أبو نعمان إبراهيم አቡ ኑዕማን
Відкрити в Telegram
ይህ ቻናል ከሁሉም የጥመት አንጃ የፀዳ ኢስላማዊና ኪታብ አስፈላጊ የዲን እውቀት የሚተላለፍበት ነው። أحب السنة وأهلها وأبغض البدعة وأهلها https://t.me/eibrahimkeyeredin
Показати більше5 238
Підписники
-224 години
+527 днів
+33530 днів
Архів дописів
ከታች ካሉት ውስጥ የቱ ነው የሰለፊዮች ሌላኛው መጠሪያ👇👇
ትክክለኛውን መልስ በመንካት የዳእዋ ቻናሎችን ይቀላቀሉ
🟢በሙብተዲዖች መስጂድ እና መርከዝ ሄዶ ዳዕዋና ቂርኣት መስጠት (ማስተማር) እንዴት ነው?!!
🎤ፈታዋውን ከሰጡት ዑለማዎችውስጥ፡
አሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን
አሸይኽ ሱለይማን አሩሀይሊይ
⏸ከፈታዋዎቹ ከሚገኙ ቁምነገሮች ውስጥ፡
አይቻልም በተለይም፡⤵️⤵️
✏️የሱነህ መስጂድ ትቶ እነርሱ ጋር መስጠት
✏️አንዴ ሱኒይ ዳዒ ሌላ ጊዜ ሙብተዲዕ ሰው እያፈራረቁ መድረክ የሚሰጡ ከሆነ ወይም ቀላቅለው የቀጠሩ ከሆነ
✏️እዛው እነርሱ ጋር ቢደዓቸው በግልፅ የማይብራራ እና ረድ የማይደረግባቸው ከሆነ
✏️ለእነርሱ መተናነስ ካለበት
✏️በሰዎች ላይ ብዥታ የሚፈጥር ከሆነ
✏️ከሙብተዲዕ ጋር ሙጃለሳ (መቀማመጥ) ካለው።
✏️በእነርሱን በዲን እንቅስቃሴያቸው ማገዝ ካለበት።
👉በሱፊይ ፣ በኢኽዋን ፣ በሙመይዓህ ወይም በጥምራቸው መስጂዶችና መድረሳዎች ተቀጥረው የሚያገለግሉ ከእነዚህ ችግሮች ፀድተዋል⁉️
ሙብተዲዕን መራቅ (ተመዩዝ) እኮ መሰረታዊ ጉዳይ (አስል) ነው።
ሙብተዲዕን በቀረብክ ቁጥር ሰለፊዮችን እየራቅክ ትሄዳለህ።
https://t.me/FATTAWAS
ሸይኹ ለደረሶች የሚሰጡት የቀኑ ደርስ ቀጥታ ስርጭት በኢማሙ አህመድ መስጂድ እና መድረሳ ቻናል ላይ ይተላለፋል
የኢማም አህመድ ቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Imamu_Ahmed1448
t.me/Imamu_Ahmed1448
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ!
ይህ የሌራ ኢማሙ አሕመድ ጀመዓ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
በዚህም መሰረት መስጂዱ ላይ በሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል ለተሚይ የሚሰጡ ዱሩሶች በዚህ ቻናል ላይቭ (ቀጥታ) የሚተላለፍ ይሆናል።
የቻናሉ ሊንክ ፦
t.me/Imamu_Ahmed1448
🗓 ጁማደል ኡላ 1/5/1448
🔷 የነብያቶችን መቀማመጥ ማየት የፈለገ የዑለሞችን መቀማመጥ ይመልከት !
يقول سهل بن عبد الله التستري – رحمه الله –
" من أراد إلى مجالس الأنبياء فلينظر إلى مجالس العلماء " .
مفتاح دار السعادة ص (1/118)
ሰህል ኢብኑ ዐብዲላሂ አትቱስትርይ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –
" የነብያቶችን መቀማመጥ ማየት የፈለገ ( የሱና) የዑለሞችን መቀማመጥ ይመልከት" !።
http://t.me/bahruteka
👉 ስጁድ የወረድክበት መሬት የሞትክ ቀን ያለቅሳል !
