1 379
Підписники
-224 години
+77 днів
+730 днів
Завантажуємо дані
Схожі канали
Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
жовтень '26жовт '26
жовтень '26
+186
в 1 каналах
вересень '260
в 0 каналах
Get PRO
серпень '260
в 0 каналах
Get PRO
липень '260
в 2 каналах
Get PRO
червень '260
в 4 каналах
Get PRO
травень '260
в 0 каналах
Get PRO
квітень '260
в 1 каналах
Get PRO
березень '260
в 0 каналах
Get PRO
лютий '260
в 0 каналах
Get PRO
січень '260
в 1 каналах
Get PRO
грудень '250
в 0 каналах
Get PRO
листопад '250
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '250
в 1 каналах
Get PRO
вересень '250
в 0 каналах
Get PRO
серпень '25
+23
в 0 каналах
Get PRO
липень '25
+24
в 0 каналах
Get PRO
червень '25
+25
в 0 каналах
Get PRO
травень '25
+47
в 2 каналах
Get PRO
квітень '25
+57
в 4 каналах
Get PRO
березень '25
+26
в 3 каналах
Get PRO
лютий '25
+39
в 2 каналах
Get PRO
січень '25
+71
в 3 каналах
Get PRO
грудень '24
+111
в 4 каналах
Get PRO
листопад '24
+135
в 4 каналах
Get PRO
жовтень '24
+185
в 5 каналах
Get PRO
вересень '24
+126
в 6 каналах
Get PRO
серпень '24
+78
в 3 каналах
Get PRO
липень '24
+92
в 5 каналах
Get PRO
червень '24
+129
в 5 каналах
Get PRO
травень '24
+528
в 9 каналах
Get PRO
квітень '240
в 11 каналах
Get PRO
березень '240
в 4 каналах
Get PRO
лютий '24
+5
в 2 каналах
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 20 жовтня | 0 | |||
| 19 жовтня | +1 | |||
| 18 жовтня | +2 | |||
| 17 жовтня | +3 | |||
| 16 жовтня | +1 | |||
| 15 жовтня | +1 | |||
| 14 жовтня | +1 | |||
| 13 жовтня | +3 |
Дописи каналу
| 2 | በአዲሱ አዋጅ የተካተቱት 5ቱ የግዥ ዘዴዎች እና አዳዲስ ስልቶች በዝርዝር!
በአዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቀደም ሲል 6 የነበሩት የግዥ ዘዴዎች ወደ 5 ዋና ዋና ዘዴዎች ተጠቃልለዋል። በተጨማሪም የግዥ አፈጻጸምን ፈጣን፣ ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ የሚያደርጉ አዳዲስ የግዥ ስልቶች (Procurement Strategies) ተካተዋል። ዝርዝሩን እንመልከት፦
1. አምስቱ (5) የተሻሻሉ የግዥ ዘዴዎች (Procurement Methods)
ግልፅ ጨረታ (Open Tendering):
የመንግሥት መስሪያ ቤቶች መከተል ያለባቸው ዋና እና መደበኛ የግዥ ዘዴ ነው። ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟላ ተወዳዳሪ እንዲሳተፍ በማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግበትና ከፍተኛ ውድድር የሚፈጥር አሰራር ነው።
በማጣሪያ የሚከናወን ጨረታ (Two-Stage/Restricted Tendering):
ግዥው ውስብስብ ሲሆን ወይም ዝርዝር ፍላጎቶችን (Technical Specifications) አስቀድሞ በግልጽ ማስቀመጥ በማይቻልበት ጊዜ በሁለት ደረጃ የሚከናወን ዘዴ ነው።
ይህ ዘዴ 3 አሰራሮችን ያጠቃልላል፦
ሁለት ደረጃ ጨረታ (Two-Stage Tendering)፦ በመጀመሪያው ደረጃ የቴክኒክ ሀሳብ ብቻ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፤ በሁለተኛው ደረጃ የተስተካከለው የቴክኒክና የዋጋ ማቅረቢያ ይቀርባል።
የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ (Pre-qualification)፦ ውስብስብ ለሆኑ ግዥዎች ብቃት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች አስቀድሞ ለማጣራት የሚያገለግል ነው።
የፍላጎት መጠየቂያ (Expression of Interest - EOI)፦ በተለይ ለምክር አገልግሎት (Consultancy) ግዥዎች አቅም ያላቸውን አማካሪዎች ለመጋበዝ ያገለግላል።
