cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስር በመሆን አስፈላጊና አስተማሪ ንፅፅራዊ ትምህርቶችን፦ - ቪድዬዎችን - ኦድዬዎችን - አጫጭር መጣጥፎችን እያዘጋጀ በሀገርኛ ቋንቋ ያቀርባል፡፡

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
4 955
Obunachilar
+124 soatlar
-47 kunlar
+6730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አልገደሉትም ገቢር ሁለት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا ነጥብ አንድ "ታሪካዊ ዳራ" ኢየሱስ ከፈጣሪ የሚናገረውን ትምህርት ተሰቶት ነበር፤ ይህ ትምህርት የፈጣሪ ቃል ነው፤ ከእርሱ የሚሰማው ትምህርት የፈጣሪ ወንጌል ነው፦ ዮሐንስ 17:8 *የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና*፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ዮሐንስ 17:14 እኔ *ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ*፤ ዮሐንስ 14:24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ *የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም*። ዮሐንስ 7፥16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። *ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም*፤ ዮሐንስ 12:49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*። ሉቃስ 5፥1 ሕዝቡም *የእግዚአብሔርን ቃል እየሰሙ* ሲያስጠብቡት ሳሉ፥ እርሱ ራሱ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ነበር፤ ማርቆስ 1፥14 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ *የእግዚአብሔርን ወንጌል* እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፡ *በወንጌልም እመኑ* እያለ ወደ ገሊላ መጣ። "በወንጌልም እመኑ" ሲል ከመለኮት የተሰጠውን ወንጌል ብቻና ብቻ ነው፤ ይህንን ወንጌል ለሃዋርያቱ አስተላልፏል፤ "የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ኦሪገን የተሰጠው ወንጌል የአስራ ሁለቱ ወንጌል ሲሆን ጠፍቷል ይለናል። ጄሮም ደግሞ የአስራ ሁለቱ ወንጌል የሃዋርያት ወንጌል እንሆሃነ ተናግሯል፤ ሐዋርያቱ ለደቀመዛሙርቶታቸው ሲያስተላልፉ ቀደ መዛሙርቶቻቸው ይህንን ወንጌል ከሚሰሙት ታሪክ ጋር ቀላቅለው ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ሞክረዋል፦ ሉቃስ 1:1-4 የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።”
Hammasini ko'rsatish...
አልገደሉትም ገቢር አንድ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا “ታሪክ”history” ያለፈውን ክስተት የሚተርክ የምርምር ጥናት”study” እና አሰሳ”investigation” ነው፤ በታሪክ ጥናት ውስጥ ለታሪክ ምንጭ የሚሆኑ ሁለት መረጃዎች አሉ፣ አንደኛው ትውፊት”tradition” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሥነ-ቅርስ ጥናት”archology” ነው፤ “ትውፊት” ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል የሚተላለፍ ቅብብል ሲሆን “ሥነ-ቅርስ ጥናት” ደግሞ በተለያየ ቁስ ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች አስሶና ቆፍሮ የሚያቀርብ የታሪክ ምንጭ ነው፤ ትውፊት ሆነ ሥነ-ቅርስ በባህል”culture” ላይ እና በስልጣኔ”civilization” ላይ መሰረት ያደረጉ ግምት”speculation” ናቸው፤ ስለ ኢየሱስ ማንነት በዓለማችን ላይ አንድ አይነት አቋም ያለው የታሪክ ፍሰት የለም፤ አንዱ ሃሳዌ መሲህ ሲለው ሌላው አምላክ ሲለው፣ አንዱ የፈጣሪ እረዳት ሲለው ሌላው ብቸኛ የፈጣሪ ልጅ ይለዋል፤ አንዳንዶች እንደውም በታሪክ ላይ አልነበረም የሚሉም አልታጡም፤ ስለ እርሱ አራቱ ወንጌል ላይ የምናየውም ትረካም ቢሆን እርስ በእርሱ የተዛባ እና በቅብብል የተገኘ እንጂ ግህደተ-መለኮት አይደለም፤ ታዲያ ይህ ዓለማችንን ያነጋገረ የፈጣሪ ነብይ ትክክለኛ ማንነቱን መናገር ያለበት እራሱ ላኪው ፈጣሪ ነው፤ ኢየሱስን የላከው አላህ ስለ ዒሳ ሲናገር፦ 19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፡፡ *ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው*፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ “የምተሩነ” يَمْتَرُونَ ማለትም “የሚከራከሩበት” የሚለው የግስ መደብ ይሰመርበት፤ ይህ “መከራከር” የሚለው ቃል “ሚርያህ” مِرْيَة ሲሆን “ጭቅጭቅ” “ንትርክ” ክርክር” ማለት ነው፤ በዒሳ ጉዳይ ሰዎች በመወዛገብ መጨቃጨቃቸውን፣ መነታረካቸውን እና መከራከራቸውን ያሳያል፤ ዒሳ ካረገበ በኃላ ቁርኣን እስከሚወርድበት ጊዜ አራጥቃና በጥራቃ እየተባባሉ መቅኖ ሲያሳጣቸው እንደነበር ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ አስፍሮታል። “ያ“ በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው” የሚል ነው፤ “እርሱ” በሚለው ቃል ላይ “በ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህ የሚያመለክተው ስለ ዒሳ አላህ የነገረን ንግግር ሁሉ እውነተኛ ቃል ነው ማለት ነው፤ “በ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ፊ” فِي  ሲሆን “ስለ”about” ማለት ነው፦ That is Jesus, son of Mary. ˹And this is˺ a word of truth, “about” which they dispute. “ቀሰስ” قَصَص የሚለው ቃል “ቀሰሰ” قصص “ተረከ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ትረካ” ማለት ነው፤ አላህ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማና ሁሉን የሚያውቅ ስለሆነ ያለፈውን ክስተት “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ “እንተርክልሃለን” በማለት በነብያችን”ﷺ” ላይ ይተርካል፦ 11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ ስለዚህ ከመልክተኞች ታሪክ አንዱ የዒሳ ታሪክ ስለሆነ ይህ ታሪክ ሲከሰት ነብያችን”ﷺ” በህልውና ደረጃ ስላልነበሩ ሁሉን ዐዋቂው አምላክ ለነብያችን”ﷺ” ይህንን ታሪክ ያወርዳል፤ ይህ ስለ ዒሳ ትረካ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው፦ 3፥62 *”ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው”*፡፡ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም፡፡ አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْقَصَصُ ٱلْحَقُّ ۚ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ ሰዎች በዒሳ ጉዳይ ከሚወዛገቡበት፣ ከሚጨቃጨቁበት፣ ከሚነታረኩበት፣ ከሚከራከሩበት ነጥብ አንዱ ዒሳ ተሰቅሏል ወይስ አልተሰቀለም ነው፤ አምላካችን አላህ፦ ዒሳን አልገደሉትም አልሰቀሉትምም ግን የገደሉትና የሰቀሉት መስሏቸዋል፦ 4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا "እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም" ይህንን መለያየት አስመልክቶ ስለ ወንጌላት ታሪካዊ ዳራና ፍሰት፤ በቁርኣን እና በሐዲስ ያለውን እሳቤ ነጥብ በነጥብ ኢንሻላህ እንቀጥላለን...... ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሰላሙ አለይኩም
Hammasini ko'rsatish...
