uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Відкрити в Telegram

This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.

Показати більше
4 437
Підписники
-324 години
-357 днів
-8630 днів
Архів дописів
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በኒቃብ ጉዳይ ጥቁር ታሪክ ያለው ግቢ ነበር ••• በ2016 ዓ.ል 60 ገደማ ተማሪዎች በኒቃብ ጉዳይ ከትምህርታቸው ተሰናክለዋል ••• ከዚያም ቡሃላ አልፎ አልፎ መሠል ትንኮሳዎች እየ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በኒቃብ ጉዳይ ጥቁር ታሪክ ያለው ግቢ ነበር ••• በ2016 ዓ.ል 60 ገደማ ተማሪዎች በኒቃብ ጉዳይ ከትምህርታቸው ተሰናክለዋል ••• ከዚያም ቡሃላ አልፎ አልፎ መሠል ትንኮሳዎች እየተፈፀሙ ተማሪዎችም ችለው እያለፉ 2017 ዓ.ል ደረሰ ••• በዚህም አመት ዩኒቨርሲቲው "ከኒቃባችሁ እና ከትምህርታችሁ ምረጡ!" - በሚል ያልሆነ ምርጫ ሊያስመርጣቸው ሞከረ:: ተማሪዎቹም "ኒቃቡም ትምህርቱም ምርጫዎቻችን ሳይሆኑ ግዴታዎቻችን ናቸው!" - ብለው ወደ ትግል ገቡ:: ስለ መብታቸው ሲሉ ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ አልፈው ዞን ክልል ፌደራል ማሰኑ:: እምቢኝ ተብለው ከግቢ ሲባረሩም እምቢኝ ብለው ለ10 ቀናት ከትምህርት ምግብ እና ዶርም ተከልክለው ከመስጂድ ተጠለሉ:: በስተመጨረሻም በአላህ ፈቃድ መብታቸውን አስጠብቀው ተባረውበት ወደነበረው ግቢ በክብር ገቡ:: ይህ በሙስሊም ተማሪዎች ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ሂደት ውስጥ በተምሳሌትነት ከሚጠቀሱት ነው:: ይህንንም እውቅና በመስጠት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ባካሄደው 4ኛ አመት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የምስክር ወረቀት ሰጥቷል::

አባጅፋር (ረህመቱላሂ ዐለይሂ) ጅማ በእርሳቸው እስክትታወቅ ድረስ የፍትሕ: የጀግንነት እና የጥበብ ተምሳሌት ነበሩ:: ከተማቸው ጅማም እንዲሁ በተመሳሳይ:: ሆኖም አባጅፋር ባፀኗት ከተማ የአባጅፋር
አባጅፋር (ረህመቱላሂ ዐለይሂ) ጅማ በእርሳቸው እስክትታወቅ ድረስ የፍትሕ: የጀግንነት እና የጥበብ ተምሳሌት ነበሩ:: ከተማቸው ጅማም እንዲሁ በተመሳሳይ:: ሆኖም አባጅፋር ባፀኗት ከተማ የአባጅፋር ልጅ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሠረታዊ ሐይማኖታዊ መብታቸው ተገፎ ለአመታት ዘልቀው ነበር:: ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሐይማኖት መገለጫቸው የሆነውን ኒቃብ ለብሰው መማር ተከልክለው ነበር:: ሙስሊም ወንድ ተማሪዎች ጀለብያ እና አማኢማ ለብሰው መማር ይከለከሉ ነበር:: ሆኖም የዚህ ትውልድ ልጆች ••• ሊበቃ ሊያበቃ ይገባል ብለው በ2017 ዓ.ል በወርሐ ረመዳን ስለ መብታቸው ጠይቀው ታገሉ ••• በስተመጨረሻም ለአመታት ሲፈፀም የነበረውን የመብት ጥሰት አስቁመው መብታቸውን አስከበሩ:: ይህንንም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት እውቅና በመስጠት ባካሄደው 4ተኛ አመት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል!