ውስን ጨረታ (Restricted Tendering):
ዕቃው ወይም አገልግሎቱ ከተወሰኑ የተወሰኑ ድርጅቶች/አቅራቢዎች ብቻ የሚገኝ ሲሆን፣ ወይም በግልጽ ጨረታ ለመሄድ የሚያስፈልገው ጊዜና ወጪ ከግዥው አጠቃላይ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር ተመጣጣኝ ባልሆነበት ጊዜ (በተቀመጠው የገንዘብ ጣራ መሠረት) በጥቂት አቅራቢዎች መካከል የሚደረግ ውድድር ነው።
በዋጋ ማቅረቢያ የሚፈጸም ግዥ (Request for Quotation / Proforma):
አነስተኛ የገንዘብ መጠን ያላቸውን እና በገበያ ላይ በቀላሉ የሚገኙ መደበኛ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን በፍጥነት ለመግዛት የሚያገለግል ነው።
አዲስ ለውጥ፦ በቀድሞው አሰራር በእቅድ ያልተያዙ ግዥዎች ይፈጸሙበት የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ አዋጅ ግን ይህ ግዥ ግዴታ በበጀት ዓመቱ የግዥ እቅድ ውስጥ መካተት አለበት።
በቀጥታ የሚፈፀም ግዥ (Direct Procurement):
ያለ ውድድር ከአንድ አቅራቢ/ድርጅት ብቻ ግዥ የሚፈጸምበት ልዩ ሁኔታ ነው።
የሚፈቀድባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፦
ዕቃው ወይም አገልግሎቱ ከአንድ አቅራቢ ብቻ የሚገኝ ሲሆን፤
ግዥው በጣም አስቸኳይ ከመሆኑ የተነሳ ወዲያውኑ ካልተፈጸመ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት የሚያስከትል ሲሆን፤
የመንግሥት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ወጪያቸውን በመሸፈን ከሌላ የመንግሥት ባለበጀት መስሪያ ቤት ግዥ መፈጸም ሲያስፈልጋቸው።
2. አዳዲስ እና ዘመናዊ የግዥ ስልቶች (Procurement Strategies)
እንደ ግዥው ባህሪ፣ መጠን እና ውስብስብነት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚከተሉትን አዳዲስ ስልቶች መጠቀም ይችላሉ፦
ስትራቴጂያዊ ግዥ (Strategic Procurement)፦ ለከተማው ከፍተኛ ባጀት እና ስትራቴጂያዊ ፋይዳ ያላቸውን ግዥዎች የገበያ ሁኔታን በማናትናትና የረጅም ጊዜ ጥቅም በማስገኘት መንገድ መፈጸም።
በማዕቀፍ የሚፈፀም ግዥ (Framework Agreement)፦ ተደጋጋሚ ፍላጎት ያላቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በጋራ የረጅም ጊዜ ውል በመያዝ በፈለጉት ጊዜ እየታዘዘ የሚቀርብበት አሰራር።
የጋራ ግዥ (Consolidated/Joint Procurement)፦ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተመሳሳይ የግዥ ፍላጎታቸውን በማስተባበር በጋራ በትልቅ መጠን በመግዛት ወጪን የሚቆጥቡበት ስልት።
በሊዝ ስምምነት የሚፈፀም ግዥ (Leasing)፦ ውድ የሆኑ መሣሪያዎችንና ማሽነሪዎችን ከመግዛት ይልቅ በሊዝ/በኪራይ ውል መጠቀም የሚያስችል አሰራር።
በራስ ሀይል የሚፈፀሙ ስራዎች (Direct Force Account)፦ መስሪያ ቤቶች የራሳቸውን የሰው ኃይል እና መሳሪያዎች በመጠቀም ሥራዎችን የሚያከናውኑበት ስልት።
ተርን ኪ (Turnkey Contracts)፦ አንድን ፕሮጀክት ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ግንባታና ሥራ ማስጀመር ድረስ ሙሉ በሙሉ ለአንድ ተቋራጭ መስጠት።
የኤሌክትሮኒክ ልውጥ ሀራጅ ጨረታ (Reverse Auction)፦ በተዘረጋው የ e-Procurement ስርዓት ተጫራቾች በየስክሪናቸው የቀጥታ የዋጋ ቅናሽ እያደረጉ የሚወዳደሩበት ዘመናዊ የጨረታ ዘዴ። | 223 |
| 3 | አሉታዊ ሀሳቦች በህይወታችሁ ያላቸው ተፅዕኖ
✍️ 1ኛ Over Generalization ይባላል።
አንድ ሀገር ሄድኩና አንድ ናይጄሪያዊ አግኝቼው ጉዳት አደረሰብኝ እንበል። ያ ግለሰብ ያደረሰብኝን ጉዳት ከእርሱ ጋር በቀጥታ ከማገናኘት ይልቅ የናይጄሪያ ሰዎች እኮ ክፉዎች ናቸው፤ መጥፎዎች ናቸው! ብዬ እጠቀልላለሁ። ይህም የተሳሳተ መረዳት የአሉታዊ አስተሳሰብ አንዱ አካል ነው።
✍️2ኛ Polarization ይባላል።
ለምሳሌ ፦ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደርን በተመለከተ አንዳንዶች ፈጽመው ሙሉ በሙሉ ሲቃወሙት ሌሎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይደግፉታል። የሚቃወሙት ይህ አስተዳደር አንድም በጎ ነገር አያደርግም ሲሉ፣ የሚደግፉት ደግሞ ይህ አስተዳደር አንድም ጥፋት አያጠፋም፣ ፍጹም ነው ይላሉ። ይህ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ ነው Polarization የሚባለው።
✍️3ኛ Mental Filtering ይባላል።