ለምሳሌ፦ አንደኛ በ 50-138 AD የማቴዎስ ተማሪ የነበረው ባስሊዲስ በ 117 AD ላይ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የቀሬናን ስምዖንን እንደሰቀሉት ይናገራል፤ ይህንን ወንጌል በኃላ ላይ የመጡት አበው በ 130-200 AD ይኖር የነበረ ኢራኒየስ፣ በ 150-215 AD ይኖር የነበረ የአሌክሳንድሪያው ክሌመንት ተቃወሙት፤ ብዙ ጊዜ ከባስሊዲስ ወንጌል ላይ 260-340 AD ይኖር የነበረው የቂሳሪያው አውሳቢዮስ ይጠቅስ ነበረ። ሁለተኛ በ 60-135 AD ይኖር የነበረው በርናባስ የበርናባስን ወንጌል፣ የበርናባስን መልእክት እና የበርናባስ ሥራ በ 100–131 AD አዘጋጅቷል፤ በሳይናቲከስ ኮዴክስ ላይ ፓሊካርፕ ለፊሊጵስዩስ በጻፈው ፓሊላርፕ 1፥1 ቀጥሎ የበርናባስ መልእክት 5፥7 ይቀጥልል። እዚህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደሰቀሉት ይናገራል። ሦስተኛ በ 85-160 AD ይኖር የነበረው የሲኖፕ ማርኮይን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የማርኮናይት ወንጌል በ 1740 AD ከተገኙት የሙራቶሪያን ብጥስጣሽ"Muratorian fragment" አንዱ ነው፤ የካርቴጅ ጉባኤ ከማርኮናይት ግሩፕ ውስጥ የዮሐንስን አፓልካሊፕስ"ራእይ" ተቀብላ በእነርሱ የነበረውን የጳውሎስን አፓልካሊፕስ፣ የጴጥሮስን አፓልካሊፕስ፣ የቶማስን አፓልካሊፕስ፣ የእስጢፋኖስን አፓልካሊፕስ፣ የያዕቆብን አፓልካሊፕስ ደብቃቸዋለች። በማርኮናይት ወንጌል ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የሮማ ወታደር እንደሰቀሉት ይናገራል። አራተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ኤቦን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የኤቦናይት ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። በ 347-420 AD ይኖር የነበረው ጄሮም ኤቦን በዮሐንስ ዘመን ይኖር እንደነበረ መስክሯል። ነገር ግን ኤቦንን በ 36-115 AD ይኖር የነበረው የቆሮጵሮሱ ኤጵፋኒየስ አውግዞቷል።
Hammasini ko'rsatish...
▯▩ ወይይት ▩▯ "ስቅለት በኢስላም" ◍ ወንድም ኢምራን           🆅🆂 ◍ ወገናችን ሳሚ ◍ ወገናችን ሳለህ ◍ ሌሎችም
Hammasini ko'rsatish...
07:02
Video unavailableShow in Telegram
"እንኳን አደረሳችሁ?" ◍ እኅት ዘሀራ
Hammasini ko'rsatish...
አምስተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ሰርቲዩስ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የሰርቲዩስ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። ስድስተኛ በ 36 AD ጀምረው ይኖሩ የነበሩት ናዝራውያን ወንጌል አዘጋጅተዋል፤ ይህ የናዝራውያን ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። ናዝራውያን የሙሴን ሕግ ይቀበላሉ፤ የኢየሱስን በድንግና መወለድ ይቀበላሉ፣ የሌሎችን ወንጌላት አይቀበሉም። በግሪክ ኮይኔ የተዘጋጁት ወንጌሎች የትዬለሌ ናቸው፤ እነርሱም፦ የቶማስ ወንጌል፣ የይሁዳ ወንጌል፣ የባስሊዲስ ወንጌል፣ የበርናባስ ወንጌል፣ የማርኮናይት ወንጌል፣ የኤቦናይት ወንጌል፣ የሰርቲዩስ ወንጌል፣ የናዝራውያን ወንጌል፣ የጴጥሮስ ወንጌል፣ የያዕቆብ ወንጌል፣ የፊሊጶስ ወንጌል፣ የበርተሎሜዎስ ወንጌል፣ የመቅደላዊት ማርያም ወንጌል፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ የማርቆስ ወንጌል፣ የሉቃስ ወንጌል፣ የዮሐንስ ወንጌል የመሳሰሉት ናቸው፣ በቁጥር ወደ 47 ይደርሳሉ፣ ዛሬ የቀኖና ወንጌሎች የተባሉት ኦርጅናል አራቱ ወንጌሎች የለም፣ አራቱ ወንጌላት ተጻፉ የሚባሉት ከ 60-100 AD ሲሆን የእነርሱ የቅጂ ቅጂ ብጥስጣሽ"fragments" እና ደንገሎቹ"papiruses" የሚያሳዩት ግን ከ 200-250 AD ነው፦ የማቴዎስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የማርቆስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የሉቃስ ወንጌል ደንገል 75 የሚባለው በ 250 AD፣ የዮሐንስ ወንጌል ደንገል 46 የሚባለው በ 200 AD ነው፣ ዛሬ ያሉት 5800 ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት ኢየሱስ ካስተማረ ከሶስት መቶ አመት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው፤ ዋና ዋናዎቹ ሳይናቲከስ ጥራዝ በ 330 AD፣ ቫቲካነስ ጥራዝ 350 AD፣ አሌክሳንድሪየስ ጥራዝ 400 AD፣ ኤፍሬማይ ጥራዝ 450 AD ላይ የተዘጋጁ ናቸው። ይህ እንዲህ በእንዲህ እንዳለ በ 397 AD የካርቴጅ ጉባኤ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን የቅጂዎች ቅጂዎች የሆኑትን አራቱን ወንጌሎች