Ethiopian Educational Channel
Відкрити в Telegram
እንኳን ደና መጣችሁ በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኙት 1. ትምህርታዊ መረጃ መስጠት 2.የሳይኮሎጂ አስተማሪ ምክሮችንና አነቃቂ ንግግሮች 3.መፃህፍቶች በpdf እና የእንግሊዝኛ ትምህርት ይለቀቃሉ! በዚህ ቻናል ሀይማኖታዊ እና ፓለቲካ ነክ አይለቀቅበትም ! የቴሌግራሙ ቻናል ሊንክ:👉https://t.me/EEC1227 Channel created by @BA1227
Показати більше6 814
Підписники
-424 години
-157 днів
-3930 день
Триває завантаження даних...
Схожі канали
Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
червень '26
червень '26
+64
в 0 каналах
травень '26
+75
в 3 каналах
Get PRO
квітень '26
+27
в 0 каналах
Get PRO
березень '26
+37
в 0 каналах
Get PRO
лютий '26
+38
в 0 каналах
Get PRO
січень '26
+45
в 0 каналах
Get PRO
грудень '25
+38
в 1 каналах
Get PRO
листопад '25
+51
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '25
+39
в 2 каналах
Get PRO
вересень '25
+167
в 2 каналах
Get PRO
серпень '25
+294
в 1 каналах
Get PRO
липень '25
+397
в 3 каналах
Get PRO
червень '25
+800
в 3 каналах
Get PRO
травень '25
+1 206
в 2 каналах
Get PRO
квітень '25
+851
в 2 каналах
Get PRO
березень '25
+1 151
в 23 каналах
Get PRO
лютий '25
+1 289
в 0 каналах
Get PRO
січень '25
+2 145
в 3 каналах
Get PRO
грудень '24
+582
в 2 каналах
Get PRO
листопад '24
+154
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '24
+188
в 2 каналах
Get PRO
вересень '24
+100
в 3 каналах
Get PRO
серпень '24
+739
в 0 каналах
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 27 червня | +1 | |||
| 26 червня | +2 | |||
| 25 червня | +3 | |||
| 24 червня | 0 | |||
| 23 червня | +3 | |||
| 22 червня | +2 | |||
| 21 червня | +1 | |||
| 20 червня | +2 | |||
| 19 червня | 0 | |||
| 18 червня | +2 | |||
| 17 червня | 0 | |||
| 16 червня | +4 | |||
| 15 червня | +2 | |||
| 14 червня | +2 | |||
| 13 червня | +4 | |||
| 12 червня | +5 | |||
| 11 червня | +2 | |||
| 10 червня | +1 | |||
| 09 червня | +5 | |||
| 08 червня | +2 | |||
| 07 червня | +6 | |||
| 06 червня | +3 | |||
| 05 червня | +3 | |||
| 04 червня | +3 | |||
| 03 червня | +1 | |||
| 02 червня | +4 | |||
| 01 червня | +1 |
Дописи каналу
ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ በአግባቡ ሊተገብሯቸው የሚገቡ
የጥንቃቄ እርምጃዎች፡፡
=========
ደንበኞች እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ኤቲኤም፣ ፖስ፣ ሲቢኢ ብር የመሳሰሉ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከተሉትን የደህንንት መጠበቂያ ተግባራት ሊተገብሩ ይገባል፡
• የሚስጢር ቁጥርዎን በስልክዎ ውስጥ አለማስቀመጥ፣ በወረቀት ወይም በማስታወሻ ደብተር ላይ አለመፃፍ እና በአጠቃላይ ለሌላ ሰው አለማሳየት ወይም በቀላሉ በሚታይበት ቦታ ላይ አያስቀምጡ፤
• የተንቀሳቃሽ ስልክዎን በተቻለ መጠን ለሌላ ሰው አይስጡ (አያውሱ)፡፡ ነገር ግን ለሌላ ሰው የሚሰጡ ወይም የሚቀይሩ ከሆነ ግን ስልኩ ላይ ያለውን የየዲጂታል ባንክ አገልግሎት መጠቀሚያ መተግበሪያ እና ሌሎች የግል መረጃዎን የያዙ ጽሑፎችንና ኢሜሎችን ያጥፉ፤
• የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ በሚያደርጉት ነገር ላይ ብቻ ያተኩሩ፤ ትኩረትዎን የሚያስተጓጉሉ እንደ ሞባይል ስልክ እና መሰል ነገሮቸን አይጠቀሙ፤
• የኤቲኤም ማሽን ላይ ሲጠቀሙ የሚስጢር ቁጥርዎ እንዳይታይ፤ የኤቲኤም ቁልፍ ሰሌዳውን ሰውነትዎን ተጠቅመው በመሸፈን በቅርብ የቆሙ ሰዎች እንይመለከቱ ይከላከሉ፣ ከግብይት በኋላ ካርዱን መቀበሎን ያረጋግጡ፤
• የተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ የሚጭኗቸውን መተግበሪያዎች ሲያወርዱ አፕስቶር እና ፕሌይስቶርን ብቻ ይጠቀሙ፤
• ደኅንነቱ ያልተረጋገጠ ድረ-ገጽ እና የማኅበራ ሚዲያ ገፆችን አይጠቀሙ፣ አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን (links) አይክፈቱ፤
• ግብይትዎን በሚያካሂዱበት ጊዜ ችግር ቢያጋጥምዎ ከሚመለከታችው የባንኩ ሠራተኞች ውጪ የማንንም እገዛ አይጠይቁ፤
• የሚስጢር ቁጥርዎን በየጊዜው ይቀያይሩ፤
• ተከታታይ የሆኑ ወይም የስልክ ቁጥርዎን የመጨረሻ ዲጂቶች፣ ማንኛውም የግል መረጃ ለምሳሌ የልደት ቀን የሚስጥር ቁጥር አድርገው አይጠቀሙ፤
• በስልክ ምንም አይነት የባንክ መረጃዎን አይስጡ፣
• ሞባይል ሲጠፋብዎ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲቋረጥ ያስደርጉ፤
