cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Tᴏʟᴇʜᴀ Aʜᴍᴇᴅ (ጦለሃ አህመድ)☪️

Ethɪo Short Dᴀ'wa ለአስተያየትዎ እና ለጥያቄያቹ ጦለሃን ለማግኘት 👉🏿 @tolehaahmedbot👈🏿 የአረበኛ መፅሀፎችን በpdf ለማግኘት https://t.me/bintabdellahbot

Більше
Рекламні дописи
5 793
Підписники
+41924 години
+5287 днів
+1 23330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

⭕️ማሳሰቢያነገ ሰኞ - ሙሐረም 9 ⇝ማክሰኞ - ሙሐረም 10 ( ዓሹራ ) 💢 እነዚህን ቀኖች መፃም አንዘንጋ ። ለምታውቋቸው ሰዎች  ሼር አድርጉት ። በማመላከታችሁ ልክ እንደሚሰራው ሰው ምንዳ ታገኛላችሁና ። ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
Показати все...
00:15
Відео недоступнеДивитись в Telegram
📣ልዩ የሆነ የኒካህ እና የዳዕዋ ፕሮግራም የወንድማችን ጦለሀ አህመድ              እና የእህታችን ነጃት አብዱረህማን የኒካህ ፕሮግራም በማስመልከት የተዘጋጀ ―ፕሮጋራሙ ላይ ተጋባዥ ኡስታዞች      ☞አብዱራዛቅ አልባጂ       ☞ አብዱሽኩር አቡ ፈውዛን        ☞አቡ ሱፍያን ሁሴን   ርዕስ በሰአት የሚነገር ይሆናል በእለቱም  ሙሽራው  ወንድማችን ጦለሀ አህመድ  ቲላዋ የሚያስደምጠን ይሆናል። የፕሮግራሙ መሪ፦ወንድም አቡ ሱፊያን ፕሮግሙ በወንድማች ጦለሀ አህመድ ቻናል         ቀጥታ ይተላለፋል!👇 t.me/tolehaahmed t.me/tolehaahmed
Показати все...
1.29 MB
00:15
Відео недоступнеДивитись в Telegram
📣ልዩ የሆነ የኒካህ እና የዳዕዋ ፕሮግራም የወንድማችን ጦለሀ አህመድ              እና የእህታችን ነጃት አብዱረህማን የኒካህ ፕሮግራም በማስመልከት የተዘጋጀ ―ፕሮጋራሙ ላይ ተጋባዥ ኡስታዞች      ☞አብዱራዛቅ አልባጂ       ☞ አብዱሽኩር አቡ ፈውዛን        ☞አቡ ሱፍያን ሁሴን   ርዕስ በሰአት የሚነገር ይሆናል በእለቱም  ሙሽራው  ወንድማችን ጦለሀ አህመድ  ቲላዋ የሚያስደምጠን ይሆናል። የፕሮግራሙ መሪ፦ወንድም አቡ ሱፊያን ፕሮግሙ በወንድማች ጦለሀ አህመድ ቻናል         ቀጥታ ይተላለፋል!👇 t.me/tolehaahmed t.me/tolehaahmed
Показати все...
1.29 MB
የአይኖቼ ብርሀን ⇢ከህይወቴ 69 አመታትን ያለ ቤተሰብ ፣ ዘመድና ጓደኛ አሳልፊያለሁ። በ5 አመቴ ወላጆቼን በመኪና አደጋ አጥቻለሁ። ካሉብኝ በርካታ ህመሞች የተነሳ ዊልቸር ላይ ህይወቴን ያሳለፍኩ ነኝ። በዛ ላይ ስወለድ አይነ ስውር ነበርኩ! ጨለማን እንጂ ሌላን አላይም ። ባጭሩ ህይወቴ በጨለማ የተሞላች አሳዛኝ ህይወት ነች። እርግጠኛ የሆንኩበት ነገር ቢኖር ከአባቴ የወረስኩት ንብረት ባይኖር ኖሮ ከረዥም ጊዜ በፊት ሙቼ ነበር ( ከአላህ በታች)  ። ህይወቴ ላይ ያለው መልካም ነገር ጥግ የደረሰ ንብረቴ ብቻ ነው ። ያም ሁኖ ከሰዎች በመገለሌና ካለኝ የኑሮ ሁኔታ ከንብረቴ ጥቂትን እንጂ አልተጠቀምኩም። ይህ ሁላ ብስጭት ያለች፣ ፊቷ ፈገግ እንኳ የማይል አመለ ቢስ ሴት አደርጎኛል ። የምኖረው የተንጣለለ ቤት ውስጥና በርካታ ሰራተኞች እኔ ጋር ይሰራሉ ።