ብቻ ቀኖና"canon" አድርጋ ሌሎችን ወንጌሎች "አፓክራፋ" አድርጋለች፤ "አፓክራፋ" የሚለው ቃል "አፓክራፈስ" ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ድብቅ" ማለት ነው፤ ለዛ ነው አምላካችን አላህ፦ "የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?" ብሎ የተናገረው፦ 3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ 5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ “ከብዙውም የሚተው ሲኾን” ማለት የመጽሐፉ ባለቤቶች ከደበቋቸው ሁሉንም አልተናገሩም ማለት ነው፤ በቀኖና ያላካተቷቸው ግን የሸሸጓቸውን እንዳለ ይህ አንቀጽ ይጠቁማል፤ በወንጌሎች ታሪካዊ ዳራና ፍሰት ዋቢ መጽሐፍት ያደረኩት የአዲስ ኪዳን ምሁር የሆኑትን የፕሮፌሰር ባርት ሄርማን መጽሐፍት ነው፦ 1. The Other Gospels: Accounts of Jesus from Outside the New Testament. Oxford University Press, USA. 2013 by Bart D. Ehrman 2. The Orthodox Corruption of Scripture: The Effect of Early Christological Controversies on the Text of the New Testament. Oxford University Press, USA. 2011 3. Lost Scriptures: Books that Did Not Make It into the New Testament. Oxford University Press, USA. 2003 ኢንሻላህ በክፍል ሥስት እንቀጥላለን.... ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሰላሙ አለይኩም
Hammasini ko'rsatish...
25:48
Video unavailableShow in Telegram
سورة الكهف كاملة تلاوة هادئة وراحة نفسية في يوم الجمعة تريح الأعصاب محمد ديبيروف Surah al kahf አዳምጡ
Hammasini ko'rsatish...
አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በወር አበባዋ ጊዜ መነካካት፣ መብላት እና መጠጣት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ትነካካ፣ ትበላ እና ትጠጣ ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 4 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” እኔ የወር አበባ ላይ እያለሁኝ ጭኔ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር"*። أَنَّ عَائِشَةَ حَدَّثَتْهَا أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَتَّكِئُ فِي حَجْرِي وَأَنَا حَائِضٌ، ثُمَّ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ‏.‏ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 3, ሐዲስ 10 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አጥብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْسِلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 279 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አበጥር ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كُنْتُ أُرَجِّلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 686 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ በወር አበባ ጊዜ አጥንት እግጥ ነበር፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስጋውን ከእኔ ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸው በማሳረፍ ይግጡ ነበር። እንደዚሁም የወር አበባ ላይ እያለሁ በእቃ ስጠጣ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እቃውን ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸውን በማሳረፍ ይጠጡ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَتَعَرَّقُ الْعَظْمَ وَأَنَا حَائِضٌ، فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَشْرَبُ مِنَ الإِنَاءِ فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَنَا حَائِضٌ ‏.