• የሚጠቀሙበት ኮምፒዩተር ሁሌም የቫይረስ መከላከያ እንዳለው ያረጋግጡ፤
• ሂሳብዎ ላይ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲኖር ለባንኩ ወዲያውኑ ያሳውቁ፤
• የባንክ አገልግሎት በሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች እና ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የማይታወቁ መተግበሪያዎችን አይጫኑ፤
• አገልግሎት ካገኙ በኋላ አስፈላጊውን ቅደም ተከተል በመከተል ዘግተው ይውጡ፡፡
| 2 | Немає тексту... | 90 |
| 3 | ክፍል ሁለት
መብረቅ ለመታው ሰው ስለሚደረጉ እና ስለማይደረጉ ነገሮች :-
አይበለው እና ከእኛ ጋር ያለ ሰው የመብረቅ አደጋ ቢደርስበት ከአፈር ለመቅበር ወደ ጉድጓድ ቁፈራ ነው የምንሄደው ወይስ ምን እናድርግ፤ ብንነካው ቻርጁ ወደ እኛ ይተላለፋል ወይስ አይተላለፍም? የሚሉትና እና ሌሎች ጠቃሚ ሳይንሳዊ ምክሮችን እነኆ ።
፩. የባህላዊ ልማዶች ፍተሻ፦ የታሰበው እና ሳይንሳዊ እውነታው
ማንኛውም ሰው መጀመሪያ እርዳታ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን ጎጂ ልማዶች ማወቅ እና ማስወገድ አለበት፦
ሀ. መሬት ውስጥ መቅበር (እስከ አንገት/እስከ ደረት)
የሚታሰበው ፦ አፈሩ በሰውነት ውስጥ የተከማቸውን ኤሌክትሪክ ወደ መሬት ይስበዋል ተብሎ ይታመናል።
ሳይንሳዊ እውነታው፦ መብረቅ ሰውን መትቶ የሚያልፈው በሚሊሰከንዶች ውስጥ ስለሆነ ሰውነት ውስጥ የሚቀር የኤሌክትሪክ ክምችት የለም። አፈር መቆፈር እና ሰውን መቅበር ሌሎች ሕይወት አድን የሆኑ ስራወችን ለመሥራት የምንጠቀምበትን ወሳኝ የሆነውን ሰዓት (ወርቃማ ጊዜ) ያባክናል። በተጨማሪም አፈሩ ደረት ላይ የሚፈጥረው ጫና መተንፈስ ይከለክላል ፤ የሰውነት ሙቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ፤እንዲሁም በአደጋው ጊዜ በቃጠሎ ምክንያት የተፈጠሩ ቁስሎችን ለከፋ ኢንፌክሽን ያጋልጣል።
ሲጠቃለል መቅረቅ የመታውን ሰው ከአፈር መቅበር ምንም ዓይነት ጥቅም የለውም ።
ለ. ሌሎች የማይጠቅሙ እና ጎጂ ልማዶች :-
🎆ውሃ፣ ወተት ወይም ባህላዊ መድኃኒት በአፍ ማጠጣት፦ ራሱን የሳተ ሰው የመዋጥ አቅም ስለሌለው ፈሳሹ በቀጥታ ወደ ሳንባ በመሄድ ወዲያውኑ ሊያንቀው ወይም ሊገድለው ይችላል። ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ ንቁ ያልሆነ ሰው (ራሱን የሳተ) ምንም አይነት ፈሳሽ ለማጠጣት መሞከር አይመከርም።
🎆በቃጠሎ የተፈጠ ቁስል ላይ ቅቤ፣ ዘይት ወይም ሌላ ነገር መቀባት፦ የመብረቅ ቃጠሎ ከፍተኛ ውስጣዊ ሙቀት አለው። ቅቤ ወይም ዘይት መቀባት ሙቀቱ ወደ ውጭ እንዳይወጣ አፍኖ በመያዝ ቃጠሎውን ያባብሰዋል፤ ከባድ ባክቴሪያም ወደ ውስጥ ያስገባል።
🎆 አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ መቆየት፦ መብረቅ በአንድ በዝናብ ማዕበል ወቅት በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ የመምታት ዕድሉ ከፍተኛ በመሆኑ፣ እዚያው ቦታ ላይ እርዳታ ለመስጠት መሞከር ረዳቱንም ጭምር ለአደጋ ያጋልጣል።
፪. መደረግ ያለባቸው የመጀመሪያ እርዳታዎች :-
የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪው ሕክምና ባለሙያ ባይሆንም የሚከተሉትን እርምጃዎች ደረጃ በደረጃ መተግበር አለበት፦
ደረጃ 1 ፦ የቦታውን ደህንነት ማረጋገጥ
መብረቅ የደረሰበትን ሰው ወዲያውኑ በእጅ መንካት ምንም አይነት ችግር አያመጣም።
ነገር ግን ከላይ እንደጠቀስነው መብረቅ በአንድ በዝናብ ማዕበል ወቅት በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ የመምታት ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም ተጎጂውን በአስቸኳይ ይዞ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ለምሳሌ ቤት ውስጥ ካልተቻለም በአካባቢው ካለው አንጻራዊ ዝቅተኛ ቦታ ላይ መውሰድ ያስፈልጋል።
ደረጃ 2፦ ተጎጂውን ሁኔታ መገምገም እና እንደ ሁኔታው እርዳታ መስጠት
እዚህ ጋር ተጎጂው ያለበትን ሁኔታ አይቶ እርዳታውን እንደሚከተለው ማድረግ ተገቢ ነው ።
ሁኔታ ሀ፦ ራሱን ለሳተ እና መተንፈስ ለማይችል ሰው
ይህ ሁኔታ ተጎጂው የልብ ምት መቆም አጋጥሞታል ማለት ስለሆነ እጅግ አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋል።
ለእርዳታ ሌላ ሰው መጥራት ከተቻለ አምቡላስ መጥራት ጎን ለጎን የሚሰሩ ሆነው አብሮ ያለ ሰው ወዲያውኑ ተጎጅውን በጀርባው በማስተኛት በሁለቱ ጡቶች መካከል ላይ የእጅዎን መዳፍ በማድረግ፤ ሁለተኛውን እጅ በላዩ ላይ በማጣመር ክንድዎን ሳያጥፉ፣ የሰውነትዎን ክብደት በመጠቀም ደረቱን ወደ ታች ከ5-6 ሳንቲም ሜትር ጥልቀት በፍጥነት እና በኃይል መጫን ነው ።
ፍጥነት፦ በደቂቃ ከ100 እስከ 120 ጊዜ መጫን ። ይኼንንም እየተጋገዙ የሰውየው መተንፈስ እስኪመለስ ድረስ ወይም እስከ 30 ደቂቃ ድረስ መደጋገም ያስፈልጋል።
ይህን በትክክል ካደረግን ከ100 ሃያ ሰዎችን ወይም ከዚያ በላይ ማትረፍ ይቻላል።
እንደ አጋጣሚ ከመካከል ስልጠና የወሰደ ካለ ግን ደረትን ከመጫን በተጨማሪ ትንፋሽም መስጠት ያስፈልጋል (ለሰለጠኑ) ።
ሁኔታ ለ፦ ራሱን ለሳተ ነገር ግን በትክክል ለሚተነፍስ ሰው
ሰውየው ልቡ እየመታ እና እየተነፈሰ ከሆነ ነገር ግን ካልነቃ የሚከተሉትን ያድርጉ፦
A. ተጎጂውን በግራ ጎኑ ማስተኛት፣ የላይኛውን እግሩን አጥፎ ወደ ፊት ማድረግ እና እጁን ከጉንጩ ስር ማስደገፍ። ይህ አቀማመጥ ምላሱ ጉሮሮውን እንዳይዘጋው እና ቢተፋ እንኳ ትውከቱ ወደ ሳንባው ሳይሄድ ወደ ውጭ እንዲፈስ ያደርጋል።
B. የአየር መተላለፊያውን መከታተል፦ አፉ ውስጥ አፈር፣ ሳር ወይም ትውከት ካለ በንጹህ ጨርቅ በጥንቃቄ ማጽዳት::
C. ትንፋሹን መቆጣጠር፦ በየደቂቃው ደረቱ መነሳቱንና መውረዱን ማየት። ትንፋሹ ከቆመ ወዲያውኑ ከላይ ያየነውን ሁኔታ 'ሀ' ማድረግ ።
