የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካይሮ (Embassy of Ethiopia in Cairo)
Відкрити в Telegram
ለኤምባሲው አገልግሎት ጠያቂዎች የተከፈተ ቻናል ሲሆን መረጃ ከዚህ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
Показати більше2 022
Підписники
Немає даних24 години
+67 днів
+3030 днів
Архів дописів
+2
19ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ አላማ ቀን በካይሮ የኢፌድሪ ኤምባሲ ተከበረ።
የዘንድሮ 19ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ አላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትንና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም በካይሮ የኢፌድሪ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፣ ሰራተኞች፣ የኮሚኒቲ አመራር እና ነዋሪዎች በተገኙበት ብሄራዊ መዝሙር በመዘመር እና ባንዲራ በክብር በመስቀል ተከብሯል። የሚስዮኑ ተወካይ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልክት ሰንደቅ አላማ ያለውን ትልቅ ክብር በውል መገንዘብ እንደሚያስፈልግ እና ለሀገራችን ሉዓላዊነት፣ ነፃነት እና ለሰንደቃችን ክብር የተከፈውን ዋጋ በማስታወስ ሀገራዊ መግባበት እና ሕብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትን በማጠናከር ብሔራዊ አንድነትን አጽንቶ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ የተገለጸበት ነበር።
ማስታወቂያ
ዛሬ በቀን 24/01/2019ዓ.ም (እሁድ) እለት በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን ጉዳይ ለመከታተል ከቢሮ ስለምንወጣ የቆንስላ አገልግሎት የማይኖር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
+1
በግብጽ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ!
መልካም አዲስ አመት!
+3
*የስራ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁት ክቡር አምባሳደር የክብር አሸኛኘት ተከናውኗል።*
በግብጽ እና ሊብያ የኢፌድሪ ልዩ መልክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀነራል ክቡር ሃሰን ኢብራሂም ሙሳ የስራ ጊዚያቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ በዲፕሎማቶች እና በኤምባሲው ማህበረሰቦች የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል። በዚህም የስራ ባልደረቦች ክቡር አምባሳደር በቆይታቸው ለሰጡት በሳል አመራር እና ላሳዩት የአገር ፍቅር ስሜት አድናቆት እና ምስጋና በመቸር በቀጣይ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ክቡር አምባሳደር ባስተላለፉት መልክት በሚሲዮኑ ቆይታቸው የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ባደረጉት ጥረት ውስጥ የሚሲዮኑ ሰራተኞች ለነበራቸው ሚና በማመስገን ሰራተኞች መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
በግብጽ ለምትኖሩ ኢትዬጵያውያን እና ትውልደ ኢትዬጽያውያን በሙሉ!
እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም የመውሊድ በዓል ይሁን!
ማስታወቂያ!
ጉዳዩ፡- የኢትዮጵያ ብራንድ ግንዛቤ አመላካች አለም አቀፍ የግንዛቤ ዳሰሳ ጥናት ይመለከታል፤
ኢትዮጵያ የCOP32 (የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፍረንስ) ለማድረግ በዝግጅት ላይ ትገኛለች። ከዚህ ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ብራንድ ግንዛቤ ለማሳደግ ኢትዮጵያ በአለምአቀፍ ማህበረሰብ እንዴት ትታያላች የሚል መነሻ ጥናት በማስፈለጉ በዚህ መነሻ ጥናት በኢሜል በሚላክ የሰርቬይ ማስፈንጠሪያ (e-mail survey link) ላይ የሚሳተፉ 30 ወንድ እና 30 ሴት በድምሩ 60 በግብጽ የሚኖሩ ዲያስፖራዎች ስም እና ኢሜል አድራሻ በፍጥነት ስለተፈለገ መረጃውን ከታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር በአፋጣኝ እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ስልክ ቁጥር፡ 01157897711/01159744138
ማስታወሻ፡- ጥናቱ ላይ መሳተፍ የሚችሉት ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፣ ከኢትዮጵያ ውጪ ቢያንስ ከ2 ዓመት በላይ የኖረ፣ ኢትዮጵያ ተወልደው በውጭ የሚኖሩ ወይም ከኢትዮጵያዊ እናት እና አባት በውጭ አገር የተወለዱ ናቸው።
ስም ዝርዝራችሁ ከላይ የተጠቀሰው ግለሰቦች ፓስፖርታችሁ ተሰርቶ ስለመጣ የከፈላችሁበትን ደረሰኝና አሮጌውን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት በስራ ቀንና ስዓት እንድትረከቡ እናሳስባለን።
ማስታወቂያ
ነገ በቀን 28/10/2018 ዓ.ም (እሁድ) እለት በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን ጉዳይ ለመከታተል ከቢሮ ስለምንወጣ የቆንስላ አገልግሎት የማይኖር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ማስታወቂያ
ነገ በቀን 28/10/2018 ዓ.ም (እሁድ) እለት በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን ጉዳይ ለመከታተል ከቢሮ ስለምንወጣ የቆንስላ አገልግሎት የማይኖር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ማስታወቂያ
ነገ በቀን 21/10/2018 ዓ.ም (እሁድ) እለት በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን ጉዳይ ለመከታተል ከቢሮ ስለምንወጣ የቆንስላ አገልግሎት የማይኖር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ስም ዝርዝራችሁ ከላይ የተጠቀሰው ግለሰቦች ፓስፖርታችሁ ተሰርቶ ስለመጣ የከፈላችሁበትን ደረሰኝና አሮጌውን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት በስራ ቀንና ስዓት እንድትረከቡ እናሳስባለን።
ስም ዝርዝራችሁ ከላይ የተጠቀሰው ግለሰቦች ፓስፖርታችሁ ተሰርቶ ስለመጣ የከፈላችሁበትን ደረሰኝና አሮጌውን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት በስራ ቀንና ስዓት እንድትረከቡ እናሳስባለን።
ማስታወቂያ
ለክቡራን የውክልና ስልጣን መስጠት እና የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ፈላጊዎች፡-
የDigital MOFA የስልክ መተግበሪያን በተመለከተ እ.ኤ.አ. ከኤፕሪል 2026 ጀምሮ የውክልና ስልጣን መስጠት እና የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመተግበሪያው (Application) ብቻ እንዲሰጥ የተወሰነ በመሆኑ አመልካቾች መተግበሪያውን ከ (APP Store) ወይም (Play store) በማውረድ እና በመመዝገብ ባሉበት ሆነው ማመልከት እንደሚችሉ በአክብሮት እንገልፃለን።
Please note that, effective April 2026, Power of Attorney and Document Authentication services that were previously provided in person at the Embassy have been fully digitalized.
Applicants seeking Power of Attorney, document authentication, and related services should apply through the Digital MOFA mobile application.
The Digital MOFA application is available for download from both the Apple App Store and Google Play Store.
ማስታወቂያ
ዛሬ በቀን 07/10/2018 ዓ.ም (እሁድ) እለት በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን ጉዳይ ለመከታተል ከቢሮ ስለምንወጣ የቆንስላ አገልግሎት የማይኖር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ስም ዝርዝራችሁ ከላይ የተጠቀሰው ግለሰቦች ፓስፖርታችሁ ተሰርቶ ስለመጣ የከፈላችሁበትን ደረሰኝና አሮጌውን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት በስራ ቀንና ስዓት እንድትረከቡ እናሳስባለን።
