uk
Feedback
Uog zena

Uog zena

Відкрити в Telegram

Uog news 🙏

Показати більше
5 660
Підписники
+824 години
+27 днів
+6230 день
Архів дописів
ዉጤት ተመልከቱ አሁን sertual

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት exit exam result መመልከቻ ሊንክ ሰርቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ መስራት አቁሟል ተማሪዎች አሁንም በትግስት ጠብቁ ::🙏🏻 Uogzena መልካም ዉጤት ለሁላችውም ይመኛል ::

የመውጫ ፈተና ዉጤት ለማየት ዌብሳይቱ እያስቸገረ ይገኛል:: አሁንም በርካታ ተማሪዎች አልሰራልንም እያሉ ይገኛሉ system ሲስተካከል ወድያው መመልከት ትችላላችው system ለማስተካከል ትንሽ ጊዜ ይፈልጋል ሆኖም ግን አሁን ላይ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ደርሷል ስለሆነም ከጥቂት ሰዓታት በኃላ ዉጤት መመልከት ትችላላችው :: እሰክዚያው ተማሪዎች በትግስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን :: Portal ሲሰራ ወድያው ዉጤት እንዲታይላችው የምትፈልጉ direct message ላይ user name አስቀምጡልን :: መልካም ዕድል 🙏🏻 @uogzena

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የምናካሂደውን የተማሪዎቻችንን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። To watch the live broadcast of our s
ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የምናካሂደውን የተማሪዎቻችንን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። To watch the live broadcast of our students’ graduation ceremony, which will be held on June 25, 2026, use the link below. https://youtube.com/live/Y6P--G3uI5w?feature=share

#update  የ መውጫ  ፈተና ውጤት ተለቆ ተማሪዎች  ውጤት  ማየት ጀምረው ነበረ አሁን ላይ ሲስተሙ በመጨናነቁ ምክንያት  ዌብሳይቱ  not found ማለት ጀምሯል። ሰርቨሩ ዳግም መስራት እስኪጀምር በትግስት እንድጠብቁ አደራ እንላለን  ሁልጊዜም ውጤት ሲለቀቀ መሰል ችግሮች  እንደሚኖሩ  ይታወቃል ። ውጤት ሰኔ 16 እንደሚገለጸ ትላንት ተናግረን ነበር https://result.ethernet.edu.et/usernamepage ለታማኝ  እና ፈጣን መረጃ ይቀላቀላሉን

2⃣ days left for 2026 graduation ceremony የተማሪ ወላጆች እና ወዳጅ ዘመዶች እንኩዋን በሰላም ወደ ዉቢቷ ጎንደር እና ወደ አንጋፋው ጎንደር ዩንቨርስቲ በሰላም መጣችሁ :: @uogzena

መልዕክት ካላችው በ ዉስጥ መስመር ላኩልኝ uog direct message

ዛሬ exit exam እንዴት ነበር?

7⃣ DAYS LEFT FOR 2026 GRADUATION CEREMONY 🎓🎓

‼️❗️ማስታወቂያ❗️‼️ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ.ሴ.ጣ.ኮ ግቢ ተመራቂ እና መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፤ ለሁሉም ተመራቂ እና መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የዘንድሮው የትምህርት ዘመን እየተጠናቀቀ ስለሆነ፣ ተመራቂ ተማሪዎች በሪጅስትራል ኦፊስ በተገለፀው ቀን ፤ ተመራቂ ያልሆናችሁ ደግሞ ከነገ ጀምሮ እስከ "ሰኔ 19/2018 ዓ.ም" ድረስ የክሊራንስ ሂደታችሁን በአግባቡ አጠናቃችሁ ከወዲሁ ሻንጣችሁን እና ጉዟችሁን እንድታመቻቹ በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን። ይህንን አስቀድመን ለማሳወቅ የወደድነው፣ ከ "ሰኔ 21/2018 ዓ.ም" ጀምሮ ግቢው ለተማሪዎች የሚሰጠውን ማንኛውንም አይነት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የሚያቋርጥ ስለሆነ፣ ተማሪዎች ይህንን ተረድታችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ከካፌ ውጪ (Non-Cafe) ለሆናችሁ ተማሪዎች ወርሃዊ የኑሮ መደጎሚያ (Cost-sharing) ገንዘባችሁን በተመለከተ፤ ምናልባትም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት (ቢበዛ በሁለት ቀናት ውስጥ) ወደ የባንክ ሂሳባችሁ ገቢ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን። ከህ.ጤ.ሳ.ኮ ተማሪዎች አገልግሎት ዲን @uogzena

የማያልቁ የመሰሉ እነዚያ አመታቶች የማይነጉ የመሰሉ እነዚያ ምሽቶች በመጨረሻም ወደ ፍፃሜው ደረስን ምን አልባት አሁን ዳግም ግቢያችን ሊናፍቀን የሚችልበት ጊዜ እሩቅ አይደለም :: ስንት ዓመት አብረን ያሳለፍናቸው ወዳጆቻችንን የምንሰናበትበት ቀንም ቅርብ ነው አላልቅ ያሉን ቀናቶች አልቀው ለቀሩት ጥቂት ቀናቶች የምንሰስትበት ቀን ላይ ደርሰናል :: ተማሪ አንተነህ ከ GC campus ለተመራቂ ተማሪዎች አድርሱልኝ ብሎ የላከልን መልዕክት 🙏🏻 @uogzena

Count down started 1⃣1⃣day left for 2026 graduation

የመጀመሪያ ድግሪ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ከሰኔ 4 - 12/2018 ዓ/ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ተፈታኞች እንዲሁም አስፈታኝ ተቋማት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሁሉ እንዲያደርጉ አሳስቧል። 🗓️ የ2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መርሐግብር (Exit Exam Schedule) ከላይ ተያይዟል። Via @uogzena