يقول عطاء الخراساني – رحمه الله –
ما من عبد يسجد لله سجدة في بقعة من بقاع الأرض إلا شهدت له يوم القيامة، وبكت عليه يوم يموت " .
حلية الأولياء ص (5/197)
አጧእ አልኹራሳንይ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –
" ከምድር በየትኛውም ቦታ ለአላህ አንድ ስጁድ የሚያደርግ የለም የቂያማ ቀን የሚመሰክርለትና የሞተ ቀን የሚያለቅስለት ቢሆን እንጂ "
http://t.me/bahruteka
🔷 አንድ ሰው ዐቂዳው ሰለፍይ ሆኖ ስነምግባሩ ሰለፍይ ላይሆን ይችላል !
يقول الشيخ الألباني – رحمه الله –
" قد يكون الشخص سلفيا في عقيدته ، ولكنه ليس سلفيا في تربيته وسلوكه "
سلسلة الهدى والنور ص (781)
ሸይኽ አልባንይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –
" አንድ ሰው ዐቂዳው ሰለፍይ ሆኖ ነገር ግን አስተዳደጉና ግብረገብነቱ ሰለፍይ ላሆን ይችላል "።
http://t.me/bahruteka
👍ሰውን ማማት የመተው ምርጥ መንገድ
🎙قَالَ ابْنُ أَبِي حَاتِمٍ: حَدَّثَنَا أَبِي، حَدَّثَنَا حَرْمَلَةُ، سَمِعْتُ ابْنَ وَهْبٍ يَقُوْلُ:
نَذَرتُ أَنِّي كُلَّمَا اغْتَبْتُ إِنْسَاناً أَنْ أَصُوْمَ يَوْماً، فَأَجْهَدَنِي، فَكُنْتُ أَغْتَابُ وَأَصُوْمُ، فَنَوَيْتُ أَنِّي كُلَمَّا اغْتَبتُ إِنْسَاناً، أَنْ أَتَصَدَّقَ بِدِرْهَمٍ، فَمِنْ حُبِّ الدَّرَاهِمِ تَرَكتُ الغِيْبَةَ.
📚سير أعلام النبلاء
♦️ትርጉሙ;-
🎙ኢብኑ አቢ ሐቲም እንዲህ አለ፦
አባቴ ነገረኝ፤ ሐርመላህ ነገረን፤ ከኢብኑ ወህብ ሰማሁ፣ እንዲህ ሲል፦
“አንድን ሰው ባማሁት ቁጥር አንድ ቀን ልጾም ብዬ ስለት ገባሁ!!ይህ (ጾሙ) ግን አደከመኝ እያማው እጾምም ነበር!!
✅ከዚያም፦"አንድን ሰው ባማሁት ቁጥር አንድ ብር ሰደቃ አደርጋለሁ ብዬ ወሰንኩ።
ገንዘብ ስለምወድ ሐሜትን ተውኩ።”
📚 (سير أعلام النبلاء)
https://t.me/abu_abedelah_Ezedin_inbnu_Siraj
🟢ተሽከርካሪ ወንበር💺💰💎
የስልጠኗ ኩርሲይ ያቺ ተሽከሪካሪ ፣
ስንቱን አጦዘችው የኋሊዮሽ ዲድሪ ፣
ስንቱን አማለለች አቋም አስቀየረች ፣
ሙብቲዲዕ ሰቃቅሎ ሰለፊዩን ሲተች ፣
ተባብረው በድምር ሰለፊያን ቀብረው ፣
መሃላ ፈፅመው ባንድ ተሰልፈው ፣
ጀግና መሳይ ሳለ ያኔ የምናውቀው ፣
ሱና ላይበረዝ እተጋለሁ ያለው ፣
የብዥታ ንፋስ አቋሙን ሲንደው ፣
እንዲህ ሲፈዝብን ነሻጣው ደንዝዞ ፣
የጦር አፈሙዙን በሀቅ ላይ መዞ ፣
ስልጣን ሲከፋፈል ባጢልን አንግሶ ፣
ኡለሞችን ሲርቅ ንቆ አሳንሶ ፣
ካርታው ተዛብቶበት ቀጥተኛ መስመር ፣
ገርሞ የገረመን ካስተዋልነው ነገር ፣
የመገልበጥና የመቀልበስ ሚስጢር ፣
ለኡማው መበተን ዋነኛ ምክንያት ፣
ኢኽዋን እና ሟሚት የተደመሩላት ፣
ተሽከርካሪ ወንበር የስልጣን ማማ ናት !
