uk
Feedback
ካራ አሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት Karalo

ካራ አሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት Karalo

Відкрити в Telegram

ይህ ቻናል ታማኒና ወቅታዊ መልእክቶች ፣ሞደል ፈተናዎች ፣ ወርክሽቶች እንድሁም አስተማሪ መለዕክቶችን ያገኛሉ።

Показати більше
4 259
Підписники
+324 години
+437 днів
+5330 день
Архів дописів
Repost from N/a
በቀን29/09/2018 ዓ.ም . በካራአሎ ቅድመ አንደኛ ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች በፈተና ህግጋት፣የፈተና ዝግጅት ምዕራፍ ምን መምሰል እንዳለበት፣በፈተና ወቅት ስለሚኖር የስነ ልቦና ጫና እና መደረግ ስላለበት ቅድመ ዝግጅት፣የፈተና ወረቀት አጠቋቆር እንዲሁም የሠዓት አጠቃቀምና በመሣሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉም የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በተገኙበት ዝርዝር ኦረንቴሽን ተሰጠ::

Repost from Yeka Education
✔️የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም ዙሪያ ሊያውቋቸው የሚገቡ ጉዳዮች ✅የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመ
+3
✔️የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም ዙሪያ ሊያውቋቸው የሚገቡ ጉዳዮች የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ብቻ ማጥቆር አለበት፡፡ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን የአራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ መልስ (የአራት ማዕዘን ቅንፍ/Square Bracket) ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም። በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን። #️⃣ሸር 📌 ለሁሉም ተፈታኞች መልካም የጥናትና የፈተና ጊዜ! 👏👏👏👏👏 🔠🔠🔠🔠 🔠🔠🔠 Our Channel ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76

✔️ይነበብ✅
✔️ይነበብ

+4
G 6 AMH AS 1ST MODEL ANS.KEY.pdf1.94 KB

+8
2018 E.C. SAT ANSWER KEY.pdf1.19 KB

+6
G 8 A.O MODEL EXAM.ANS.KEY.pdf1.95 KB

+6
G 6 A.O AKKA 1FFAATI DEEBII.pdf6.13 KB

Repost from Yeka Education
🔠🔠🔠 ✔️በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡ (ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ
+2
🔠🔠🔠 ✔️በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡     (ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና  የሚሰጥበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡   📌በዚህ መሰረትም ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ሰኔ 8 ፣ 9 እና 10/2018 ዓ.ም ✅እንዲሁም የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና  ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰጥ ይሆናል፡፡   📌ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሰጠው በዚህ ከተማ አቀፍ ፈተና በ6ኛ ከፍል 84,882 ተማሪዎች 199  የመፈተኛ ጣቢያዎች  እንዲሁም በ8ኛ ከፍል 86,808 ተማሪዎች 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች  ፈተናዉን ለመውሰድ ተመዝግበዋል፡፡    መልካም  ፈተና✅ 🔠🔠🔠🅰️  🔤🔤🔤🔤  🔠🔠🔠 🔤🔤🔤 ቻናላችን ይህ ነው 👇👇👇👇👇👇 ❤️❤️❤️❤️❤️ https://t.me/dam76

Repost from Yeka Education
🌟ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ ✅ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። ✅አብዝተን ፈተናን እና
🌟ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ ✅ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። ✅አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። ✅ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። ✅ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር:: ✅ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ ✅በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። ✅ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። ✅በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ✅መጭው ጊዜ የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች #ሸር በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር 🤲🤲🤲🤲 መልካም  ፈተና✅ 🔠🔠🔠🅰️  🔤🔤🔤🔤  🔠🔠🔠 🔤🔤🔤 ቻናላችን ይህ ነው 👇👇👇👇👇👇 ❤️❤️❤️❤️❤️ https://t.me/dam76

