uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 318
Підписники
+324 години
+207 днів
+15030 днів
Архів дописів
የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡ #EIPC ሐምሌ 29.2018 ድሬዳዋ የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖችን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ አካሂደዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በተቋም ደረጃ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በዚህም ኮሌጁ ካሳየው ውጤታ ጉዞ ብዙ ልምዶችን መቅሰም መቻላቸውንም ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወጣቶችን ለማብቃት ከሚሰራው The Horn of Africa Youth Empowerment Academy ጋር በመተባበር ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡ የ
+1
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወጣቶችን ለማብቃት ከሚሰራው The Horn of Africa Youth Empowerment Academy ጋር በመተባበር ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን በተለያዩ ዘርፎች ላይ የማብቃት ስራ የሚሰራው HOAY(Horn of Africa Youth Empowerment Academy) ጋር በመተባበር በኮሌጁ ለሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎች ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት የተጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በመገኘት ለሰልጣኞች መልእክት ያስተላለፉትና ስልጠናውን በስኬት ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፍኬት የሰጡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም ለተከታታይ ሶስት ቀን ሲሰጥ የነበረው ይህ ስልጠና የኮሌጁን ሰልጣኞች የአመራርነት፣የተግባቦት እንዲሁም በራስ የመተማመንን ችሎታ እንድታዳብሩ የረዳ እንደመሆኑ መጠን የሰለጠናችሁትን ስልጠና ፍሬ በቀጣይ ወደ ተግባር ልትለውጡት ይገባል ብለዋል፡፡ ለሶሰት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ይህ ስልጠና ወጣቶችን ለአካዳሚክ፣ ለሙያዊ እና ለሲቪክ ስኬት የሚያዘጋጃቸውን ተግባራዊ የአመራርነት፣ የግንኙነት እና የሙያ ልማት ክህሎቶችን ለማስታጠቅ ያለመ ስልጠና ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም በቡድን ስራ፣በፈጠራ እንዱሁም በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ላይ የነበራቸውን ክፍተት መሙላት እንደቻሉ አስረድተዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች የሙያ ኔትወርኮቻቸውን የማስፋት፣ ክህሎቶቻቸውን ማዳበር እና በማህበረሰባቸው እና በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚረዱ ተግባራዊ ሀሳቦችን ማዳበር የሚያስችል አቅም መፍጠሪያ ስልጠና እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሀምሌ 29/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የስራ ማስታወቂያ ! በየአመቱ የኢትዮዽያ አየር መንገድ የሚያወጣው የስራ ማስታወቂያ በዚህም አመት በተለያዩ የስራ መስኮች ያወጣ በመሆኑ የከተማችን ወጣቶች የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪዬን አስተላልፋለው። በተለይም በዚህ አመት ከዚህ ቀደም ከነበረው በላይ ለከተማችን ወጣቶች ቁጥር የተጨመረ በመሆኑ ለሚመለከታቸው ሁሉ መረጃውን እንዲደርሳቸው እናድርግ። Via Robel Getachew

የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመጋፈጥ ወደ መልካም አጋጣሚዎች የሚቀይሩ ወጣቶችን ለማፍራት እየሰራ እንዳለ ኮሌጁ እታወቀ፡፡ በክረምቱ መርሃ ግብር የአካባቢውን ወጣቶች የአንድ ሙያ ባለቤት ለማድረግ ታልሞ
+9
የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመጋፈጥ ወደ መልካም አጋጣሚዎች የሚቀይሩ ወጣቶችን ለማፍራት እየሰራ እንዳለ ኮሌጁ እታወቀ፡፡ በክረምቱ መርሃ ግብር የአካባቢውን ወጣቶች የአንድ ሙያ ባለቤት ለማድረግ ታልሞ በተዘጋጀው መርሃግብር ላይ ለሚሳተፉ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና በመሰጠት ላይ ሲሆን በዚህ ስልጠና ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ወጣቶችን በስልጠና ቦታቸው ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆን በንግግራቸውም ወጣቶች የተለያዩ ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል ነገርግን ለችግሩ እጅን ሰጥቶ ከመቀመጥ ይልቅ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር የስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያስፈልጋል ፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሁሉ ሌሎችም ማሰልጠኛ ተቋማት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ዲን አያይዘውም እራሱን የለወጠ ወጣት ከራሱ አልፎ መንደሩን ብሎም ሃገሩን መለወጥ ይችላል ይህ የሚሆነው ግን ወጣቶች በራሳቸው የሚተማመኑና ለስራ ፈጣሪነት የተዘጋጁ ሲሆን ብቻ ነው ስለዚህ የዚህ ስልጠና ዋናው አላማ አመለካከቱ የተለወጠ እና በራሱ የሚተማመን ወጣት ለማፍራት ታልሞ እንደ መዘጋጀቱ መጠን ከስልጠናው በኋላ የስልጠናው ፍሬ ሊታይ ይገባል ብለዋል፡፡ በኮሌጁ እየተሰጠ የሚገኘው ይህ የክረምት ስልጠና የአካባቢውን ወጣቶች ገበያ ተኮር በሆኑ የአጫጭር ስልጠናዎች በማብቃት የኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታሞ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሀምሌ 28/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ****** ቃሏን አክባሪዋ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ደማቅ ክብረ ወሰን አስመዘገበች። ኢትዮ
እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ****** ቃሏን አክባሪዋ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ደማቅ ክብረ ወሰን አስመዘገበች። ኢትዮጵያ ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ 805.3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ታላቁን ሀገራዊ ዕቅድ በላቀ ስኬትና በታላቅ ድምቀት ማሳካቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ አደረጉ። ይህ ታሪካዊ ድል የዛሬው ዕለት ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተከታታይ ስምንት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያቀደችውን ግብ ያለምንም መጓደል በተግባር እያሳካች መሆኗን በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

photo content

photo content

photo content

የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብርን ዛሬ በይፋ አስጀመረ ...!!

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብርን በይፋ አስጀመረ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል። በዚህ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የደም ልገሳ፣ የችግኝ ተከላ፣ የማዕድ ማጋራት እንዲሁም የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታና እድሳት ማስጀመሪያ ስራዎች በይፋ ተከናውነዋል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በአስተዳደሩ በርካታ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ የበጎ ፍቃድ ስራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት ከተጀመረ በኋላ የበርካታ አቅመ ደካማ ዜጎችን ችግር መቅረፍ መቻሉን አቶ ኢብራሂም ጠቅሰው፣ መርሃ ግብሩ ወጣቶች በበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በስፋት እንዲሳተፉ ትልቅ አቅም መፍጠሩን አብራርተዋል። ስራና ክህሎት ቢሮ ከአቅመ ደካሞች ጎን በመቆም ላሳየው አለኝታነት ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ኢብራሂም፣ ይህ ተግባር ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በንቃት ሊሳተፍበት እንደሚገባ አሳስበዋል። የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው፣ በመደመር መንግስት በየክረምቱ የተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል። እነዚህ የበጎ ፍቃድ ስራዎች በተጨባጭ በዜጎች ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥና ውጤት ማምጣታቸውንም አቶ ሮቤል አመላክተው፣ በዛሬው የቢሮው የበጎ ፍቃድ ስራዎች የማስጀመሪያ መርሃ ግብር 30 ለሚሆኑ ዜጎች ማዕድ ማጋራት የተከናወነ ሲሆን፣ በክረምቱ ወቅት በአጠቃላይ ለ100 ዜጎች ማዕድ ለማጋራት፣ በስፋት የችግኝ ተከላ ለማካሄድ እና 50 ዩኒት ደም ለማሰባሰብ መታቀዱን ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግና የ7 አቅመ ደካማዎችን ቤት ገንብቶ የማስረከብ ስራ እንደሚሰራ ኃላፊው አመላክተው፣ ይህ ተግባር የመደመር መንግስት ለህዝቡ ያለውን ቅርበት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል። በመርሃ ግብሩ ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በበኩላቸው፥ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የህሊና እርካታን ከመስጠቱም በላይ የወገንን ችግር በተግባር ለመቅረፍ ትልቅ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። በክረምቱ ወቅት የታቀዱት የልማትና የድጋፍ ስራዎች ሙሉ በሙሉ ግባቸውን እንዲመቱ የጀመሩትን ንቁ ተሳትፎ አጠናክረው ለመቀጠልና የተጣለባቸውን አደራ በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

