ምክር ለወጣቶች
Kanalga Telegram’da o‘tish
"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
7 491
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+1467 kun
+77830 kun
Postlar arxiv
7 491
Repost from 🌸 የጀነት አበቦች 🌸
🌹 ለውድ እህቴ
አንቺ የፊተና በር አትሁኚ!
ውድ እህቴ ሆይ! አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ሴት ልጅን በተፈጥሮዋ ማራኪ እና ሳቢ አድርጎ ነው የፈጠራት። ይህ ተፈጥሯዊ ውበትሽ ደግሞ በአግባቡ ካልተያዘ በሸሪዓዊ ሒጃብና በኢስላማዊ ስነ-ምግባር ካልተገደበ ለወንዶች ትልቅ የፈተና የፊተና በር ሊሆን ይችላል
የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም በአንድ ሀዲሳቸው እንዲህ ብለዋል
مَا تَرَكْتُ بَعْدِي فِتْنَةً أَضَرَّ عَلَى الرِّجَال مِنَ النِّسَاءِ
ከእኔ በኋላ ለወንዶች ከሴቶች የበለጠ ጎጂ የሆነን ፈተና አልተዋኩም።
📚 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
🌹ስለዚህ እህቴ ሆይ! ወንዶችን ከመፈተን ራቂ ራስሽንም ሆነ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ከወንጀል ጠብቂ
🌹 ቅልብልብነትንና ኩራት-ኩራት ማለትን እርሺው
አንዲት ሙስሊም ሴት ዋነኛ መገለጫዋ ሀያዕ ሊኖራት ይገባል ከባዕድ ወንዶች (መሕረም ካልሆኑ) ጋር ለሀጃ በጣም ዶሩራ ካልሆነ አትገናኝ በስልክም ቢሆን ሀጃው ከባድ ሆኖ በምትገናኚበት ጊዜ ደግሞ በንግግርሽም ሆነ በባህሪሽ ቅልብልብ አትሁኚ ወይም ራስሽን ለማሳየት የምትሞክሪ አትሁኚ ቁምነገረኛ አላህን የምትፈራና ድንበሯን የምታውቅ ጥንቁቅ ሴት ሁኚ
🌹የድምፅና የንግግር ቃናሽን ጠብቂ
በስልክም ሆነ በአካል ከባዕድ ወንዶች ጋር መነጋገር በሚኖርብሽ ጊዜ ለአስገዳጅ ነገር ዲናዊ ሲሆን ድምፅሽን በፍጹም አታለስልሺ
🌹እህቴ ሆይ! ድምፅሽን ማለስለስና መቅለስለስ በልቡ በሽታ የስሜት መሸነፍና የዝሙት ፍላጎት ላለበት ሰው የሸይጧንን በር በሰፊው መክፈት መሆኑን አትዘንጊ ሁሌም ክብርሽን በሀያዕ ሙይው!
አሏህን ፈርቶ ፊትናን የሚሸሸ ሁሉ የአላህ ሰላም ይስፈንበት
ጆይን & ሸር እያደረጋቹህ ባረከላሁ ፊኩም
https://t.me/kuni_qewuya
https://t.me/kuni_qewuya
7 491
ማስረጃን ለፈለገ ቁርዓን በቂው ነው ፤ ረዳት የፈለገ አላህ በቂው ነው ፤ መካሪ የፈለገ ሞት
በቂው ነው። ከእነዚህ ነገሮች አንዱም ያልበቃው እሳት ይብቃው።
“አላህ ባሪያውን በቂ አይደለምን?” (ዙመር፡36)
🔖ሚንሓጅ አል-ፊርቀቱ-ናጂያህ
@aaussj
👇👇👇👇👇 አዲስ ቻናል ነው ወጣቶችን ለመምከር የተከፈተ ጆይን እና ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፋ
https://t.me/NasihaLishebab
https://t.me/NasihaLishebab
7 491
👉 ሰዎችን እናውቃለን,
" የቢዳዓ ባልተቤቶችን የሚሰድቡና የሚረግሙ የነበሩ, አብረው ተቀማምጠው ተኗኗሩዋቸው ከእነርሱም ሆኑ "
ኢብኑ በጧህ የተባለ ታላቅ ሊቅ ከተናገራቸው ንግግሮች ።
https://t.me/bahruteka
👇👇👇👇👇 አዲስ ቻናል ነው ወጣቶችን ለመምከር የተከፈተ ጆይን እና ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፋ
https://t.me/NasihaLishebab
https://t.me/NasihaLishebab
7 491
📜 | የሸይኽ ሑሰይን ስልጤ አጭር የህይወት ታሪክ!
