ግጥም
Відкрити в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Показати більше5 692
Підписники
+924 години
+627 днів
+13230 днів
Архів дописів
5 693
#ማንነት_ሲምታታ
የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 693
Repost from ዝባዝንኬ thought🗽
I really felt it when አስቴር አወቀ said "በል እራሴን በለኝ እንካ ዘነዘና" cause, boy do i wish to be caved with a ዘነዘና in my head🚶🏾
5 693
በአህያ ሞት አዝኖ ጅብ ለቅሶ ቢቀመጥ
ለማመቻቸት ነው ሲመሽ ለመለወጥ
በግ ጠፋብኝ አትበል ለቀበሮ መንጋ
ይልቅ ለአምላክ ንገር ወርዷል ለፍለጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 693
እንቅልፍ ያጡ ዓይኖቼ ማረፍን የፈሩ
በሀሳብ ነበልባል በቅዠት ያደሩ
በመስታወት መስኮት ሳያቸው ሲነጋ
እጅግ አሳዘኑኝ ለከፈሉት ዋጋ!!!
እረፍት ነፍጊያቸው በሽህ ሀሳብ ስሌት
በማይጠቅም እህ በማይነጋው እውነት
አሳርን እያዩ ማረፍ ሲናፍቁ
ደፍርሰው ያዩኛል አድረው ሲጨነቁ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 693
ተመስገን ማለት ነው ዛሬ ያደረሰን
ስንቱን ክፉ ዓመታት ሰላም ያሻገረን
በማመስገን ትግስት ሆዳችን ባይሰፋ
ያሳለፍነው ፍዳ ከዚህም በከፋ!!!
ይመስገን ፈጣሪ ብዙ ዓመት አልፈናል
የጊዜውስ መክፋት ቀን በቀን ይጥላል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
5 693
#ምንድን_ነው_ሰውነት?
የሰው ሚዛን ወርዶ
ቁስ አካል ተወዶ
ፍቅርም ተሰዶ
ጥላቻ ተለምዶ
አንድነት ተንዶ
ሰላም ጥሎን ሄዶ
ሰው እየተናቀ
ቁስ ከተደነቀ
ምንድን ነው ሰውነት? የክብር መስፈሪያው
ሁሉም ተነጣጥሎ ጥላቻ እየመራው !!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 693
ፈገግ በል ጥርሴ
ተቆጠብ ምላሴ
ቅን አስቢ ነፍሴ
ጠላት ሆኜ እንዳልቀር እራሴው ለራሴ
ከአምላክ አታጣላኝ ሰከን በል ከርሴ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 693
በጣም የሚከብደው ነገር መርሳት ነው። ሰው መውደድ...ከዛ ማጣት...የማጣት ፍራቻ...የእድሜ ልክ ህመም...የተሰበረ ጓደኝነት...
ይሰበር ይሆን...ተሰብሮስ ይቀር ይሆን...በዛ መሀል እኔስ እሰበር ይሆን...ትዝታው ቆራርጦ ይጥለኝ ይሆን....?
አሁንም የተለየ ነገር የለም..ያን ድምፅ ጥበቃ ላይ ነኝ...
✍Shewit dorka
Join for more👉 https://t.me/shewitdorka
