𝔸𝕣𝕤𝕦 𝕡𝕚𝕔ᵗᵐ🏞🏜🏙🌁
Відкрити в Telegram
Arsu pic ❤️ Ezi chanale lay des yemil profile pictures😘 , yefekr tksoch ❤️, endihum zefenoch 🎶 yelekekalu join bemalet yekelakelun
Показати більше728
Підписники
-124 години
-27 днів
+430 днів
Архів дописів
~ ተሳስተሻል ~
"ሳሮን እባክሽን እንዴ ላውራሽ
ሳሮን እባክሽ ቁሚ አንቺ ሳሮን"
"የው ቆምኩኝ ምን ነበር"
"ተጠፋፋን"
" አው ዓመታት ሞላው መጠፋፋት ሳይሆን መረሳሳት ነው"
"እረሳሽኝ ? እኔ ግን አልረሳሁሽም"
"በስታውስህም ጥቅም የለውም እና ለምን አስቆምከኝ"
"ስጠራሽ ለምንድን ባልሰማ ምትሄጂው ለዓመታት በዚህ መንገድ ሸሽተሽኛል አንድ ቀን እንኳን ስልኬን አትመልሺም ቴክስቴቹን እንኳን አላየሽም"
"ልታለቃቅስብኝ ነው"
"ሳሮን ቆይ ምን አድርጌ?"
"እሱን እራስህን ስጠይቀው ይሻላል ምን አልባት ከኔ የተሻለ ስራህን ልብህ ያቀዋል"
"ንገሪኝ እና አልከተልሽ በቃ እንደረሳሽኝ እረሳሻለው እንዳልነበርሽ ንገሪኝ ልወቀው ድርጊትሽ እውነት ከሆነ እምላለሁ ራሴን ነው ማጠፋው"
"ስማኝ ያሬድ ባለቤቴ እየጠበቀኝ ነው መሄድ አለብኝ"
"እውነትም አገባሽ እንዴ"
"ታድያ በህይወቴ ስትጫወት እያየሁኝ ቆሜ ልቅር እ ቆሜ ልቅር እንዴ ባመንኩህ ባከበርኩህ ባፈቀርኩ በስተመጨረሻ ከማንም ጋር አሸሼ ገዳሜ ማለት ነው ለእኔ ሚገባው አታፍርም አገባሽ እንዴ? አው አግብቻለው ምን የመሰለ ባል ለኔ ስሊ የሚሞት እሺ ከንቱ"
"ቆይ አንዴ ማነው አሸሼ ገዳሜ ያለው ማነው ከአንቺ ውጪ ሌላ ሴት ቀና ብሎ ያየው ንገሪኝ"
"አጠገብህ ሆኜ እንኳን ስትዋሸኝ ትንሽ አታፍርም ትንሽ ገና ከሀኪም ቤት እንደዋጣሁኝ ሳላገግም እኮ ነው ሌላ ህመም የሆንከኝ እንዴት እንዴት ትዋሸኛለህ እምኜህ ነበር እኮ ቆይ እሷ ከኔ በምን ተስላ ነው "
"ሳሮን"
"ስሜን አትጥራው ድጋሚ ላወራህ መቆሜ እራሱ ትልቅ ስህተት ነው ምን አለ ብተወኝ አልበቃ አለችህ እ ወይስ አስጠላችህ አላሳዝንህም እንዴ ዕለት ተዕለት እኮ ተሳቅቄ ነው ከቤት የምወጣው እንዳላገኝህ እየፀለይኩ ናፍቆቴ ስለጠና መጥቼ እንዳላቅፍ እየሰጋሁኝ ነው እኮ ምኖረው ባሌን ልወደው እየጣርኩኝ ነው ግን አልቻልኩም ተወኝ እስቲ ሰባብረህኝ አንተ ነህ ምትታየኝ ጉድተህኝም አንተው ነህ ምትናፍቀኝ ሲከፋኝ ሳዝን ከቅፍህ መግባት ፈልግ ነበር ግን ያደረኩውን ሁሉ ደጋግሜ ለልቤ ብነግረውም አልጠላህም አንዴ እንኳን አልረገመህም ተወኝ ተወኝ እስቲ ልኑር አንዴ ልሳቅ"
"ሳሮን እኔ እኮ ወድጄው አይደለም ልንግርሽ አልችልም ለዛ ነው ይቅርታ በጣም"