በደሌ ካምፓስ ላይ የነበረውን የሚረሳ ያለ አይመስለኝም ••• በ2017 ዓ.ል በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ከደረሰባቸው የመብት ጥሰቶች መካከል በመቱ ዩኒቨርሲቲ በደሌ ካምፓስ የሚገኙ
በደሌ ካምፓስ ላይ የነበረውን የሚረሳ ያለ አይመስለኝም ••• በ2017 ዓ.ል በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ከደረሰባቸው የመብት ጥሰቶች መካከል በመቱ ዩኒቨርሲቲ በደሌ ካምፓስ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ይጠቀሳሉ:: ዩኒቨርሲቲው "ወይ ኒቃባችሁን አውልቃችሁ ተማሩ --- ወይ ደግሞ እቃችሁን ሸክፋችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ!" የሚልን አማራጭ ለሙተነቂቦች ሲያቀርብ ••• ሁሉም ተማሪ ጁምዓ ቀን "እህቶቻችን ገብተው ካልተማሩ እኛም አንማርም!" በማለት ከበር ላይ ከጧት ጀምሮ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ ቆመው ከብዙ ንግግር ቡሃላ በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን አስከብረው ነበር:: ይህ በበደሌ የነበረው የተማሪዎች ጥያቄ ከዚያ ቡሃላ ለነበሩ የመብት ጥያቄዎች ፈርቀዳጅ ነበር ••• የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረትም ይህንን ተምሳሌታዊ ተግባር ባካሄደው 4ተኛ አመት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እውቅና ሰጥቷል:: መቱ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረትም ተማሪዎቹን በመወከል የእውቅና ምስክር ወረቀቱን ተቀብሏል!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ተወካዮች በኬንያ በተዘጋጀው የምስራቅ አፍሪካ ተማሪዎች ኮንፈረንስ ላይ ተሳተፉ! •••••••••••••••••••••••••••••••••••
+3
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ተወካዮች በኬንያ በተዘጋጀው የምስራቅ አፍሪካ ተማሪዎች ኮንፈረንስ ላይ ተሳተፉ! ••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ረቡዕ:- ነሐሴ 14/2017 ዓ.ል ••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ተወካዮች በኬንያዋ ናይሮቢ ለአምስት ቀናት በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ተማሪዎች ኮንፈረንስ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል:: በኮንፈረንሱ የኬንያ: ታንዛኒያ: ሩዋንዳ: ቡሩንዲ እና ኡጋንዳ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን በተማሪዎቹ መካከል የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ተካሂዷል:: የህብረቱ ተወካዮች ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች የተወከሉ ሲሆን ለጀመዓዎቻቸው የሚጠቅሙ ልምዶችን ከተለያዩ ሀገራት ጀመዓዎች እንዳገኙ ገልፀዋል::

ሐርቫርድ ዩኒቪርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች አዲስ የመስገጃ ሥፍራ አዘጋጀ ። በአሜሪካ ማሳቹሴትስ የሚገኘው ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ፤ ለሙስሊም ተማሪዎች አዲስ የመስገጃ ሥፍራ ማዘጋጀቱን አስታውቋል። የዩኒቨር
+1
ሐርቫርድ ዩኒቪርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች አዲስ የመስገጃ ሥፍራ አዘጋጀ ። በአሜሪካ ማሳቹሴትስ የሚገኘው ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ፤ ለሙስሊም ተማሪዎች አዲስ የመስገጃ ሥፍራ ማዘጋጀቱን አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ጋዜጣ ሐርቫርድ ክሪምሰን በድረ ገጽ ባሠራጨው መረጃ መሠረት፣ በማደሪያ ክፍሎችና በጊዜያዊ መስገጃነት በተዘጋጁ ሥፍራዎች ተወስነው የቆዩ ሙስሊም ተማሪዎች ከመስከረም ወር አንስቶ በተዘጋጀላቸው አዲስ መስገጃ ሥፍራ መስገድ ይችላሉ። ዩኒቨርሲቲው ያሳለፈው ውሳኔ በሙስሊም ተማሪዎች ማኅበራት አድናቆት ተችሮታል። የሐርቫርድ እስላማዊ ማኅበር የውስጥ ግንኙነት ተባባሪ ዳይሬክተር ሻኪራ ዓሊ፤ ዩኒቨርሲቲው ቋሚ የመስገጃ ሥፍራ ማዘጋጀቱ የኀላፊዎችን ቁርጠኝነት ያሳያል ብላለች። ሙስሊም ተማሪ እንደመሆኔ መጠን ያለ ሐሳብ  የመስገጃ ሥፍራ ማግኘቴ እፎይታ የሚሰጥ ስለሆነ እንደ ቀላል ነገር የምወስደው አይደለም ስትል አክላለች። በሐርቫርድ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች እ.አ.አ ከ1995 ጀምሮ የመስገጃ ሥፍራ ችግር እንዳለባቸው ሲገልጹ መቆየታቸው ተዘግቧል። የዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ኢማም ዓብዱልረሺድ ለተማሪዎች በላኩት ኢሜይል ለዓመታት ሲነሳ የነበረው ቅሬታ መፈታቱን ገልፀዋል። @MohammadamminKassaw