እንደውም አረብ የሆነ እንዲያነብልኝ ብቻ የቀጠርኩት ሰራተኛ ነበረኝ ። ማየት የተሳናቸው የሚያነቡበትን ( braille) አልችልም ነበር ። ለምንም ነገር የመማር ፍላጎት አልነበረኝም… ካለኝ ፀባይ የተነሳ ሰራተኞቼ ራሱ አይወዱኝም ነበር ። የምከፍላቸው ደሞዝ ይዟቸው ነው እንጂ ጥለውኝ ይሄዱ ነበር ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ጀመሩ ። ጤናዬን ዶ/ር (عارف) አሪፍ ጋር እየተከታተልኩኝ ባለሁበት ጊዜ ከሩስያ የአይን ዶ/ር ጓደኛ እንዳላው ይነግረኛል ። ለአይኔም ችግር መፍትሄ የሚሆን ህክምና ነገረኝ ። ይህም በህይወቴ ከሰማኋቸው መልካሙ ዜና ነበር ። ምክንያቱም ከእሱ በፊት ማንም ለአይኔ መፍትሄ  አልነበረውም ።ለመጀመሪያ ጊዜ ተስፋ ተሰማኝ!  ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረ! ከዛም ዶ/ር አሪፍን በጉጉት ዶ/ሩ የት እንዳለ ስጠይቀው እዛው ሀገሩ ሩስያ ላይ መሆኑን ነገረኝ ።እዚህ (ኩወይት) እንዲመጣ እፈልጋለሁ አልኩት ። ጠይቆት መልሱን እንደሚያሳውቀኝ ነገረኝ ።እኔም መልሱን በጉጉት እየጠበቁ ነበር ። ሩስያዊው ዶ/ር ፍቃደኝ እንደሆነ ነገረኝ ። መጀመሪያ ላይ ግን እምቢ ብሎ ነበር ። ምክንያቱም ይህ ህክምና አዲስ ነው ። በራሱ ተመራምሮ ያገኘው በመሆኑ ሰዎች ላይ ገና ተግባራዊ አልተደረገም ። ስለዚህ ይህ ህክምና ህጋዊ አይደለም ።ነገር ግን የሚፈልገውን ገንዘብ እንደምሰጠው ሲያውቅ እሺ አለ ። ወደ 250,000 ዲናር ጠየቀ ። ለኔም ተራ የገንዘብ መጠን ስለነበር  ተስማማሁ … ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ነበር ። ችግሩ ብቻ ህክምናው ያልተሳካ እንደሆነ ነው ። ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ለመሞከርም እድል አይኖረኝም ። ሰውነቴ አቅም ስለሌለው ። ዶ/ሩ ከሁለት ሳምንት ዝግጅት በኋላ ኩወይት ደረሰ ። ወደ operation ክፍል እየወሰዱኝ ነው… ህክምናው አለቀ ። ከ operation ክፍል አስወጡኝ ። ዶ/ር አሪፍ በእኔና በሩስያዊው ዶ/ር መካከል ተርጓሚ ነበር። አይኔን አሁን መግለጥ እንደማልችል ነገሩኝ ። ምክንያቱም አይኔ ገና ለብርሀን አዲስ ስለሆነ ቀስ በቀስ ነው መግለጥ ያለብኝ ። ከዶ/ሩ ይህንን ከሰማሁ በኋላ ማሰላሰል ጀመርኩ…  69 አመታትን በጨለማ ካሳለፍኩ በኋላ ብርሀንን ላይ ነው! በመጨረሻም ከሆስፒታሉ አውጥተው ቤቴ ወሰዱኝ ። ለዶ/ር አሪፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አይኔን ስገልጥና  ስመለከት ብቻዬን መሆን እንደምፈልግ ነገርኩት ። እድሜ ልኬን ቤቴ ውስጥ ያሉትን ቅርፆች ማየት የተመኘኋቸውን ለብቻዬ ማየት እፈልጋለሁ ። ዶ/ሩ ቢለምነኝም እምቢ አልኩት። ከክፍሌ እንዲወጡም ጮኽኩኝ ። እንዲህም አልኩ … በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ፀሀይን ላይ ነው ! ቲቪ ላይ ነው! … ህክምናው ተሳክቶ ማየት ከቻልኩ ብዙ አዳዲስ እቅዶችን ማቀድ ጀመርኩ ። ዶ/ሩ ፋሻውን ከአይኔ ማንሳት እንደምችል ነገረኝ። በድጋሚ እንዲወጡ ነገርኳቸው። ዶ/ሩ ሁኔታዬን ማየት ቢፈልግም ሁለቱም እጅ ሰጥተው ከቤቴ ወጡ ። ብቻዬን መሆኔን ሳውቅ ፋሻውን ቀስ በቀስ አወጣሁት ። ትንሽ ብርሀን ወደ አይኔ መግባት ጀመረ።  ህመም ተሰማኝ ብርሀኑ ጠንካራ በመሆኑ በሂደት ግን መመልከት ቻልኩ! ማየት የምችል መሆኔን ባለማመን ክፍሌን መዛር ጀመርኩ። ብዙ ነገሮች ምን እንደሆኑ አላውቅም ። ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት እየቻልኩ ነው!!! አይኖቼ በእንባ ተሞሉ በጣም ደስ አለኝ …ክፍሌ ውስጥ ያሉ ነገሮችን እየተመለከትኩኝ ባለሁበት ጊዜ ድንገት እይታዬ ጠፋ! ምንም ማየት አልቻልኩም! … አው በድጋሚ ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ አይነ ስውር ሆንኩ!  