— "ዶክተር/ ሸይኽ ሑሰይን ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲ'ላህ ፤ አል-ኢትዮጵይ ፤ አስ’ስልጢይ ይባላሉ። (ሐፊዞሁ'ሏህ)"
— "ተወልደው ያደጉት ኦሮሚያ ክልል ወለጋ [ደምቢዶሎ] ውስጥ ሲሆን ፤ በልጅነታቸው እዚያው በሚገኙ ሸይኾች "ኪታቡ ተውሒድ" ፤ "ኡሱሉ ሠላሣ" ፤ "ሪያዱ ሷሊሒን" ፤ "ቡሉጉል መራም" ፤ "ነሕው" እና በሻፊዒያ መዝሀብ የተለያዩ የፊቅህ እውቀቶችን ተምረዋል።"
— "በ 1993 እድሜያቸው 18 አመት ሲሞላው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ መዕሀድ አን’ነጃሺይ በተባለው ኢስላማዊ የትምህርት ተቋም የአረብኛ ቋንቋ እና ሲራ ፤ ሐዲስ ፤ ሙስጦላሕ እና የመሳሰሉ ሸሪዓዊ እውቀቶችን ከተማሩ በኋላ በ 1996 ወደ ሱዑዲያ አቅንተዋል።"
— "ሱዑዲያ ከሚገኙ የተለያዩ የአህሉሱና ሸይኾች የሸሪዓ እውቀትን ቀስመዋል። ከእነዚህ ሸይኾች መካከል፦ ከታላቁ ዓሊምና ሙሐዲሥ ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ዑመይር አል-መድኸሊይ [ረሒመሁ'ሏህ] ድፍን አስር አመታትን የሐዲስ እውቀት ቀስመዋል። ከሸይኹ ጋር በነበራቸው ልዩ ቁርኝትና ቅርበት ፤ ከሸይኹ ቤት የማይጠፉ እንደነበሩ የዓይን እማኞች መስክረዋል።"
— "ሸሪዓዊ እውቀትን ከቀሰሙባቸው ሌላው ታዋቂ ሸይኽ ፤ ታላቁ ሙሐዲሥ ፤ ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ኣደም ፤ አል-ኢትዮጵይ ፤ አል-ወለዊይ [ረሒመሁ'ሏህ] ናቸው። ሸይኹ ከዚህ ዓለም በሞት እስከተለዩበት ሰዓት ድረስ ፤ የተለያዩ ሸሪዓዊ እውቀቶችን ሸይኽ ሑሰይን ከእርሳቸው ቀስመዋል።"
— "ከዚህ በተጨማሪ በሐዲሥ የዕውቀት ዘርፍ ፤ ዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። የተለያዩ መፅሐፎችንም ጽፈዋል ፤ በተጻፉ መጽሐፎች ላይ ትንታኔ ሰጥተዋል።"
📚 ለአብነት ያክል፦
✓ አል’ዋዲህ ፊ ተይሲሪ መንሀጂ ሰለፊ አስ’ሷሊህ
✓ ሚንሀጁ ሰላም ሸርሁ ቡሉጊ’ልመራም [ያልተጠናቀቀ]
✓ ሉዙሙ’ስሱነና ቢሸርሒ ኡሱሊ’ስሱንና [ሊል ኢማሚ አሕመድ]
✓ አል’ጃሚዕ ሊሹቡሃቲ አል-ሙመዪዐህ
✓ ተዕዚሙል ኢስላም ሊዒሳ ዓለይሂሰላም
✓ ሸርሁ ኡሱሉ’ስ'ሠላሠህ [የታተመ]
✓ አል’ጃሚዕ ሊሹቡሃቲል’አሕባሽ ..
