው የተከፈለኝ ባይ ናቸው። ዳይሬክተሩ በቀን 18 ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም 13,650  ብር እንዲገባላቸው የታዘዘበት ዶክመት የተገኘ ሲሆን በቀን 23 / 2013 ዓ/ም 15,600 ብር እንዲገባላቸው ታዟል በተመሳሳይ ቀን 19,600 ብር እንዲገባላቸው ተደርጓል። ሌሎችም በርካቶች ናቸው ነው ያሉት። ዶ/ር ተመስገን ጨምሮ አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ዶክተር ሀብታሙ አበበ ጋር የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ስም በክፍያ ዶክመት ላይ " ፕሮጀክት " ተብሎ ተገኝቷል። በአጠቃላይ በዋቸሞም ሆነ በመሰል ተቋማት በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ብር እጅግ ብዙ ፣ ከደመወዛቸው እጥፍ፣ ግልጽነት የጎደለው ነው። ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎችስ ? @tikvahethiopia
1350Loading...
16
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ? በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲፈጸም እንደቆየ የተነገረለት እጅግ በጣም የለየለት የህዝብ ገንዘብ እና ሀብት ምዝበራን የሚያሳይ የ " ፋና ቴሌቪዥን " የምርመራ ዘገባ ከሰሞኑን ለህዝብ ተሰራጭቶ ነበር። 👉 በአበል መልክ የሚመዘበረው ገንዘብ ፦ የተቋሙ ገንዘብ በአበል መልክ ይመዘበራል። ለአብነት ሁለት የፋይናንስ ቡድን መሪዎች ከፍተኛ አበል ለራሳቸው ከፍለዋል። አቶ መሰረት ለማ የተባሉት ግለሰብ በ6 ወራት ብቻ የ1 ሺህ 496 ቀን ይህ ማለት 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል ተከፏላቸዋል። አቶ ደስታ ደቦጭ የሚባሉት ደግሞ የ940 ቀን አበል ወስደዋል። ➡️አቶ ደስታ የስንት ቀን አበል ወሰዱ ? ሲባሉ " የ790 ቀን ነው የወሰድኩት " ብለዋል። ወስደዋል እንዴ ? ተብለው በመርማሪ ጋዜጠኛው ሲጠየቁ " #አልወሰድኩም " ሲሉ ቃላቸውን አጥፈው ተናግረዋል። ➡️አቶ መሰረት የ1 ሺህ 496 ቀን አበል ወደ አካውንቶ ገብቷል ? ተብለው ሲጠየቁ " ይሄ ስህተት ነው የተሰሳሳተ ነው " ሲሉ መልሰዋል። የተቋሙ ፋይናስ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ዮሐንስ ፥ " እኔ ለረጅም ወራት ፍቃድ ላይ ነበርኩኝ የህመም ፍቃድ ላይ ከመጣሁ በኃላ ነው እንደዚህ አይነት ነገር እሰማ ነበር " ብለዋል። አቶ ደስታ ግን በዚህ አይስማሙም፤ አቶ ማርቆስ ታመው ቤት የተቀመጡት 2 ወር ብቻ እንደነበር የወጣው ደግሞ የ5 ወር መረጃ እንደሆነ ገልጸዋል። 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ አጋልጠዋል። ቀደም ሲል " እኔ አበል አልወሰድኩም " ያሉት አቶ ደስታ 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ እሱ እያለ ነው የተከፈሎት ? ተብለው ሲጠየቁ " ምኑን ? እንደ ስራ ባህሪ የተከፈለኝ ነገር ሊኖር ይችላል " ሲሉ መልሰዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ሀብቶሙ አበበ (ዶ/ር) ፥ " በሰነድ የተረጋገጠ ነው ብሎ የውጭ ኦዲት ያመጣውን ያክል አስመልሰናል ሰራተኞቹ ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል፤ በዲስፒሊም እየተጠየቁ ናቸው የኛ ኦዲት ያመጣውን የትራዛክሽኑን ቼክአፕ በህግ እንዲጣራ ክትትል እየተደረገ ነው " ብለዋል። የፋይናስ ስርአታቹ ክፍተት ያሉት ይመስላል ሲባሉ " በፍጹም በፍጹም !! " ሲሉ መልሰዋል። 👉 ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ስለወጣበት ፕሮጀክት ፦ ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ግልጽነት በጎደለው መልኩ ተፈጽሟል። በዚህ ጉዳይ ፕሬዜዳንቱ እና የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እርስ በእርስ የሚያወዛግብ ምላሽ ነው የሰጡት። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ያለ ሰነድ ከእውቅናቸው ውጭ ገንዘቡ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይገልጻሉ። ክፍያ ሲፈጸም ሰነድ እጃቸው ላይ እንደሌለ እና እሳቸውም እንዳልተሳተፉ ተናግረዋል። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ " እኔ እኮ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠኝም ፤ እንደሚንቀሳቀስ አያለሁ እሰማለሁ " ብለዋል። ገንዘቡን እኔ አላንቀሳቅስም ነበር ብለዋል። ፕሬዜዳንቱ ግን የኦክስጂን ፕሮጀክት በጀቱ ሲመራ የነበረው በፋይናንስ ነው ሲሉ መልሰዋል። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እኔ ሳላውቅ ነው ክፍያው የተፈጸመው ሲሉ ተናግረዋል። የቀድሞ ም/ፕሬዜዳንት ፀደቀ ላምቦሬ (ዶክተር) ፤  የአካውንቱ ጉዳይ በዋነኝነት የሚመለከተው ፕሬዜዳንቱን እንደሆነ ገልጸዋል። ▪️ለኦክስጅን ማምረቻው መሳሪያውን ያቀረበው ያለጨረታ ያለፍቃድ ያለውድድር 240 ሚሊዮን 988 ሺህ ብር ተሰጥቶታል። ለድርጁ ሙሉ ክፍያ ቢከፈልም ዝርጋታው ግን አላለቀም ስራውም አልተሰራም። ከተጀመረ 2 ዓመት አልፎታል። የምርመራ ዘገባውን ይመልከቱ👇 https://youtu.be/wREkP5S8zNM?feature=shared (አዘጋጅ ፦ ጋዜጠኛ አፈወርቅ እያዩ) @tikvahethiopia