photo content
+9

በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በሙያና ክህሎት የዳበሩ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በኮሌጁ የሚሰጡ ገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚሰጡ ተገለጸ፡፡ ክረምትን በክህሎት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በሚል መሪ ቃል የአካባቢውን ወጣቶች ቢያስ የአንድ ሙያ ባለቤት ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀው የክረምት የክህሎት ስልጠና በዛሬው እለት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው እለተ ተጀመረ፡፡ የአካባቢው ወጣቶች ክህሎት ያለውና አመለካከቱ የተለወጠ ወጣት ከራሱ አልፎ ሃገሩን መለወጥ ይችላል ያሉት እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ ይህንንም ለውጥ ለማምጣት ደግሞ ትክክለኛ ምርጫ የሚሆነው ሙያና ክህሎትን ወደሚያስጨብጠው የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ደግሞ የአካባቢውን ወጣቶች በሙያ የዳበሩ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የተለያዩ ገበያ ተኮር ስልጠናዎችን በማዘጋጀት በክረምቱ እንዲሁም በበጋው የስልጠና ወቅት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል የዘንድሮውን የክረምት ስልጠና ለመሳተፍ ኮሌጃችንን ስለመረጣችሁና የእረፍት ጊዜያችሁን በክህሎት ለማሳለፍ ስልመጣችሁ አመሰግናለሁ የስልጠና ጊዜያችሁ የተሳካ እንዲሆን መልእክቴን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ም/ዲን የውጤት ተኮር ት/ት ስልጠና ኃላፊ አቶ ቢቂላ ታደሰ እንዳሉት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወጣቶችን ሙያና ክህሎት እንዲኖራቸው እንዲሁም አመለካከታቸው የተቀየረና ከራስ አልፈው ለሀገር የሚተርፉ ወጣቶችን በሚሰጠው ስልጠና እያፈራ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለትም ገበያ ተኮር በሆኑ የክረምት አጫጭር ስልጠናዎችን ለመውሰድ ወደ ኮሌጁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን የስልጠና ጊዜያችሁም የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ነገር እናደርጋለን ብለዋል ፡፡ በዘንድሮ የክረምት ስልጠና በኮሌጁ ለመሳተፍ በርካታ የአካባቢው ወጣቶች በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ፣በአውቶ ሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ፣በኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ፣በውድዎርክ ቴክኖሎጂ እና በሌዘርና ፋሽን ዲዛይን እንዲሁም በሆቴል ቱሪዝምና ICT ዘርፎች ስልጠናቸውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል፡፡ ኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሀምሌ 24/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የ2018 የክረምት የክህሎት ስልጠና በኮሌጁ ተጠናክሮ መካሄዱን ቀጥሏል:: #EIPC ሐምሌ 23. 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 "የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" የክረምት ስልጠና ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለሶስት ቀናት ሲከተታተሉ የቆየውን የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና አጠናቀቁ:: ሰልጣኞቹ የህይወት ክህሎት ስልጠናቸውን እንዳጠናቀቁ በኮሌጁ የሚገኙ ዲፓርትመንቶች እና ስልጠና የሚሰጥባቸውን ወርክሾፖች ተዘዋውረ የተመለከቱ ሲሆን ስለ ሙያ ዘርፎችም ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል:: የክረምት ክህሎት ሰልጣኞቹ በተፈጠረላቸው ግንዛቤ መነሻነት ሚፈልጉትን የሙያ ስልጠና አይነት የመረጡ ሲሆን ቀጣይ በተቀመጠላቸው መርሀ-ግብር መሰረትም ስልጠናቸውን የሚከታተሉ ይሆናል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1