ግጥም
Відкрити в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Показати більше4 823
Підписники
+324 години
+557 днів
+23030 день
Архів дописів
4 827
በጣም የሚከብደው ነገር መርሳት ነው። ሰው መውደድ...ከዛ ማጣት...የማጣት ፍራቻ...የእድሜ ልክ ህመም...የተሰበረ ጓደኝነት...
ይሰበር ይሆን...ተሰብሮስ ይቀር ይሆን...በዛ መሀል እኔስ እሰበር ይሆን...ትዝታው ቆራርጦ ይጥለኝ ይሆን....?
አሁንም የተለየ ነገር የለም..ያን ድምፅ ጥበቃ ላይ ነኝ...
✍Shewit dorka
Join for more👉 https://t.me/shewitdorka
4 827
#ዛሬም_በመጠበቅ
ይመጣል እያልኩኝ የተሻለ ግዜ
ዛሬን አልፈዋል በተስፋ ትካዜ
በሁለት ስሜት ስልት በቀነ ቀጠሮ
ተስፋና ትካዜ አብሮ ተደምሮ
እየወዘወዘኝ አዲስ ቀን ፍለጋ
አለሁ በክርስቶስ በተመስገን ጸጋ።
ይመጣል ያልኩት ቀን መምጫው እየራቀ
እድሜም እንደዋዛ ፈጥኖ እየዘለቀ
በማመስገን ዜማ በስጋት ቅልቅል
በተስፋ ትካዜ እያነሳሁ ስጥል
ዛሬም በመጠበቅ የተሻለን ዘመን
የለሁም አልልም ይኸው ዛሬም አለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
4 827
የጊዜውን ክፋት በጥርስ እየሸኙ
የህይወትን ዜማ በእውነት እየቃኙ
አንጀት እያረረ ይለፍ በፈገግታ
እስኪገለጥ ድረስ የፈጣሪ እውነታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
በመረረ ሀዘን ልባችን ተሰብሮ
ኑ " ሳቁ ይሉናል የጉድ ነው ዘንድሮ
እንኳንስ ለመሳቅ ከትከት ለማለት
ፈገግታም ታምር ነው አሁን ባለው ስሜት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#የጭዋ_ዝምታ
አድማጭ ከሌለበት ከብዙ ጫጫታ
እጅጉን ያስፈራል የአንድ ሰው ዝምታ
ቃላትን ሰድሮ ብዙ ከሚያወራ
በስሜት ጋጋታ ስሙ ከሚጠራ
የጨዋ ዝምታ ቅኔ አለው አብዝቶ
ይፈሳል ማስተዋል ከልቡ ውስጥ ሞልቶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
Repost from ከእለታት....📖📚📖📚📖📚
አዎ ባሌን 12 ቦታ ቆራርጬዋለሁ።
ባሌን ከመግደሌ በላይ አስራ ሁለት ቦታ መቆራረጤ አጀብ አስብሏል....እነርሱ ምን ያውቃሉ እኔን ስንት ቦታ እንደቆራረጠኝ...እንደውም ደግ ነኝ...በሚወደው ቁጥር ልክ ነው የቆራረጥኩት....አንድ ሰው እንኳን አበጀሽ አላለኝም....ሰው ግን ገራሚ ፍጥረት ነው...
"እንደው ምን አረጋት ሚስኪን ሰላምተኛ....ሰው ቀና ብሎ አያይም እኮ..."....ይላሉ ለእርሱ ሲያደሉ....ታዲያ እርሱ እኮ ነው ችግሩ...ሰው ቀና ብሎ አለማየቱ....ይሄ እንኳን መቆራረጥ ሌላስ ነገር አያስደርገውም.....
አታስቡ ሙሉ ጤነኛ ነኝ....እንዲሁ ግን ጣት ገማ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም ከሚሉት ወገን አይደለሁም...ይቆረጣል....ባስ ሲልም ይቆራረጣል...ልክ እኔ እንዳደረግኩት....ሁሉም ሰው እንዲህ ቢያደርግ ስል እመክራለሁ....
ከአንገቱ አልጀመርኩም....እንዲያ ካደረግኩማ ምኑን ገደልኩት....
ከውብ ጣቶቹ ጀመርኩ....ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ ጮኸ....ደስ አለኝ....እንዲያም ሆኖ ከእኔ የዘመናት ጩኸት ጋር ሊቀራረብ ቀርቶ ጫፉም አልደረሰም..... ጣቶቹ የእኔን ፀጉር መዳበስ ካቆሙ ዘመን ተቆጥሯል...እና ምን ይሰራሉ...እንደውም ገላገልኳቸው....
