Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 064
Obunachilar
-124 soatlar
-47 kunlar
+530 kunlar
Postlar arxiv
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ዕቅድን መነሻ በማድረግ የቢሮው ዕቅድ መዘጋጀቱንና ሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴዎችንም ከቢሮው እስከ ወረዳ አንድ ማዕከላት ድረስ እንዲሁም በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች መዋቀር በቢሮው ማኔጅመንት እንዲጸድቅ ማድረግን ተከትሎ የተዘጋጀ ሆኗል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት ቢሮው ይህን በአገር አቀፍና በአስተዳደር ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የሪፎርም ስራዎች እንቅስቃሴ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፈጸም የሚያስችለውን ስራዎች በአግባቡ መርቶ ከዳር ለማድረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለዩኒቨርስቲ እና ኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች የኢንተርፕርነርሺፕ እና የማይንድ ሴት ስልጠና በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ስልጠናው በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ስራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ስራ እንዲፈጥሩ በሚያነሳሳ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ተወካይ ወ/ሮ ቤተልሄም ድንበሩ ተናግረዋል።
በዚህም ተሳታፊ የሆኑ የዩኒቨርስቲ እና የኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች ከዚህ በፊት ተቀጥሮ ለመስራት ብቻ ይጠብቁ የነበሩ ከስልጠናው በሚያገኙት ግንዛቤ በግልም ሆነ ተደራጅቶ ለመስራት መነሳሳት እንዲፈጠርባቸው ታሳቢ ያደረገ ሆኗል።
ቢሮው በአስተዳደሩ ትኩረት የተሰጠውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የተጀመሩ የተለያዩ ስራዎችን በተለይም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ተመራቂዎች ተደራጅተው ወደ ሰራ እንዲሰማሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 2 ዋናው እና ወረዳ 4 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የተደረገ የመስክ ምልከታና ልየታ በምስል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የማሰልጠን ስነ-ዘዴ/ Training Methodology/ ላይ ስልጠና ላልወሰዱ ከሁለቱ የመንግስት እና ከግል ኮሌጆች በተለያዩ ሙያዎች ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ለተከታታይ 8 ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፤
በስልጠናውን መጀመር በንግግር የከፈቱት የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል የስልጠና አሰጣጥ ሥርዓትን በመተግበር ሙያው የሚጠይቀውን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት በበቂ ሁኔታ ለሰልጣኞች በማስረጽ በክህሎት የዳበሩና ስኬታማ የሆኑ ሰልጣኞችን ለስራ ገበያው ለማቅረብ የሚችሉ በአስተዳደራችን የሚገኙ ብቁ አሰልጣኞችን ማፍራት የቢሮው፤ የኤጀንሲው ብሎም የዳይሬክቶሬቱ ቁልፍ ተግባር መሆኑን በመግለፅ ሰልጣኞች በስልጠናው በሚቆዩባቸው ቀናት የሚጠበቅባቸውን የተግባር ስራዎች በማሟላት በስልጠናው ማጠናቀቂያ የሚኖረውን ምዘና ብቁ ለመሆን በንቃት ተሳታፊ እንዲሆኑ አሳስበዋል፤
የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ በበኩላቸው አሰልጣኞች በሙያቸው የሚጠበቅባቸውን የእውቀት፣ የክህሎትና የሙያ ስነምግባር በመላበስና በሙያቸው ብቃታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር፣ የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና/Training Methodology/ በመሰልጠን አሰልጣኞች ሊኖራቸው የሚገባውን የሙያ ብቃት ማዕቀፍ/ Training Qualification Frame Work/ ስታንዳርድ ማሟላት እንዳለባቸው የዘርፉ ስትራቴጂ ማስቀመጡን አውስተው፤ የዘርፉ ስልጠና አሰጣጥ ስርአትም ውጤትን መሰረት ያደረገ/Out Come Based Training / መሆኑ፤ ይህንንም የሚያስተገብሩት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት ብቁ የሆነ የሰው ሀይል የማፍራት ተልዕኮን በመወጣት እረገድ ምንግዜም የማይተካ ሚና ያላቸው አሰልጣኝ መምህራን መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችና ስራ ሂደቶች የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር ማካሄድ ጀመረ::
በኮሌጁ ዲን በሚመራው በዚህ የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር በድጋፍና ክትትል ቡድኑ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ትምህርትና ስልጠና ክፍሎች፣ ዋና ስራ ሂደቶችና የስራ ክፍሎች በግማሽ አመቱ በእቅድ አፈፃፀም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በስልጠና ጥራት፣ በመረጃ አደረጃጀት፣ በሀብት ማፍራትና ግብዓት አጠቃቀም ላይ ባተኮሩ ነጥቦች መነሻነት ሂደቶችና ክፍሎች ያሉበትን ቁመና የሚገመግም የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር መሆኑም ተገልጿል::
የዚህ ድጋፍና ክትትል ዋና አላማ በተቋሙ የሚገኙ ስራ ሂደቶችና ክፍሎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃርና ካስቀመጡት ግብ አኳያ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ክትትል ለማድረግና በአፈፃፀም ክፍተት የሚታይባቸውን ተግባራቶች ተለይተው ክፍተቶች እንዲሞሉ ድጋፍ የማድረግ ሲሆን በተጨማሪም የተሻለ አፈፃፀም ለታየባቸው ስራ ሂደቶችና ክፍሎች እውቅና በመስጠት ለሌሎች ሞዴል እንዲሆኑ ማስቻል እንደሆነው ተገልፇል::
በድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ እስካሁን የአውቶሞቲቭ፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የአይ.ሲ.ቲ፣ የውድ ዎርክ እና የኮስትራክሽ ትምህርትና ስልጠና ክፍሎችን ማካሄድ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት የድጋፍና ክትትሉ የሚቀጥል መሆኑም ታውቋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
ከደረጃ 5 ወደ 8፤ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ አዲስ ምዕራፍ
+6
አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!!!
