4 483
Obunachilar
-124 soatlar
+507 kun
-3230 kun
Postlar arxiv
4 483
#የደረት_ህመም
#Ethiopia
የደረት ህመም በራሱ በሽታ ሳይሆን የተለያዩ ችግሮች ምልክት ነው።
ህመሙ ከልብ፣ ከሳንባ፣ ከጡንቻና አጥንት፣ ከሆድ/የምግብ መተላለፊያ ወይም ከጭንቀት ሊመጣ ይችላል።
#ምክንያቶች
ከልብ የሚመጣ ህመም (Angina )
የልብ ጡንቻ በቂ ደምና ኦክሲጅን ሳያገኝ ይከሰታል። ብዙ ጊዜ በመራመድ፣ በመሮጥ ወይም በከባድ ስራ ጊዜ ይጀምራል፤ እረፍት ሲደረግ ሊቀንስ ይችላል።
📌 Heart attack (Myocardial infarction) ግን የልብ ደም ስር በመዘጋቱ የልብ ጡንቻ ክፍል መጎዳት ነው። ከባድ የደረት መጫን/መጨናነቅ፣ ላብ፣ ማቅለሽለሽ፣ ድካም እና ህመሙ ወደ እጅ፣ ጀርባ፣ አንገት ወይም መንጋጋ መስፋፋት ሊኖር ይችላል።
👉 ከሳንባ የሚመጣ
እንደ ሳንበ ምች፣ የሳንብ ሽፋን መቆጣት ፣ በሳንባ ከረጢት ውስጥ ደም ፣ አየር መከማቸት እና የሰንባ ደም መላሸ መሰመሮቾ መዘጋት ያሉ ችግሮች የደረት ህመም ሊያመጡ ይችላሉ።
በተለይ ህመሙ በጥልቅ መተንፈስ ወይም በሳል ሲባባስ ከሳንባ/pleura ጋር የተያያዘ መሆኑ ሊጠረጠር ይችላል።
👉 ከጡንቻና ከደረት ግድግዳ
ከባድ ስራ፣ እቃ መሸከም፣ ስፖርት ወይም ጉዳት በኋላ የደረት ጡንቻ ሊወጠር ይችላል። Costochondritis ደግሞ የጎድን አጥንትና የደረት አጥንት መገናኛ አካባቢ እብጠት/ህመም ነው።
እንዲህ ዓይነቱ ህመም በመንካት ወይም በአንዳንድ እንቅስቃሴ ሊባባስ ይችላል።
👉 ከሆድ አሲድ — GERD
የሆድ አሲድ ወደ የምግብ መተላለፊያ ሲመለስ የደረት ማቃጠል (heartburn) ሊያመጣ ይችላል። ብዙ ጊዜ ከምግብ በኋላ፣ በመተኛት ጊዜ ወይም በመጎንበስ ይባባሳል።
👉 ከጭንቀት ወይም panic attack
ከፍተኛ ጭንቀት የደረት መጨናነቅ፣ ፈጣን የልብ ምት፣ መንቀጥቀጥ፣ ላብ እና እስትንፋስ እንደሚያጥር ስሜት ሊያመጣ ይችላል። ነገር ግን የደረት ህመምን በቀጥታ በጭንቀት ላይ ማስቀመጥ አይገባም—በተለይ ከባድ የልብ ወይም የሳንባ ችግር ምልክቶች ካሉ።
#መቼ_አስቸኳይ_ነው?
#የደረት_ህመም፦
🚫 በድንገት ከጀመረ
🚫 ከባድ መጨናነቅ/መጫን ከሆነ
🚫 ወደ እጅ፣ ጀርባ፣ አንገት ወይም መንጋጋ ከተሰራጨ
🚫 ከእስትንፋስ ማጣት ጋር ከሆነ
🚫 ከብዙ ላብ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማዞር ወይም ራስን መሳት ጋር ከሆነ አስቸኳይ የህክምና ምርመራ ያስፈልጋል።
#መፍትሔውስ?
👉 የደረት ህመም ሁሉ በአንድ መድሀኒት አይታከምም። መጀመሪያ ምክንያቱን መለየት ነው ዋናው ነገር። ለምሳሌ GERD ከሆነ የአሲድ መቀነሻ ህክምና ሊሰጥ ይችላል፤ የጡንቻ ህመም ከሆነ የተለየ አቀራረብ ይፈልጋል፤ የልብ ድንገተኛ ጥቃት ግን አስቸኳይ የሆስፒታል ህክምና ይፈልጋል።
ስለዚህ “የደረት ህመም አለኝ” ብቻ በመስማት መድሀኒት መጀመር አይገባም። የህመሙ ቦታ፣ ባህሪ፣ መጀመሪያ ጊዜ፣ ከእንቅስቃሴ/ምግብ/መተንፈስ ጋር ያለው ግንኙነት እና ተያያዥ ምልክቶች መጠየቅ ያስፈልጋል።
Abebaw Mebratu
የጁቤ ጤና መረጃ Health Information
4 483
#የወባ_በሽታ_ምንድን_ነው ?
