የጥበብ እመቤት 📜
Kanalga Telegram’da o‘tish
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
271
Obunachilar
-124 soatlar
+77 kunlar
+15230 kunlar
Postlar arxiv
272
ዛሬን እንዳታጣ !!!
በግዜ እያሳበብክ ስህተትክን አትደብቅ፣
ይልቅስ ታርመህ ሰው በመሆን ድመቅ፣
ግዜ ለሰው እንጂ ሰው ለግዜ አይደለም፣
ያመኑት ጥፋት ነው ድልን የሚሸልም፣
የሰራ መሳሳት ያለ ነው በላቸው፣
በድጋሚ ጥረት ቆመህ አሳያቸው፣
በአለፈው ስህተት ዛሬ ቢመዝኑህ፣
ለማሸማቀቅ ጉባኤ ቢጠሩህ፣
የትላንቱንማ ለትላንት ትቻለሁ፣
ላይመለስ ዛሬ ተምሬበታለሁ፣
ብለህ ንገራቸው ጥቂት ቃላት አውጣ፤
በአለፈው ማንነት ዛሬን እንዳታጣ!!!
272
መልካም ፍሬን አፍራ
ማፍራትህ ከአልቀረ ልክ እንደዚህ አፍራ
ያለህን አትደብቅ መልካም ዘርን ዝራ
አንተን ቢከብድህም ያፈራኸው ፍሬ
ጎንበስ ቢያደርግህ ብስል ሆኖ ጥሬ
ለሌሎች ተስፋ ነው የነገ ምግባቸው
ይጠቀሙበታል መልካም ዘር ስጣቸው!
272
ከራስ ጋር አዎንታዊ ንግግር
ስለራሳችን የምናስበው እያንዳንዱ ሀሳብ ለእራሳችን የምንሰጠው ግምት ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ አለው። ለእራሳችን የምንነግረው ሀሳብ አሉታዊ ከሆነ ቀስ በቀስ ለእራሳችን የምንሰጠው ግምት እየወረደ ይመጣል። ስለዚህ እነዚህን አሉታዊ ሀሳቦች በአዎንታዊ ሀሳቦች የምንተካበት መንገድ መፈለግ አለብን። አዎንታዊ ሀሳቦችን ማሰብ ስለእራሳችን ያለን ግምት በጣም ጥሩ እንዲሆን ያደርጋል። የእራስ መተማመናችንም እንዲያደግ ያግዘናል።
🍎 ሄዋን
272
አንዳድ ቀን እኮ ሚነጋም አይመስልም እሄው ነጋ ነገን አላወቀውም አምላኬ አንተግን አውቅሀለው ከነገሩ ግዝፈቱ ይልቅ አንተን አውቅሀለው የገዘፈ ነገር ሁሉ ትልቅ አይደለም እኔ ሁሌም አምላኬን ትልቅ አደርጋለው❤️
🍎ሄዋን
272
👉 ስለ ትዕግስት እና ስለ ጊዜ አጠቃቀም ❤
• "ምርጥ ነገሮች ጊዜ ይወስዳሉ፤ ዘር ከተዘራ በኋላ ወዲያውኑ ፍሬ አይበላም፣ በትዕግስት ውሃ ማጠጣትና መጠበቅ ያሻል።"
• "በህይወትህ ውስጥ የሚገጥሙህ ፈተናዎች የመንገድህ ማብቂያ ሳይሆኑ፣ ይበልጥ ጠንካራና አስተዋይ የሚያደርጉህ ድልድዮች ናቸው።"
• "በጣም አስቸጋሪው ጊዜ ለታላቅ ለውጥ መነሻ የሚሆንበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፤ ጨለማው ሲበረታ ንጋቱ ይቀርባልና።
272
ለመኖሬ
ሁሉ የሚጎድለኝ፣አንችን ያጣዉ ዕለት
መሙላትን ፍለጋ፣በሀሳብ ስዋትት
ከጎኔ ሁኝና፣ሙላት እስኪ ይሰማኝ
የከበደኝ ነገር፣ተሎ እንዲቀለኝ
ባንች መኖር ምክንያት፣ተስፋ እንዲያንሰራራ
ዛሬን እየኖርኩኝ፣ነገን እንዳልፈራ.!!!
272
አንድ ሰው ለኛ የሚሰጠው ግምት የእርሱን የአስተሳሰብ ልክ እንጂ የእኛን ማንነት አይገልፀም ። አልማዝ በድንጋዮች መሃል ስለተቀመጠ ድንጋይ አይሆንም ፤ ዋጋውን የሚያውቅ ባለሙያ እስኪያገኝ ድረስ ግን እንደ ተራ ድንጋይ ሊረገጥ ይችላል ። ወዳጄ ሰዎች ስላልተረዱን ብለን ብርሃናችንን አናጥፋ ።
https://t.me/artladyart
272
ዛሬ የምታውቀውን ትናንት ስላላወቅህ ራስህን ላይ አትፍረድ።
አንዳንድ ትምህርቶች በመፅሐፍ አይመጡም…
ጊዜ ሲያሳልፍህ ብቻ ይገቡሃል።
ስለዚህ ራስህን ይቅር በል።
272
ጊዜያዊ ፈተና የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ የተስፋ ቃላት እንዲያስረሳህ አትፍቀጂ። ዛሬ እያለፍሽበት ያለሺው ማዕበል የሚያበቃበት ቀን አለው፤ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለው ፀጋሽ ግን ለዘላለም የሚኖር ነው። ዓይኖችሽን በማዕበሉ ላይ ሳይሆን ወደ ወደቡ (ወደ እግዚአብሄር) አቅኚ።"
✍️ሄዋን
272
ጡሩ ወዳጆ እና ጡሩ ቡና ሁለቱም ልብን የማሞቅ አቀም አላቸው በሂወታችን ውስጥ መከፋትን በትዝታ ድብርትን በፈገግታ የሚቀይሩ ውድ ሰወች አሉ ልክ እንደማለዳ ቡና ቀናችንን ለሚደምቁልን ንፁህ ልቦች ሰላም ለነሱ ይሁንላቸው ❤🥰
272
ግን አንድ ሰው አለ...