"ምን አድርጌሽ ነው ይሄን ያሀል....አሁን ፍቺኝ እና እንነጋገር..."....ይላል በየጩኸቱ መሀል...
"የማይሆነውን....የምን መነጋገር...እሱ ድሮ ቀረ..."....ዘና ብዬ እንደ ቲያትረኛ እየተንጎራደድኩ እመልስለታለሁ....ይጮሀል..."የሰው ያለህ...እንደው ስለ ወንድ ልጅ አምላክ...."....ይማፀነኛል....በዚህም አልረካሁም... ጣቶቹ ተዘርዝረው ሳያቸው አንዳች የማላውቀው ነገር እስከ እግር ጥፍሬ ነዘረኝ...አንድ በአንድ በእግሬ ጨፈለቅኳቸው....አሁንም አልረካሁም....ቃሌን ስሜቴን ሴትነቴን የረገጠብኝን ሳስብ እያደረግኩት ያለውት ነገር ኢምንት ሆነብኝ....
ቀጠልኩ።
አልሰሙኝ ወዳሉኝ ጆሮዎቹ ተጠጋሁ...
"ለካ ጆሮም ነበረህ...."....አሽካካሁ....
"እባክሽ ማሬ ፍቺኝ አንዴ...እማ...."....ከቅድሙ ይበልጥ አሽካካሁ....ደስ አለኝ....ምላሱ መጨረሻ ላይ ነው መቆረጥ ያለበት አልኩ በሆዴ....
ጆሮውን ዘነጠልኩት...የቅድሙ ጩኸቱን ጮኸ...እኔም የቅድሙ ሳቄን ደገምኩት...ቦታ ተቀያየርን...ድሮ እኔ ነበርኩ የምጮኸው....
ጩኸቱ ይብስ ዘና እያደረገኝ መጣ....
ቀጠልኩ....ካቀፉኝ የሰነባበቱት እጆቹ ላይ አነጣጠርኩ......
የማይሰሩ እጆች ይቆረጡ ይባል የለ...እኔን ካላቀፉ ምንድን ነው ስራቸው....ምንም...ቆረጥኳቸው።
የመጨረሻውን ክፍል ለማግኘት👇
https://t.me/shewitdorka
✍Shewit dorka
4 827
Repost from Infinite happiness✨
*Puts cocaine in my lipgloss so when he kisses me, he thinks I'm god*
4 827
#ካልመጣሽ_ላይነቃ
በመቅረትሽ ዜማ በናፍቆት ቆዝሜ
ደህና ነኝ እያልኩኝ በፍቅርሽ ታምሜ
እጠብቅሻለሁ ከትዝታሽ ማዶ
ልቤ ከልብሽ ጋር አንድ ላይ ተዛምዶ።
ልብ አልባ እኔነቴ በደመነፍስ ቀርቶ
በድንዛዜ ስልት ብቻውን ሸፍቶ
ከሰው በመነጠል የእራሱ ዓለም ሰርቶ
ካልመጣሽ ላይነቃ ለእራሱ ቃል ገብቶ
ዛሬም ይጠብቃል ተስፋን ባለመቁረጥ
ከአስቀመጥሽው ቦታ ታምኖ በመቀመጥ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#ሁሉም_በጋራ_ነው
ቤተ ሰሪ በዝቶ ይላል ማገር ማገር
መቼ ሊኖርበት ጸንቶ ሳይቆም ሀገር
ይልቅስ ይቀድማል መሰረቱን ማጽናት
ሁሉም በጋራ ነው ለማአገሩ መትጋት ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
/// " አምላክ ጥበበኛ " ///
የሚታደል ቢሆን እድሜ በስም ጥሪ
ሁሉም ድሃ ሞቶ ሀብታም ነበር ነዋሪ
ስልጣኑ ቢገባ በቀበሌው መሪ
ልክ እንደ ዳቧችን ቢሆን በስም ጥሪ
የድሃ እድሜ ሁሉ ለሀብታም ተሽጦ
ከምድሩ በጠፋ እስካሁን ተመርጦ
አምላክ ጥበበኛ ሰውን ጥንት ሲሰራው
እንኳን የእድሜን ገደብ በእራሱ አደረገው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
አይነጋም አትበሉ ይነጋል በግዜው
ሁሌም በክርስቶስ ነገር ለበጎ ነው
በእርሱ የሚሆነው ለመልካም ነውና
ሲነጋም ሲመሽም መኖር በምስጋና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