ሁኔታ ሐ :- የቃጠሎ ቁስሎችን በአደጋው የተፈጠረ የአጥንት ስብራት ካለ የሚደረጉ እርዳታወችን የሚተነትን ነው ይታወቃሉ።
የመጨረሻ ማሳሰቢያው መብረቅ የደረሰበት ሰው ምንም ጉዳት የሌለበት ቢመስልም፣ አልፎ ተርፎም ተነጋግሮ በገዛ እግሩ ቢሄድም እንኳ፣ በግዴታ ወደ ሆስፒታል መወሰድ አለበት።
ምንጪ: -
የአሜሪካ ቀይ መስቀል (American Red Cross) ፣
የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (CDC) እና
የአሜሪካ የልብ ማኅበር (AHA - American Heart Association) ንን
ተጠቅመናል።
ሰዎች በአፈር ሲቀበሩ የሚያሳየው ፎቶ iloveafrica.com በሰራው ጥናታው ጽሑፍ ላይ የተገኘ ነው። | 88 |
| 4 | ክፍል አንድ
ስለመብረቅ እና ነጎድጓድ ልንወስዳቸው የሚገቡ እውነተኛ ጥንቃቄዎች! ⛈️
''በር ላይ አትቁም ወደ ውስጥ ግባ !'' ትለኝ ነበር እናቴ
እንደዛሬው ሳይንስ ገና ሳይራቀቅ እናቶቻችን ያውቁት የነበረውን እውነት ሳይንስ አስፍቶ እና አብራርቶ እንዲህ ይተነትነዋል ።
የአሁኑ ወቅት የክረምት ወቅት በመሆኑ የነጎድጓድና የመብረቅ አደጋዎች በብዛት የሚሰሙበት ጊዜ ነው። በተለይ የክረምት መግቢያ እና መውጫ በሆኑት ሰኔ እና መስከረም ላይ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከሌሎች በተለየ ያዘዎትራል።
መብረቅ ተፈጥሯዊና በጣም ከፍተኛ ኃይል ያለው የኤሌክትሪክ ፍሳሽ በመሆኑ ራሳችንንና ቤተሰባችንን ለመጠበቅ ትክክለኛውን መረጃ ማወቅ ወሳኝ ነው።
በተለይ በገጠር አካባቢ የምንኖር ሰፊ ሜዳ ላይና ለእርሻ ሥራ ስለምንወጣ ለአደጋው የመጋለጥ ዕድላችን ከፍተኛ ነው።
በዚህም ምክንያት ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ጥበቃ የሌለበት በጥበባችን እና በብስለት ብቻ የምናመልጠው ነገር ባይኖርም በእኛ በኩል መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ማዎቃችን ግን በጣም አስፈላጊ ነው ።
፩. መደረግ ያለባቸው እውነተኛ ጥንቃቄዎች:-
ሀ. ወዲያውኑ ወደ መጠለያ መግባት : ነጎድጓድ ሲሰሙ "ገና መብረቁ አልመጣም" ብለው ከቤት ውጭ አይቆዩ። በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ ቤት ወዲያውኑ መግባት ያስፈልጋል ። የቤቱ ክዳን የቆርቆሮ ካልሆነ መብረቅን ተከላክሎ ቻርጁን ወደ መሬት የመስደድ አቅም ስለሌለው ከተቻለ የጣራው ክዳን ቆርቆሮ ሆኖ ግድግዳዎቹም በቡሉኬት የተሰራ ቢሆን ይመረጣል ። ግድግዳው የእንጨት እና የጭቃ ከሆነም ጣራው በመብረቅ ሲመታ ቆርቆሮው ላይ ያረፈው ቻርጅ በግድግዳው በኩል አድርጎ ወደ መሬት ይገባል። አንዳንድ ጊዜ ግድግዳው እርጥበት ሲይዝ ሾልኮ የመግባት እና ተጠግተው በቆሙ ሰዎች ላይ ጉዳት የማድረስ እድል ይኖረዋል ፤ እንዲሁም የግድግዳው እንጨት በጣም የሰባ ከሆነ የመቀጣጠል እድል ሊኖረው ይችላል። እንደ አጠቃላይ ግን ጣራቸው ቆርቆሮ የለበሱ ቤቶች ውስጥ ወደ ግድግዳም ወደ በርም ሳይጠጉ መሃል መቀመጥ ይመከራል ።
ለ. ከረጅም ዛፎች ስር ፈጽሞ አይጠለሉ: መብረቅ ሁልጊዜም በአቅራቢያው ያለውን ረጅሙን ነገር ቀድሞ የመምታት ባህሪ አለው። በገጠርም ሆነ በከተማ ነጎድጓድ ሲኖር ረጅም ዛፍ ስር መቆም ለአደጋው በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣል። ዛፍ ስር መጠለል የግድ ሆኖ ከተገኘም ብቻውን ከቆመ ዛፍ አለመጠለል ከብዙ ዛፎች መካከል ከአጭሩ ስር መሆን ይመከራል ።
ሐ. ከሜዳማ ቦታዎች መራቅ: ሰፊ የእርሻ ሜዳ ወይም ባዶ ቦታ ላይ ከሆኑ እርስዎ በአካባቢው ላይ ረጅሙ ነጥብ ስለሚሆኑ መብረቅ ሊስቡ ይችላሉ። ወዲያውኑ ወደ ዝቅተኛ ቦታ ይሂዱ ወይም ወደ መጠለያ ይሻገሩ።
መ. የውሃ አካላትን እና የብረት አጥሮችን ይራቁ:
በወንዝ፣ በኩሬ ወይም የዝናብ ውሃ በፈጠረው ጎርፍ ውስጥ ከሆኑ ወዲያውኑ ይውጡ። ውሃና ረጅም የብረት አጥሮች ኤሌክትሪክን በጣም በፍጥነት ይስባሉ።
ሠ. በቤት ውስጥ ሲሆኑ: በምግብ ማብሰያ (የኤሌክትሪክ ለምትጠቀሙ) ፣ በገላ መታጠቢያ ወይም በቧንቧ ውሃ አይጠቀሙ (መብረቅ የብረት ቧንቧዎችን ተከትሎ ሊገባ ይችላል)።
ረ. በኬብል (ገመድ) የተገናኙ ስልኮችን (የቤት ስልክ ወይም ለቻርች የተሰካ ተንቀሳቃሽ ስልክ) እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን አይንኩ። ከቻሉ ከኤሌክትሪክ ጋር የተሰኩ እቃዎችን ይንቀሉ (እቃው ላይ ጉዳት እንዳይደርስ)
፪. ባያደርጓቸውም ምንም ችግር የሌላቸው ጉዳዮች
ማኅበረሰባችን ውስጥ መብረቅን ለመከላከል ተብለው የሚደረጉ ነገር ግን በሳይንሳዊ መንገድ ምንም ፋይዳ የሌላቸው፣ ባናደርጋቸውም ምንም ችግር የሌለባቸው በርካታ ልማዶች አሉ። እነሱንም ማወቅ አላስፈላጊ ጭንቀትን ይቀንሳል፡-
ሀ. መስተዋትን መሸፈን ወይም መድፋት: መስተዋት መብረቅን የመሳብ ኃይል የለውም። መስተዋት ስለተከፈተ መብረቅ አይመጣም፤ ስለተሸፈነም መብረቅ አይከላከልም። ስለዚህ መስተዋት ባይሸፍኑ ምንም ችግር የለውም።
ለ. በሞባይል ስልክ ማውራት (ገመድ አልባ): ሞባይል ስልክ ከግድግዳው ሶኬት ጋር በቻርጀር ካልተገናኘ በስተቀር፣ ዝም ብሎ በስልክ ማውራት መብረቅን አይስብም። መብረቅ የሚስበው የብረት ማማዎችን (ታወሮችን) እንጂ በእጅዎ የያዙትን ትንሽ ስልክ አይደለም።
ሐ. የሞባይ ዳታ ወይንም Wifi መጠቀም : ይኼም ምንም ችግር የለውም
በቀጣይ የመብረቅ አደጋ የደረሰበት ሰው የመጀመሪያ እርዳታ እንዴት እንሰጣለን በሚለው ዙሪያ እንወያያለን ።
በዚህ ዙሪያ ያጋጠመዎ ልምድ ካለ ወይንም ጥያቄ ካለዎ እንወያይበታለን ።
ከድንገተኛ ሞት ልዑል እግዚአብሔር ይጠብቀን። | 87 |
| 5 | Немає тексту... | 11 |
| 6 | ክፍል ሁለት
መብረቅ ለመታው ሰው ስለሚደረጉ እና ስለማይደረጉ ነገሮች :-
አይበለው እና ከእኛ ጋር ያለ ሰው የመብረቅ አደጋ ቢደርስበት ከአፈር ለመቅበር ወደ ጉድጓድ ቁፈራ ነው የምንሄደው ወይስ ምን እናድርግ፤ ብንነካው ቻርጁ ወደ እኛ ይተላለፋል ወይስ አይተላለፍም? የሚሉትና እና ሌሎች ጠቃሚ ሳይንሳዊ ምክሮችን እነኆ ።