Repost from Yeka Education
✔️ሞዴል ፈተና መፈተን የሚያስገኛቸው ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው። ✅1. ያላችሁን እውቀት መመዘን እና ድክመታችሁን መለየት፡ ሞዴል ፈተናዎች በእጃችሁ ያለውን እውቀት ምን ያህል እንደሆነ ለመገምገምና
✔️ሞዴል ፈተና መፈተን የሚያስገኛቸው ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው።1. ያላችሁን እውቀት መመዘን እና ድክመታችሁን መለየት፡ ሞዴል ፈተናዎች በእጃችሁ ያለውን እውቀት ምን ያህል እንደሆነ ለመገምገምና የትኞቹ አካባቢዎች ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ያግዛሉ። ለምሳሌ፣ አንድን ሞዴል ፈተና ከሰራችሁ በኋላ በተወሰኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ደጋግማችሁ እንደተሳሳታችሁ ከተመለከታችሁ፣ በእነዚያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ጥናት ማድረግ ትችላላችሁ። 2.ከፈተና ጥያቄዎች እና የፈተና ሁኔታ ጋር መለማመድ፡ ሞዴል ፈተናዎችን መለማመድ የፈተና ጥያቄዎችን ቅርፅና አቀራረብ እንድታውቁ ይረዳችኋል። በተጨማሪም፣ በፈተና ጊዜ ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉትን ጭንቀቶች ለመቀነስና ከፈተናው ሁኔታ ጋር እንድትላመዱ ያደርጋል። 3. የፈተና ጊዜ አጠቃቀም ክህሎትን ማሳደግ፡ ሞዴል ፈተናዎችን ስትሰሩ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ምን ያህል ጊዜ መመደብ እንዳለባችሁ ትማራላችሁ። ይህም በፈተናው ወቅት ጊዜያችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት ይረዳችኋል። ⭐️ ለምሳሌ፣ በአንድ ጥያቄ ላይ ብዙ ጊዜ እንደምታጠፉ ከተመለከታችሁ፣ በቀጣይ ፈተናዎች ላይ ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም ስልት መንደፍ ትችላላችሁ። 4. በራስ መተማመንን መጨመር እና የፈተና ላይ ጭንቀትን መቀነስ፡ በተደጋጋሚ ሞዴል ፈተናዎችን መስራት በራስ መተማመናችሁን ይጨምራል እንዲሁም በፈተና ጊዜ የሚሰማችሁን ጭንቀት ይቀንሳል። በሞዴል ፈተናዎች ላይ ጥሩ ውጤት ስታገኙ፣ ለዋናው ፈተና የበለጠ በራስ መተማመን ይኖራችኋል። 5. የተማራችሁትን የማስታወስ እና የማስተዋል አቅምን መጨመር፡ ሞዴል ፈተናዎች የተማራችሁትን ነገር እንድታስታውሱና እንድትረዱ ያግዛሉ። ጥያቄዎችን ለመመለስ ስትሞክሩ፣ ቀደም ሲል ያጠኗችሁትን ርዕሰ ጉዳዮች በድጋሚ ታስታውሳላችሁ፣ ይህም ትምህርቱን በደንብ እንድትረዱት ያደርጋል። 6. የፈተና ጥያቄዎችን እና የተለያዩ የአጠያየቅ አይነቶችን ስልት ለማወቅ፡ ሞዴል ፈተናዎች የተለያዩ የጥያቄ አይነቶችን (ለምሳሌ፡ ምርጫ፣ እውነት ወይም ሐሰት፣ ወዘተ) እንድታውቁና ለእያንዳንዱ አይነት ጥያቄ እንዴት መልስ መስጠት እንዳለባችሁ እንድትረዱ ይረዳችኋል። 7. ትኩረት ማድረግ የሚያስፈልጉ ርዕሶችን እና አጠቃላይ ክለሳ ማድረግ ያለብንን ቦታዎች ለመለየት፡ ሞዴል ፈተናዎችን ከሰራችሁ በኋላ በየትኞቹ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደተሳሳታችሁ በመገምገም፣ በእነዚያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ትኩረት ማድረግ ትችላላችሁ። ይህም ለፈተናው ስትዘጋጁ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ማተኮር እንዳለባችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል። ✔️በአጠቃላይ፣ ሞዴል ፈተናዎችን መፈተን እውቀታችሁን ለመገምገም፣ ለፈተናው ሁኔታ ለመለማመድ፣ ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም፣ በራስ መተማመናችሁን ለመጨመር እና ለዋናው ፈተና በተሻለ ሁኔታ ለመዘጋጀት ጠቃሚ ነው:: መጭው ጊዜ የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች #ሸር በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር 🤲 🔠🔠🔠🅰️  🔤🔤🔤🔤  🟢Our channel 👇👇👇👇 https://t.me/dam76

➡️የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል በ16ቱ የፈተና ጣቢያ የት/ቤቶች ድልድል(በድጋሜ የተለጠፈ)

+7
300 grade 8 English questions with answers and explanation Prepared by: Belay K. from nigat kokeb school

+4
የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ሞዴል ፈተና 👉አዘጋጅ ንፋስ ስልክ  ክ/ከተማ

+5
የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ሞዴል ፈተና 👉አዘጋጅ ንፋስ ስልክ  ክ/ከተማ

+5
የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ሞዴል ፈተና 👉አዘጋጅ አራዳ ክ/ከተማ

+5
የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል የመጀመሪያ ሴሚስተር ሞዴል ፈተና 👉አዘጋጅ አራዳ ክ/ከተማ