Gamtaan barattoota musliima dhaabbilee barnoota Olaanoo Ityophiyaa yaa'ii waliigala isaa taasiise! •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• Wiixata: Adoleessa 12/2017 A.L.I •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• Gamtaan barattoota musliima dhaabbilee barnoota Olaanoo Ityophiyaa Adoleessa 12/2017 irraa kaasee guyyoota walitti aanan shaniif  yaa'ii waliigala isaa finfinneetti  gaggeesseera. Walgahicharrattis Amiroota jama'aa yunivarsiiti 35 olii kan argaman yoo ta'u, Sarbiinsa mirga barattoota musliima yunivarsiiti irratti gahaa jiranii fi rakkowwan waloo kana fakkaatan irratti marii taasifameera. Jama'awwan bara 2017 A.L.I tti mirga isaani karaa nagaatin kabachisanif beekamti kan keennamee yoo ta'uu, Sochiwwan gara fulduraa ilaalchisees mariin taasifameera. Rabbii, Kun akka milkaa'u nu dandeessiisef galanni isaa haa gahuu. Qaamoonni Kun akka milkaa'u nu gargaaranis rabbin mindaa khayrii isaani haa keennu. Gamtaa barattoota musliima dhaabbilee barnoota Olaanoo Ityophiyaa!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ! ••••••••••••••••••••••••••••••••••• ሰኞ:- ነሐሴ 12/2017 ዓ.ል ••••••••••••
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ! ••••••••••••••••••••••••••••••••••• ሰኞ:- ነሐሴ 12/2017 ዓ.ል ••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከነሐሴ 05/2017 ዓ.ል እስከ ነሐሴ 10/2017 ዓ.ል ለተከታታይ አምስት ቀናት ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ አካሂዷል:: በጉባዔው ከ35 በላይ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች አሚሮች የተገኙ ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሱ ያሉ የመብት ጥሰቶች እና መሠል የጋራ ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል:: በ2017 ዓ.ል መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ላስከበሩ የዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች እውቅና የተሰጠም ሲሆን ለወደፊት በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች ዙሪያም ምክክር ተደርጓል::    ይህ እንዲሳካ ላስቻለው አላህ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን:: ይህ እንዲሳካ ላገዙን አካላትም አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይከፍልልን ዘንድ ዱዓችን ነው:: የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!

አማናችሁን አድርሰናል ••• ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ከእናንተ የተሰበሰበው 83,770 ብር በመጀመሪያ ዙር ገቢ ሆኗል! ባለፉት ጊዜያቶች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ማሞመዘምር ካምፓስ የሚ
+1
አማናችሁን አድርሰናል ••• ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ከእናንተ የተሰበሰበው 83,770 ብር በመጀመሪያ ዙር ገቢ ሆኗል!    ባለፉት ጊዜያቶች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ማሞመዘምር ካምፓስ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎችን መስጂድ ለመገንባት ጥሪ አስተላልፈንላችሁ በጥሪው መሠረት ርብርብ አድርጋችሁ ነበር:: በሁሉም አቅጣጫ የሚገኝ ሙስሊም ተማሪ ርብርብ አድርጎም በመጀመሪያ ዙር 83,770 ብር ተሰብስቦ ለወንድሞቻችን መስጂድ ገቢ ሆኗል::    በዚህ እንቅስቃሴ በአምቦ የሚገኙ ወንድሞቻችን የተደሰቱ እና ምስጋናቸውን የገለፁ ሲሆን እኛም ምስጋናችንን በአላህ ስም እየገለፅን መስጂዱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከጎናቸው እንደሆንን ለማሳወቅ እንወዳለን:: አላህ የሁላችንንም መልካም ስራ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይቀበል:: ጭማሬ:- ለወንድሞቻችን ገቢ የተደረገበት አካውንት የጀመዓቸው ፋይናንስ ዘርፍ ሀላፊ ሲሆን የሆነበትም ምክንያት በጣምራ የጀመዓውን አካውንት የከፈቱት ወንድሞች ለእረፍት ክ/ሀገር በመግባታቸውና አሁን ላይ የመስጂዱን ግንባታ እርሱ እየተከታተለ ስላለና ገንዘቡ ለአሁን ስራ ማስኬጂያ ስለተፈለገ ነው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!