1110Loading...
17
" በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " - ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የትምህርት ሚኒስቴር እና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው መገምገሙን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምር እና የ14 የአፕላይድ አጠቃላይ 22 ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር መገምገሙ ተነግሯል። በግምገማው ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ፤ የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ይገባል ብለዋል። አስፈጻሚ መ/ቤቶች እና የስራ ሀላፊዎች በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ፤ " በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " ብለዋል። ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡ @tikvahethiopia
1090Loading...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " አምባሳደሩ ንግግራቸው ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለብን ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " - መንግሥት የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ አምባሳደር የተንጸባረቀው ሀሳብ " ሀሰተኛ እና ተቀባይነት የሌለው ነው " ብሎታል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ትላንት አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በንግግር ማሰማታቸው ይታወሳል። ይህን በተመለከተ ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ በኩል መግለጫ አውጥቷል። በዚህም የአምባሳደሩ ንግግር " በተረጋገጠ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው " ብሎታል። " በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣን መንግስት እንጥላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ፣ ንጹሃንን ከሚያግቱና ከሚያሸብሩ አካላት ጋር መንግስትን መጥቀሳቸውም ተገቢ አይደለም " ብሏል። ንግግራቸው " የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " በማለት ገልጾታል። " ከሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ወዳጅነት ላይ ከተመሰረተው ግንኙነት የተቃረነ ነው " ሲልም አክሏል። መንግሥት በመግለጫው ላይ ፤ " የተፈጸመው ዲፕለማሲያዊ ስህተት ነው " ያለ ሲሆን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመስራት የተፈጠረውን ስህተት እንዲታረም እንደሚደርግ ገልጿል። ኢትዮጵያ የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮችን ጨምሮ ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ያላትን ዝግጁነትም ገልጿል። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለንም " - የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሙያዎች " መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው " - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ6 ጤና ጣቢያዎች የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው፣ እንዲከፈላቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ጤና ባለሙያዎቹ በሰጡት ቃል፣ " እንዲከፈለን ጠይቀን ነበር። ‘#ገንዘብ የለንም እንከፍላለን’ እያሉ ነው የተበጀተ በጀት እያለ ገንዘቡን ለሌላ ጉዳይ እየተጠቀሙ ያቆዩት " ብለዋል። - ጪጩ - አንድዳ - ስሶታ - ወቸማ - ኡዶ - ቱምትቻ በተሰኙ የወረዳው 6 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከ01/06/2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/09/2016 ዓ/ም ለ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለም ነው ያሉት። ያልተከፈላቸውን ገንዘብ መጠን ሲገልጹም አንዷ ቅሬታ አቅራቢ፣ " የእኔ ከ80,000 ብር በላይ ነው። ከእኔ በላይ ደመወዝ እርከን ላላቸው ደግሞ ይጨምራል። የአንድ ሰው ከዚህ በላይ ሲሆን፣ የ6ቱ ጤና ተቋም ብዙ ገንዘብ ነው " ሲሉ አስረድተዋል። ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ የጠየቅናቸው የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ፣ " ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው " ብለዋል። ባለሙያዎቹ፣ 'የተበጀተ በጀት አለ ግን ለሌላ ጥቅም እያዋሉት ነው ያዘገዩብን' ላሉት ቅሬታ በሰጡት ምላሽ ኃላፊው፣ " እንደዛ አይደለም። በጀቱ ተይዟል እውነት ነው። ነገር ግን የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንጂ ወረዳውም ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል። የዞኑ የብልጽግና ጽ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አይደፈር ሽፈራው በበኩላቸው ፤ ችግሩ የጥሬ ገንዘብ እጥረት መሆኑን ገልጸው፣ ለ3 ዓመታት የዱቲ ክፍያ 6.4 ሚሊዮን ብር እንደተበጀተ፣ ገንዘቡን ለማፈላግለግ እየተሰራ እንደሆነና ዱቲ የሚከፈላቸው የባለሙያዎች ብዛት መረጃም እየተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈተ ህይወት ጋር በተያያዘ ምርመራ እያደረገ ነው " - አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ህይወቷ አልፏል። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን ሞት 'ድንገተኛ ህልፈት'  በማለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ የሀዘን መልዕክት አሰራጭቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዋ ' #በጩቤ_ተወግታ ህይወቷ እንዳለፈ ' የሚገልፁ መረጃዎችን ተመልክቷል። ይህን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን አነጋግሯል። በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አመራር፤ " ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈት ጋር በተያያዘ የጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ሾር በማዋል ምርመራ እያደረገ ይገኛል " ብለዋል። " በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተሰራጨው መረጃ ጉዳዩ ገና በፖሊስ የተያዘ በመሆኑን ነው " ሲሉ አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን አስክሬን ወደቤተሰቦቿ አሸኛኘት ማድረጉንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። Via @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ችግሩ በሚባለዉ ደረጃ የተጋነነ ባይሆንም ጊዜያዊ እርምጃ ለመዉሰድ እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባሉ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህራን ሁሉም በሚባል መልኩ ትምህርታቸዉን በፋይናንስ እጥረት እየተማሩ አለመሆኑን የደቡብ ኢትዬጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል። ወንዶች ትምህርት መማር ሲገባቸው የቀን ስራ እየሰሩ እንደሆነና ሴቶችም ላልተፈለገ ችግር መጋለጣቸውን ጠቁሞ ነበር። ተማሪዎቹ በ2015 ዓ/ም ወደ ኮሌጆች ሲገቡ ከመንግስት የሚሰጣቸዉ 450 ብር በቂ እንዳልሆነ እየታወቀ ቢጀመርም እስካሁን አለመስተካከሉንና ለዚህም በተከታታይ ደብዳቤ መጠየቁን ማህበሩ መግለጹ አይዘነጋም። ጉዳዩን በተመለከተ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስተያየቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቷል። የቢሮው ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ታምራት ይገዙ ፤ " ጉዳዩ በተባለዉ ልክ የተጋነነ ባይሆንም የተወሰነ ችግር መኖሩን አውቀን እየሰራንበት ነው " ብለዋል። " ለችግሩ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ለመስጠት እንቅስቃሴ ጀምረናል " ያሉት ሀላፊው " አሁን ላይ ተማሪዎቹ ያለባቸዉን የቤት ኪራይ ችግር ለማቅለል ከዲላ እና ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መነጋገር ጀምረናል " ብለዋል። ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጥሩ መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት ዶ/ር ታምራት ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋርም ሂደቱ ጥሩ መሆኑን አመልክተዋል። " በቋሚነት ችግሩን ለማስተካከል እየሰራን ነው። ምናልባትም ለሚቀጥለዉ አመት ሲመጡ የሚከፈላቸዉ ገንዘብም ይጨምራል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ገልጸዋል። #TikvahEthiopiaFamilyHawassa @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
Photo unavailableShow in Telegram