‏ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 675 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ለእኔ፦ *"ከመሥጂድ ሰሌኑን አምጪልኝ" አሉኝ፥ እርሷም፦ "በወር አበባ ላይ ነኝ" አልኩኝ" አለች። እርሳቸውም፦ "የወር አበባሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ አይደለም" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ نَاوِلِينِي الْخُمْرَةَ مِنَ الْمَسْجِدِ ‏"‏ ‏.‏ فَقُلْتُ إِنِّي حَائِضٌ ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ لَيْسَتْ حَيْضَتُكِ فِي يَدِكِ ‏ አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በፆም ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር መነካካት፣ መሳሳም እና አብሮ መተኛት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በፆም ጊዜ ትነካካ፣ ትሳሳም ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 89 ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በፆም ወር ውስጥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ይስሟት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ فِي شَهْرِ الصَّوْمِ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 79 ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ከሚስታቸውን አንዷን(ዓኢሻህን) ይስሙ ነበር፥ ከዚያም ደስ ይላት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ إِحْدَى نِسَائِهِ وَهُوَ صَائِمٌ ‏.‏ ثُمَّ تَضْحَكُ ‏ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 83 ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ሚስታቸውን ይስሙ ነበር፥ ከእናንተ ይልቅ እሳቸው ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يُقَبِّلُ وَهُوَ صَائِمٌ وَكَانَ أَمْلَكَكُمْ لإِرْبِهِ "ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር" የሚለው ኃይለ-ቃል በፆም ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ክልክል መሆኑን ለማሳየት ነው። አንዲት እንስት ከባሏ ጋር የጨዋታ ጊዜ ሊኖራት እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የጨዋታ ጊዜ እንደነበራት ትናገራለች፦ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 102 አቢ ሠለማህ ከዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደዘገበው፦ "ዓኢሻህ ከነቢዩ"ﷺ" ጋር በጉዞ ላይ ሳለች እንዲህም አለች፦ *"ከነቢዩ"ﷺ" ጋር ሩጫ ተወዳደሩኝ እኔም አሸነፍኳቸው፥ ያሸነፍኳቸው ሳልወፍር በፊት ነበር፡፡ ከወፈርኩ በኃላ ግን ተወዳደርኳቸው አሸነፉኝ። እንዲህም አሉኝ፦ "ብድር መለስኩኝ"*። وَعَنْ أَبِي سَلَمَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّهَا كَانَتْ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي سَفَرٍ قَالَتْ فَسَابَقْتُهُ فَسَبَقْتُهُ عَلَى رِجْلَىَّ فَلَمَّا حَمَلْتُ اللَّحْمَ سَابَقْتُهُ فَسَبَقَنِي فَقَالَ ‏ "‏ هَذِهِ بِتِلْكَ السَّبْقَةِ ‏"‏ ‏.‏ እውነት ሚሽነሪዎች እንደሚሉት ዓኢሻህ በነቢያችን"ﷺ" የሥነ-ልቦና እና የተክለ-ሰውነት ጥቃት ደርሶባት ቢሆን ከላይ ያለውን የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመግባባት ጊዜ ለአማንያን ይጠቅማል ብላ ትተርክ ነበርን? ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ ሆነው በተነሱበት ጊዜ የነበሩ የኢሥላም ጠላት ነቢያችንን"ﷺ"፦ "ጠንቋይ፣ ደጋሚ፣ መተተኛ፣ ዕብድ" ወዘተ ሲሉ በዓኢሻህ እና በእሳቸው መካከል የነበረውን ጋብቻ ለምን አልተቹም? እርሷ ስለ ጋብቻዋ በአሉታዊ መልኩ አንድም ቀን አምርራና አማራ የማታውቀውን ሚሽነሪዎች ዙሪያ ገቡን ሳያዩ ኢሥላምን ለማጠልሸት እና ሙሥሊሙን ለማብሸቅ "አስገድዶ መድፈር" የሚሉት የአእምሮ ስንኩላን ስለሆኑ ነው። ብዙ ጊዜ በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ነገር ግን አላህም ብርሃኑን ገላጭ ነው፦ 61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Hammasini ko'rsatish...
• من سورة ق .. 🌸 ..° } ..• @slmatawahi
Hammasini ko'rsatish...