cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Thoughts

ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው? እናንተስ ጎራ አትሉም? Since: Dec-10-2022 discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

Більше
Рекламні дописи
2 618
Підписники
+424 години
+257 днів
+32630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Repost from ካሲና🫳🏿
እንባ እንባ ይለኛል      ይተናነቀኛል እንባ የት አባቱ ደርቋል       ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል   ስቆ ላይስቅ ጥርሴ     ስቃ እየነደደች መከረኛ ነብሴ             ፨ ፨ ፨ ❇️በአሉ ግርማ
Показати все...
👍 15🔥 6
"ሆጵላስ!" ይሄን ያውቃሉ ? ይህ ቃል የተፈጠረበት አጋጣሚ  አንድ ፈረንጅ በሀገራችን የድንጋይ ናዳ መንገድ ይዘጋበታል። ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ድንጋዩን ከዘጋው መንገድ ለማስወጣት አብሮ መግፋት ይጀምራል። እየገፋም "hopeless!" (ተስፋ የለሽ!) ይላል። ይህንን በሰሙት የአበሻይቱ ልጆች አማካኝነት "ሆጵላስ!" ማበረታቻ ሆና በቋንቋችን ውስጥ ተፈጠረች። ሆጵላስ ደና ደሩ 😂
Показати все...
😁 48👍 6 1
Repost from ካሊድ አቅሉ
Denzel 🙏🙏
Показати все...
13🔥 5
Repost from ኑ እናንብብ
" ያ ደግ ሰው በመንገዱ እየኼደ ሳለ ሽፍታ አገኘ፡፡ ያ ደግ ሰው፤ “ሰላም ለአንተ ይኹን! በዚህ ስፍራ ለምን ብቻህን ትዘዋወራለህ?” አለው። ያ ሽፍታም፡ “እኔ ሽፍታ ነኝ! ለዚህም ነው በዚህ ሰዋራ ስፍራ የምዘዋወረው:: ይልቅ ምን ይዘሃል? ወዲህ በል የያዝኸውን ኹላ! አምጣው!” አለው። ያ ደግ ሰው፡ “ለምን ግን ሠርተህ አትበላም? ሰው የደከመበት ገንዘብ ላንተ ምን ያደርግልሃል?" አለው፡፡ ያ ሽፍታ እየሣቀ፡ “ስማ! ማር በልተህ ታውቃለህ?" አለው:: ያ ደግ ሰው፡ “እንዴታ! በደንብ አድርጌ ነዋ የምበላው!" አለው:: ያ ሽፍታ፡ “ሠርተህ ነው ወይስ ከንብ ቀምተህ ነው? በጭስ እያስፈራራህ፣ እንዳትታይ በጭንብል እየተከለልህ ነው ንብ ለፍታ የሠራችውን የምትቀማት” አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፤ ኹሉም ስው “ለፋኹበት” በሚለው ጕዳይ ወስጥ መዝረፍ እንዳለበት ዐወቀ። ከዚያም፣ ለሽፍታው “ብዙ ገንዘብ የለኝም:: ምናልባት ይህቺ ኹለት ፈረንካ ከበቃችህ እንካ” አለው፡፡ ያ ሽፍታ፡ “ለዛሬው ምሬሃለኹ፣ ከዚህ በኋላ ግን በማያገባህ ጕዳይ አትግባ" አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፡ “እንኳን ማርኸኝ እንጂ በል ደኅና ሰንብት" ብሎት ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ፡፡ በመንገዱም ላይ ሳለ እንዲህ እያለ እያሰበ ነበር፡፡ “አኹን ግን የእውነት እንቁላልን ዶሮ የምትሸጠው ቢኾን ዋጋው ስንት ይኾን ነበር? ሰው ከዕቅፏ ፈልቅቆ ይወስድባታል እንጂ መቼ ይጠይቃታል። እና፣ ከደምና ከዐጥንቴ ያልሠራኹትን ገንዘብ ሽፍታ ወስዶብኝ እንዲህ ከተንገበገብኹ ልጅ ይኾነኛል ያልኹትን፣ ከብቤ ያኖርኹትን ቢያነሡብኝ ቀድሜ አበድኹኝ” እያለ ኑሮውን እየታዘበ ኼደ፡፡ " " ግርባብ ያ ደግ ሰው " በፍቃዱ አየልኝ መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል :: @jafbok
Показати все...