"አመንክ አይደል ይህው አስመሳይ ነህ ቆይ ስለታመምኩኝ ትሞታለች ብለህ አሰብክ ቆይ ምን አስቸኮለህ መሞቴን ከፈለከው እኮ ትራስ ነበር ለምን ከሀኪም ቤት ሳሎጣ እዛው አትገለኝም ነበር እሱ ይቀል ነበር ይቅርታ አደርግልህ ነበር"
"ሳሮን ተረጂኝ "
"ያሬድ ተውኝ እንድረሳው ፍቀድልኝ ይህው እራት ዓመት ሙሉ በሰቀቀን አለው ተወው ቢነሳም ለውጥ ለሌለው ጉዳይ ልቤን አታድማው"
"ነይ አውን ነገርሻለሁ ግቢ ነይ ግቢ አትይኝ ግቢ"
"ያሬድ ምን እየሆንክ ነው አቁመው ባጃጂን "
"ሁሉንም ነገር አይደል ማወቅ ምትፈሊግው ቆይ ታገሺ ታቂዋለሽ"
....
"ያሬድ እሺ ተረጋጋ"
"ነይ ደርሰናል ልንገርሽ "
"የመቃብር ሰፈር እኮ ነው እዚህ ምን እናደርጋለን "
"ሳሮን ይህው የእናቴ መቃብር ልማልልሽ እኔ አፈቅርሻለሁ "
" ማይሆን ነገር አታውራ"
" አንቺ ታመሽ ለህክምናሽ ሚሆን ገንዘብ አየልጉኝ ነበር አክስቶሽን ስጠይቅ ፊት ነሱኝ ምን ላድርግ ታቃለሽ ድሮ ይህቺ ባጃጅ እንኳን የለችኝም ያቺ የሰፈራችን ሀብታሞን ሴት ጠየኳት በምላሹ አብሯት እንዳድር ጠየቀችኝ ለሳምንታት እንቢ ብዬ ነበር ልታመንልሽ ሞክሬ ነበር ግን ህመምም ጠናብሽ ብሩን ተቀብዬ ከታከምሽ በኃላ በቃሌ መሰረት ህሊናዬን ሸጥኩኝ እኔ አልካድኩሽም እንድትኖሪልኝ ብዬ ነው በእናታ ምዬልሽ እንደማልዋሽ ታቃለሽ "
" ያሬድ እየቀለድኩ ነው በለኝ "
" እውነቴን ነው ይቅርታ "
" ታድያ ለምን ብሩን ከአክስቶቼ እንደተቀበልክ ነገርከኝ እሺ ብለሽ እንድትታከሚልኝ ስል እንድትኖሪልኝ ብዬ "
" ያሬድ ይቅርታ ሳላውቅ ኮነንኩህ ትልቅ ስህተት ሰርቻለሁኝ ልሰማህ ይገባ ነበር ይቅርታ "
"እኔ ሁሌም ይቅርታ አድርጌልሻለሁኝ አላወቅሽም ተሳስተሽ ነበር አውን ደግሞ ገብቶሻል "
" ያሬድ "
"ነይ ነይ ልቀይሽ " ተቃቅፈው ለደቂቃዎች ተላቀሱ
"ያሬድ አመሰግናለሁኝ በቃ ሊሂድ ባሌ ይጠብቀኛል "
"ሳሮን እባክሽን ወደ እኔ ተመለሺ አፈቅርሻለሁኝ "
" እኔም አፈቅርሃለው ሁሉሜ ነው ደግሞ ማፈቅርክ ይቅርታ ድጋሚ ሌላ ስህተት መስራት አልፈልግም "
" ከሄድሽ እራሴን አጠፋለው "
" መኖር አለብህ ትናፍቀኛለህ እኮ "
"አብረን እንሁን እባክሽን "
" ያሬድ አግብቻለሁኝ እንደተውኩህ እኮ ያስባል ልክ እንደ እኛ መጉዳት የለበትም"
" ሳሮን አትሂጅ እባክህሽን እሱን መርጠሽ አትሳሳቺ እውነቱን ስነግርሽ እኮ የኔ እንደምትሆኚ ሳስብ ነው አመታትን ያለፍኩት እኔስ መደሰት የለብኝም ምን አጠፋው"
" ቻው ያሬድ አፈቅርሃለሁኝ መኖር አለብህ "
" እሺ አንዴ እቀፊኝ ተሰናበቺኝ"
"እሺ "
ለደቂቃዎች ተቃቅፈው አለቀሱ ያሬድ በፈገግታ
" አፈቅርሻለው"
" እኔም ቻው "
ሄደች እሱም በፍጥነት በሚመጣው መኪና ውስጥ ገብቶ ተገጨ የደረሰበት ጉዳት ከባድ ነበር እና ወድያው ሞተ...