✓ ስቢሉ ረሻድ ፊ ሀድዪ ኸይሪል ዒባድ [የታተመ]
✓ አል’አርበዑን አል’መኪየህ .. [ሐዲስ]
✓ አል’ሙቅኒዕ ሸርሁ’ል’አጁሩሚየህ .. [ነሕው]
⚠️ ዝንባሌያቸውን በሚከተሉ የተለያዩ ሰዎች ላይ የጻፏቸው አጫጭር ጽሁፎችም አሏቸው። ከነዚህ መካከል፦
✓ በአቡበክር አል’አህባሽ ፤
✓ በኢልያስ አህመድ ፤
✓ በኢብኑ ሙነወር ፤
✓ በኸድር ከሚሴ ፤
✓ በሙሐመድ ሰዒድ እና በሌሎችም ላይ የጻፏቸው በርካታ ምላሾች አሏቸው።
🤲 አ'ሏህ በእውቀታቸው ከሚጠቀሙት ያድርገን።
✅ "ከሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ የ "ተዕዚሙል-ኢስላም ሊዒሳ ዐለይሂሰላም" ኪታብ ትርጉም መግቢያ የተወሰደ።"
|| ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abu_Hessan
https://t.me/Abu_Hessan
https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1
7 491
እርድና ሲለካ
በኒቃብ ነው ለካ
አራዳ ነኝ የምትዪ ከሆነ በኒቃብ ገላሽን በሀያእ ስብእናሽን ሰትሪው🙌
👇👇👇👇👇 አዲስ ቻናል ነው ወጣቶችን ለመምከር የተከፈተ ጆይን እና ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፋ
https://t.me/NasihaLishebab
https://t.me/NasihaLishebab
7 491
የስም ሳይሆን የተግባር ዲነኛ የሆነች ሴት ካገባህ በቃ ዝም ብለህ የዱኒያን ጀነት ታኖርሃለች👌
ይወፍቀን🙌
👇👇👇👇👇 አዲስ ቻናል ነው ወጣቶችን ለመምከር የተከፈተ ጆይን እና ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፋ
https://t.me/NasihaLishebab
https://t.me/NasihaLishebab
7 491
ሴቷ ብቻ አይደለችም የማይሰትራትን ልብስ ስትለብስ ሙተበሪጃህ የምትባለው ወንዱም የአይኑን ግርዶ አውልቆ ሲጥል ሙተበሪጅ ነው !!
وصل؟؟
በዚህ ፈተና በበዛበት ዘመን ለሁለቱም ወገን የራስን ስነ-ምግባር ጠብቆ መጓዝ ትልቅ ጥረትና የአላህን እገዛ ይጠይቃል አላህ ያግራልን
የተወሰደ🙌
7 491
🔷 ከኡድሒያ ህግጋቶች
– ሸሪዓዊ ብይኑ
➲
ኡድሒያ ከፊል ዑለሞች እንደ አቡ ሐኒፋ ፣ አል አውዛዒ፣ ለይስ ኢብኑ ሰዕድና ሌሎችም አቅም ባለው ሰው ላይ ግዴታ (ዋጂብ) ነው ሲሉ ሌሎች ጁሙሁሮች ደግሞ ሱና ሙአከድ ነው ይላሉ ። ነገር ግን አንድ ሰው በኡድሒያ የሚገኘውን አጅር ዝም ብሎ ሊያስመልጥ አይገባም ።
– የሚታረደው ከብት አይነትና እድሜው
– ለኡድሒያ የሚታረደው የከብት አይነት
– ግመል ➡️ 5 አመት የሞላውና ከዛበላይ
– በሬ ➡️ 2 አመት የሞላውና ከዛ በላይ
– ፍየል ➡️ 1 አመት የሞላውና ከዛ በላይ
– በግ ➡️ 6 ወር የሞላውና ከዛ በላይ መሆን ይኖርበታል ።
↪️ ለኡድሒያ እንዳይሆን የሚከለክሉ አይቦች
➧ እውርነቱ ግልፅ የሆነ (ማየት የማይችል)
➧ ግልፅ የሆነ በሽታ ያለበት
➧ እግሩ ላይ ችግር ያለበት (ከከብቶች ጋር እኩል መሄድ የማይችል የሚያነክስ)
➧የማይድን ስብራት ያለበት
➽ በሚታረድበት ጊዜ
➻ በሚያርድበት ጊዜ በግራ ጉኑ ማስተኛት ይኖርበታል ። ኢማሙ ነወዊ በዚህ ላይ የዑለማዎች ስምምነት ይጠቅሳሉ ። ወደ ቂብላ አዙሮ ማስተኛቱ የተወደደ ለመሆኑ አራቱም አኢማዎች ይስማማሉ ከሶሓቦች ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ይገኝበታል ። ከዛ ቢስሚላሂ አላሁ አክበር , አላሁመ ሚንከ ወለከ, ይልና ማረድ ሲጀምር ቢስሚላሂ አላሁመ ተቀበል ሚኒ ወሚን አህሊ በይቲ ይላል ። የሚያርድበት ቢላዋ ስል መሆን ይኖርበታል ። የሚታረደው ከብት እንዳይሰቃይ ቶሎ ማረድ ይኖርበታል ። በሚታረድበት ቦታ ነው መጣል ያለበት እንጂ ጥሎ እግሮቹን ካሰሩ በኋላ እየጎተቱ ማሰቃየት አይፈቀድም ።