እርጅና ሲጫንሽ
እድሜ ተጠራቅሞ እንድ አስም ሲያፍንሽ
ሽበት እንደማዳይ
በጭንቅላትሽ ላይ
በድንገት ሲፈላ ያይን ከረጢቱ በእንቅልፍ ሲሞላ
ምድጃ ዳር ሁነሽ
መጣፍሽን ከፍተሽ
ያለፈው ዘመን ገልጠሽ ስታነቢ
የኔን ቃል አስቢ
ስንቶች አፈቀሩ በሀቅ በይሰሙላ
የገፅሽ አቦል የውበትሽ አፍላ
ግን አንድ ሰው አለ
ከሌሎች የአዳም ልጆች ያልተመሳሰለ
በእቅብ ድንቋ ነፍስሽ በፍቅርሽ የነደደ
የመልክ ፀዳል ሲያልፍ
ልክ እንደ መስቀል ወፍ ጥሎሽ ያል ነጎደ
ግን አንድ ሰው አለ .....
272
ህይወት በራሷ ፍፁም ባትሆንም፣ እኛ በውስጧ የምንፈጥራቸው ትናንሽ ምክንያቶች እንደ ጠዋት የፀሀይ ብርሃን፣ እንደ ወዳጅ ሰላምታ እና እንደ ግል ህልሞች—ሁሉንም ነገር ውብ ያደርጉታል።
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
እንዴት አደራችሁ🦋🥰"ህይወት መፅሃፍ ናት፤ ትላንት ያለፈ ገፅ ነው፣ ዛሬ አዲስ መስመር ነው፣ ነገ ደግሞ ገና ያልተገለጠ አጓጊ ታሪክ ነው።" ✨መልካም ቀን🌸
https://t.me/artladyart
272
" ዛሬ! ስጥ!!! "
ዛሬ ላይ ተርቦ ተጠምቶ ለመጣ፣
እምነት ባንተ ጥሎ ከቤቱ ለወጣ፣
ፊትህ አጥቁረኽ ለነገ አትበለው፣
እርሱን የቸገረው ዛሬን መሻገር ነው!
ማድረግ ሳይቸግርህ ገንዘብ በእጅህ ኖሮ፣
በተራበ ሰው ላይ አታብዛ ቀጠሮ!!!
ለነገ ነገ አለ ባለቤትም አለው፣
እኔን የቸገረኝ ዛሬን መሻገር ነው!
እንኳን ለተቀባይ ለሰጭም ዋስትና፣
ዛሬ እንጂ ነገማ የእኛ አይደለምና!
272
ሳቄን መልሱልኝ
ተጨዋች ነበርኩኝ ሲበዛ ቀልደኛ
ሳቂተኛም ነበርኩ ሆኘ ደስተኛ
አሁን ግን ከፍቶኛል ነገሩን ሳላውቀው
እስቲ መልሱልኝ ሳቄን ማን ሰረቀው
ግን ምን አጠፍሁኝ እኮ ምን ሰርቸ
ደስ ብሎኝ እዳልኖር ስቄ ተደስቸ
አረ ምን ሰርቸ ምን አደረኮችሁ
የምወደውን ሳቄን ለምን ሰረቃችሁ
አልችልም ያለሳቄ መኖር ተደስቸ
አልጠግብም እርቦኝ በልቸ ጠጥቸ
አንተ ትሁን እሶ እኔ ምን አውቄ
አልገባኝም እኔ ሳቄን መሰረቄ
ሳቄ ትርጉም አለው ለኔ ትልቅ ቅኔ
መልሱልኝ ይቅር አልግባ ኩነኔ
በትንሽ ትልቁ መናደድ ስራየ
ከየትስ መጣ እድህ አይነት ፀባየ
ሳቄን መልሱልኝ ልኑር እደበፊቱ ሁኘ ደስተኛ
ሳላውቀው ሳቄን ተሰርቄአለሁ እናንተ መልሱ
እህህህህህህ ሳቄን መልሱልኝ!!!🤗🤭🌸
https://t.me/artladyart
272
ዋጋህን እወቅ....
ሰዎች እንዲያከብሩህ ከፈለክ መጀመርያ አንተ ራስህን ለራስህን ክብር መስጠትን ተማር። ለራስህን ምትሰጠው ዋጋ ነው ሰዎች እንዲያከብሩህ የሚያስገድዳቸው።
ድክመትህ ላገኘሀው ሁሉ አትንገር። ቁጡብ ሁን ንግግር ለውጥ የሚያመጣ ከሆነ ብቻ ተናገር። ባልተጋበዝክበት አትሂድ። ባለህ ማንነት ደስ ይበልህ በራስ መተማመን ይኑርክ።
272
ስትበስል...
💡 መረጋነት ትጀምራለህ
💡 ስሜትህን መቆጣጠር ትጀምራለህ
💡 ለውጥም አትፈራም
💡ብቸኝነት መቋቋም ትችላለህ
💡ሀላፊነት መውሰድ ትጀምራለህ
💡 ለዓላማህ ትኖራለህ
💡ትችትን በፀጋ ትቀበላለህ
💡 ውድቀት እንደ ትምርት ታያለህ
💡 ራስህን አታመካኝም
💡 ለቃልህ ትጠነቀቃለህ
