uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 326
Підписники
+224 години
+87 днів
+9730 днів
Архів дописів
photo content
+6

የአክሱም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራር አባላትን የያዘ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት ትግበራ እያሳየ በሚገኘው ከፍተኛ አፈፃፀም ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ ኮሌጆች ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማችን እየመጡ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው እለትም በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚገኘው የአክሱም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋማችን የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አድርጏል:: ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያለውን የአፈፃፀም ሂደት በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በተለያዩ ተግባራት እያከናወናቸው የሚገኙ የለውጥ ስራዎችም በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገልፃ ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ ባደረገው ምልከታና የተደረገላቸው ገለፃ መነሻ በማድረግ በተካሄደው የጋራ ውይይት ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው በሚገኘው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች መደነቃቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ በአጭር ጊዜ እያሳየ ያለው የላቀ አፈፃፀም ለሌሎች አቻ ተቋማትም ሞዴል ተደርጎ መወሰድ የሚችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ሀሳባቸውን ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎች እንዲሁም ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን እዚህ በኮሌጁ ያገኟቸውን በርካታ ልምዶችንም ቀምረው በመጡበት ኮሌጅ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም

መሶብ የአንድ መዐከል አገልግሎት

ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሰራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

በአስተዳደሩ  የተጀመረው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ቀጥሎ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ በሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች አዲስ በተከለሰው የሙያ ደረጃና የሆልስቲክ ምዘና አሰጣጥ ስርዓት የሙያ ምዘና በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል በዚህም በአስተዳደሩ 232 የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና በ12 ዘርፎች በ23 ሙያዎች(Occupation) ይመዘናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም ከሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አስር ቀናት  በ5 ሙያዎች/occupations/ 38አሰልጣኞች በደረጃ 4 እና 5 Practical እና Knowledge Test የወሰዱ ሲሆን በቀጣይም ያልተመዘኑ አሰልጣኝ መምህራን በተመሳሳይ የሚመዘኑ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራንን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ለኢትዮ-ጣልያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሆቴልና ቱሪዝም ዲፓርትመንት አሰልጣኝ መምህራን ስልጠና ተሰጠ፡፡ በዚህም ስልጠናው በትምህርት ክፍሉ ትምህርትና ስልጠናን በተሻለ መልኩ ለመስጠት እንዲያስችል አሰልጣኝ መምህራኑን በሼፍነት ሙያ እውቀትና ልምድ ባላቸው ተጋባዥ አሰልጣኞች አማካይነት ከኮሌጁ ጋር በመተባበር በተፈጠረው መልካም አጋጣሚ አሰልጣኞች የእውቀት እና ክህሎት ሽግግር እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው  ሆኗል፡፡ በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና በመዘጋጀቱ በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ዘንድ ያለውን የክህሎት ክፍተት መሙላት ከመቻሉ ባሻገር በቀጣይ በ2018 ዓ.ም ትምህርትና ስልጠና ዘመን እንዲሁም ለምዘና ዝግጁ የሚያደርጋቸው እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራንን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ለኢትዮ-ጣልያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሆቴልና ቱሪዝም ዲፓርትመንት አሰልጣኝ መምህራን ስልጠና ተሰጠ፡፡ በዚህም ስልጠናው በትምህርት ክፍሉ ትምህርትና ስልጠናን በተሻለ መልኩ ለመስጠት እንዲያስችል አሰልጣኝ መምህራኑን በሼፍነት ሙያ እውቀትና ልምድ ባላቸው ተጋባዥ አሰልጣኞች አማካይነት ከኮሌጁ ጋር በመተባበር በተፈጠረው መልካም አጋጣሚ አሰልጣኞች የእውቀት እና ክህሎት ሽግግር እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው  ሆኗል፡፡ በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና በመዘጋጀቱ በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ዘንድ ያለውን የክህሎት ክፍተት መሙላት ከመቻሉ ባሻገር በቀጣይ በ2018 ዓ.ም ትምህርትና ስልጠና ዘመን እንዲሁም ለምዘና ዝግጁ የሚያደርጋቸው እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 17/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የአፈጻጸም ደረጃና ውጤታማነት ላይ የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ በኮሌጆች በኩል ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሲሰጥ የነበረውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የአፈጻጸም ደረጃና ውጤታማነት የዳሰሳ ጥናት ለማድረግና ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ለመለየት፣ የተገኙ ትምህርቶችን ለመቀመርና በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚቀርቡበት ይሆናል፡፡ በዚህም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የሚያደርጉ የቢሮው ባለሙያዎችና ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን በክህሎት፡ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፡ በጥራትና ምርታማነት፡  በገበያ ትስስር  የሚታዩ ክፍተቶችንና ውስንነቶችን ለመለየትና ለመረዳት እንዲሁም የተሰጠው ድጋፍ ምን ያህል ውጤታማ እንደነበር ለማወቅ ይህ የዳሰሳ ጥናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል፡፡  የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 17/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

ሶስተኛው ዙር ብቃት_የወጣቶች_የስራ_ላይ_ልምምድ_ፕሮጀክት ትግበራ ሁለተኛው ዙር የህይወት ክህሎት እና የስራ አፈላለግ ስልጠና ወጣቶች በስልጠና ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራ ክህሎት ቢሮ "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት" ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የወረዳ አንድ ማዕከላት የተመዘገቡ ወጣቶችን በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና  በኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል በዚህም ሰልጣኞች ስልጠና ከመጀመራችው በፊት አስፈላጊውን ኦሬንቴሽን የተሰጣቸው ሲሆን ስልጠናውን ለቀጣይ 12 ቀናት በኮሌጆቹ እየወሰዱ የሚቆዩ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 17/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

የስራ ማስታወቂያ ለድሬዳዋ ነዋሪዎች በሙሉ የኢትዮጲያ አየር መንገድ አዲስ የስራ ማስታወቂያ ያወጣ ሲሆን በኤሌክትሮኒክስ በሜካኒካል ፣ በኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች የተመረቁትን ለመቅጠር ይፈልጋል ። በመሆኑም እድሜያቸው ከ 18 እስከ 25 እንዲሁም ቁመት ሜትር ከ ስልሳ የሆናቹ ከሚያዚያ 20 አንስቶ እስከ ሚያዚያ 24 2017 ዓ.ም ድረስ አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ እና ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በአካል በመገኘት መመዝገብ ይኖርባቸዋል ። አስታውሱ የምዝገባው ቀን አጭር ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ !

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እና የወረዳ አንድ ማዕከላት አመራሮች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአንድነትና የአብሮነት መርሀ-ግብር አካሄዱ፤      መርሃ-ግብሩ በተለይም የቢሮው እና የአንድ ማዕከላት አመራሮች በስራ ላይ ካለው አብሮነት እና አንድነት ጎን ለጎን በማህበራዊ ጉዳይም ጠንካራ መስተጋብር መፍጠር መቻሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል።     ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የረመዳን ጾም ላይ አመራሩ በጋራ መርሃግብር ማዘጋጀቱ የሚታወስ ሲሆን ይህም የድሬዳዋዊ ዕሴት መገለጫ መሆኑን ያሳየ ሆኗል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 13/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+3