የ12ኛ ክፍል የዘንድሮ ተፈታኞች በአንዳንድ ት/ቤት ኦረንቴሽን ሲሰጡ «ኒቃብ መልበስን እንዳታስቡት!» መባላቸውን እየተናገሩ ነው። መጅሊስና የመጅሊሱ የህግ ክፍል ቀኑ ደርሶ እህቶች ከመንገላታታቸው በፊት ከወዲሁ ከሚመለከተው አካል ጋር መነጋገር ቢችሉ መልካም ነው። https://t.me/EHEMSU

" እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።" 2ቆሮ 5፡20
✨✨✨Summer Mission Report✨✨✨ ሰላም የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች😊😊😊 እንደሚታወቀው ከባለፈው ሃሙስ ሰኔ 5 ጀምሮ በደብረብርሃን ከተማ ለ አንድ ሳምንት የቆየ የወንጌል ስርጭት ጊዜ ነበረን። በነዚህ ጊዜያትም እጅግ ታላቅ የሆነ የጌታን ማዳን ያየንበት እግዚአብሄር አደራን ሰጥተነው ሳያሳፍረን በታላቅ ክንዱ ከኛ ጋር ሆኖ አጅግ ድንቅ ጊዜን አሳልፈናል። በዛ በነበረን ቆይታም ፡- ▶️ 444 ሰዎች ይህንን የምስራች ወንጌል ሰምተዋል ▶️ 77 ሰዎች ተስፋን ሰጥተዋል ▶️ 32 ሰዎች ደግሞ ንስሃ በመግባት ክርስቶስን የህይወታቸው ጌታ እና አዳኝ አርገው ተቀብለዋል። ይህንን ያደረገው እግዚአብሄር ክብሩን ሁሉ ይውሰድ😊😊 ለዚህ የወንጌል ቃል ምስክሮች ለመሆን በቦታው የተገኛችሁ (Dosayis Family😁)፤ በጸሎት ከኛ ጋር ስትተጉ የነበራችሁ prayer warriors🔥 እንዲሁም በጣም ስትረዱን ለነበራችሁ ተማሪዎች እና graduates እግዚአብሄ ዘመናችሁን ይባርክ☺️☺️ በመጨረሻም ለደብረ ብርሃን ከተማ እና ህዝቦችዋ እለት እለት በጌታ ፊት እንድትማልዱ አደራ ለማለት እንወዳለን። #5KECSF #Summer_Mission

Congratulations 🎉🎉🎉 አልፍ መብሩክ! ለዛሬው ቀን ያበቃችሁ ያደረሰን አምላክ አላህ ምስጋና ይድረሰው:: በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ከብዙ ልፋት እና ድካም ቡሃላ ከስኬት ደጅ ደርሳችሁ የስኬታችሁን ፍሬ በማክበር ላይ ያላችሁ ሙስሊም ተመራቂ ወንድም እህቶቻችን ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ:: ይህ የምርቃት ቀን የትግላችሁ የጥረታችሁ የልፋታችሁ ውጤት ነውና እንኳን አደረሳችሁ:: በመቀጠል እያንዳንዱ የስኬት መዝጊያ ለቀጣይ ፈተና መክፈቻ ነውና በቀጣይ የሕይዎት ፈተናችሁ ውስጥ ያለፉትን ስህተቶች ባለመድገም ጥንካሬያችሁን አጉልታችሁ ለራሳችሁ ለቤተሰብ እና ለሙስሊም ማህበረሰብ ብሎም ለሀገር መልካምን ነገር ሰርታችሁ ታሳልፉ ዘንድ አደራችን ነው:: አላህ በሄዳችሁበት ሁሉ ስኬትን እና ከፍታን ይወፍቃችሁ ••• Congratulations 🎉🎉 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት! https://t.me/EHEMSU