16👍 5
Repost from እንማር
#ዋጋህን_እወቀው! መነበብ ያለበት አስተማሪ ታሪክ "ትናንት ማታ አንድ ቪዲዮ እያየሁ ነበር። ሰባኪው የመቶ ብር ኖት ይዟል። እንዲህ ሲል ሰማሁት 'ይህ የብር ኖት እንደታተመ ምንም ዓይነት መጨማደድ አልነበረበትም። ከዚያ በኋላ ግን ሰዎች፦ ➡️እጽ ለመግዛት ተጠቅመውታል። ➡️ ለዝሙት ከፍለውታል። ➡️ጭቃ ውስጥ ነበር። ➡️ተቀዷል፣ ➡️ጠርዞቹ ተቆርጠዋል። ✅️ከዚህ ሁሉ ቀኋላ ይህ የመቶ ብር ኖት አሁን ዋጋው ስንት ነው? አሁንም ዋጋው ያኔ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ዋጋ ነው። አምላካችንም እኛንም የሚያየን እንደዚህ ነው። ያለፈው ታሪካችን ምንም ሆነ ምንም፣ የቱንም ያህል የተጎዳን እንሁን፤ ለእሱ ዋጋችን ያኔ ሲፈጥረን እንደነበረው ነው።' " ✅️👉#የተሰቀለው_ንጉሥ መጽሐፍ (አዲስ መጽሐፍ) 👉 #The_Crucifixion_of_the_King_of_Glory ✅️@Enmare1988 ✅️✅️@Enmare1988
Показати все...
7
ሁለቱም እኩል ደወሉ እነማናቸው? ሳባ እና ዳዊት ለማንኛቸው እንደማነሳ ግራ ስጋባ ተዘጋ ሳባ መልሳ ደወለች እሱ text ላከ "ሚኪዬ ተቆጣኝ" አለቺኝ ይሄንን ሀረግ አውቀዋለው  የእሱም መልዕክት "ዛሬ ቀኑ ፈካ አላለብህም?" ይላል የሁለቱም ሀሳብ ትርጓሜው አዲስ ሰው ተዋውቀው ተመችተዋቸዋል ማለት ነው። "ኧ? ተቆጣኛ" አለቺኝ ምን ልበላት? ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው እሷ የመጨረሻ ኮስታራ ወንድ አጠገቧ የማታደርስ አይነት ሴት ናት የመጀመሪያዬ ጥሎኝ ሲሄድ ነው እንደዚህ የሆንኩት ትላለች እሱ ደግሞ የለየለት ሱሰኛ ነው እሱም  "ተከድቼ ነው" ነው ሰበቡ   በአንድ የተቀደሰ ልበለው የተረገመ ቀን አስተዋወቅኳቸው አጠገባቸው እኔ የሌለው ያህል በነፃነት ተሸኮረሟመሙ ከዛማ በቃ እፍ አሉ ሌላ ሰው የሌለ ያህል በየጎዳናው በየጥጋጥጉ በየቦታው አብረው ታዩ ከዛ ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳያብራሩልኝ በቃ ተደባበርን ብለው ተለያዩ ከዛ ዳዊት የሆነ ቅዳሜ ቀን መጥቶ "በቃ ንሰሀ ገብቼ መጣሁ ለእስከዛሬው ከዚ በኋላ ሱስ ደጅ ብደርስ" ብሎ እየተንጎራደደ ነገረኝ "ወገኛ! ሲሉ ሰምተሀል" ብዬ ችላ አልኩት እውነቱን ነው ብዬ አላሰብኩማ!! እሱ ግን አምርሮ ኖሯል እንዳለውም እርግፍ አድርጎ ተወው ሳባ እንዲተው እንዴት ትፈልግ እንደነበረ አስታውሼ "በእሷ ምክንያት ነዋ?" ብዬ ስጠይቀው ፊቱ ልወውውጥ ብሎ "ምንም ከሷ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም" አለኝ መልሴን ከፊቱ ላይ ስላገኘሁ "እሺ" አልኩት በሳምንቱ ከሳባ ጋር ተገናኝተን እያወራን እያለ በመሀል "እና በቃ ረሳሽው?" አልኳት ፊቷ ድምን ሲል እያየሁት "ማንን" አለቺኝ "ሳባ አትቀልጂ የእውነቴን..." ስላት ስልኳ ጠራ "ዳጊ" ይላል "ወዪዬ ዳጊዬ"  ብላ አነሳችው ዳግም ሲቆላመጥ ዳጊ ቆይ ዳጊዬን ምን አመጣው?! ደግሞ እኔ የማላውቀው ዳግም ማነው? እያልኩ ሳሰላስል "እኔም ናፍቀኸኛል እንገናኛለን" ብላ የውሸት ጥርስ በጥርስ ሆና ዘግታው "ዳግም ማነው" ስላት "አለ ባክህ የሚያዝገኝ" አለች "ፈገግታሽ እያዛገሽ አይመስልም" አልኳት "እ" አለች ከስልኳ ላይ ቀና ሳትል ከእጇ ላይ ነጥቄ ሳየው "እዩ" ይላል "መቼ ነው የማገኝሽ" ብሏት ሳትመልስለት ነው የተቀበልኳት "ተው ይደብረዋል ልመልስለት" ብላ መልሳ ወሰደችው "ምንድነው" አልኳት ዝም አለቺኝ የመጀመሪያው ፍቅረኛዋ ዝምተኛ አደረጋት የኔው ጉድ ጋር ስትለያይ ደግሞ የማንም ሆነች እሱ ደግሞ የመጀመሪያዋ ሱስ ውስጥ ዘፈቀችው ሳባ ስትተወው ደግሞ ሱስ ለምኔ አለ። ዛሬ ሁለቱም አዲስ ሰው እንደተዋወቁ እና ያ የተረገመ "ልዩ ስሜት" ስለተሰማቸው ነው የደወሉልኝ። እሺ አሁንስ ደግሞ እንዴት ያደርጋቸው ይሆን ምን አይነት ተፅዕኖ አሳድሮ ምን አይነት አሻራ ጥሎባቸው ያልፍ ይሆን? "ሄሎ ሚኪ አይሰማም እንዴ ተቆጣኝ እያልኩህ እኮ ነው" አለቺኝ ለካ እያናገርኳት ነው "ለምን እቆጣሻለው ጥፋት እኮ አይደለም" አልኳት "በምን አወቅክ" አለች በጥርጣሬ "አዲስ ነገር አይደለም ይሄ ለሶሰተኛ ጊዜ ስናስተናግደው ነው ብቻ አንድ የምልሽ ምንም ነገር እንደዚ እንዲያናውጥሽ እንዳትፈቅጂ እሺ" አልኳት "እሺ" ብላ ስልኩ ተዘጋ ወዲያው ለዳዊት መለስኩለት "ገና ለገና ሌላ ሴት መጣች ብለህ ወደዛ ሱስህ እመለሳለሁ ብትል እፈነክትሀለሁ" ብዬ መለስኩለት ✍nani
Показати все...