ለወንበሯ ፍቅር ለሹመት አበዱ ፣
በዲን ስም ነገዱ ዲኑን እየናዱ ፣
ባንድነት መፈክር ልዩነት ማገዱ ፣
ምክር አልገታቸው በስሜት ተነዱ ፣
በቤተ መጅሊሱ በህገ መጅሊሱ ፣
ለመውሊድ ለሺርኩ ሰርክ ቢደግሱ ፣
መውረዳቸው ላይቀር ወንቧራም ማርጀቷ
ዱንያም ሸብራቃ ሲራገፍ ውበቷ ፣
ወደ ቀብር ቤቱ አይቀርም ማምራቱ ፣
አፈር ተንተርሶ ባፈር መተኛቱ ❗️
يقول الله تعالى ذكره :
﴿تِلْكَ الدَّارُ الآخِرَةُ نَجْعَلُهَا لِلَّذِينَ لا يُرِيدُونَ عُلُوًّا فِي الأرْضِ وَلا فَسَادًا وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ﴾ [القصص ٨٣]
✍ሸምሱ ጉልታ ዐብዱረህማን
https://t.me/Abuhemewiya
ገባገባበሉ
በኡስታዝ ሙሀመድ ኸድር
ተጀመረ
ተጀመረ
ተጀመረ
ተጀመረ
ተጀመረ
➢ ገባ
➢ ገባ
➢ገባ
➢ገ ባ
➢ በሉ
➢ ገባ ገባ በሉ ጆይን በሉ ሸር አድርጉ ባረከላህ ፊኩም👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇https://t.me/eibrahimkeyeredin
https://t.me/eibrahimkeyeredin
الســـلام عــليكـم ورحـــمةالله وبــــركاته
በአሏህ ፍቃድ ዛሬ ኢሁድ ማለትም በቀን 27/03/2017 ላይ ታላቅ 15ታዊየዳዕዋ ፕሮግራም
ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።
የሲቶች ደዕዋ
⏰ ሰዓት: ከ500እስከ ዙህር
🕌 ቦታ:– ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ዘሞ ባቴ መንደር (ዳሩል ሒጅራ መስጅድ) ላይ ይሆናል።
ሼርርርርር
https://t.me/eibrahimkeyeredin
https://t.me/eibrahimkeyeredin
👉 የእቁብ ሰብሳቢዮች ግድፈቶች !
እቁብ ማለት በአንድ ወይም በተወሰኑ ሰዎች አማካይነት የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እየተሰሰበሰበ ለሰብሳቢው /ዎች የተወሰነና የእቁብ ከፋዮቹ የተስማሙበት የገንዘብ መጠን እንደ ደሞዝ እየተከፈ በአማና አስቀምጠው ሀላፊ ሆነው ሰብስበው በየተራ ለእቁብተኛው በእጣ ወይም ያለ እጣ እንዲሰጥ የሚደረግበት አሰራር ነው ። የዚህ አይነቱ አሰራር ከሸሪዓዊ ህግጋቶች በማይጋጭ መልኩ ከተሰራ በመልካም ከመተባበር ውስጥ ሊመደብ ይችላል ።
የዘመናችን የሸሪዓ እውቀት ባልተቤቶች የዚህ አይነቱን አሰራር በመልካም መተባበርና መልካም ብድር ውስጥ ይገባል ይላሉ ።
