1 318
Підписники
+324 години
+207 днів
+15030 днів
Архів дописів
የብቃት ፕሮጀክት 4 ተኛ ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዛሬው እለትም ቀጥሎ ውሏል
" የድሬ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት " በሚል መሪ-ሀሳብ የብቃት ፕሮጀክት 4 ተኛ ዙርን አስመልክቶ በትናንትናው እለት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር መጀመሩ ይታወቃል ።
መድረኩ በተለይም ወጣቶች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት የስራ ላይ ልምምድ በማድረግ በቀጣይ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማስቻል ያለመ መድረክ ነው ። በትናንትናው እለትም የወረዳ 01 ፣ 02 እና 03 ወጣቶች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የወረዳ 04 ፣ 05 እና 06 ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ባለፍት አመታት ወጣቶችን በስራ ብቁ አድርጎ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ከማድረግ አኳያ በርካታ ስራዎችን መሰራቱን አስታውቀው በአራተኛ ዙርም ወጣቶችን በተለያዩ የሙያ መስኮች በማሰልጠን እና ብቁ በማድረግ ወደ ስራ እንዲሰማሩ እንደሚደረግም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ያስታወቁት።
በመድረኩም በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የድሬዳዋ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር አመለካከትን ከመቀየር አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ እስከመክፈት በሚል ርዕስ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሰነዱንም መነሻ በማድረግም ውይይት ተካሂዷል ።
©️ DGC ነሐሴ 8/2018
ባለፉት አምስት አመታት ከ70 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተገለፀ
" የድሬ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት " በሚል መሪ-ሀሳብ በዛሬው እለት የብቃት ፕሮጀክት 4 ተኛ ዙርን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር ተካሂዷል ። መድረኩ ወጣቶች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት የስራ ላይ ልምምድ በማድረግ በቀጣይ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማስቻል ያለመ መድረክ ነው።
በመርሀ-ግብሩ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች በሚሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውንም በኢኮኖሚ በማገዝ እንዲሁም ደግሞ ከተማቸውን እና ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ወጣቶች መሆን እንዳለባቸውም ነው ክቡር ከንቲባው በእለቱ ያስታወቁት ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ባለፍት ሶስት አመታት ወጣቶችን በስራ ብቁ አድርጎ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ከማድረግ አኳያ በርካታ ስራዎችን መስራቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ አስታውቀው በአራተኛ ዙርም ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በተመሳሳይ ሰልጥነው ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀዋል ።
ባለፍት አምስት አመታት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ከ 70 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር ከመቻሉም በላይ በሁለቱም ቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጆች በአጫጭር እና መደበኛ ከ 30 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሰልጠን ለስራ ብቁ ማድረግ መቻሉንም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው በእለቱ ያስታወቁት ።
አቶ ሮቤል ጌታቸው አክለውም አሁን ላይ ካለው የስራ አጥነት ቁጥር አንፃር እንዲሁም በየጊዜው እየጨመረ ካለው የወጣቶች ቁጥር አንፃር እየተፈጠረ ያለው የስራ እድል በቂ አለመሆኑን ተናግረው ይህንንም ለመፍታት ተቋሙ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ነው አቶ ሮቤል ጌታቸው ያስታወቁት ።
በመድረኩም በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የድሬዳዋ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር አመለካከትን ከመቀየር አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ እስከመክፈት በሚል ርዕስ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሰነዱንም መነሻ በማድረግም ውይይት ተካሂዷል ።
©️ DGC ነሐሴ 7/2018
በድሬዳዋ "ክረምትን በክህሎት" በሚል መሪ ቃል ከ600 በላይ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እየወሰዱ መሆኑ ተገለጸ
በድሬዳዋ አስተዳደር "ክረምትን በክህሎት" በተሰኘው መርሃ-ግብር 607 የወጣት ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኝ ተገልጿል። ይህ የአጭር ጊዜ የሙያ ሥልጠና ተማሪዎች ከንድፈ-ሀሳብ ይልቅ በተግባር ላይ እንዲያተኩሩና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።