#Ethiopia
➡ የወባ በሽታ ፕላስሞዲየም በተባሉ ረቂቅ ጥገኛ የደም ተዋሲያን (ፓራሳይትስ) ተህዋስያን የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ በሰው አካል ውስጥ በመራባትና በማደግ ለበሽታው የሚያጋልጡ አራት የፕላስሞዲየም ተህዋስያን ዝርያዎች ብቻ ናቸው እነሱም፡-
1. ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም
2. ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ
3. ፕላስሞዲየም ማላሪዬ
4. ፕላስሞዲየም ኦቫሌ ይባላሉ፡፡
ተህዋስያኑ የተለያዩ የቅርጽ ፤የእድገት ፤የትውልድ ብዛት፤ለመራባት የሚወስዱት የጊዜ ፍጆታ ፤የበሽታው ጥንካሬ ፤በሰው ላይ የሚያሳዩት የግርሻ አይነትና ወቅት በመድሀኒቶች የመጠቃት ዝንባሌ ፤በአካል ውስጥ የሚያደርሱት ጉዳት ዓይነት የተለያዩ ነው፡፡ ከነዚህ የወባ ተህዋስያን ዝርያዎች በሀገራችን ደረጃ በዋነኛነት የሚገኙት ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም እና ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ ናቸው፡፡
የወባ በሽታ በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት የደም ህዋሳትን በመጨረስ ፡የአእምሮ መዳከም፡እንደ ጉበት ኩላሊት አንጎል በሚገኙ የውስጥ አካላት ላይ ቀውስ በመፍጠር ጉስቁልና ችግርና ሞት ያስከትላል፡፡ በነፍሰጡሮች በወላጆችና በህጻናት ላይ ከባድ ጉዳትና ሞት ከማድረሱም ባሻገር ለሌሎች ተላላፊ በሽታም ያጋልጣል፡፡
#ምልክቶች ፦
የተህዋስያኑ በቀይ ደም ህዋሳት ውሳጥ የሚያካሂዱትን የማደግና የመራባት ሂደት በመጨረስ ከቀይ ደም ህዋሳት ውስጥ በመውጣትና በመሰራጨት እንዲሁም ወዲያውኑ ቀጥለው ሌሎች ጤነኛ የደም ህዋሳትን ከማጥቃት ሁኔታ ጋር የስሜቶችና የምልክቶች መከሰት የተያያዘ ነው፡፡
➡ በሽተኛው ህመም ሲጀምረው የብርድ ብርድ ማለት ስሜት ይከሰታል
➡ ትኩሳትና ማላብ
➡ ምግብ ማስጠላት ቢመገብም ማስመለስ
➡ ራስ ምታትና ውሀ ጥም ሲሆኑ በተጨማሪም
➡ በጀርባና በአካል መገጣጠሚዎች ቁርጥማት መሰማት
➡ ማንቀጥቀጥ
➡ ማቅለሽለሽ
➡ ሳል
➡ ተቅማጥ
➡ የደምማነስ(ማዞር)
➡ የጣፊያ ማበጥ የመሳሰሉት በበሽታው የመያዝ ምልክቶች ናቸው።
#መተላለፊያ_መንገድ
የወባ በሽታ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፈው በሴቷ አኖፊለስ በምትባል የወባ ትንኝ ዝርያ ንክሻ አማካኝነት ነዉ።
ትንኝ ሁሉ ወባን አያስተላልፍም፡፡ የወባ አስተላላፊ ትንኝዋ የምትጥለው እንቁላል እንዲዳብር የሚያስፈልጋት ምግብ ደም ነው፡፡ ከአንድ በወባ የታመመ ሰው በአጋጣሚ ደም ስትመጥ ፤የወባ በሽታ ተህዋስያን ከደሙ ጋር በመውሰድ በሆዷ ውስጥ በአማካኝ ከ10-14 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ በማደግና ቅርጻቸውን በመለዋወጥ ይራባሉ፡፡ከዚያም በኋላ ይህች ትንኝ እንደገና ደም ለመመገብ ጤነኛን ሰው ስትነክስ የምትመጠው ደም እንዳይጓጉል /እንዳይረጋ / በመጀመሪያ ምራቋን በምትረጭበት ጊዜ ጥገኛ ተህዋስያኑም ከምራቅ እጢ ውስጥ ከምራቅ ጋር ተቀላቅለው ወደ ጤነኛው ሰው ደም ስር ይገባሉ፡፡
በጤነኛሰው ደም ውስጥ ትንኟ ጥገኛ ትዋስያኑን ስተተፋ ወዲያውኑ ህመም አይሰማም ፡፡ ስሜት ሳይሰማው ግለሰቡ የተለመደ የእለት ተእለት ተግባሩን እያከናወነ ከ10-14 ቀናት ደህና ሆኖ ይሰነብታል፡፡ በነዚህ ቀናት ውስጥ በጉበቱ ውስጥ ተህዋስያኑ ገብተው ይራባሉ፡፡ ከጉበት ህዋሳት እድገታቸውን ጨርሰው ወደ ደም ቧንቧ በመሰራጨት ቀይ የደም ህዋሳትን ይወራሉ፡፡ ይህም ክስተት በአራቱም የወባ ዝርያዎች የተለያዩ ጊዜና ጠባይ አለው፡፡ የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዘዴዎች፦
- የአካባቢ ቁጥጥር( ማፋሰስ፣ ማጨድ፣ማዳፈን
- የጸረ እጭ ኬሚካል ርጭት
- በጸረ ትንኝ ኬሚካል ርጭት
በተነከረ አጎበር መጠቀም እና ምልክቱ በታዬ በ24 ውስጥ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ተገቢ ነው።
የጁቤ ጤና መረጃ Health Information
