ግጥም
Відкрити в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Показати більше5 341
Підписники
+824 години
+687 днів
+18230 днів
Архів дописів
5 341
ስለ fintopio የተወሰነ ማብራሪያ እና እንዴት መስራት እንችላለን የሚለውን ያላያችሁ ልጆች በዚህ ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ
እንዲሁም በአሁኑ ዙር የወርሀዊ ውድድር አራት ኢትዮጵያዊ ከ 1-50 ውስጥ መመልከት ችያለሁ በርቱ በዚህ ዙር ሁሉም ተፎካክሮ ማሸነፍ አለበት
እንዲሁም fintoopio ባለንበት ደረጃ token እየሰጠ ነው እና check አድርጉ
ለመጀመር 👉 https://fintop.io/77iZhSV
5 341
ስለ fintopio የተወሰነ ማብራሪያ እና እንዴት መስራት እንችላለን የሚለውን ያላያችሁ ልጆች በዚህ ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ
እንዲሁም በአሁኑ ዙር የወርሀዊ ውድድር አራት ኢትዮጵያዊ ከ 1-50 ውስጥ መመልከት ችያለሁ በርቱ በዚህ ዙር ሁሉም ተፎካክሮ ማሸነፍ አለበት
እንዲሁም fintoopio ባለንበት ደረጃ token እየሰጠ ነው እና check አድርጉ
ለመጀመር 👉 https://fintop.io/77iZhSV
5 341
ግዜ አንደበት ኖሮት ብሶቱን ቢናገር
ተበዳይ በሰው ልጅ እኔ ነኝ ይል ነበር
እራሳቸው ከፍተው ዘመን ለሚከሱ
ሰው ነው ተጠያቂ ነበር ግዜ መልሱ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
#ምኑንስ_ተኖረ
እንቅልፍ አልባ ሌሊት
ትርጉም የለሽ ህይወት
መግፋት ቢሰለቸኝ ዋ! አልኩ ለራሴ
ግራ ብትጋባ ብትጨነቅ ነፍሴ
ድሃ እንቅልፍ አግኝቶ ህልምን ካላለመ
ህይወት ትርጉም አጥታ ቀኑ ከጨለመ
ምኑንሰ ተኖረ ተመስገን ተብሎ
ነገን ለመናፈቅ የዛሬን አቅልሎ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
የዲጂታሉ ዓለም ልብን ተቆጣጥሮ
መነጋገር ቀረ ሰው ከሰው ጋራ አብሮ
ህሊናችን ዛሬ መርጦ ብቼኝነት
ማንም ከማን አይደል ቢኖርም አንድ ቤት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
#ተፈጥሮም_ያኮርፋል
በእኔና አንቺ ፍቅር ሲታጀብ የኖረው
ድንገት ብንቀርበት ጭር አለ ጎዳናው
አብረን ያረፍንበት ተቃቅፈን ያን ግዜ
ልማዱን ነፍገነው ውጦታል ትካዜ
የእኛ መኮራረፍ እንኳን ለኛ ቀርቶ
መርዶ ሆኖበታል ጎዳናው ተከፍቶ
በኔና አንቺ ኩርፊያ ተፈጥሮም ያኮርፋል
ከሰው በላይ አውቆን ከልቡ ለምዶናል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
#ወፊቷን_በሆንኩኝ!!
በራሴ ችሎታ ቤቴን በሳር ሰሪ
ሳልዘራ ሳላጭድ ቀለቤን ሰፋሪ
በእግዚአብሔር ቸርነት ሳልጨነቅ ነዋሪ
ወፊቷን በሆንኩኝ በሰማይ በራሪ!!!
ዶላር ሰማይ ነክቶ ብር መሬት ወድቆ
እያሉ ከመኖር በሁሉም ተጨንቆ
ምነው ወፍ በሆንኩኝ ከዛፍ ዛፍ በራሪ
ቀለብ የማይጨንቀኝ ቤቴን ብቻ ሰሪ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
ዛሬ በሰው ችግር በግፍ የምትስቁ
ቀን መጣሉ አይቀርም ይህነን እወቁ
ሞልቶልኛል ብሎ በጎደለው መሳቅ
አወይ ነገን መርሳት ወየው አለማወቅ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
#እኛም_የእኛ_አይደለን!
