es
Feedback
HOP Ministry

HOP Ministry

Ir al canal en Telegram

HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
560
Suscriptores
+324 horas
+217 días
+5530 días
Número de Publicaciones

Carga de datos en curso...

Reacciones
Comentarios
Estrellas de Telegram
PUBLICACIONES TOP por

Carga de datos en curso...

Análisis de publicación
Mensajes
Ver dinámicas
ዘማሪ_ቤተልሄም_ወልዴ_አንተን_የታመነ_መች_አፈረ_Protestant_mezmur_ፕሮቴስታንት_መዝሙሮች128k.m4a
64000Loading...
#የእግዚአብሔርን_የጊዜ_ሰሌዳ_አለመቅደም። #በእግዚአብሔር_አሳብ_ውስጥ_መቆየት። #እግዚአብሔርን_መታመን። #የእግዚአብሔርን_ፈቃድ_ማወቅ። #የእግዚአብሔርን_ጊዜ_መጠበቅ። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional https://t.me/hopministry10
354101Loading...
#የማለዳ_ጸሎቴ፦ እግዚአብሔር ሆይ የቀኑ ክፋት እንዳይዘኝ፣ በቀኑ ሸክም እንዳልያዝ፣ አንተን በማሳብ ውስጥ ሕይወቴን እንዳኖር፣ እንዳቆይ እርዳኝ!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 September 18, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
601202Loading...
በጎ ፈቃዱን ማድረግ እንዳለብን ነግሮን፣ አድርጉ ብሎ፣ ለብቻችንን ጥሎን ዘወር የማይል አምላክ እግዚአብሔር! ይልቁንም በጎ ፈቃዱን መፈለግ እንድንችል ልባችንን ያሰፋል፤ ደግሞም በጎ ፈቃዱንም በእኛ ውስጥ በሚኖረው በመንፈሱ በእኛ ውስጥ ይሠራዋል። ታዲያ በእግዚአብሔር #ድግፍ! ማለት፣ እርሱ በእኛ ውስጥ እንዲሰራ ራሳችንን ለእርሱ ማስገዛት እንዴት አያዋጣንም?! እግዚአብሔርን ማክበር ሽቶ በተቃራኒው ደግሞ ያለ እግዚአብሔር ሮጦ፣ በራስ ታግሎ የትም አይደረስም! ይልቁንም እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእኛ ውስጥ በሚሠራው በእግዚአብሔር እርፍ፣ ድግፍ ብሎ፣ እርሱን ተጠግቶ ሲኖር ክርስትና ቀላል ነው። ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹² ስለዚህ፣ ወዳጆቼ ሆይ፤ ሁልጊዜም ታዛዦች እንደ ነበራችሁ ሁሉ፣ አሁንም እኔ በአጠገባችሁ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም አሁን በሌለሁበት ጊዜ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ ¹³ እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። ✍️ መክሊት አየለ 📆 September 15, 2024 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
975104Loading...
#በየዕለቱ_የሚጨምር_እምነት። ከእግዚአብሔር ጋር በቆየን፣ በፊቱ በሰነበትን መጠን እግዚአብሔር ላይ ራስን ወደ መጣል፤ ይበልጥ እርሱ ላይ ጥገኛ ወደ መሆን ማደግ፣ በእውቀት በበሰልን እና ከእግዚአብሔ
#በየዕለቱ_የሚጨምር_እምነት። ከእግዚአብሔር ጋር በቆየን፣ በፊቱ በሰነበትን መጠን እግዚአብሔር ላይ ራስን ወደ መጣል፤ ይበልጥ እርሱ ላይ ጥገኛ ወደ መሆን ማደግ፣ በእውቀት በበሰልን እና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ብዙ በቆየን መጠን እምነታችንን እያደረጀን መሄድ እንዴት መታደል ነው?! ትናንት በመንፈሳዊው ነገር ልጅ በነበርኹ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በቅጡ ሳልረዳ እግዚአብሔር ላይ የበረታ እምነት ነበረኝ። ከእርሱ በላይ ስለእኔ የሚያውቅልኝ እንደሌለ ጠንቅቄ አውቃለሁ። በሆነው