ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше4 416
Підписники
+1224 години
+287 днів
+1 15930 днів
Архів дописів
Repost from Amhara Revolution
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ድረስ ሞላ የትግሉን አሁናዉ ሁኔታ በማስመልከት ያስተላለፈዉ መልዕክት!!!!!!
አብይ አህመድ በአራቱም ማዕዘን ጦሩን አዝምቷል እንደ አመጣጡ ጀግኖች ስራ ላይ ናቸው።
ድሎች አሉን አጠናክርን እንመለሳለን እኛ ጋ አማራ ነፃ ሳይወጣ በአራቱም ማዕዘን አዲስ አበባን ጨምረን መተኛት የለም!!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ትግላችን የአማራ ትግል ሾተላዮችንም በአስተማማኝ ሁኔታ ማምከን ጭምር ነው‼️ በ አረፋይኔ ተጎድ Arefyne T Sraye
**
ባለን አጭር የትግል ተሞክሮና ውስን ንባብ እንደተገነዘብነው እንደገባንም፧ ከትናንት እስከ ዛሬ የአማራን ትግል ስምረት የሚያከሽፉ ኹለት ሾተላዮች አሉ።እነሱም:-
፩| የ ተቋም ግንባታ ክሽፈት
፪|መሪ የመውለድ /ራሱን ዝግጁ አድርጎ የተገኜን መሪ ጠብቆ ለተገቢው ደረጃ የማድረስ ሾተለይ ናቸው።
አማራ ከተቃጣበት አደጋ ራሱን ለማዳን እና የሚወዳትን ሀገሩን እየጠሏት ከሚመሯት አፍራሾቿ እጅ ለመታደግ ትግል ማድረግ ከጀመረ ዋል አደር ብሏል።በትግል ሂደቱ ውስጥም ከመዐህድ እስከ አዴሃን፣ከቤተ አምሓራ እስከ አብን ከአስራት እስከ..... የተለያዩ የትግል ተቋማትና ድርጅቶችን ለመመስረት (በብዙ ዋጋ )ብርቱ ሙከራ ሲደረግ ቆይቷል። ተቋማቱን ማጽትና ማስቀጠል ላይ ግን ተደጋጋሚ ክሽፈት እያጋጠመ በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ ለመቆየት ግድ ሆኖ ቆይቷል።
እንደተጠቀሰው ሁለተኛው የአማራ ትግል ሾተላይ(መጨንገፍ) መሪ መውለድ አለመቻል እና በአንዳች አጋጣሚ የተገኙትን ደግሞ ጠብቆና ተንከባክቦ የሚሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ ማድረግ አለመቻል ነው።
በተለይ በዚህ ረገድ ከባዱ ነገር መሪ መውለድ አለመቻሉ ብቻ አይደለም። በታሪክ አጋጣሚ በዘመን አንድ ጊዜ ብልጭ ያሉ የትውልድ አብሪ ክዋከብትን ጠብቆ ደግፎና አጎልምሶ ህዝብን ወደ አንዳች ምዕራፍ መርተው እንዲያሻግሩ ከማብቃት ይልቅ፣ የድመት ፖለቲካ በወለደው ልጅን የመብላት ክፉ በሽታ ተለክፎ ብቅ ያሉ መሪዎችን ማጥፋት የተቆየበት የታሪክ ርግማን ነው።
[ከአስማረ ዳኜ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ከሳሙኤል አወቀ እሰከ ከጎቤ መልኬ ..እስከ ነብዩ ጀኔራል አሳምነው ጽጌ፣ ከአስቻለው ደሴ እስከ ሻምበል መማር ጌትነት ፣ ከነ አዲሱ ቢተው አስከ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ .....] ጆሮ ነፍጎ፣ ለጠላት አሳልፎ በመስጠትና አዋክቦ ማጥፋት የተፈጸመባቸው መሪዎችን መጥቀስ ከበቂ በላይ ነው።
~ ~
ዛሬም ከጠላት በላይ እየታገልን ያለነው እነዚህን የአማራ ትግል ሾተላዮች ለማምከን ነው። ትግሉ ከዚህ አዙሪትና መጥፎ የታሪክ ድግግሞሽ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመውጣት ጭምር ነው።
ለዚህም ነው ተቋምና ተቋማዊነትን ማንበር እንዲሁም መሪ ጥበቃን አውራ ተግባራቶቻችን አድርገን የምንለው፤ የትግላችን ግብ /ስኬት በነዚህ አልፎ የሚሆን ስለሆነ!
የሦስት ትውልድን ምጥና ህልም ተሸክሞ የሚቃትተው የኛ ትውልድ ግን በእውነት ሾተላዩን ያመክናል፤አዎ ለድል የታጨው እና የታሪክ ሙሽራ የሆነው አዲሱ ትውልድ ሁሉንም ያሳካል !!!!!