፩. የባህላዊ ልማዶች ፍተሻ፦ የታሰበው እና ሳይንሳዊ እውነታው
ማንኛውም ሰው መጀመሪያ እርዳታ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን ጎጂ ልማዶች ማወቅ እና ማስወገድ አለበት፦
ሀ. መሬት ውስጥ መቅበር (እስከ አንገት/እስከ ደረት)
የሚታሰበው ፦ አፈሩ በሰውነት ውስጥ የተከማቸውን ኤሌክትሪክ ወደ መሬት ይስበዋል ተብሎ ይታመናል።
ሳይንሳዊ እውነታው፦ መብረቅ ሰውን መትቶ የሚያልፈው በሚሊሰከንዶች ውስጥ ስለሆነ ሰውነት ውስጥ የሚቀር የኤሌክትሪክ ክምችት የለም። አፈር መቆፈር እና ሰውን መቅበር ሌሎች ሕይወት አድን የሆኑ ስራወችን ለመሥራት የምንጠቀምበትን ወሳኝ የሆነውን ሰዓት (ወርቃማ ጊዜ) ያባክናል። በተጨማሪም አፈሩ ደረት ላይ የሚፈጥረው ጫና መተንፈስ ይከለክላል ፤ የሰውነት ሙቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ፤እንዲሁም በአደጋው ጊዜ በቃጠሎ ምክንያት የተፈጠሩ ቁስሎችን ለከፋ ኢንፌክሽን ያጋልጣል።
ሲጠቃለል መቅረቅ የመታውን ሰው ከአፈር መቅበር ምንም ዓይነት ጥቅም የለውም ።
ለ. ሌሎች የማይጠቅሙ እና ጎጂ ልማዶች :-
🎆ውሃ፣ ወተት ወይም ባህላዊ መድኃኒት በአፍ ማጠጣት፦ ራሱን የሳተ ሰው የመዋጥ አቅም ስለሌለው ፈሳሹ በቀጥታ ወደ ሳንባ በመሄድ ወዲያውኑ ሊያንቀው ወይም ሊገድለው ይችላል። ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ ንቁ ያልሆነ ሰው (ራሱን የሳተ) ምንም አይነት ፈሳሽ ለማጠጣት መሞከር አይመከርም።
🎆በቃጠሎ የተፈጠ ቁስል ላይ ቅቤ፣ ዘይት ወይም ሌላ ነገር መቀባት፦ የመብረቅ ቃጠሎ ከፍተኛ ውስጣዊ ሙቀት አለው። ቅቤ ወይም ዘይት መቀባት ሙቀቱ ወደ ውጭ እንዳይወጣ አፍኖ በመያዝ ቃጠሎውን ያባብሰዋል፤ ከባድ ባክቴሪያም ወደ ውስጥ ያስገባል።
🎆 አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ መቆየት፦ መብረቅ በአንድ በዝናብ ማዕበል ወቅት በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ የመምታት ዕድሉ ከፍተኛ በመሆኑ፣ እዚያው ቦታ ላይ እርዳታ ለመስጠት መሞከር ረዳቱንም ጭምር ለአደጋ ያጋልጣል።
፪. መደረግ ያለባቸው የመጀመሪያ እርዳታዎች :-
የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪው ሕክምና ባለሙያ ባይሆንም የሚከተሉትን እርምጃዎች ደረጃ በደረጃ መተግበር አለበት፦
ደረጃ 1 ፦ የቦታውን ደህንነት ማረጋገጥ
መብረቅ የደረሰበትን ሰው ወዲያውኑ በእጅ መንካት ምንም አይነት ችግር አያመጣም።
ነገር ግን ከላይ እንደጠቀስነው መብረቅ በአንድ በዝናብ ማዕበል ወቅት በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ የመምታት ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም ተጎጂውን በአስቸኳይ ይዞ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ለምሳሌ ቤት ውስጥ ካልተቻለም በአካባቢው ካለው አንጻራዊ ዝቅተኛ ቦታ ላይ መውሰድ ያስፈልጋል።
ደረጃ 2፦ ተጎጂውን ሁኔታ መገምገም እና እንደ ሁኔታው እርዳታ መስጠት
እዚህ ጋር ተጎጂው ያለበትን ሁኔታ አይቶ እርዳታውን እንደሚከተለው ማድረግ ተገቢ ነው ።
ሁኔታ ሀ፦ ራሱን ለሳተ እና መተንፈስ ለማይችል ሰው
ይህ ሁኔታ ተጎጂው የልብ ምት መቆም አጋጥሞታል ማለት ስለሆነ እጅግ አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋል።
ለእርዳታ ሌላ ሰው መጥራት ከተቻለ አምቡላስ መጥራት ጎን ለጎን የሚሰሩ ሆነው አብሮ ያለ ሰው ወዲያውኑ ተጎጅውን በጀርባው በማስተኛት በሁለቱ ጡቶች መካከል ላይ የእጅዎን መዳፍ በማድረግ፤ ሁለተኛውን እጅ በላዩ ላይ በማጣመር ክንድዎን ሳያጥፉ፣ የሰውነትዎን ክብደት በመጠቀም ደረቱን ወደ ታች ከ5-6 ሳንቲም ሜትር ጥልቀት በፍጥነት እና በኃይል መጫን ነው ።
ፍጥነት፦ በደቂቃ ከ100 እስከ 120 ጊዜ መጫን ። ይኼንንም እየተጋገዙ የሰውየው መተንፈስ እስኪመለስ ድረስ ወይም እስከ 30 ደቂቃ ድረስ መደጋገም ያስፈልጋል።
ይህን በትክክል ካደረግን ከ100 ሃያ ሰዎችን ወይም ከዚያ በላይ ማትረፍ ይቻላል።
እንደ አጋጣሚ ከመካከል ስልጠና የወሰደ ካለ ግን ደረትን ከመጫን በተጨማሪ ትንፋሽም መስጠት ያስፈልጋል (ለሰለጠኑ) ።
ሁኔታ ለ፦ ራሱን ለሳተ ነገር ግን በትክክል ለሚተነፍስ ሰው
ሰውየው ልቡ እየመታ እና እየተነፈሰ ከሆነ ነገር ግን ካልነቃ የሚከተሉትን ያድርጉ፦
A. ተጎጂውን በግራ ጎኑ ማስተኛት፣ የላይኛውን እግሩን አጥፎ ወደ ፊት ማድረግ እና እጁን ከጉንጩ ስር ማስደገፍ። ይህ አቀማመጥ ምላሱ ጉሮሮውን እንዳይዘጋው እና ቢተፋ እንኳ ትውከቱ ወደ ሳንባው ሳይሄድ ወደ ውጭ እንዲፈስ ያደርጋል።
B. የአየር መተላለፊያውን መከታተል፦ አፉ ውስጥ አፈር፣ ሳር ወይም ትውከት ካለ በንጹህ ጨርቅ በጥንቃቄ ማጽዳት::
C. ትንፋሹን መቆጣጠር፦ በየደቂቃው ደረቱ መነሳቱንና መውረዱን ማየት። ትንፋሹ ከቆመ ወዲያውኑ ከላይ ያየነውን ሁኔታ 'ሀ' ማድረግ ።
ሁኔታ ሐ :- የቃጠሎ ቁስሎችን በአደጋው የተፈጠረ የአጥንት ስብራት ካለ የሚደረጉ እርዳታወችን የሚተነትን ነው ይታወቃሉ።
የመጨረሻ ማሳሰቢያው መብረቅ የደረሰበት ሰው ምንም ጉዳት የሌለበት ቢመስልም፣ አልፎ ተርፎም ተነጋግሮ በገዛ እግሩ ቢሄድም እንኳ፣ በግዴታ ወደ ሆስፒታል መወሰድ አለበት።
ምንጪ: -
የአሜሪካ ቀይ መስቀል (American Red Cross) ፣
የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (CDC) እና
የአሜሪካ የልብ ማኅበር (AHA - American Heart Association) ንን
ተጠቅመናል።
ሰዎች በአፈር ሲቀበሩ የሚያሳየው ፎቶ iloveafrica.com በሰራው ጥናታው ጽሑፍ ላይ የተገኘ ነው። | 8 |
| 7 | ማስታወቂያ ለግል የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ:-
ቀን 20/10/2018 ዓ.ም