በድሬዳዋ "ክረምትን በክህሎት" በሚል መሪ ቃል ከ600 በላይ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እየወሰዱ መሆኑ ተገለጸ
በድሬዳዋ አስተዳደር "ክረምትን በክህሎት" በተሰኘው መርሃ-ግብር 607 የወጣት ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኝ ተገልጿል። ይህ የአጭር ጊዜ የሙያ ሥልጠና ተማሪዎች ከንድፈ-ሀሳብ ይልቅ በተግባር ላይ እንዲያተኩሩና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ ቢቂላ ታደሰ እንደገለጹት፤ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተማሪዎችን በተወሰኑ የሥራ መስኮች ላይ በተግባር የተደገፈ እውቀትና ክህሎት የሚያስታጥቅ ነው። ሥልጠናው ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ዕውቀት ቀስመው በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲሰማሩና የራሳቸውን የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ የሚያስችላቸው መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።
አሁን ላይ ሥልጠናው በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ በቅንጅት እየተሰጠ እንደሚገኝም አቶ ቢቂላ አክለው ገልጸዋል።
በዚሁ መሠረት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 196 ሴቶችንና 172 ወንዶችን በድምሩ 368 ሰልጣኞችን በመመዝገብ እያሰለጠነ የሚገኝ ሲሆን፤ በሌላ በኩል የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 115 ሴቶችንና 124 ወንዶችን በድምሩ 239 ተማሪዎችን በአሥር የሙያ መስኮች ተቀብሎ ሥልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በኮሌጆቹ ውስጥ ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ የተጀመረው የሙያ ሥልጠና በቀጣይ የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው ለመሥራት ትልቅ መሠረት እንደሚጥልላቸው ተናግረዋል። ወጣቶቹ አክለውም የክረምቱን ዕረፍት ጊዜ አልባሌ ቦታዎች ላይ ከማሳለፍ ይልቅ በዚህ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፋቸው ከፍተኛ የዕውቀትና የሙያ ብቃት ማግኘታቸውን በደስታ ገልጸዋል
©️ DireTvአማርኛ | ነሐሴ 06 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራርና ሰራተኞች የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካላ መርሃ-ግብር አካሄዱ::
#EIPC ነሃሴ 6.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው እለት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ማስጀመርያ መርሃ-ግብር እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም በኮሌጁ ተካሂዷል::
የኮሌጁ አመራና ሰራተኞች በክረምቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ምክንያት በማድረግ በኮሌጁ ባካሄዱት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የተለያዩ ለምግብነት የሚውሉ የችግኝ አይነቶችን በተቋሙ በተመረጡ ቦታዎች ላይ በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል::
ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ በቀጣይ የክረምት በጎ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን በዚህም የደም ልገሳ፣ የማዕድ ማጋራት እንዲሁም አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የመሳሰሉ በጎ ተግባራት በኮሌጁ ማሀበረሰብ እንደሚከናወኑም ተገልፇል::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
በድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪ ለሆኑ ከስደት ተመላሾች እና ለአደጋ የተጋለጡ ወጣቶች ከስራ ጋር የሚያስተሳስር ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ፤
በዚህም በአስተዳደሩ ተግባራዊ የሚደረገው ይህ ፕሮጀክት በኢንተርፕርነር ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ከሥራና ክህሎት ሚንስቴር (MoLS) እና ከዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር የሚተገበር ይሆናል።
በዛሬው ዕለትም ከዚህ ቀደም በአስተዳደሩ የሚገኙ የሚመለከታቸውን አካላትን በማሳተፍ የተዘጋጀ የሥራ ገበያ ጥናት ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት መድረክ የተካሄደ ሲሆን በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ከስደት ተመላሽ እና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶች ወደ ሥራ ለማስገባት ያለባቸው የክህሎት ክፍተት በሰፊው ተመላክቷል፡፡
በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ መዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ተገኝተው ፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ የአስተዳደሩ ነዋሪዎችን አቅም በመገንባት የሥራ ዕድል በመፍጠሩ ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን ተናግረው በቀጣይ የአሰልጣኞች ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው እና ይህንን ተከትሎም ሁለት መቶ ሀምሳ የሚሆኑ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ስልጠና ወስደው ወደ ዘላቂ የስራ እድል እንዲገቡ ለማድረግ የስራ ማስጀመሪያ ድጋፎች የሚያገኙ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች እና ተጠሪ ተቋማት የ2019 ዓ.ም ዕቅዳቸውን ከቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ጋር ተፈራረሙ።
****
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የማኔጀመንት አባላት በዛሬው ዕለት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የተወያዩ ሲሆን በዋናነትም በቢሮው ስር የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች እና ተጠሪ ተቋማት የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ከቢሮው ኃላፊ ጋር የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አከናውነዋል።
ከፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ባሻገር ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች እና ተጠሪ ተቋማቱ በበጀት አመቱ ያቀዷቸውን ዕቅዶች ባቀዱት መሰረት እንዲፈፅሙ የሚያስችል እና በመካከላቸው ጠንካራ የሆነ ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር ለተሻለ አፈፃፀም በጋራ መስራት በሚችሉባቸው አግባቦች ዙሪያ የማኔጅመንት አባላቱ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የሥራና ክህሎት ቢሮን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ገመገመ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ ለ 2019 በጀት ዓመት ያዘጋጀውን የሥራ ዕቅድ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዝርዝር ገምግሟል።
ቢሮው በቀጣዩ በጀት ዓመት ለማሳካት ያቀዳቸው የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ የክህሎት ልማት፣ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚደረጉ ድጋፎች፣ የብድር አቅርቦት፣ የመረጃ ሥርዓት ማጠናከሪያ እንዲሁም የወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ስትራቴጂዎች በግምገማ መድረኩ ላይ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በቀረበው ዕቅድ ላይ ባደረገው መሻሻል፤ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ዘላቂና ለዜጎች ተጨባጭ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚገባቸው አሳስቦ፣ ለዚህም በውጤት ላይ የተመሠረተ የክትትል አሠራር ሊዘረጋ እንደሚገባ ገልጿል። በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናዎች ከወቅቱ የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋር ተጣጥመው እንዲሰጡና ሰልጣኞች ከምረቃ በኋላ በቀጥታ ወደ ሥራ የሚሰማሩበት ሥርዓት እንዲዘረጋ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በተለይም በገጠር የሚገኙ ሥራ ፈላጊዎችን ማዕከል ያደረጉ አጫጭር ሥልጠናዎች ተጠናክረው እንዲተገበሩ ያሳሰበው ቋሚ ኮሚቴው፤ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ሌሎች ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች በበለጠ ተጠቃሚ የሚሆኑባቸው የክህሎት ማበልጸጊያና የሥራ ዕድል ፕሮግራሞች በዕቅዱ ውስጥ በትኩረት እንዲካተቱ አዝዟል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ በበኩላቸው፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ ያዘጋጀው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ "የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት" መስፈርትን ያሟላ በጣም ጥሩ ሰነድ መሆኑን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን የፋይናንስ፣ የሥራ ቦታና የገበያ ትስስር ችግሮች ለመፍታት እንዲሁም የንግድና አገልግሎት ዘርፎችን የሰው ኃይል ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የሙያ ሥልጠናዎች ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ሰብሳቢዋ በግምገማው ወቅት በውስንነት የተለዩ ማሻሻያ ጉዳዮች በዕቅዱ ውስጥ ተካተው በቀጣዮቹ ቀናት ለቋሚ ኮሚቴው እንዲላክ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
©️DireTvአማርኛ | ሐምሌ 30 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ውድ የኢትዮጵያ ወጣቶች፤
ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል። የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ የሚገኙ ሲሆን፥ የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ነው።
5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው ወስነዋል፣ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው!
🔗አሁኑኑ ይመዝገቡ፡ ethiocoders.et