አማራነት ያሸንፋል !
ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም
የአፋብሀ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ የ6ኛ ክ/ጦር ፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ
አረፋይኔ ተጎድ Arefyne T Sraye
[ ከሰም ያደርጋል ክስም ]
"ከሰም ያደርጋል ክስም" የተባለለት ግዙፉ ክ/ጦር በቀጣይ ወደ ኮር ማደግ አለበት ከሚሉ ቀዳሚ ሰዎች አንዱ ነኝ!!
እውነት ለመናገር በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ አሉ ከተባሉት ጠንካራ ክ/ጦሮች አንዱ ነው።
ከሰም ክ/ጦር እንደ ድርጅት የዘመነ፣የህዝብ አደረጃጄቶች በሁሉም ቀበሌዎች እና በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሁሉ ሲቪል አስተዳደር ያዋቀረ፣የሰለጠነ፣የክ/ጦር ስታፍ ያለው፣የስራ ስምሪቱን ድርጅታዊ መዋቅሩ በጠቅላላው ችግር ፈቺ የሆነ ፣አመራሩንና አባሉን በተደጋጋሚ የሚያሰለጥን፣ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓትን የሚከተል፣ከሰም ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው ሁሉም ቀበሌዎች ባንዳን የሚከታተል የማህበረሰብ መረጃ ፍሰት ያለበት እንድሁም በመልካም አስተዳደር እና ተያያዥ ጉዳዮች ጭምር እጅግ ፍትሃዊ የሆነ ስራ የሚሰራበት ፣አማራ የሆነ ሁሉ በማንነቱ በእምነቱ ተከብሮ የሚታገልበት ክ/ጦር ነው።
ከሰም ክ/ጦር ብዙ የተግባር አማራዎች የተሰበሰቡበት፣ሰፊ ሰብአዊ ሃብት ያለው በሰራዊት ቁጥር ከፍ ያለ፣ከጠላት በቅርብ ርቀት የሚገኝ እንዲሁም የትግላችን መደማደሚያ ቦታዎችን ሸፍኖ የሚታገል ክ/ጦር መሆኑ ከሌሎች የአፋብኃ አደረጃጀቶች የተለየ ያደርገዋል።
ስለሆነም እኔም እንደ ታጋይ በከሰም ክ/ጦር ውስጥ ሆኘ በቅንነት ስታገል እና ሳታግል በመቆየቴ ኩራት ይሰማኛል!!
ስትራቴጅካዊ የመታገያ ቀጠና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሁሉም የአፋብኃ አመራር እና ሰራዊት የቀጠናውን አስፈላጊነት በደንብ አስበው እና ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩበት ስል በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ!!
ከሰም ክ/ጦርም እስከ አሁኑ ይዞት የነበረውን አስተዳደራዊ ልምድ በማሳደግ እና ተጨማሪ አቅም በመፍጠር የአማራው ኩራት ለመሆን የጀመራችሁት አጠቃላይ ለውጥ እና ጠንካራ ዝግጁነት በእጅጉ የሚያስደንቅ ነው።
በተግባር አማራዎች እና የድርጊት አመራር እና ሰራዊት የተገነባው ከሰም ክ/ጦር በአፋብኃ አሳምነው ዕዝ ስር ሆኖ ለቀጣይ ግዳጅ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመገኘታችሁ ኮርተናል!!
ከሰም ክ/ጦር በአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ውስጥ ከሚገኙት ጠንካራ ኮሮች ውስጥ ተመድቦ እንደምናየው አልጠራጠርም!!
አይበገሬዎቹ የአሳምነው ልጆች በቀጣዩ ተልዕኳችሁ አስደማሚ ተጋድሎ እንደምታደርጉ አልጠራጠርም!!
ከሰሞች በርቱ!!💪
እኔም እንደ ታጋይ አማራም እንደ ህዝብ ይኮራባችሗል!!
ምስሉ፦ የከሰም ክ/ጦር እና የድርጅት አመራሮች በክትትል ስራዎች ወቅት የተነሳነው ነው!!