አይሆንም… ይህ ሊሆን አይችልም!  ከዚህ ሁላ ትግል…  ከዚህ ሁላ ገንዘብ በኋላ ??? … የታለ ዶ/ሩ…  መጮህ ጀመርኩ ። እየጮህኩ መሬት ላይ ወደኩ ።ልቤን ህመም ተሰማኝ ። እየሞትኩ ነው መሰለኝ…  ልቤ እንዲህ አይነት ድንጋጤን መቋቋም አይችልም… እየመሞትኩ ነው… ------------------------------------ ከጊዜ በኋላ ዶ/ር አሪፍ የዚችን ሴትዮ መሞት ሲሰማ በጣም አዘነ ። እሱም ይሁን ሩስያዊው ዶ/ር ህክምናው መሳካቱንና አለመሰካቱን አላወቁም ። ሴትየዋም ትሁን ዶ/ሮቹ ያላወቁት ነገር ህክምናው በጥሩ ሁኔታ መሳካቱን ነው !! ነገሩ ብቻ  ምን መሰላችሁ በዛን ሰሞን ሴትየዋ የምትኖርበት አካባቢ ላይ መብራት መጥፋቱ ነው !! ሴትየዋም ባንዴ ብርሀኑ ሲቋረጥ እይታዋን ያጣች መስሏት ነው !!! 📌 ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን 📘 حكايات من العالم الأخر ትርጉም :  ቢንት አብደላህ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
Показати все...
00:18
Відео недоступнеДивитись в Telegram
በ አንድ ቀን ፆም የአመት ወንጀልህ/ሽ ይማራል!!! ሱብሃነሏህ አላህ ይቀበልህ! ይቀበልሽ!
Показати все...
5.59 KB
😢 1
00:22
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ታስረዋል ድምፅ እንሁናቸው። ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ጀግኖቻችን ትላንትና አዲስ አበባ ቄራ አካባቢ ሰላማዊ ደዕዋ በሚያደርጉበት አጋጣሚ በድንገት በፖሊስ ታፍነው ተወስደዋል። በየ ቦታው ጉረሮ እያነቁ የጆሯችን ታንቡር እስኪቀደድ ለብሽሽቅ በሚመስል መልኩ በየ አስር ሜትር ርቀት ላይ የሚጨፍሩብን ጴንጤወች አንድም ቀን ሀይ ተብለው አያውቁም #ጀግኖቻችንን ግን በብርሀን ቅፅበት ያለ ምንም ወንጀል የሀገሪቱን ህግ የነፃነት መብት በሚጋፋና #ለእስልምና_ያላቸውን_ጥላትነት ለማሳየት በሚመስል መልኩ በማናለብኝነት አስረዋቸዋል። እነዚህን ጀግኖቻችንን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንድፈቱልን እንጠይቃለን። ለምንድነው ሁሉም ሙስሊሞችን ሲያይ አይኑ እሚቀላው እንዴ!? ስንት ጋጠ ወጦች የሌሎችን ክብር የሚዳፈሩ ስርዓት አልበኝነት ያደነዘዛቸው ከፖለቲከኛ በላይ ውሸታምና አጭበርባሪ የሆኑት ፓስተር ነን ባይ ደናቁርቶች በሚበጠረቁባት#ኢትዮጲያ እንደት ሰላማዊ ሙስሊም ለምን አየንህ ተብሎ ይታሰራል!? ሀገሪቱ ዛሬም ለአንድ እምነት ከማጋደል አልተቆጠበችም ማለት ነው!? ዛሬም ዘመናዊ አንባ-ገነንነትን የመረጡ መንጋወች አሉ ማለት ነው!? የዚህ አይነት ርካሽ ተግባር የሚፈፅሙና የሰውን ክብር ብሎም በኢስላምን ጥላቻ የታነፁ መሀይማኖችን እየፈተሸ እርማት ሊሰጥ ይገባል። ይህ የዋህ ህዝብ ነው ሁሉን ችሎ ይህች ሀገር እንድትቀጥል የመጨነሻው ተስፋ እና ተስፋችሁን ባታጨልሙት እመክራለሁ። እንዴ ለምን እነዚያ አጭበርባሪ በየጎዳናው የሚጮሁት አልታዩም!? እስር ቤቱ የሙስሊም ዳዒወችን ብቻ ነው የሚቀበለው!? ለሙስሊሞች ብቻ ነው የናንተ ስልጣን የሚያገለግለው!? ጀግኖቻችንን በአስቸኳይ ፍቱልን!? ሁላችንም ሸር በማድረግ መረጃውን እናሰራጭ ኑረዲን አል አረብ http://t.me/nuredinal_arebi
Показати все...