ተሳስተሻል
ሁሌም ቢሆን ሰውን ማድመጥ አለብን በደቂቃዎች መፈታት የሚችሉ ችግሮች ናቸው አመታትን ሰንብተው ስህተትን የሚያመጡት አታርፍዱ
ህይወት ይቀጥላል ሀሳባችሁን አጋሩኝ
ከ ልብ የተቀዱ 💔
አንዳንዴ ዝም ብለህ የሀብታም ጨዋታ ስማ የሚበልጡት ሀብታሞች ያላቸውንና እሱ የሌለውን ሲነግርህ በባዶ ኪስህ እዝን ነው የምትልለት።
~ ከሄድሽ ~
ናታን እና ፅሆን ይባላሉ በጣም ነው ሚዋደዱት ፍቅራቸውን ሁኔታ ሊቀይረው ቢሞክርም አንድ ቀን እንኳን ተሳክቶለት አያቅም ። ምን አልባት ፍቅር ሳይሆን መተማመን አቆያቸው ማለት ይቻላል አንድ ቀንም ቢሆን ተቀናንተው አያቁም አንዱ አንዱን በሌላ አይጠረጥረም አንዴ ሁሉም ሰው በእነሱ ይገረማል ምን ያህል በፍቅራቸው እርገጠኝነት ቢሰማቸው ነው ይህን ያህል ክፉ ማያስቡት ምን ያህል ቢዋደዱ ነው ለደቂቃዎች እንኳን ሌላ ማይመኙት ሰው እኮ የወደደው ሳለ የሚሻል ሲመለከት ወይ እኔ ይህ ሰው የኔ በሆነ ይላል እንዴት ፍፁም መሆን ተቻለ ናቲና ፅሆን የተገናኙት አስረኛ ክፍል ሲሆን አስራ ሁለተኛ እንደተፈተኑት ናቲ ይዞት ኮበለለ ። ወደ አዲስ አበባ መጡ ህይወትን ግን እንደጠበቋት አላገኟትም እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ ያጠራቀሙት ብርም እያለቀ መቷል ትንሽዬ የሸራ ቤት ከተከራዩ በኃላ ተፍተፍ ብለው ኑሮን ተያያዙ ፅሆን ልብስ አጠባ፣ጉሊት አንዳንዴም ልጆችን መጠበቅ ናሆምም ተፍተፍ ብሎ አንዳንዴ ሊስትሮ አንዳንዴ የቀን ስራ መስራትን ጀመሩ ትንሽ ነገር እየተመገቡ ገንዘብ ማጠራቀም ጀምረዋል ከ አምስት ዓመት ልፋት በኃላ እድል ፊቷን ወደ እነሱ አዞረች እንዴት በሚያስብል ሁኔታ ሁሉም ነገር ኖራቸው በማግኝታቸው ተደስተው ሳይጨርሱ በስድስተኛው ወር ፅሆን በጠና ታመመች ወደ ህክምና ሲሄዱ ኩላሊቷ መቀየር እንዳለበት ተነገረው የሚያስፈልገውን የብር መጠን ሲነገረው ተረጋጋ ምክንያቱም ያላቸው ገንዘብ መጠንና ህክምናው እኩል ነበር ወድያውም ዶክተሩን ኩላሊት የኔን ተቀበል አለው ዶክተሩም በጣም ተገረመ ማንም ሰው እዛው በዛው ይህን ብሎት አያውቅም ዶክተሩም በትኩረትና በጥርጣሬ እየተመለከተው
" ናታን ይህ ቀላል ነገር አይመስለኝም አስብበት"