እንበርታ አማራ💪
[አርበኛ አሸናፊ ገናን ]
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
በሀብሩ ወረዳ በምትገኘዉ በመርሳ ከተማ መሸጎ የሚገኘዉ የመከላከያ ሀይል ኒኒ በር ያለዉን የወገን ሀይል ለማስለቀቅ ሲል በቀን 2/2/2018 ዓ/ም ከወልደያና መርሳ ተነስተዉ ወደ ደሴና አድስ አበባ ሲጓዝ የነበረን ህዝብ ከመኪና አዉርደዉ በግር አሰልፈዉ ሲያስመሯቸዉ ተይተዋል ጥንቃቄ ይደረግ ሲሉ የንስረ አማራ ምነጮች ገልፀዋል‼️
02/ዐ2/2018 ዓ.ም
[ አሳምነው ዕዝ ]
የአማራይቱ ልጅ አሳምነው እዝ በቀኝ በግራ የተፈተነው
ኢንጂነር ደሳሣለኝ ሲያስብ ሸዋ የሚመራው አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ይችላል !💪
ይሄ የፋኖ ኃይል ከአየር ኃይል ልዩ ኮማንዶ ዩኒት እስከ special ኮማንዶና መከላከያ ፣ ከአማራ ሚሊሻ፣ፖሊስና አድማ በትን እስከ ኬሚሴ የልዩ ዞኑ ሚሊሻ ፣ፖሊስ ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል እስከ ሸኔ ሀይል ጋር እየተፋለመና ከወገን በኩልም በተቃራኒው የተሰለፉ ወንድሞቹ ጋር ብዙ ፈተናወችን እያለፈ አሁን ካለበት ጠንካራ ቁመና ላይ የደረሰ አስተማማኝ የአማራ መከታ ኃይል ነው።
ይሄ የአፋብኃ ደ/አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ የሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናወች ለወደፊት ለሚደረጉ ወሳኝ ፍልሚያወች ለወገን ሃይል ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን ለዚህ ከሚያግዙ ወሳኝ ስትራቴጅክ ቦታወች አንዷ የሆነችውን ግሸራቤል ከተማን በነበልባል ክንዱ ከወራሪው ቡድን ነፃ አድርጓል💪
አሳምነው ዕዝ ይችላል ስልህ💪
የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በአፋብኃ የደረሰበትን ጥቃት መቋቋም ሲያቅተው በወገንን አሰላለፍና መጠነኛ ውጊያ ብቻ ከመደምሰስ ለመዳን የወረዳ ከተሞችን ጥሎ መፈርጠጥ ጀመረ።
================
ከሰሞኑ በዘመቻ አደም አሊ(አባናደው) በምኒሊክ ዕዝ ከፍተኛ ውርደት የተከናነበው የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በአሳምነው ዕዝ ተጨማሪ ውርደት ተከናንቦ ከተሞችን ለቆ እየወጣ ነው::
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በሸዋ ቀጠና በተደጋጋሚ በብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን ላይ በወሰደው የደፈጣና የመደበኛ ውጊያ ክፉኛ የተቀጠቀጠው ግሪሳ የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት በፍረሃት ቆፈን ተውጦ የግሸ ራቤል ወረዳ ዋና መቀመጫ ራቤል ከተማን ለቆ ወጥቷል::
ይህ የጥፋት ቡድን ከራቤል ከተማ ሲወጣ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጠላቻ በሚያሳይ መልኩ በርካታ የማህበራዊ ተቋማትን እና የፋይናንስ ተቋማት ዘርፎና አውድሞ የሔደ ሲሆን በተለይም ባንኮችን እና የጤና ተቋም ንብረት በሚዘገንን ሁኔታ ዘርፎ ወጥቷል::
በአሳምነው ፅጌ የመንፈስ ልጆች ከበባ ውስጥ የነበረችውን የራቤል ከተማ ለቆ የወጣው የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን በባንዳው አበባው ታደሰ ከመደምሰስ ለቀህ ውጣ በሚል ቀጥተኛ ተዕዛዝ እንደሆነ ከቦታው ማረጋገጥ ተችሏል::
የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን የግሸ ራቤል ወረዳ ዋና ከተማ ራቤልን ለቆ እንደወጣ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የብሩኬ ደምሴ ክፍለ ጦር ከተማዋን ተቆጣጥሮ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር በደጅ አዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድና እና በአብራጂት ብርጌድ መካከል ጠላት የአቀደው የደም መፋሰስ እልቂት ከሸፈ።
፨በረሀ ላይ በሌብነት በአሰማራቸው የደም ነጋዴ ሌቦች አማካኝነት ለዘመናት አብረው የኖሩትን ማህበረሰቦች በወሰን አጥሮ እርስ በእርስ ለማታኮስ እና ለማመታታት አቅዶ የሰራ ቢሆንም ከሁለቱም ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዋች፣የቀበሌ የጎበዝ አለቆችና ከሁለቱ በተውጣጡ የብርጌዱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዚህ የወሰንና የድንበር እንካለል አጀንዳ የጠላት እቅድ እንጅ ለዘመናት አብሮ የኖረው ማህበረሰብ ጥያቄ አለመሆኑን ግንዛቤ ተፈጥሯል።
፨ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ በጎጃም የዛሬው አፋብኃ በአወጣው የወል መሬት ማስከበሪያ ደንብ መሰረት ጉዳዩ መፍትሄ የሚሰጠው መሆኑን በማስገንዘብ እርስ በእርስ ማህበረሰቡን በማጋጨት ትርፍ ሊያገኙ የነበሩ የደም ነጋዴዋችን በመለየት ከሁለቱም ወገን ስልክ የዘረፉ ሌቦችን ተከታትለን ለፍርድ ለማቅረብ ከስምምነት ላይ በመድረስ ጉዳዩን በሽምግልና መፍታት ተረ ችሏል።
አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
የሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ታናሽ ወንድም የኔጌታ ልንገረው ❤
ከአንድ ቤት 3 ወንድማማቾች ናቸው ለነፃነት እና ለዚህ ለታላቁ የአማራ ሕዝብ ትግል ማቄን ጨርቄን ሳይሉ የወጡት!