የ2018 ዓ. ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የምትወስዱ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የግል(private)ተፈታኞች የፈተና መርሃግብራችሁ እንደሚከተለው ይሆናል።
#የአየርጤና እና የቀራንዮ መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህህርት ቤት የግል ተፈታኝ ተማሪወዎች
👉የመጀመሪያ ዙር
👉መፈተኛ ጣቢያ አብርሆት ቤተ-መጽሔት
#የሰጲ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ
👉ሁለተኛ ዙር
👉የመፈተኛ ጣቢያ አድዋ መታሰቢያ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:-
ለተፈታኞች የተከለከሉ
❌ ስልክ ይዞ መግባት አይቻልም
❌ ካልኩሌተር
❌ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
❌ ሰዓት
❌ በሀኪም ከታዘዘ ውጪ የሆኑ መነጽሮች
❌ የሚነበቡ ጽሁፎች በሙሉ | 90 |
| 8 | 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል አመታዊ እቅድ የምትፈልጉ
👉@ba1227 አናግሪኝ | 226 |
| 9 | Africa's Largest Countries by land area.
1. Algeria 🇩🇿
2. Democratic Republic of the Congo 🇨🇩
3. Sudan 🇸🇩
4. Libya 🇱🇾
5. Chad 🇹🇩
6. Niger 🇳🇪
7. Angola 🇦🇴
8. Mali 🇲🇱
9. South Africa 🇿🇦
10. Ethiopia 🇪🇹 | 222 |
| 10 | የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፓስፖርት ለማሳደስ የምትፈልጉ ደንበኞቻችን የመደበኛ እና የአስቸኳይ ፓስፓርት እድሳት አገልግሎት ክፍያ ዋጋ
• መደበኛ 5,000 ብር
• አስቸኳይ የ2 ቀን 25,000 ብር
• አስቸኳይ የ5 ቀን 20,000 ብር ነዉ
ማሳሰቢያ፦
• ከዚህ ውጪ ክፍያ ከተጠየቁ በነፃ የስልክ ቁጥር 8133 በመደወል ወይም በተቋሙ የቅሬታ ማቅረቢያ "ICS Resolve" መተግበሪያ (App) ቅሬታ ማቅረብ፡ የገጠመዎትን ማንኛውንም የአገልግሎት ችግር በቀላሉ ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
• ለየትኛዉም የፓስፖርት አገልግሎት በኦንላይን ለመመዝገብ ትክክክለኛው ዌብሳይት አድራሻችን www.immigration.gov.et መሆኑን እንገልፃለን።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ ! | 220 |
| 11 | የማስተርስ ትምህርት አራት አመት‼️
"የማስተርስ ትምህርት ወደ 4 ዓመት ሊያድግ ይገባል " ተባለ‼️
የአሰራር ለውጥ ካልተደረገ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች እውቅና ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት ይፈጥራል ብሏል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጠው የሁለተኛ ዲግሪ (የማስተርስ) ትምህርት ፕሮግራም ከሁለት ዓመት ወደ አራት ዓመት ሊያድግ እንደሚገባ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ይህንን ያስታወቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰጠው ሙያዊ ማብራሪያ፣ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በሁለት ዓመት መደበኛ መርሃ ግብር እየተሰጠ ያለው የማስተርስ ትምህርት፣ አዲስ ከጸደቀው የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብና ከአለም አቀፍ በተለይም ከአውሮፓ ስታንዳርድ ጋር የማይገናኝ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ ክፍተት በአስቸኳይ የማይስተካከል ከሆነ፣ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች የትምህርት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ወይም እውቅና (Authentication) ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት እንደሚሆን ባለስልጣኑ አስገንዝቧል።
ከእነዚህም መካከል በሀገራችን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ሳያመጡ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ከተማሩ በኋላ፣ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ የሚጠይቁት የብቃት ማረጋገጫ ጉዳይ ትልቅ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም ያጸደቀው የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብ፣ እውቅና ካላቸው የውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት የተገኙ የብቃት ማረጋገጫዎች በሀገሪቱ መመዘኛ መሰረት ተመዝነው እውቅና እንዲሰጣቸው ቢደነግግም፣ አሁን ያለው አሰራር ግን ይህንን ለመተግበር አስቸጋሪ አድርጎታል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዳመለከተው፣ ለአማራጭ የትምህርት ክሬዲት ስርአት (ECTS) በአውሮፓ (ከፍተኛ) የሆነው መስፈርት፣ በኢትዮጵያ ደንብ ውስጥ ' (ዝቅተኛ) ሆኖ ተቀምጧል። ይህንን ወደ ዓመት ሲተረጎም የማስተርስ ፕሮግራም ደንቡ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ የ4 ዓመት ፕሮግራም መሆን እንዳለበት ያስገድዳል።
ጉዳዩን በተመለከተ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም ለትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ ቢገለጽም እስካሁን ምንም ምላሽ አልተገኘም ተብሏል፡፡
source:ethiofm | 357 |
| 12 | Немає тексту... | 524 |
| 13 | Xenderን ለፋይል ማስተላለፊያ ብቻ የሚጠቀሙ ከሆነ እነዚህን 4 ድብቅ ጥቅሞች አምልጠውዎታል!