➪ በተቻለ መጠን እላይ ከተጠቀሱት ነውሮች በተጨማሪ ምንም ነውር የሌለበት ከብት ማረድ ይኖርበታል ።
– የሚታረደው ከብት መልክ
➤ ከላይ እንዳየነው ከኡድሒያ የሚከለክሉ ነውሮች አራት ናቸው ። ከዛ ውጪ ኡድሒያን ወድቅ የሚያደርግ ወይም አጅር የሚያሳጣ ነውር የለም ። እንደ ጥርስ መሰበርና ጆሮ በተወሰነ መልኩ መቆረጥ ወይም ጥቁር መልክ መሆኑ ኡድሒያ የሚያበላሽ አይደለም ። ነገር ግን የሚወደደው መልክ የአላህ መልእክተኛ ያረዱት አይነት ቢሆን ይመረጣል ። እሱም ቦቃ ይባላል ። ነጭ ሆኖ ግንባሩና ጉልበቱ አካባቢ ጥቁር ያለበት እሱም አምለሕ ይባላል ።
➼ አቅም ያለው ሰው የፈለገውን ያክል ከብት ገዝቶ ማረድ ይችላል ። በተለይ ለሚስኪኖች በዚህ ጊዜ አረዶ ለዒዳቸው ስጋ ሰጥቶ ማስደሰት በጣም ትልቅ እድል ነው ። ምንዳውም እጥፍ ድርብ ነው ። አርዶ ደም ባፈሰሰ ቁጥር ወደ አላህ ይቃረባል ። ድሆችን በማስደሰቱ ደግሞ ሌላ ዒባዳ ይሰራል እጥፍ ድርብ የሆነ ምንዳ ።
«خِتَامُهُ مِسْكٌ ۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ الْمُتَنَافِسُونَ»
المطففين (26)
" ማተሚያው ምስክ ከኾነ ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ ።"
https://t.me/bahruteka7 491
ስማ ወንድሜ
ህይወት አስቸግራሃለች
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
ግረፋት
ፈገግ በሉ🙌
https://t.me/NasihaLishebab
7 491
🔶#የቀድሞ የመሃይማንን መገላለጥ አትገላለጡ! በጊዜያችን አስገራሚና እንግዳ የሆኑ የሙስሊም ሴቶች ሁኔታ ተዳሷል 🔶በአዲስ አበባ አል- ወሰጢየህ መርከዝ እና መድረሳ የተደረገ ሙሐደራ። 🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ) 📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇 🌐 https://t.me/shakirsultan👇👇👇👇👇 አዲስ ቻናል ነው ወጣቶችን ለመምከር የተከፈተ ጆይን እና ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፋ https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab
7 491
🔶#የቀድሞ የመሃይማንን መገላለጥ አትገላለጡ! በጊዜያችን አስገራሚና እንግዳ የሆኑ የሙስሊም ሴቶች ሁኔታ ተዳሷል 🔶በአዲስ አበባ አል- ወሰጢየህ መርከዝ እና መድረሳ የተደረገ ሙሐደራ። 🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ) 📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇 🌐 https://t.me/shakirsultan👇👇👇👇👇 አዲስ ቻናል ነው ወጣቶችን ለመምከር የተከፈተ ጆይን እና ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፋ https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab
7 491
አንዳንድ ጊዜ ልባችን ሲደክም መፍትሔው ለሰዎች መንገር አይደለም ይልቁንስ ሁለት ረከዓ ሰግዶ ለአላህ መናገር ነው ሰላት ሸክም አይደለችም ሸክማችንን የምታቀልልን ከሸክማችን የምንሸሽባት መጠጊያ ናት ዱንያ ቢያስጨንቅህም አዛን ሲጠራ ፈገግ በል በአሁን ጊዜ ለጥቅምህ የሚጠራህ ሙዐዚን ብቻ ነው ያኺ ነቃ በል
https://t.me/kuni_qewuya
https://t.me/NasihaLishebab
https://t.me/NasihaLishebab