እኔ በአንድ አዳራሽ ውስጥ 2000 ሰዎች በተሰበሰቡበት ስልጠና ሰጠሁ እንበል። እያስተማርኩ እያለ አንድ ሰው ብድግ ብሎ አዳራሹን ጥሎ ወጣ። ማታ ቤቴ ስገባ የማስበው ሰለተማሩት እና ስለተደሰቱት 1999 ሰዎች ሳይሆን ጥሎ ስለወጣው አንድ ሰው ይሆናል። ይህ Mental Filtering ይባላል፡፡
✍️4ኛ Discounting the Positive ይባላል።
በዚህ መገለጫ ማንኛውም እኛ ያለንን ጥሩ ነገር እናጣጥለዋለን። ለምሳሌ አንድ ሰው አንዲት ሴትን “ቆንጆ ነሽ" ካላት መልሷ "ምን ዋጋ አለው ቁንጅና? ታጥቦ አይጠጣ!" ትለዋለች። ጥሩ ተምረሃል" ከተባለ ሌላው ሰው “ምን ዋጋ አለው ብለህ ነው ትምህርት! ገንዘቡ ያለው እንደሆነ ያልተማሩት ጋር ነው" ይላል። የሚነገራቸውን ጥሩ አስተያየት ሁሉ ያጣጥሉታል፤ አይቀበሉትም ይህም Discounting the Positive ይባላል።
✍️5ኛ Jumping to Conclusion ይባላል።
አንድ ሰራተኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋል። ንግግሩን ከጨረሰ በኃላ አንድ ክፍል ሀላፊ የእርሱን ንግግር የሚቃወም የሚመስል ነገር ተናገረ እንበል። በሌላ ቀንም ባጋጣሚ ይህ ሰራተኛ ከተናገረ በኃላ ያው የቢሮ ሀላፊ የሰራተኛውን ሀሳብ የሚቃወም ሀሳብ ተናገረ። በዚህ ጊዜ ሰራተኛው ይሄ ሰውዬ በጣም ይጠላኛል ብሎ እርግጠኛ ይሆናል። ይህም Jumping to Conclusion ይባላል።
✍️6ኛ Magnification ነው።
ይህ ደግሞ ችግሮችን ከመጠን በላይ አጉልተን እንድናይ የሚያደርግ ነው፡፡ ቤት ውስጥ የምትሰራ ስራተኛ ስሀን ስታጥብ ከእጇ አምልጦ ተስበረባት እንበል፡፡ እመቤቲቱ መጥታ ለምን ስበርሽው? ትላታለች። ትቀጥልና እስከመቼ ነው እቃ እየሰበርሽ ምትኖሪው? ትላለች። አሁንም ትቀጥልና እኔ ገንዘብ ከየት የማመጣ ይመስልሻል? ወይስ አውቀሽ ነው ምትሰብሪው? ሰሀኑ መሰበሩ እውነት ነው እመቤቲቱ ግን በጣም ከመጠን አብልጣ ታጎላዋለች። ይህም Magnification ነው።
✍️7ኛ Emotional Reasoning ይባላል።
ይህም በስሜት ሆኖ መወሰን ነው። አንድ አለቃ በጣም ሚጠቅመውን ሰራተኛ በድንገት ተነስቶ ያባርረዋል፡፡ ይህ ግን የተሳሳተ ውሳኔ ነው! ያንን ሰራተኛ መልሼ ላግኝህ ቢለው እንኳን ያስቸግረው ይሆናል። ውሳኔውን በስሜት ነው የወሰነው። አስቦበት አይደለም የወሰነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ አንዲት ሚስት በባሏ ተበሳጨች እንበል፡፡ ድንገት ተነስታ ቀለበቷን አውልቃ ወርውራ፣ ሻንጣዋን ሽክፋ፣ በጣም መጥፎ ነገር ባለቤቷን ተናግራ ከቤት ትወጣለች፡፡ ይህም ትዳራቸውን ያናጋዋል ወይንም ያፈርሰዋል። ይህ ነው Emotional Reasoning የሚባለው። | 269 |
| 4 | ✍️✍️ይከበር #መምህሩ#✍️✍️
የሙያዎች ቁንጮ የከፍታው ማማ፣
መስጠት የማይሰለች የጥበብ አውድማ።
የሃገራችን ልማት የእድገት መሠረቱ፣
የሃብት ብልፅግና መነሻ ውጤቱ ፣
የስልጣኔ ምንጭ የዕውቀት ፍንጭነቱ።
አንተ ቅኑ መምህር ስራህን አክባሪ ፣
ስንቱን አደረከው ጥበብን ቀማሪ ፣
በቢሮ ቢሰራ ቢሆን ሃገር መሪ ፣
ገጠር ካለው መ/ር ነበረ ተማሪ።
ቤት ቀያሽ መሃንዲስ ተብሎም እንጂነሩ፣
ሠው ፈዋሽ ሃኪሙ የሆነው ዶክተሩ ፣
በስልጣን ማማ ላይ ህዝብን የምትመሩ፣
መቼ ?? ይገኝ ነበር መምህሩ ባይኖሩ ፣
እናም ወገኖቼ ዋናው ቁም ነገሩ ፣
የዚህ ሁሉ ምንጩ ይከበር መምህሩ::
!!
✏️ Written by Teacher Abebaw Dereje
✍️ 2019 E.C
| 254 |
| 5 | 3. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወጣውን መስፈርት መሰረት በማድረግ በከተማው ውስጥ የሚገኙት ትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
4. የመምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን የአቅም ግንባታ ሥራ ያከናውናል፤
5. በከተማው ውስጥ ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ያስፈጽማል፤ በከተማው ውስጥ በሚገኙ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘጋጅተው የሚወጡ ፈተናዎችንና የምስክር ወረቀቶችን ሕጋዊነት ያረጋግጣል፤
6. ከተማ አቀፍ የሆኑ ፈተናዎችን ያዘጋጃል፤ ያስፈጽማል፤
7. በመገናኛ ዘዴዎች የተደገፉ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲሰጡ ያደርጋል፤ መደበኛና ኢ-መደበኛ የትምህርት ፕሮግራሞች የሚስፋፉበትን ሁኔታ ይቀይሳል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
8. ለሴቶች፣ ለህጻናት፣ ለጎልማሶችና ልዩ የትምህርት ፍላጎት ላላቸው ዜጎች ለሚሰጡ የትምህርት አገልግሎቶች ልዩ ድጋፍ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
9. በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚወጣው የብቃት መመዘኛዎች መሰረት መምህራንና ሌሎች የትምህርት ባለሙያዎችን ያሰለጥናል፤ እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፤ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
10. ትምህርት ቤቶችን ማቋቋምና ማስፋፋት ለሚፈልጉ አካላት የመረጃ አገልግሎትና ድጋፍ ይሰጣል፤
11. በከተማው ውስጥ በሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት በበላይነት ይመራል፤ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
12. የተማሪዎች ምግብ፣ የመማሪያ ቁሳቁስ እና የትምህርት መርጃ መሳሪያ ድጋፍ ማከናወን የሚያስችል ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር ይዘረጋል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤ አፈጻጸሙንም ይቆጣጠራል፤
13. በመንግሥት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ፣ የትምህርት መርጃ መማሪያ፣ የደንብ ልብስ እና ሌሎችን የንጽህና መጠበቂያ ያሰራጫል፤
14. በመንግሥት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ፣ መካከለኛ ደረጃ እና እንደአስፈላጊነቱ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ ተማሪዎች የምግብ አገልግሎት ይሰጣል፤
15. በተማሪዎች ምግብ፣ መማሪያ ቁሳቁስ፣ በትምህርት መርጃ መሳሪያ እና በተማሪ የደንብ ልብስ ድጋፍ በሚመለከት ከከተማ ነዋሪዎች፣ ከመንግስታዊ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር በቅንጅትና በቅንጅት ይሰራል፤
16. የተማሪዎች ምግብ ፕሮግራሙን ከሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም ጋር በማቀናጀት እንዲፈጸም ያደርጋል፤
17. የተማሪዎች ምግብ ፕሮግራም በተጠቃሚዎች ጤንነት፣ ንጽህና ጥበቃና የሥርዓተ ምግብ መሻሻል ላይ ያተኮረ መሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያረጋግጣል፤
18. ለአጠቃላይ የትምህርት ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ከሚመለከተው አካል የምስክር ወረቀቱ መሰረዙን የሰረዛ ውሳኔ ሲደርሰው ወዲያውኑ መዝገቡን ያስተካክላል፤
19. በሕገ ወጥ መንገድ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያገኘ የትምህርትና ስልጠና ተቋም ላይ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ ይሰርዛል፤ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ እንዲጠየቅ ሥልጣን ላለው አካል ያሳውቃል፤
20. አጠቃላይ የትምህርት ተቋማትን መረጃ ያደራጃል፤ ያሰራጫል፤
21. የአጠቃላይ የትምህርት ተቋማት ብቃት እና ምዘና መከታተያና መገምገሚያ ሥርዓት ዘርፎች ተግባራዊ ያደርጋል፤
22. ለአጠቃላይ ትምህርት ተቋም ዕውቅና ይሰጣል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc | 564 |
| 6 | በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 94/2019 መሰረት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተሰጡ 22 ስልጣንና ተግባራት፡፡
(መስከረም 28/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት እና በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ሙሉ ለሙሉ ሥራ ላይ በማዋል የከተማዋን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይበልጥ እንዲፋጠን ለማድረግ የአስፈጻሚ አካላቱን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ወስናል፡፡
የከተማ አስተዳደሩን ተወዳዳሪ፣ ብቁና ነፃ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ለመገንባት እና አስፈጻሚ አካላቱ ከፌዴራል ጋር በተቀናጀ እና በከተማ ደረጃ ከሚገኙ ተቋማት ጋር ያላቸው የጎንዮሽ ተናባቢነት ይበልጥ የተጠናከረ እንዲሆን ለማድረግ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ (1) ተራ ፊደል (ሀ) መሠረት አዲስ አዋጅ ያወጣ ሲሆን በዚህ መሰረትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስልጣንና ተግባራት እንደሚከተለው በአዲሱ አዋጁ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
1. የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንዲቻል ትምህርት ቤቶችን ያስፋፋል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እንዲገነቡ እና መሰረተ ልማታቸው በአግባቡ እንዲሟላ ያደርጋል፤
2. የሀገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ደረጃ በመጠበቅ የከተማውን አስተዳደር ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤ መደበኛ ያልሆኑ፣ ቅድመ መደበኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ሥርዓተ ትምህርት ያዘጋጃል፤ መጻሕፍት ያሳትማል፤ የትምህርት ግብዓት መሟላታቸውን ያረጋግጣል፤ | 398 |
| 7 | Немає тексту... | 253 |
| 8 | ተጨማሪ ሹመቶሽ ተሰጡ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የተለያዩ ተጨማሪ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
1) አቶ አደም ፋራህ በም/ጠ/ሚ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ
2) አምባሳደር በትረ መንግስቱ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3) ወ/ሮ እናትአለም መለሰ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር
4) አቶ ፍቃዱ ተሰማ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም | 289 |
| 9 | የሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህ/ ተ/ም/ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አቶ አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር
5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር
6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር
8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር
20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም | 1 118 |
| 10 | በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የተሰየሙት የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት በይፋ ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
#የመደመርመንግሥት | 281 |
| 11 | Немає тексту... | 295 |
| 12 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ሱልጣን ወሌ (ዶ/ር ኢንጂነር) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 192 |
| 13 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አክሊሉ ታደሰን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
*****
(ዶ/ር) አክሊሉ ታደሰ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቅርበዋል።
#የመደመርመንግሥት | 189 |
| 14 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ኢንጂነር ሙሐመድ አብዱራህማን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 157 |
| 15 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 209 |
| 16 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 186 |
| 17 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 183 |
| 18 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ የማዕድን ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 186 |
| 19 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አቶ ሳዳት ነሻ የሎጂስቲክስ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 179 |
| 20 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አቶ በረከት ፍስሐፅዮን የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቀረቡ
#የመደመርመንግሥት | 190 |