ብዙዎቻችን Xenderን የምናውቀው ፎቶ እና ቪዲዮ ከስልክ ስልክ ለመላላክ ብቻ ነው። ነገር ግን ይህ መተግበሪያ ህይወታችንን የሚያቀሉ ሌሎች አስገራሚ ጥቅሞችን በአንድ ላይ ይዟል።
መተግበሪያው ውስጥ ተደብቀው የሚገኙትን 4 ዋና ዋና ጥቅሞች እነሆ👇
1️⃣ ቪዲዮን ወደ MP3 (ኦዲዮ) መቀየር
ጥቅሙ፡ የቪዲዮ ሙዚቃዎችን ወይም ንግግሮችን ወደ ኦዲዮ (Audio) ለመቀየር ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያ መጫን አያስፈልግዎትም።
አጠቃቀም፡ Xender ውስጥ ገብተው ከታች "ToMP3" የሚለውን ይጫኑ ➡️ "Select Video" የሚለውን በመንካት ቪዲዮዎን ይምረጡ። በሰከንዶች ውስጥ ወደ MP3 ይቀየርልዎታል።
2️⃣ የማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮዎችን ማውረጃ (Downloader)
ጥቅሙ፡ ከፌስቡክ፣ ከኢንስታግራም ወይም ከቲክቶክ ቪዲዮዎችን በቀላሉ ማውረድ ይችላሉ።
አጠቃቀም፡ Xender ውስጥ ከታች "Social" የሚለውን ይጫኑ ➡️ ማውረድ የሚፈልጉትን የቪዲዮ ሊንክ (Link) ኮፒ አድርገው እዚህ ላይ ይለጥፉ (Paste ያድርጉ) ➡️ "Download" የሚለውን ይንኩ።
3️⃣ ያለ ኬብል ስልክን ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት
ጥቅሙ፡ ምንም አይነት የዩኤስቢ (USB) ኬብል ሳይጠቀሙ ፋይሎችን ከስልክ ወደ ላፕቶፕ/ኮምፒውተር በፍጥነት መጫን ያስችላል።
አጠቃቀም፡ Xender ላይ በቀኝ በኩል ያለውን ምልክት ነክተው "Connect to PC" ይምረጡ ➡️ የስልክዎን Hotspot አብርተው ኮምፒውተርዎን ያገናኙ ➡️ ኮምፒውተርዎ ብሮውዘር (Browser) ላይ ስልኩ ያሳየዎትን የድር አድራሻ (IP Address) ይተይቡ።
4️⃣ አዲስ ስልክ ሲገዙ ዳታ ማዛወሪያ (Phone Clone)
ጥቅሙ፡ አዲስ ስልክ ሲቀይሩ በድሮ ስልክዎ ላይ ያሉትን ስሞች (Contacts)፣ ፎቶዎች እና መተግበሪያዎች በአንድ ጊዜ ወደ አዲሱ ስልክ ያዛውራል።
አጠቃቀም፡ በሁለቱም ስልኮች Xender ላይ "Phone Clone" የሚለውን ይምረጡ ➡️ አንዱን "Old" ሌላኛውን "New" በማድረግ ያገናኙ እና ሁሉንም መረጃዎች በቀላሉ ያዛውሩ። | 469 |
| 14 | ወላጅ እናቱን የሚኒስትሪ ፈተናው ቀን በሞት ያጣው ተማሪ ኻሊድ የባንክ አካውንት ይፋ ሆኗል።
ተማሪ ኻሊድን መርዳት የምትፈልጉ የሲንቄ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ አካውንት ተከፍቷል። ተማሪ ኻሊድ እድሜው 18 ስላልሞላውና ዘመድም ስለሌለው፤ ብቻውን ገንዘብ አውጥቶ መጠቀም ስለማይችል፣ አካውንቱ በአካባቢው መስጅድ ኡስታዝ፣ ከሀገር ሽማግሌ እና ከራሱ ጋር በጋራ በመሆን አካውንት ተከፍቶለታል።
①) ስንቄ ባንክ
11 14385901915
②) አዋሽ ባንክ
013201115433100 | 458 |
| 15 | የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ መዘግየት ቅሬታና የቦርዱ ምላሽ !
የ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ አስፈፃሚዎች የውል ክፍያቸው በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት ለከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና መዳረጋቸውን ገለጹ።
" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በውል ስምምነቱ ላይ የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ አላከበረም " ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
እንደ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገለጻ፣ ከቦርዱ ጋር በተደረገው የስራ ውል መሠረት ለ54 የሥራ ቀናት በቀን 548 ብር ታስቦ በአጠቃላይ 29,592.00 ብር ሊከፈል ስምምነት ተደርጓል።
ይሁን እንጂ አጠቃላይ የምርጫ ሥራው ተጠናቆ የሥራ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች በሰነድ በተረከቡ በ15 ቀናት ውስጥ መፈጸም የነበረበት የ60 በመቶ የመጨረሻ ክፍያ (17,755.20 ብር) እስካሁን ሊከፈላቸው አልቻለም።
ከዚህም በተጨማሪ የ14 ቀናት የሥራ ክፍያ 7,672 ብር እና የ4 ቀናት የስልጠና አበል 2,192 ብር በደብዳቤ ሊከፈላቸው ቃል ተገብቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
አሁን ባለው የኑሮ ውድነት ወቅት የክፍያው መዘግየት የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን ከማናጋቱም በላይ፣ ለተከናወነው ከፍተኛ አገራዊ ሥራ የሚገባውን ሙያዊ ክብር የሚያሳጣ መሆኑን አስፈፃሚዎቹ ጠቁመዋል።
ስለሆነም፣ ምርጫ ቦርድ የገባውን የውል ስምምነት በማክበር፣ የተዘገየውን አጠቃላይ ክፍያ በሰነድ ላይ በተጠቀሰው የባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው መሠረት በአስቸኳይ ገቢ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
ምን ምላሽ ተሰጠ ?