" አስቤበታለው ዶክተር ያለ እሷ መኖር አልችልም እባክህን አውኑኑ ጀምር"
" ናታን"
" ዶክተር ምንም አትበለኝ ገና እኮ ልጅ አሎለደችልኝም ገና እኮ አልሳቀችልኝም ገና እኮ ህልሟን አልኖረቹትም እንደልቧ አልበላችም እንደልቧ አለበሰችም እንደልቧ መኪና ከመኪና አልቀየረችም አይሆንም ዶክተር እንደውም ሁለቱንም ኩላሊቴን ወስደህ አድንልኝ የኔ መኖር ይቅር እሷ ብቻ እሷ ብቻ ትኑርልኝ እባክህን አውን ጀምር አውን ንገራቸው"
" ናታን እንድታስብበት አንድ ሰምንት ሰጥሃለው አስብበት እስከዛ ድረስ አስፈላጊውን ነገር እኛ እናደርጋለን አንተ ግን ተረጋግተህ አስብ"
" ዶክተር..."
" ናታን አንተ ስትኖር ነው ሚስትህን ማዳን ምንችለው እባክህን"
" እሺ ዶክተር"
" ኩላሊት የሚሰጥ ሰው እየፈለክ"
ምንም ሳይናገር በሩን በኃይል ዘግቶት ወጣ ። ለሳምንታት ቀኑ እስከሚደርስ ጓግቶ እንጂ ሀሳቡን ለአፍታም አልቀየረም ይልቁና ያላቸውን መኪናቸውን እና ሱቃቸውን ሽጦ ገንዘቡን አዘጋጀ እለት ዕለት ከአጠገቧ ርቆ አያውቅም አይን አይኗን እያየ ሁሌንም እንደሚጠብቃት ይነግራታል የማይደርስ ቀን የለም ሳምንት አለፈ ዶክተሩ ምንም ቢል እንደማይሰማው ነገረው ። ዶክተሩም በሀሳቡ እየተገረመ እና እያደነቀው ሰኞ ቀን ጉዞ እንዳላቸው ነገረው ናታንም ዝግጁቱን ጀመረ ። ሁሉም ነገር በድል ተጠናቀቀ ከሄዱበትም በድል ተመለሱ ፅሆንም ትንሽ ትንሽ ማውራት ጀመረች ሁሉም ነገር ሰላም እየሆነ እየመጣ ነበር ግን ፅሆን በድጋሚ በፀና ታመመች ህመሟ ምን እንደሆነ አልታወቀም ሆስፒታል በሄደችው በሶስተኛው ቀን ይህችን ዓለም በሞት ተለየች ። ናታን ይህን ሲሰማ ቀን ጨለመበት መኖር ለእርሱ ትርጉም አጣ ። እርሷ እስክትቀበር ለሳምንታት ታገሰ ሁሉም ነገር ለሰው መቀዛቀዝ ጀመረ እሱ ግን አዲስ ቁስል አዲስ ህመም አዲስ ስብራት እየሆነበት መጣ ። እሱም ተስፋ ቆረጠ አብረው ያለሙትን ብቻውን ማድረግ ከበደው ይልቁኑ እሷ ጋር መሄድን መረጠ እራሱን አጠፋ ትርጉም ያጣውን ህይወት ትርጉም እንዲኖረው አደረገ ። ምናልባት በሕይወት ኖረው በናፍቆት ከመንደድ ይሻላል ።
ከሄድሽ ልከተልሽ ከራቅሽም ልቅረብሽ
የማፍቀር ጥጉን ነፍሴን ነው ምሰጥሽ...
ህይወት ይቀጥላል ...