ጎንደር ዩንቨርስቲ የ አመቱን ትምህርት ያጠናቀቀቁ ተማሪዎችን እየሸኘ ይገኛል ተማሪዎች ወደየ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ሲሆን uogzena ዘንድሮም ለተማሪው ድምፅ እየሆነ ብዙ መረጃዎችንም እያደረሰ መልካም የትምህርት ዓመት አሳልፋችው ወደየ ቤተሰቦቻችው ለምትቀላቀሉ ዉድ ቤተሰቦቻችን መልካም የእረፍት ጊዜ እንዲሆንናልችው እንመኛለን :: በጉዞ ላይ ያላችው ሰላም ያግባችው ለመሄድ ያሰባችው መልካም ጉዞ እንመኝላችዋለለን :: አሁንም በግቢው የሚካሄዱ ሁነቶችን በጥራት እና በታማኝነት ማድረሳችንን እንቀጥላለን :: @uogzena

የምርቃት ቀን ሐሙስ ሰኔ 18 የሚሆን ይሆናል:: ዉድ ተመራቂ ተማሪዎች የታላችው @uogzena
የምርቃት ቀን ሐሙስ ሰኔ 18 የሚሆን ይሆናል:: ዉድ ተመራቂ ተማሪዎች የታላችው @uogzena

ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የአመቱን ትምህርት የጨረሳችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ስትመጡ የፋይዳ መታወቂያና የቲን ቁጥር  /TIN Number/ ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ምዝገባ ያለፋይዳ መታወቂያና ቲን ቁጥር  /TIN Number/ እንደማይደረግ እናሳውቃለን።

27/09/2018 ለሬሜዲያል ተማሪዎች በሙሉ ዛሬ ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ላይ በነበረው ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዘግይተው በመምጣታቸው በቀጣይ በነበረ ፈተና ላይ የተወሰነ ሰዓት ወስዷል። ስለሆነም ከነገ ጀምሮ የጠዋት 2:00 ሰዓት ተፈታኞች 1:30 ላይ በመፈተኛ ክፍሎች እንድትገኙ እያሳሰብን። በሰዓቱ ባለመገኘት ለሚፈጠረው የሰዓት መሸራረፍ ኃላፊነቱ የተማሪው መሆኑን እናሳውቃለን።

ውድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና አጋሮች እንኳን ደስ አላችሁ! ******** የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ምዘና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች
ውድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና አጋሮች እንኳን ደስ አላችሁ! ******** የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ምዘና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ፣ መምህራንና ተመራማሪዎች ፣ ተማሪዎችና ሰራተኞት እንዲሁም አጋር አካላት እንኳን ደስ አላችሁ! በ2026 የCenter for World University Rankings (CWUR) ዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር መሠረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚከተሉትን ደረጃዎች አስመዝግቧል፦ በኢትዮጵያ ካሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ 2ኛ ደረጃን ፣ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ የ4ኛ ደረጃን ሲያገኝ ከአፍሪካ 43ኛ ሲሆን እንዲሁም በዓለም ደረጃ 1,517 በአጠቃላይ 68.0/100 ውጤት በማስመዝገብ ከዓለም ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ከከፍተኛዎቹ 7.2% ውስጥ ሊካተት ችሏል። ይህ ታላቅ ስኬት የዩኒቨርሲቲው ማ/ሰብ እና የአጋር አካላት በጋራ በመቀናጀት በመማር ማስተማሩ ፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎቱ እየተከናወነ ያለው ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየላቀ በመምጣቱ ይህ ከፍተኛ ውጤት ሊመዘገብ ችሏል። ስለሆነም ለዚህ ያላሰለሰ ጥረታችሁ ለዚህ ልዩ ስኬት ደርሳችኃልና ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ! ወደፊትም ከዚህ የበለጠና የላቀ ስኬት ለማስመዝገብ የሚያበረታታ ውጤት ነውና በአንድነት ተባብሮ በመስራት ለተሻለ ውጤት እንነሳ! ******** ለልህቀት እንተጋለን! የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ግንቦት 27/2018 ዓ.ም.

Global Recognition, National Pride. *** University of Gondar Ranked 2nd in Ethiopia, 43rd in Africa, and is among the top 7.2
Global Recognition, National Pride. *** University of Gondar Ranked 2nd in Ethiopia, 43rd in Africa, and is among the top 7.2% of universities globally. The University continues to make its mark on the world through excellence in research, innovation, and academic achievement. **** Devoted to Excellence! Public Relations Directorate June 4, 2026 Follow us on: Facebook: https://www.facebook.com/TheUniversityofGondar?mibextid=9R9pXO LinkedIn: https://www.linkedin.com/school/university-of-gondar/ Twitter: https://twitter.com/UoGondar?t=rgtSo_84UZRyWznpPej3-g&s=09 Telegram: https://t.me/UofGondar WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaKhoG11XquVQkSDPM3F YouTube: https://www.youtube.com/@UniversityofGondarOffici-lv9ml

Greetings, All first-time Exit Exam candidates are required to complete identity verification using the National ID in order to sit for the exam. Please visit the link below to verify your identity: 👉 https://verify.ethernet.edu.et Video Guide: 🎥 https://youtu.be/6sH8UVac1Cg If you have any questions, please leave your comments in the comment section. Thank you. --- ሰላም፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የ መውጫ ፈተና የሚትወስዱ ተፈታኞች በሙሉ፣ ፈተናውን ለመውሰድ በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) የመለያ ማረጋገጫ ማረጋጋ ገጥ ይጠበቅባችኃል። መለያዎን ለማረጋገጥ የሚከተለውን ዌብ ሳይት ይጎብኙ፡ 👉 https://verify.ethernet.edu.et @Uogzena