uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

HOP Ministry

HOP Ministry

Kanalga Telegram’da o‘tish

HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
616
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+37 kun
+6830 kun
Postlar soni

Ma'lumot yuklanmoqda...

Reaktsiyalar
Izohlar
Telegram Yulduzlari
Eng yaxshi postlar bo'yicha

Ma'lumot yuklanmoqda...

Nashrni tahlil qilish
Postlar
Ko'rish dinamikasi
#ከድካም_ሸሽቶ_ወደ_እግዚአብሔር_መሮጥ፡፡ ድካም እኛን አስሮ፣ ገንዘቡ አድርጎ ለማቆየት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች ዋና ዋናው በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ብቁ አለመሆናችንን ማሳየት፤ የዛልንበትን ነገር፣ ውድቀታችንን በልባችን ላይ ማግዘፍ፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የማይገባን መሆናችንን፣ እግዚአብሔርም በእኛ ደስ እንደማይሰኝ ማሳሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ በእግዚአብሔር ፊት መጸለይ፣ ቃሉን ማጥናት፣ ፈቃዱን ማድረግ ሲገባን ፈቃድ፣ ጊዜ፣ ትኩረታችንን ለሌላ ነገር ሰጥተን ከእግዚአብሔር ፊት ስንጠፋ #ልባችን_እግዚአብሔርን_እንዲሰማ_ክፍት_ካላደረግነው በቅድሚያ ለማድረግ የሚቀናን ሁሉን አልፎ ወደ እግዚአብሔር መገስገስ ሳይሆን፣ በጀመርነው የስህተት መንገድ መቀጠል፣ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ አለመብቃታችንን እያሰብን ወደኋላ ማፈግፈግ ነው፡፡ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እግዚአብሔር የሚወደው፣ የሚሻው በድካማችን ተሸማቀን ከፊቱ እንድንርቅ ሳይሆን ከድካማችን ሸሽተን ወደ እርሱ፣ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድንመለስ ነው፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የእረፍት ጥሪ ብርቱዎችን ወደ እርሱ ለማሮጥ የተነገረ ሳይሆን፤ ደካሞችን፣ ሸክም የከበደባቸውን ወደ አሳራፊው ለመሳብ፣ለማሳረፍ የተነገረ ነው፡፡ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" — ማቴዎስ 11:28 በእግዚአብሔር የጸጋ ዙፋን ፊት በእምነት የምንቀርበውም ያለ አንዳች ድካም የሆንን፣ በራሳችን የበቃን እና ጥንቅቅ ያልን ሰዎች መሆናችንን ለማሳየት ሳይሆን፤ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ምህረትን እንድንቀበል፣ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ነው፡፡ "እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።" — ዕብራውያን 4:16 ከድካም ጋር ስታገል፣ ስንፍናዬ፣ አለመብቃቴ፣ ስህተቴ ገዝፎ ሲታየኝ፣ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ሳፍርና ስሸማቀቅ፣ ለመጸለይ፣ ቃሉን ለማጥናት አቅም ሳጣ እግዚአብሔር ለልቤ አንድ ነገር ሲናገር ተሰማኝ፡፡ ይህም፦ ለድካም፣ ለስንፍና፣ ለየትኛውም ስህተትና አለመብቃት መፍትሔውና መድኃኒቱ ከእግዚአብሔር መሸሽ፣ ወደኋላ ማፈግፈግ ሳይሆን አንዳሉ፣ የሆኑትን ሆኖ፣ በተሰበረ ልብ፣ በእምነት ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ጸጋው ዙፋን መቅረብ ነው፡፡ ይሄ ሲገባኝ በእግዚአብሔር እግር ስር ለመውደቅ አቅም አገኘሁ፡፡ ለእግዚአብሔርም እንዲህ አልኩት፡-  እግዚአብሔር ሆይ ከድካሜ ስሸሽ ወደ አንተ እሮጣለሁ፡፡ ድካም አቅም የሚያጣው፣ ድል የሚነሳው  በአንተ ፊት ብቻ ነው፡፡ አቤቱ ድካሜን እይ፣ ሸክሜን ተመልከት፣ በጸጋህ ጉልበት ከላዬ አንሳው፣ እንደገና አድሰህ፣አጽንተህ አቁመኝ፡፡ ሳልዝል እንድከተልህ ጸጋህን አብዛልኝ አሜን!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 October 11, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
363300Statistikani ko‘rish uchun tizimga kiring
ፀሎቴ__Tselote_Prayer(128k).m4a
87000Statistikani ko‘rish uchun tizimga kiring
#ጸሎቴ፦ እግዚአብሔር ሆይ ብዙዎች አሁን ታይተው ወዲያው እንደ ጤዛ በሚጠፉበት በዚህ ዘመን፤ በምድር ብሰነብት ለአንተ እንዳድር፣ እንድኖር እርዳኝ!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 October 10, 2026
633100Statistikani ko‘rish uchun tizimga kiring
#የፈለግነውን_ነገር_በማጣት_ውስጥ_የእግዚአብሔር_ጥበቃ_አለ። #የፈለግነውን_ነገር_ባለማግኘት_ውስጥ_ለሚያስፈልገን_ነገር_በእግዚአብሔር_ተጠብቆ_መቆየት_አለ። በሕይወታችን ውስጥ ፈልገን ስላጣነው ነገር፣ ከእግዚአብሔር ለምነን ስላልተቀበልነው ነገር እግዚአብሔር ይመስገን። ምክንያቱም እግዚአብሔር የለመነውን ነገር ለእኛ ባለመስጠቱ ውስጥ እኛን ከጥፋት እየጠበቀን ነው። የለመነውን ነገር በመከልከል ለሚያስፈልገን ነገር ጠብቆ፣ ሸሽጎ ለሚያቆየን አምላክ ክብር ይሁን!! #የእግዚአብሔር_ፈቃድ #የእግዚአብሔር_ጊዜ #የእግዚአብሔር_ጥበቃ ✍️ መክሊት አየለ 📆 October 10, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
686403Statistikani ko‘rish uchun tizimga kiring
"ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ። መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።" — ኢሳያስ 40:27-31 (አማርኛ 1954)
811304Statistikani ko‘rish uchun tizimga kiring
Track_14_Erasih_Asitemarekegn_እራስህ_አስተማርከኝ_Aster_Abebe_Vol_2128k.m4a
196200Statistikani ko‘rish uchun tizimga kiring
" #ጉዳይ_የለኝም_ከአንተ_የሚያጎድለኝ፤ #ቁምነገሬ_ነህ_ሌላ_ምን_አለኝ። " #በየዕለቱ_ከእግዚአብሔር_ጋር #እግዚአብሔርን_ማስቀደም #እግዚአብሔርን_መፈለግ #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional https://t.me/hopministry10
1 197201Statistikani ko‘rish uchun tizimga kiring