ባልሆነው፣ ሰበብ አስባብ እየፈለግኹ ወደ እግዚአብሔር ለመሮጥ፣ ራሴንና ነገሬን እርሱ ላይ ለመጣል አቅም ነበረኝ። በእግዚአብሔር ቤት ስጎለምስ፣ በእውቀትም እንዳደግኹ ሲሰማኝ፣ አእምሮዬም ሁሉን ለመመርመር ሲቸኩል እግዚአብሔርን አምኖ ከመከተል ይልቅ ለሁሉ ነገር ማብራሪያ መጠየቅ ሲቀናኝ ራሴን አገኘሁ። በእድሜ፣ በእግዚአብሔር ቤትና በፊቱ በመሰንበት፣ በእውቀት እያደግኹ በሄድኹ መጠን እምነቴም እየጨመረ፣ እግዚአብሔርን መደገፌ እየበረታ ቢሄድ ብዬ ተመኘሁ፤ በዚህ ማለዳም ለእግዚአብሔር ይህንን ልመና ላቀርብ ወደድኹ፦ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ከአንተ ጋር በመሰንበት በነገር ሁሉ ሳድግ በየዕለቱ በሚያድግ እምነት፣ ዘወትር በሚጨምር አንተን መደገፍ ባርከኝ። አንተን ይበልጥ እያወቅሁኽ ስመጣ፣ የቃልህ ፍቺ ሲበራልኝ አንተ ላይ ያለኝ መደገፍ፣ ራሴን አንተ ላይ መጣሌ ይጨምር። አቤቱ ያለ ቅድመ ሁኔታ የሆነ እምነት፤ ሳያይ፣ ለእያንዳንዱ ነገር ማብራሪያ ሳይጠይቅ አንተን የሚከተል ልብ፤ ከሚያየው ነገር በላይ ቃልህን የሚያምን ማንነት ስጠኝ!! አሜን!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 September 15, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
922405Loading...
ቃልህ___Kalih(128k).m4a
880201Loading...
#ከእግዚአብሔር_ቃል_ጋር_መቆየት። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በምንወስደው ጊዜ፣ በምንቆየው ቆይታ እጅግ አትራፊዎች ነን። ሕያው፣ የሚሰራ ብቸኛው ቃል የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። እኛን በሚያይ፣ በሚያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ሁሉ ነገራችን የተገለጠና የተራቆተ ነው። ሆኖም እግዚአብሔር ድካምን ቢያይብን፣ እንከን ቢያገኝብን፣ ገልጦ ሊያዋርደን ሳይሆን፣ በቃሉና በመንፈሱ ሊሰራን፣ ሊገራን፣ እርሱ የወደደውን ቅርጽ ሊያስይዘን የታመነ ነው። የክርስቲያናዊ ሕይወት ቱምቢ፣ የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መለኪያ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በቃሉ ተመዝኖ ያለፈ፣ ይሁንታን እንደሚያገኝ ሁሉ፣ በቃሉ ተመዝኖ የወደቀም ከቃሉ መስፈርት የራቀ መሆኑ ይገለጣል። የእግዚአብሔር ቃል በአንባቢው ላይ ያለውን ሥራ እንደማንኛውም መጽሐፍ ንባብ፣ አእምሮአዊ እውቀትን ማስፋት ላይ ብቻ አያቆምም። ይልቁንም የአንባቢውን ሁለንተና አንዳች ሳያስቀር ይመረምራል፣ ይሰራል፣ ይቀይራል። ምክንያቱም ቃሉ ሕያውና የሚሰራ ነውና። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ለመቆየት ብርታት ከሚሆነን ነገር መካከል አንዱ፣ የቃሉ ሕያው መሆንና የሚሰራ መሆኑ ነው። በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደ እርሱ ብንቀርብ እንደነበርን የማይተወን፣ ዘወትር ሊሰራን የታመነ፣ አላስፈላጊ ሸክሞቻችንን አራግፎ በእግዚአብሔር ሸክም የሚሞላን፣ ቸሩ እግዚአብሔር የሰጠን የሕይወታችን መመሪያ ቅዱስ ቃሉ ነው። እውቀትን ከመቅዳት እልፍ ያለ ዓላማ ይዞ ወደ እግዚአብሔር ቃል የተጠጋ፣ ከቃሉ ጋር የቆየ፣ ቃሉን ሁነኛ ወዳጅ ያደረገ ሰው፣ መቼም የማይሳሳት መካሪ፣ እውቀት የማይጎድለው አስተማሪ፣ መስራትና ማበጃጀት የማይደክመው ፍጹም አድርጎ ሰሪ ያገኛል። ከሁኔታዎች እልፍ እያልን ከቃሉ ጋር እንቀመጥ፣ እንቆይ፤ እስከ ዛሬ ያላየነውን እልፍ በረከት እናገኛለን!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 September 14, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
1 092402Loading...