ይህ አሰራር ብዙዎችን የስራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያደርግ ሲሆን አብዛኞች በራሳቸው ለእቁብ በሚሰጡት ትኩረት ልክ አጠራቅመው መፈፀም የማይችሉዋቸውን ተግባራት በእቁብ አማካይነት ይፈፅማሉ ። ለምሳሌ የተለያዩ የስራ አይነቶችን መጀመር ፣ ትዳር መያዝ ፣ ቤት መግዛት ፣ መኪና መግዛትና የቤት ቁሳቁሶችን እንደሟሟላት የተወሰኑ ሰዎች በዚሁ መንገድ በማጠራቀም ሐጅና ዑምራ እንደማድረግ ያሉ ተግባራትን በእቁብ በመታገዝ ያከናውናሉ ።
ይሁን እንጂ ለእንደነዚህ አይነት መልካም ተግባራት አጋዥ የሆነው እቁብ ከ90% በላይ የሚሆነው በሰብሳቢዮቹ አማካይነት የሸሪዓ ጥሰት ያስተናግዳሉ ። የእቁብ ሰብሳቢዮችም ሆነ ከፋዮቹ አብዛኞቹ ከሸሪዓ እውቀት ጋር ግንኙነት የሌላቸው በመሆኑ ተግባሩን አሉታዊ ገፅታ ያላብሱታል ።
በሰብሳቢዮች ከሚሰሩ የሸሪዓ ጥሰቶች ውስጥ የተወሰኑትን እንይ : –
አንደኛ – ለአራትና ለአምስት ወር ያለ እጣ ዝም ብለው በመሰብሰብ አማና በተቀመጠባቸው የሰዎች ገንዘብ ያለ ፈቃዳቸው በመነገድ ከየትኛውም ነጋዴ በላይ ይበለፅጉበታል ። ወይም ለሌላ በትርፍ በማበደር ሐራም የሆነ ያልተገባ ጥቅም ያገኙበታል ። አደራ በተቀመጠ የሰዎች ገንዘብ ያለ ሰዎቹ ፈቃድ መነገድ ከባድ ሐራም የሆነ ተግባር ሲሆን ለሌሎች አበድሮ ትርፍ መቀበል ወለድ ነው ።
ሁለተኛ – ሰብሳቢዮቹ እቁብ ከፋዮችን በማሳመን አንድ እጣ ወጥቶ ለእቁብተኛ እንዲሰጥና አንድ ደግሞ ሽያጭ እንዲኖር በማድረግ የተቸገረ ሰው እቁቡን ያለ እጣ ወስዶ ለእቁብተኛው ከተወሰነው ክፍያ ውጪ በግዢ መልክ እንዲከፍል ያደርጋሉ ። ይህም የገዛው ሰው ከተወሰነው የእቁብ ክፍያ ውጪ ስለሚከፍል ወለድ ውስጥ ይገባል ።
ሶስተኛ – በቀኑ ያልከፈሉ ሰዎችን ቅጣት እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን ይህም ሪባ አንነሲኣ ( በጊዜ ምክንያት) የሚመጣ ወለድ ውስጥ ይገባል ።
እነዚህ ተግባራት ከሸሪዓ ያፈነገጡና የአብዛኛው እቁብ ሰብሳቢ አላማ ሰዎችን መጥቀም ሳይሆን ያለ አግባብ በሰዎች ለመጠቀም ያለመ መሆኑን ያሳያል ። ከዚህ በላይ እቁቡ ከወለድ ጋር የተነካካ በማድረግ ብዙዎች በማያውቁት መንገድ በገንዘባቸው ከአላህ ጋር ጦርነት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል ። በመሆኑም እቁብ ሰብሳቢዮች አላህን እንዲፈሩና የተሰጣቸውን ገንዘብ አማናውን ጠብቀው ለከፋዮቹ በስምምነታቸው መሰረት በእጣ ወይም በየተራ በማስረከብ በሚከፈላቸው ደሞች እንዲብቃቁ አደራ ለማለት እወዳለሁ ።
ማስታወሻ : –
ለሰብሳቢዮቹ የሚከፈለው እቁብተኞቹ የተስማሙበትና መጠኑን ያወቁት ገንዘብ በየተኛውም መመዘኛ ወለድ ውስጥ የማይገባ ሲሆን ትርፍ ከሚያስገኝ ብድርም ጋር ግንኙነት የለውም ።
http://t.me/bahruteka