ትላንት በነበረው መግለጫ ወቅት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንኑ የአስፈጻሚዎች ቅሬታ ለቦርዱ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉም በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።
ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ምን አሉ ?
" ከምርጫ አስፈጻሚዎች ጋር በነበረው ውል መሰረት የመጀመሪያውን 40% ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከፍሏል። ይህንን ለመክፈል ትልቅ ችግር ገጥሞን የነበረው በሶማሌ ክልል እና አፋር ክልል ነው።
አስፈጻሚዎቻችን አስፈጻሚዎቻችን የባንክ አካውንት ስላልነበራቸው የምርጫ ቦርድ ሰራተኞች በቦታው ተገኝተው ገንዘብ በካሽ አውጥተው መክፈል ነበረባቸው ይህንን አድርገዋል፤ የክፍያ ሂደቱን አጠናቀዋል።
ቀሪ 60 በመቶው የሚከፈለው የምርጫ አስፈጻሚዎች ከቦርዱ የተቀበሉትን ንብረት ለቦርዱ ሙሉ ለሙሉ አስረክበው ሲጨርሱ የሚከፈል ይሆናል። ይህንን የማጥራት ሂደት ጀምረናል።
ምንም አይነት የቦርዱ ንብረት በእጃቸው የሌለ አስፈጻሚዎች መክፈል ጀምረናል። ከእነሱ ጋር ያለው ንብረት ተጠናቆ ሲገባ ከሥር ከሥር ክፍያው ይፈጸማል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ | 371 |
| 16 | የመጨረሻ የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ!!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ብልጽግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን በማሸነፍ በፓርላማው ውስጥ አብላጫውን ይዞ መቀጠሉ ተረጋግጧል።
ውጤቱን ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ ሲሆኑ፣ የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ ሥነ-ሥርዓቱ በፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሲቪክ ማህበራት፣ በውጭ ሀገራት አምባሳደሮች እና በመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል።
ጠቅላላ ምርጫው በ1,139 የምርጫ ክልሎች የተካሄደ ሲሆን፣ 501 የፌዴራል ፓርላማ መቀመጫዎችን እና 638 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎችን አካትቷል።
ዋና ዋና ውጤቶች
• ብልጽግና ፓርቲ – 438 መቀመጫዎች
• ተቃዋሚ ፓርቲዎች – 41 መቀመጫዎች
• የግል ዕጩዎች – 8 መቀመጫዎች | 224 |
| 17 | 🗳️ ከምርጫው ሂደት ግምገማ እስከ ድጋሚ ቆጠራና ምርጫ ውሳኔዎች፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ የምርጫውን አጠቃላይ አፈፃፀም፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችን እና ድጋሚ ቆጠራና ምርጫ የሚደረግባቸውን ክልሎች አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ዋና ነጥቦቹ የሚከተሉት ናቸው፦
📊 የምርጫው ቁጥራዊ መረጃዎች በአጭሩ፦
ተሳትፎ፦ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 80 የግል እጩዎች።
መራጭና አስፈፃሚ፦ 54 ሚሊየን 57 ሺ 861 መራጮች፣ 350 ሺ ምርጫ አስፈፃሚዎች እና 260 ሺ የፓርቲ ወኪል ታዛቢዎች።
ልዩ ተሳትፎ፦ 126 ሺ ወታደሮች፣ ከ28 ሺ በላይ ተፈናቃዮች እና ከ20 ሺ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምርጫው አካል ነበሩ።
ሚዲያና ጋዜጠኞች፦ 73 መገናኛ ብዙሃን (1,827 የአገር ውስጥና 45 የውጪ ጋዜጠኞች) ዘግበውታል። 19 የክርክር መድረኮችም ተካሂደዋል።
🤝 የሲቪክ ማህበራትና የውጪ ታዛቢዎች ሚና፦
169 አገር በቀል ማህበራት የመራጮች ሲቪክ ትምህርት ፈቃድ ያገኙ ሲሆን፣ 114ቱ ከቦርዱ የገንዘብ ድጋፍ አግኝተዋል።
55 ማህበራት ከ64 ሺ በላይ ታዛቢዎችን በማሳተፍ ድምፅ አሰጣጡን ታዝበዋል።
ከውጪ፡ 63 ከአፍሪካ ህብረት፣ 26 ከኢጋድ፣ 21 ሚሲዮኖች እና 1 የውጪ ምርጫ አስፈፃሚ በታዛቢነት ተሳትፈዋል።
⚠️ ያጋጠሙ ዋና ዋና ፈተናዎችና የህግ እርምጃዎች፦
የቴክኖሎጂ ክፍተት፦ በፓርቲዎች ዘንድ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓቱን የመረዳት ክፍተት የታየ ሲሆን፣ ቦርዱ አድሚኖችን በራሱ ወጪ በመቅጠር ደግፏል። በ22 ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የመረጃ ፍሰት አስቸጋሪነትና የመሰረተ ልማት እጥረት ኦፕሬሽኑን ፈትኖታል።
የአስፈፃሚዎች ገለልተኝነትና ጣልቃ ገብነት፦ የፓርቲ ወኪሎችን መከልከል፣ በአስፈፃሚዎች ላይ መደለያ ማቅረብ እና አንዳንድ ዝቅተኛ የመንግስት አስተዳደር እርከን ላይ ያሉ አካላት በቦርዱ ስራ ውስጥ የመግባት ችግሮች ተስተውለዋል።
ህጋዊ ተጠያቂነት፦ በህግ ጥሰት የተሳተፉ የአስተዳደር አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ የህግ ሂደት ላይ ናቸው። በ129 የምርጫ ክልሎች የቀረቡ አቤቱታዎችን ምክንያት በማድረግ ቦርዱ የድጋሚ ቆጠራና ምርጫ ውሳኔ አሳልፏል።
የመራጮች ብዛት፦ በህጉ መሰረት በአንድ ጣቢያ ከ1,500 መራጭ መብለጥ ባይኖርበትም፣ ከዛ በላይ የተመዘገበባቸውና የሰልፍ መራዘም የታየባቸው ጣቢያዎች ነበሩ።
🚨 ድጋሚ ቆጠራ እና ድጋሚ ምርጫ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ይፋ ሆኑ!