#ቡሬ ➡️ “ 15 ተፈናቃዮች ናቸው በሚሊሻ የተወሰዱት ” - በአማራ ክልል የሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች ➡️“ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” - አቶ ኃይሉ አዱኛ በ2013 ዓ/ም ከኦሮማያ ክልል #ተፈናቅለው በአማራ ክልል ቡሬ ፣ ቻግኒ ፣ ፍኖተ ሰላም ፣ ባሕር ዳር የነበሩ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ወደ ወለጋ ለመመለስ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ሰንቶም ቀበሌና ጣቦ የገጠር ከተማ ላይ ድንገተኛ ችግር እንደገጠማቸው አሳውቀዋል። ተፈናቃዮቹ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፣ “ እየሄድን እያለ ሶንቶምና ጣቦ ላይ አደጋ አጋጠመን። የሕዝብ ማዕበል መጣብን። ኬላ ላይ ተይዘን በ1ዐ ተሽከርካሪዎች የተሳፈርን ተፈናቃዮች አወረዱን እና ተሰቃየን በጣም ” ብለዋል። “ ወጣቶች ድንጋይ፣ መሳሪያ ይዘው (ያልያዙት መሳሪያ የለም) ወጡ፣ ልክ አሸባሪ እንደሄደ እንጂ ተፈናቃይ አልመሰልናቸውም። ‘ከዚህ ቀደም በጦርነት ሲሳተፉ የነበሩ ናቸው’ እየተባለ ተፈናቃዮቹ እየተመረጡ ተያዙ ” ነው ያሉት። “ 15 ተፈናቃዮች በሚሊሻ ተወስደዋል ፤ ሊገድሏቸው ሲሉ መከላከያ ወደ ካምፕ ወስዷቸዋል። ቀሪዎቹ ጫካ አድረን ወደ #ቡሬ_ተመልሰናል። በድንጋይ የተመቱ አሉ። ሰዎቹ ' እንደምትመጡ ማወቅ ነበረብን ጠብ እንዳንፈጥር ' ነው ያሉት ” ሲሉ ተናግረዋል። ተፈናቃዮቹን ወደ ምሥራቅ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገር መከላከያ አጅቦ ሊመልሳቸው ፣ የወለጋ ኃላፊዎች ደግሞ ሊቀበሏቸው ቅድሚያ ቢነገራቸውም የሸኟቸው ሚሊሻዎች መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ አስረድተዋል። ሚሊሻዎቹ ከዓባይ ወደዛ ለመሻገር ስላልቻሉ፣ የወለጋ ዞኖች ኃላፊዎችም ‘ ትዕዛዝ አልተሰጠንም ’ በማለት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከሞት አምልጠው ወደ ቡሬ ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል። የአማራ ክልል ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ለምን ጥበቃ እንዳልተደረገላቸው ጥያቄ የቀረበላቸው የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛም፣ “ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” ነው ያሉት። “ ደብረ ብርሃን፣ ወሎ ካምፕ ያሉትን ቅድሚያ ተሰጥቶ በ1ኛው ዙር 1,600፣ በ2ኛው ከ400 በላይ ሰዎች ተመልሰዋል” ሲሉ አስታውሰው ፣ “ በሶስተኛው ዙር ለመመለስ ደግሞ ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ” ብለዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#የአሜሪካ_አቋም! " ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ሾለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ? - በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው። - የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል። - ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል። - የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል። - ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ። - በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም። - ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው። - ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው። - የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ። - በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው። - በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።   - ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት። - የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል። - ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች። - የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል። - ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል። - ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው። - የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል። - ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል። - ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል። #USEmbassyAddisAbaba #VOA #EthiopiaInsider @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
10:08