Obboleessii keenya wallagaa irrraa ijaarsa masjiida barattoota yunivarsiiti amboof birri 200 galii godheera. Rabbi dunyaa fi akhiraa isaa haa milkeessu! Ammas hanga dandeetti keenya tumsa haa goonu! Akkaawunti: 1000699582976 (Bilal Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students Union). screenshot @Abduw99 irratti nuf eergaa.:: https://t.me/EHEMSU

"Exitን ካለፍኩ ለአምቦ መስጂድ 100 ብር አስገባለሁ!" ብሎ የተሳለ ወንድማችን በጥሩ ውጤት አልፎ ስለቱንም ሞልቷል:: ፈተናውን ያለፋችሁ ወንድም እህቶቻችን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ: እንኳንም
+1
"Exitን ካለፍኩ ለአምቦ መስጂድ 100 ብር አስገባለሁ!" ብሎ የተሳለ ወንድማችን በጥሩ ውጤት አልፎ ስለቱንም ሞልቷል:: ፈተናውን ያለፋችሁ ወንድም እህቶቻችን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ: እንኳንም ለዚህ ቀን በቃችሁ:: Congratulations 🎉🎉🎉 up on your achievement! አላህ መልካም ስራንና ሕይዎትን ይገጥማችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው:: ያላለፋችሁ ደግሞ ይህ የአላህ ውሳኔ እና ፍላጎት ነውና ተቀበሉት! ኸይሩንም ተመልከቱ! ለተሻለ ውጤት እና ሕይዎት የሚያበቃችሁን መንገድ ዳግም ተመልከቱ! በድጋሜ Congratulations 🎉🎉🎉 https://t.me/EHEMSU

Jama'aa barattoota yunivarsiiti waraabee masjida barattoota yunivarsiiti ambof birri 6,000.00 galii godhan! Allaahu Akbar. Obbolawwan keessan akka gammachiistan, rabbi dun-yaa fi akhiraatti isin haa gammachiisu. Ammas hanga dandeetti keenya tumsa haa goonu! Akkaawunti: 1000699582976 (Bilal Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students Union). screenshot @Abduw99 irratti nuf eergaa.:: https://t.me/EHEMSU

ማንኛውም ስራ ሰንሰለቱ ሳይበጠስ ለነገ ትውልድ ሊሻገር የሚችለው በተቋማት በኩል ነው:: እንደ ሙስሊም የእስልምና አስተምህሮዎቻችንን እና ኢስላማዊ እሴቶቻችንንም ከትላንቱ የተረከብነው በየሰፈራችን በ
+2
ማንኛውም ስራ ሰንሰለቱ ሳይበጠስ ለነገ ትውልድ ሊሻገር የሚችለው በተቋማት በኩል ነው:: እንደ ሙስሊም የእስልምና አስተምህሮዎቻችንን እና ኢስላማዊ እሴቶቻችንንም ከትላንቱ የተረከብነው በየሰፈራችን በታነፁት መስጂዶች በኩል ነው:: ለነገው ትውልድም የዛሬውን አስተካክለንና ሰርተን ልናስረክብ የምንችለው በነዚሁ ተቋማት በኩል ነው:: እንደ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ደግሞ በካምፓስ ዙሪያ የሚኖሩ መስጂዶች ፋይዳ ከነዚህም በላይ ነው:: ለዚህም ሲባል ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ መረባረብ ከጀመርን ሰነባብተናል:: ሁሉም ከየአቅጣጫው ተረባርቦ እስካሁን 82500 ብር ደርሰናል:: ጀመዓዎቹም ወጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ:: አሁን ላይ ጭቃ አብኩተው ለመምረግ በመሰናዳት ላይ ናቸው:: ከምርጊት ባሻገርም ብዙ ወጪ አለባቸውና በህብረት በአንድነት ለአላህ ቤት እንረባረብ:: የማስገቢያ አካውንት:- 1000699582976 (Bilal Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students Union) --- ያስገባችሁበትን screenshot @MOHAMMADAMMINM ላኩልን:: https://t.me/EHEMSU