እንኳንስ ሀገሩ እንኳንስ መሬቱ፤
እኛም የእኛ አይደለን ይኸ ነው አውነቱ።
ቀኑም ድንገት ከድቶ በሞት የሚተካ፤
ገንዘብና ስልጣን ህይወት ላያረካ፤
ለዚህች ከንቱ ምድር ለወረተኛ ዓለም፤
የእኛ ያልነው ሁሉ መቼም የእኛ አይደለም።
በድንገት ለምታልፍ ለኮንትራት ህይወት፤
አፈር ለሚበላው ለከንቱ ሰውነት!።
እንኳን ቁሳቁሱ ተራ ገንዘብ ቀርቶ፤
እኛም የእኛ አይደለን መኖር ነው ተስማምቶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
ሀዘኔ ሀዘናቸው ሳቄ ነው ሳቃቸው
ለሚወዱኝ ሰዎች ጥርሴ ሸልማቸው
ለሚጠሉን ሰዎች ባይሰጥም ደስታ
ለሚወዱን ሁሉ ምግብ ነው ፈገግታ
ፈገግ በል ጥርሴ ለሌሎች ስጥ ቦታ
ውስጣዊ ሀዘኔን በመታገል እርታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
#ጠርጥሪ
አንበሳና ነብር በጋራ እየሳቁ
ውበትሽን አጉልተው እያደናነቁ
ወደ አንቺ ሲመጡ ባልነበር ፈገግታ
ባልተለመደ መልክ የወዳጅ ሰላምታ
ያኔ ያንቺ ነገር አክትሟል መኖርሽ
ተማክረዋልና ቀድሞውን ሊበሉሽ።
ስለዚህ ጠርጥሪ
በልማድሽ ፍሪ
ተፈጥሮ ነውና መቀየር ላትችይ
አደነቁኝ እያልሽ ፊን ፊን አትበይ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
ነፍሴ ለስጋዬ ባክሽ አታሽቃብጪ
ነገ አፈር ነው እርሱ አንቺ ስትቀጪ
ይልቅ እንቢ በይው በጸሎት ይረታ
እዳው ላንቺ እንዳይተርፍ የማታ የማታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
#አፋልጉኝ?!
ጉድለቴን ሳይቆጥር ድክመቱን ሳልቆጥር፤
ጓደኛ የሚሆን በሰውነት ክብር፤
ሳጠፋ ሚየመክረኝ ሲያጠፋ የምመክረው፤
በጎን የማያማኝ ከጀርባ የማላማው፤
አፋልጉኝ ጓደኛ መስተዋት የሆነ፤
በግልጽ ንግግር አምኖ የዘመነ፤
ግዜ አይቶ የማይጥል ሀብት አይቶ ማይከዳ፤
ውስጡን የምረዳው ውስጤን የሚረዳ፤
አፋልጉኝ ጓደኛ ከወረት የራቀ፤
ሰው መሆን የገባው ሰውነት ያወቀ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
DOGS
Finally
የመጨረሻ ቀን $DOGS Earn ለማድረግ = August 14
Aug 14 ላይ ስለ Listing መረጃ ይለቀቃል!
$DOGS፣ OKX ላይ Premarket ተጀምሯል!
Task ስሩ፣ ሰው Invite አድርጉ፣ Stay Updated
ለመጀመር፡
https://t.me/dogshouse_bot/join?startapp=AeiKTXdIQKmMbGDdO3C3dg
5 341
DOGS
Finally
የመጨረሻ ቀን $DOGS Earn ለማድረግ = August 14
Aug 14 ላይ ስለ Listing መረጃ ይለቀቃል!
$DOGS፣ OKX ላይ Premarket ተጀምሯል!
Task ስሩ፣ ሰው Invite አድርጉ፣ Stay Updated
ለመጀመር፡
https://t.me/dogshouse_bot/join?startapp=AeiKTXdIQKmMbGDdO3C3dg
5 341
ለሆዱ ሲንጫጫ ኮሚቴ በሞላ
ወርቁን አመጣልሽ ያ ታምራት ቶላ❤
ሀገር ለማሳነስ ዘወትር ለሚተጉ
ሀገሩን ለሚወድ ወርቅ ነው ማዕረጉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 341
#ልቤን_መልስልኝ!
ቀንና ሌሊቱ ጊዜም ተሻጋሪ
ትዝታህ ብቻ ነው ከኔ ጎጆ ነዋሪ
ሀምሌና ነሐሴ ይጥላል አብዝቶ
ሰውም ድንገት ያልፋል ትዝታን ተክቶ
አንተስ ካለህበት እንዴት ነው ትዝታ
ከኔ ቤት በርትቷል ጠዋት ሆነ ማታ
ጊዜን እንደዘበት የሗሊት መልሶ
አንተን ያገዝፍሐል እኔን አኮስሶ
በልቼ እንዳልበላሁ
ጠጥቼ እንዳልጠጣሁ
ዛሬም በመራቅህ አለሁ እንደከሳሁ
አመታት አልፈውም አንተን አስባለሁ
ስራመድ ብቻዬን ስተክዝ ለራሴ
በትዝታ ማእበል ስትሰቃይ ነፍሴ
እስቲ ልጠይቅህ ስላንተ ሁኔታ
እኔ አልሰነብትም ሟች ነኝ በትዝታ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