17👍 12
Repost from ውብ ወግ
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ይህን👆 የገብረ ክርስቶስ ደስታን ገጠመኝ እና ስዕሉን ባየ ጊዜ ልቡ ተነካና ብዕሩን አንስቶ እንዲህ ሲል ተቀኘለት እዩት ይህን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ በቀይ እየወጋ በደም እየሳለው እንጨት አመሳቅሎ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው። ቀራኒዮ ሆነ የወጠረው ሸራ ጎለጎታ ሆነ የወጠረው ሸራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ። ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር ብሩሹን አሹሎት እንደጎኑ ጦር። እየወጋ ሳለው በጣም ጨከነበት ገብረ ክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ የቆዳው አይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ። እየወጋ ሳለው እየሳለ ወጋው ደሙ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው አገር። እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር እንዳንለው ቀይ በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ። በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው። ከቀናት ባንዱ ለት ሰዎች ሲሟገቱ በቀለሙ ጉዳይ ሲከራከሩበት በተመፃዳቂ የምሁር አንደበት። በአንዱ አፍ ሲጠቁር በአንዱ አፍ ሲነጣ መታገስ አቃተው ሰዓሊው ተቆጣ ስሜቱ ገንፍሎ በብሩሽ ጫፍ ወጣ ሀሳቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ። ሸራ ላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ አልወጣልህ አለው ፍቅርን ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ስሎ ፍቅርን ስሎ ስሎ በሳለው እየወጋ በደማው እየቀባ። ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይሄ አይደለም። እያለ እስኪናገር የስዕሉ አንደበት ገብረ ክርስቶስም ለክርስቶስ ’ሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት በነጩ ሸራ ላይ እስካሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት። ቀለም ቀይ ቀለም የደም ቀለም የጥላ ቀለም የሁሉም ነው እንጂ የማንም አይደለም ፍቅር ዘር አይደለም። @wegochi
Показати все...
❤‍🔥 14👍 1
You realize you wouldn't have learned how to ride a bike if someone you trusted hadn't let you go. God works differently
Показати все...
👍 2
Repost from ውብ ወግ
ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ስእል በሚያስተምርበት ወቅት ተማሪዎቹ የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ስለዉ እንዲያመጡ በቤት ስራ መልክ አዘዛቸው ። ሁሉም በመሠለዉ መልክ ኢየሱስ ክርስቶስን ስሎ ሲያመጣ አንድ ተማሪ ግን የክርስቶስን ስዕል በጥቁር ወይም አፍሪካዊ መልክ ስሎ ያስረክባል ። ገብረ ክርስቶስ በስእሉ ተገርሞ ለምን ክርስቶስን ጥቁር አድርጎ እንደሳለው ሲጠይቀው ተማሪው «ክርስቶስ ፈረንጅ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ፈረንጆች በጣም ጨካኞች ናቸው። ኢየሱስ ነጭ ሳይሆን ጥቁር ነው» ብሎ ይመልሳል። ይህን ግዜ ነው ገብርዬ ወደቤቱ ሲበር ሄዶ ኢየሱስ ክርስቶስን ቀለም እንዳይኖረው ፣ ዘር እንዳይኖረው ፣ ነገድ እንዳይኖረው አርጎ ከፀጉሩ እስከእግር ጥፍሩ ድረስ በደም ለውሶ ሳለው። ገብርዬ በስዕሉ "ፍቅር ዘር የለውም። ፍቅር ቀለም የለውም። ፍቅር የነገድና የቀለም አጥርን ይሻገራል። ክርስቶስ ሲያድነን ዘር ቀለም ፆታ አልመረጠም። ክርስቶስ ያዳነን በደሙ እንጂ በቆዳው ቀለም ወይም በዘሩ አይደለም። በመስቀል ላይ የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ለሁሉ ይበቃል።እኔነት ባለበት ፍቅር በዚያ የለም!!!" ሲል ይህን ዘመን ተሻጋሪ ስዕል ሊስለው ችሏል። ገጣሚና ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ኢትዮጵያዊ ባይሆን ኑሮ በዚህ ስዕሉ ከዳቪንች እኩል በመላው ዓለም እውቅና በተጎናጸፈ ነበር። . እንኳን አደረሳችሁ!!! @wegochi
Показати все...
26👍 11