🔄 የድምፅ አቆጣጠር በድጋሚ የሚካሄድባቸው የምርጫ ክልሎች፦
በደቡብ ኢትዮጵያ፦ ብርብር፣ ገረሴ እና ዳሞት ወይዴ
በሲዳማ ክልል፦ ገረሰላም እና ጨኮ
በኦሮሚያ ክልል፦ ወልመራ፣ ክብረ መንግስት እና አሊቦ
በሱማሌ ክልል፦ ቀላፎ እና ሀርሺ
በአፋር ክልል፦ አሚባራ
በሀላባ፦ የሀላባ 1 ምርጫ ክልል (ለክልል ምክር ቤት)
🗳️ ድጋሚ ምርጫ (በአዲስ መልክ) የሚካሄድባቸው የምርጫ ክልሎች፦
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፦ ሶሮ 1 እና ጠንባሮ
በሱማሌ ክልል፦ ሀርገሌ፣ ዳሮ፣ ሀዲጋላ፣ ሀዋሌ እና ዳራቶሌ
ሌሎች አካባቢዎች፦ ባቱ ዝዋይ፣ ቤጊ፣ አሮሬሳ እና ጨንቻ የምርጫ ክልሎች።
#ምርጫ2018 #NEBE #EthiopianElection | 196 |
| 18 | አጠቃላይ የምርጫ ውጤት (ፓርላማ)
1. አዲስ አበባ ከተማ (23 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 20 መቀመጫዎች
- ኢዜማ 2 መቀመጫዎች
- የግል ዕጩ 1 መቀመጫ
2. አፋር ክልል (8 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 7 መቀመጫዎች
- የአፋር ህዝብ ፓርቲ 1 መቀመጫ
3. አማራ ክልል (ምርጫ የተካሄደባቸው 130 የፓርላማ መቀመጫዎች )
- ብልጽግና 117 መቀመጫዎች
- አብን 6 መቀመጫዎች
- አዲህን 3 መቀመጫዎች
- አርጎባ አንድነት ጀበርቲ ፓርቲ 1 መቀመጫ
- ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 1 መቀመጫ
- ኢዜማ 1 መቀመጫ
- ነጻነትና እኩልነት 1 መቀመጫ
4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (9 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 8 መቀመጫዎች
- ጉሙዝ ብሔራዊ ንቅናቄ 1 መቀመጫ
5. ድሬዳዋ (2 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 2 መቀመጫዎች
6. ጋምቤላ ክልል (3 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 3 መቀመጫዎች
7. ኦሮሚያ ክልል (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 173 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና 167 መቀመጫዎች
- 5 የግል ዕጩዎች 5 መቀመጫዎች
- አዲስ ትውልድ ፓርቲ 1 መቀመጫ
8. ሐረሪ ክልል (2 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 2 መቀመጫዎች
9. ሲዳማ ክልል (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 16 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 13 መቀመጫዎች አሸንፏል
- መድረክ 3 መቀመጫዎች
10. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (20 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 17 መቀመጫዎች
- ኢዜማ 1 መቀመጫ
- ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ 1 መቀመጫ
- ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 1መቀመጫ
11. ደቡብ ኢትዮጵያ (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 45 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 35 መቀመጫዎች
- ኢዜማ 7 መቀመጫዎች
- የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 1 መቀመጫ
- የወላይታ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ 1 መቀመጫ
- የግል እጩ 1 መቀመጫ
12. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 33 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልጽግና ፓርቲ 28 መቀመጫዎች
- ኢዜማ 2 መቀመጫዎች
- የግል ዕጩ 1 መቀመጫ
- ትብብር ለኢትዮጵያ 1 መቀመጫ
- ነጻነትና እኩልነት 1 መቀመጫ
13. ሶማሌ ክልል (22 የፓርላማ መቀመጫዎች)
- ብልፅግና ፓርቲ 19 መቀመጫዎች
- የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር 1 መቀመጫ
- ሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ 1 መቀመጫ
- ህብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ፓርቲ 1 መቀመጫ
ማስታወሻ ፦በትግራይ ክልል በ38 የፓርላማ መቀመጫዎች ምርጫ አለመከናወኑ ይታወቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia | 189 |
| 19 | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጉልህ የሆነ የምርጫ ሕግ ጥሰት መፈጸሙን ባረጋገጠባቸው የምርጫ ክልሎች ላይ ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ውስኗል።
በዚህም ቦርዱ በ5 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ በሚደረግባቸውና በ8 ለክልል ምክር ቤት ምርጫ በሚደረግባቸው ምርጫ ክልሎች ድጋሜ ምርጫ ይካሄድባቸዋል ተብሏል።
ድጋሜ ምርጫ የሚካሄድባቸው ምርጫ ክልሎች የትኞቹ ናቸው ?
ሶሮ 1 — ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣
ጠምባሮ ምርጫ ክልል — ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤
ሀርገሌ ምርጫ ክልል — ሶማሌ ክልል ለክልል ምክር ቤት ምርጫ፣
ዳሎል ምርጫ ክልል — ሶማሌ ክልል ለክልል ምክር ቤት ምርጫ፣
ሀዲጋላ ምርጫ ክልል — ሶማሌ ክልል ለክልል ምክር ቤት ምርጫ፣
አዋሬ ምርጫ ክልል — ሶማሌ ክልል ለክልል ምክር ቤት ምርጫ፣
ዳራቶሌ ምርጫ ክልል — ሶማሌ ክልል ለክልል ምክር ቤት ምርጫ፣
ባቱ ዙሪያ ምርጫ ክልል — ኦሮሚያ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤት ምርጫ፣
ቤጊ ምርጫ ክልል — ኦሮሚያ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት፣
አሮሬሳ ምርጫ ክልል — ሲዳማ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ፣
ጨንቻ ምርጫ ክልል — ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፥ ለክልል ምክር ቤት ምርጫ፤ ድጋሚ ምርጫ የሚካሄድባቸው የምርጫ ክልሎች ናቸው ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም | 164 |
| 20 | #ምርጫ2018 : ብልፅግና ፓርቲ ዛሬ ይፋ በተደረገው ውጤት 438 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) መቀመጫዎችን አግኝቷል።
ፓርቲው ያሸነፈው ከፍተኛ የፓርላማ መቀመጫ ቁጥር መንግሥት መመስረት የሚያስችለው ነው።
በሌላ በኩል ፦
- የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 👉 13 መቀመጫዎች
- የግል ዕጩዎች 👉 8 መቀመጫዎች
- አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 👉 6 መቀመጫዎች
- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) 👉 3 መቀመጫዎች
- የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ 👉 3 መቀመጫዎች
- ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ 👉 3 መቀመጫዎች
- ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ 👉 2 መቀመጫዎች
- የአፋር ህዝብ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ
- አርጎባ አንድነት ጀርበቲ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ
- ጉሙዝ ብሔራዊ ንቅናቄ 👉 1 መቀመጫ
- አዲስ ትውልድ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ
- ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 👉 1 መቀመጫ
- የጌዴኦ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ
- የወላይታ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ 👉 1 መቀመጫ
- የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር 👉 1 መቀመጫ
- ህብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ
- ሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ ... አግኝተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia | 251 |
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