Video unavailableShow in Telegram
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም ' ማለታቸው ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " ብለዋል። ከመንግስት ጋር በታንዛንያ የሰላም ንግግር ሲያደርጉ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) ተዋጊዎችን " በድርድር ተስፋ ሳትቆርጡ ፤ መተማመንን ለመገንባት ጥረት አድርጉ " ብለዋቸዋል። አሜሪካ ይህን ያለችው ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ በአምባሳደሯ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት ነው። በአዲስ አበባ ፤ መርካቶ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የአሜሪካን ግቢ በነበረ መርሀ ግብር የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር። Video Credit : US Embassy Addis Ababa / Ethiopia Insider @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል። በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም። ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመመገብም ሆነ ልጆቻቸዉን ለማስተማር መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል። የገዢዉ ፓርቲና የክልሉ ባለሥልጣናት ሠራተኞቹን " በትዕግሥት ጠብቁን " የሚል ምላሽ ቢሰጡም ሠራተኞቹ ግን " ረሐብ እንዴት ቀን ይሰጣል ? " በማለት ጠይቀዋል። ሠራተኞቹ በወረዳው በተለያዩ ጽ/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሠራተኞቹ ተወካዮች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ProsperityParty #TPLF ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል። ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል። ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል። ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል። " ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል። ከዚህ ባለፈ ፦ - " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። - ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል። - የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል። - ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል። - የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ #ProsperityParty #TPLF @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ከማረት ከተስረቁት 2 መኪኖች አንደኛዋ መገኘቷን ፓሊስ አስታወቀ። ማሕበር ረድኤት ማሕበር (ማረት) በመጋቢት እና በያዝነው ግንቦት ወር አንድ ላንድክሩዘር V8 እና ላንድክሩዘር ማርክ 2 መኪናዎችን ተዘርፏል። የድርጅቱ ንብረት የሆነች በሰሌዳ ቁጥር 35 - 2723 የተመዘገበችው V8 መኪና መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተሰርቃ ሳትገኝ የውሃ ሽታ ሆና ቀርታ ነበር። ይህች መኪና ሳትገኘ ከቀናት በፊት ላንድ ክሮዘር ማርክ 2 መኪና ተዘርፋለች።  ፓሊስ የድርጅቱ መኪኖች ያየና ያገኘ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ በያዝነው ሳምንት የተሰረቀችው ላንድክሩዘር ማርክ2 መኪና ከመቐለ በ250 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አክሱም ከተማ በፓሊስ ተይዛለች። የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ መኪናዋ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 በፓሊስ ቁጥጥር ሾር መዋልዋን አሳውቋል። ፖሊስ መኪናዋን ያገኘው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ክትትል ነው። በሰዓቱ መኪናዋን የያዛት ሹፌር ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ማክሸፉን አሳውቋል። ከነሹፌሩ በተጨማሪ " የኔ ንብረት ናት " የሚል አመልካችም በፓሊስ በቁጥጥር ሾር ማዋሉ ተሰምቷል። የአክሱም ከተማ ፖሊስ " መሰል ስርቆት ከጦርነቱ በኋላ መታየት የጀመረና በትግራይ ያልተለመደ ነው " ያለ ሲሆን " ማንኛውም ወንጀለኛ ከህዝብ አይንና ጀሮ መደበቅ አይችልም ብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ሾለ መኪኖቹ ስርቆት ከማሕበር ረድኤት ትግራይ (ማረትረት) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።                                             @tikvahethiopia            
Hammasini ko'rsatish...