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ 6000 ብር አስገብተዋል ••• አላሁ አክበር! አላህ በዱንያም በአኼራ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈል:: ማህበረሰባቸው
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ 6000 ብር አስገብተዋል ••• አላሁ አክበር! አላህ በዱንያም በአኼራ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈል:: ማህበረሰባቸውን በኸይር ነገር ደጋግመው የሚነስሩበትን የሚያስደስቱበትን ቁዋ ይስጣቸው:: ወራቤዎች ይለያሉ 😍 82280 ብር ላይ ደርሰናል ••• 100K ልንሞላ 18K ብቻ ማለት ነው! ተረባርበን አምቦ ላይ ታሪክ እንስራ ••• ይህ ደግሞ የመጀመሪያችን እንጂ የመጨረሻው አይደለም ••• የዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን አጠናክሮ የተሻለ ነገን የመገንባት ሀላፊነት የዛሬው ትውልድ ነው:: የማስገቢያ አካውንት:- 1000699582976 (Bilal Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students Union) --- ያስገባችሁበትን screenshot @MOHAMMADAMMINM ላኩልን:: https://t.me/EHEMSU

የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ 3000 ብር አስገብተዋል! "ሙስሊም የሙስሊም ወንድሙ ነው:: እስከመጨረሻው ድረስ ከጎናቸው ነን:: ይህ የመጀመ
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ 3000 ብር አስገብተዋል! "ሙስሊም የሙስሊም ወንድሙ ነው:: እስከመጨረሻው ድረስ ከጎናቸው ነን:: ይህ የመጀመሪያችን ነው:: በዱዓም ከጎናችሁ ነን::" የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል:: አላህ በዱንያም በአኼራም መልካም ነገሮችን ይስጣቸው:: የአኼራ ቤታቸውን አሳምሮ ይገንባ:: እስካሁን 76K ብር ደርሰናል ••• የሰጡትን ሁሉ አላህ ይስጥልን ••• ሆኖም ግን ገና ነንና እንረባረብ! የማስገቢያ አካውንት:- 1000699582976 (Bilal Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students Union) --- ያስገባችሁበትን screenshot @MOHAMMADAMMINM ላኩልን:: https://t.me/EHEMSU

ከአመት በፊት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ይህንን ይመስል ነበር ••• አሁን ከላይ በምታዩት መልኩ ሰፍቶ እና አምሮበት ሊጠናቀቅ ነው:: በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!
+2
ከአመት በፊት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ይህንን ይመስል ነበር ••• አሁን ከላይ በምታዩት መልኩ ሰፍቶ እና አምሮበት ሊጠናቀቅ ነው:: በድጋሜ እንኳን ደስ አለን! https://t.me/EHEMSU

+1
እንኳን ደስ አለን ••• የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ!   ከአመት በፊት ይሰግዱበት ይማሩበት የነበረው መስጂድ ከአግልግሎት ውጪ በመሆኑ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኝ ሙስሊም ተማሪ ያግዛቸው ዘንድ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ጥሪ አቅርበው ነበር:: የዚያኔም በሁሉም አቅጣጫ የሚገኝ ሙስሊም ተማሪ ተረባርቦ የአቅሙን አበርክቶ ነበር:: ከዚያም ቡሓላ የተማሪዎችን ጥሪ የሰሙ አህለል ኸይሮች ከሐዋሳ ሪፈራል ካምፓስ ጀመዓዎችን ጥሪ ሰምተው ግንባታው እንደምታዩት ሆኗል:: እንኳን ደስ አለን ••• ማሻ አላህ:: በቅርቡ ተጠናቆ በጀመዓ የምንሰግድበት ያድርገን::    ጀመዓዎቹ ደስታችንን ተጋሩ ብለዋልን ••• በጀመዓ እንደሰት! እኛም እንደ ህብረት የዚያኔ ጥሪያችንን የተቀበላችሁን ተማሪዎች ••• ከዚያም ቡሓላ የዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን ለማጠናከር በምናደርጋቸው ንቅናቄዎች ውስጥ የምትሳተፉትን ሁሉ በአላህ ስም እናመሰግናለን:: ከአላህም ጋር ብዙ ደማቅ ታሪኮችን አብረን የምንፅፍ ይሆናል ••• ኢንሻ አላህ!