በድሬዳዋ አስተዳደር 130ኛው የአድዋ ድል በዓል ከአኩሪ ታሪክ፤ ወደ ብሩህ አድማስ ! በሚል መሪ ቃል በለገሀር አደባባይ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በድምቀት ተከበረ።
በበዓሉ አከባበር መርሀ ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የካቢኔ አባላትና በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የፀጥታ አመራርና አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
©️ DGC
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ የአምራች ኢንዱስትሪውን ፍላጎት መለየት የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ::
ከተማችን ድሬደዋ የኢንዱስትሪ ማዕከል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አምራች ኢንዱስትሪው የሚጠይቀውን ብቁና የሰለጠን የሰው ሀይል በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ አሰልጥኖ ለማቅረብ ታሳቢ ያደረግ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናትና የምክክር መድረክ ከኮልጁ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ አካላት ጋር ማካሄድ ተችሏል::
የምክክር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው "ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ወጣቶች ከረጅም ጊዜ ስልጠና ይልቅ ወቅቱ ሚጠይቀውን የአጫጭር ሙያ ስልጠናዎች ላይ ትኩረት በማድረጋቸው አምራች ኢንዱስትሪው በሚፈልገው ልክ የበቃ የሰው ሀይል የማቅረብ ውስነት እንዲስተዋል እድርጎታል ያሉ ሲሆን ይህን ክፍተት በዘላቂነት ለመቅረፍ የአምራች ኢንዱስትሪውን የሙያ ፍላጎት መሰረት ያደረገ የአጫጭር ስልጠና ፕሮግራም መቅረፅ አስፈላጊ በመሆኑ ከኢንዱስትሪ አድቫይዘሪግ ቦርድ አባላት ጋር ለመወያየት ይህ መድረክ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል::
በEASE ፕሮጀክት ትኩረት ተደርጎባቸው ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ለኢንዱስትሪው ግብዓት የሚሆኑ ብቁ ባለሙያዎችን የማፍራቱን ሂደት መደገፍ አንደኛው መሆኑን ያስታወሱት የፕሮጀክቱ ኮርዲኔተር ኢ/ር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ የፕሮጀክቱ ባለሙያዎች ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ጋር በመቀናጀት በሚያዘጋጁት የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደርገ የአጫጭር ስልጠና ፕሮግራም ላይ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ገልፀዋል::
የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አስፈላጊነት ዝርዝር ዓላማ እንዲሁም የአጫጭር ስልጠና ሞጁሉን በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ የሚያካተቱ ዝርዝር ተግባራትን በተመለከተ በኮሌጁ ም/ል ዲን እና የትምህርትና ስልጠው ዋና ሀላፊ በሆኑት አቶ ኤሊያስ አህመድ አማካኝነት ለባለ ድርሻ አካላት ግንዛቤ መስጠትም ተችሏል::
በመድረኩ በነበረው ውይይት ኢንዱስትሪውን ወክለው የተገኙ ተስታፊዎች አምራች ኢንዱስትሪዎች ከበቃ የሰው ሀይል አኳያ ያላቸው ፍላጎት ለጥናት ቡድኑ በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት የተካሄደት ሲሆን ለፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችም የተገኙበት መድረክ ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 21/6/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ጋር በመተባበር የኩባንያ ውስጥ ስልጠና ለማጠናከር የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ይህም ስልጠና በ2018 ዓ.ም የኩባንያ ውስጥ ስልጠና ለመስጠት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ለትብብር ስልጠና መስጫነት ከተመረጡ ኩባንያዎች በ4 የሙያ ዘርፎች ማለትም በማኑፋክቸሪንግ፣ ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፣ በሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም በአውቶሞቲቭ ሙያዎች ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በተውጣጡ አሰልጣኞች የኩባንያዎቹን ሰራተኞች ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየት ስልጠና ለመስጠት ያስችል ዘንድ ከ4ቱ ዘርፎች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራንና ስልጠና አስተባባሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠናው መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የኩባንያ ሰራተኞችን በማብቃት፤ የቴክኖሎጂ ክፈተቶችን በመሙላት ምርትና ምረታማነትን ማሳደግ ሲሆን በተጨማሪም የአሰልጣኝ መምህራንን አቅም በማሳደግ በትብብር ስልጠና ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጥራት ችግሮችን ከወዲሁ ለመፍታት ማስቻል ነው ሲሉ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ምንልክአለው ወርቅነህ ገልጸዋል ፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 21/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Endi mavjud! Telegram Tadqiqoti 2025 — yilning asosiy insaytlari 