2.87 KB
00:11
Відео недоступнеДивитись в Telegram
صيام يوم عاشوراء | الشيخ صالح الفوزان حفظه الله የአላህ መልዕክተኛነብያችንﷺ የአሹራን ፆም በመፆሜ አላህ ዘንድ ያለፈው የ 1 ዓመት ወንጀሌ እንዲማርልኝ እከጅላለሁ ቀጣይ ዓመት ከቆየሁኝም 9ኛውን ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ۞ اللهم صل وسلم على نبينا محمد ۞         ﷺ  ﷺ  ﷺ   ﷺ  ﷺ  ﷺ #الصلاة_على_النبي ﷺ •@tolehaahmed
Показати все...
صيام_يوم_عاشوراء_الشيخ_صالح_الفوزان_حفظه_الله_3snckbuEun4_134.mp45.01 KB
01:00
Відео недоступнеДивитись в Telegram
የአሹራ ቀን ሙሀረም 10ኛው ቀን ! በ Toleha Ahmed የተተረጎመ ይህንንና ሌሎችንም የትርጉም ስራዎቼን ቶሎ እንዲደርሳችሁ በ ዩቱብ ለማግኘት👇👇 https://youtube.com/channel/UCqwSE5q7REmxHTJWFXEHcWw ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓ @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛ ለሌሎች ሼር የሚያደርግን አካል አላህ ይዘንለት❕
Показати все...
የአሹራ_ቀን_ሙሀረም_10ኛው_ቀን_tG2WGj3Q6sY_134.mp41.67 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከምክንያት ወደ ውጤት! ስላላችሁበት ሁኔታ ምክንያት እየሰጣችሁ ባላችሁበት ከመርገጥ ይልቅ ለውጤት ወደመስራት አለፋችሁ እንድትሄዱ . . . 1. በዚህ አመት የሚሰራ ስራ ካጣችሁ በአንድ ዘርፍ ላይ ያተኮረን ክህሎት ያለማዳበራችሁን ጉዳይ አስቡብ፡፡ በተቃራኒው፣ መስራት የምታስቡት ነገር በዝቶባችሁ ከየትኛው እንደምትጀምሩ ግራ ከገባችሁ የትኩረት ችግር አለባችሁና እሱ ላይ ስሩ፡፡ 2. በዚህ አመት ጊዜያችሁን የምታሳልፉበት ነገር ካጣችሁ ራእይና ዓላማ እንደሌላችሁ ጠቋሚ ነውና እሱ ላይ ስሩ፡፡ በተቃራኒው፣ የማሕበራዊው ግንኙነትና የስራው ብዛት ጊዜ ካሳጣችሁ ነገሮችን ቅደም-ተከተል የማስያዝ ብቃተችሁን አስቡበት፡፡ 3. በዚህ አመት ጓደኛ ካጣችሁና ብቸኝነት ከተሰማችሁ የባህሪያችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡ በተቃራኒው፣ ጓደኛ በዝቶ ለራሳችሁ ጊዜ እስከማጣት ድረስ ከደረሳችሁ እንደዚህ የሚያጦዛችሁ የብቸኝነት ስሜት እንዳይሆን ሁኔታውን ለማጤን ሞክሩ፡፡ 4. በዚህ አመት ገንዘብ ካጣችሁ የሰዎችን ችግር የመፍታት ብቃታችሁን አስቡበት፤ ገንዘብ የምናገኘው ለፈታነው የሰዎች ችግር ስለሆነ ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ገንዘብ በዝቶ በምን ላይ እንደምታውሉት አጠቃቀሙን ግራ ከገባችሁ የፈጠራ ብቃታችሁ ላይ ስሩ፡፡ ዝም ብላችሁ የመጣውን እየተቀበላችሁ፣ የሚሄደውን ደግሞ እየሸኛችሁ አትኑሩ! አስቡ! ጠይቁ! መልስ እስከምታገኙ አትረፉ! ሞክሩ! ተንቀሳቀሱ! ©️dreyob ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.