+5
#አፋብሀ
ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያቆብ ፩ኛ ኮር አናብስቶቹ የብሩኬ ደምሴ ክፍለጦር አመራሮች ራቤል ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብላ ተቀብላቸዋለች።
የባንዳው መጨረሻ የአብይ ጦር ጀብዱ
*
ባንዳው ሚሊሻ 8 ቁጥር ታስሮ ተደበደበ
================
👉 ነገሩ እንዲህ ነው፤ በቀን መሰከረም 29/2018 ሰከላ ግሽ አባይ ከተማ የመሸገው 2 የአሸባሪው አባላት ከአቅም በላይ ጠጥቶ በመስከር ከምሽቱ 12:00 ላይ በግሽ አባይ ከተማ ማህበረሰብ ላይ የተኩስ እሩምታ ይከፍታሉ። የመከላከያዎችን ድርጊት ያዬ፤ ሙሉነህ የሚባል ሚሊሻ የመከላከያ አባላቱን መሳሪያቸውን ተቀብሎ ይልካቸዋል። የመከላከያ አባላቱም ወደ ካምፕ በመሄድ ለአለቆቻቸው ያመለክታሉ።
ባንዳው ሙሉነህም መሳሪያውን ከተቀበለ በኋላ ለጌቶች አሰረክቤ ሽልማት አገኛለሁ እሰከዚያ አረቄዋን አንድ ሁለት ብዬ ልውጣ በማለት ወደ አረቄ ቤት ይገባል። የመካላከያው ሻለቃ ከተት ሰራዊት በማለት ከተማዋን አስከበባት፤ አረቄ ቤቶች ተፈተሹ። ባንዳው ሚሊሻ ሙሉነህ ከእራሱ መሳሪያ ጋር 3 ክላሽ እንደያዘ አረቄ ቤት ተገኘ። ጨካኙ እና አሸባሪው የመከላከያ ኃላፊ ባንዳው ሙሉነህን አረቄ ቤት እንዳለ በሰደፍ ጭንቅላቱ ላይ አሳረፈበት።
ሚሊሻ ሙሉነህን ከአረቄ ቤት በሰደፍና በአፈሙዝ እየቀጠቀጡ ወደ መስመር አወጡት። ባንዳው ሙሉነህን የ10 ደቂቃ መንገድ አንበርክከው ሲነዱት ካመሹ በኃላ ውሀ የሞላ ጉድጓድ ውስጥ ተንበርክኮና 8 ቁጥር ታስሮ ከ12:30 እስከ ሌሊቱ 6:00 አስመሽተውታል። አንዳንድ የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚሉት ሌሊቱን በሙሉ ተንበርክኮ አድሯልም ይላሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን ለሚሊሻ ሙሉነህ አንድም የብልጽግና አመራር አልደረሰለትም፤ ሁሉም በሚባል ደረጃ ባላዬ ባልሰማ ጀሮ ዳባ ልበስ በማለት አልፎታል።
✍️"የአህያ ባል ከጅብ አያድንም" አይደል የሚባለው፤ ብልጽግናን አምኖ የተጠጋ ከመበላት አይድንም።
👉ሰከላ የገባችሁ የሚሊሻ አባላት በሙሉ የሙሉነህ እጣ ፈንታ ሳይገጥማችሁ አባቶች ሲተርቱ ሳይቃጠል በቅጠል ይላሉና፤ ተበልታችሁ ሳታልቁ ይቅርታ እየጠየቃችሁ ወደ ማህበረሰብችሁ እንድትቀላቀሉ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን። ከእነ ትጥቁ ለሚወጣ ሚሊሻ የስራ ማስጀመሪያ የሚሆን ደጎስ ያለ ገንዘብ ከግዮን ብርጌድ የሚከፈለው ይሆናል።
👉 ፎቶው በአገዛዙ አረመኔ አራዊት ሰራዊት የተረሸኑ አዛዉት አባት የአገዛዙን የጭካኔ ጥግና ቀጣይ ይህ እንደሚገጥማችሁ ለማስታወስ ያክል ነው!!
"የግዮን ብርጌድ ህ/ግንኙነት
ጥቅምት ፩/፳፻፲፰
ጎጃም-ዓምሓራ
