cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ካሊድ አቅሉ

"ከባባድ ጥያቄዎች በቀላል መልሶች ይረታሉ" ሀሳብ ለማስፈንጠር.... @kalu30 Facebook - https://www.facebook.com/profile.php?id=100007449047737

Більше
Ефіопія1 792Амхарська1 407Книги2 119
Рекламні дописи
12 288
Підписники
+724 години
-447 днів
-17530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ጨረቃ ያለበት ( ካሊድ አቅሉ) በየወንዙ በየአውራጃው ፋኖስ ሆነሽ ትዞርያለሽ ልጠይቅሽ አንድ ሚስጥር ሻማ ማብራት ትችያለሽ? ወይንስ የጋን መብራት ነሽ ብቻሽን በርተሽ ከዛ ምትከስሚ ጨረቃ ያለበት እያሸረገድሽ ድቅድቆች መንደር አውቀሽ ምጠሚ !
Показати все...
👍 18 12🥰 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ማንነታችንን ለማወቅ ትንሽ መሞት ያስፈልገናል ። የሚገርመው ነገር ፍልስፍናችንም ሆነ ፍርሃታችን ደስታና ሀዘናችን ከሆድ እርቆ አይሄድም ። በዓሉ ግርማ ( ከአድማስ ባሻገር)
Показати все...
👏 28 11👍 5
Repost from ካሊድ አቅሉ
( ፍቅር የመሰለሽ ) ✍ ካሊድ አቅሉ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ሰውን ለማስታወስ ምስል ምን ያረጋል በድኑ ገፅታ ነፍሱን ነው መከተብ በልብ ህያው ቦታ። ብዬ ብናገርሽ በጫወታ መሀል . . . ከስልክሽ እስክሪን ፈጥነሽ አጠፋሽኝ በቃሌ ተከፍተሽ አንቺ ከጅምሩ መሸነጋገል ነው ፍቅር የመሰለሽ ) ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ @kalidakelu
Показати все...
👍 30 14😁 8👏 4🤔 2
ጥቅም የማይሰጥ የምሽት ጥላ ( ካሊድ አቅሉ) ቃል ብሰድር አቃንቼ ፤ መልክ አስይዤ ባሻግረው ሌጣ አረገው ማንነቴን ፤ በሌሎች ዓይን አስወገረው ይሁን ብዬ ብንገላታ ፥ ቀን ላጠራ ብንደረደር የዕለት ቅፅበት ማሰብ እንጂ ለነገ አያውቅ አሉኝ ሀገር ። " ጥቅም የማይሰጥ የምሽት ጥላ " ብለው ይዙታል አብረው ሲሰግዱ ያመፀን ገላ፥ ከንፈር ለመምጠጥ ይሰናዳሉ ከዳር ለማውጣት ጥልቁን ማውጠንጠን የአቃፊ ክንዱ ይሰባብራል እንዳንራመድ ከረጋገጠን ! እስኪነጋ ተነቃቅተው ፣ በድቅድቁ ቦታ ስተው ሲዟዟሩ የነበሩ ድንገት ፀሃይ ብትከሰት ለመተኛት ተማከሩ የዶሮ ጩህት ፣ አይንን ለመክደን ከጠቀማቸው ለማንቀላፋት ደውሉን ቆሜ ማቃጭለውን እንዴት አይዩኝ እኔን በእንቅፋት ?
Показати все...
👍 9👏 5
የኔዋ ዮዲት ጉዲት ! (ካሊድ አቅሉ) ፨ ዕለቱ ሰኞ ነው ክላሱ ጢም ብሎ ብሎ ሞልትዋል ዶክተር አብርሃም በጣም ተፈሪ የግቢያችን መምህር ነው። ከዚ ቀደም የተለያዩ ኮርሶችን ሰቶናል " በሚቀር ተማሪ አልደራደርም !" ይላል ከሶስት ቀን በላይ ቀሪ አለን ማለት F እንደሚሰጠን አንጠራጠርም ለዛ ቀደም ብለን መገኘት ልምዳችን ነው ። በዚህ ሴሚስተር የሚሰጠን ኮርስ ማትስ ነው ፣ እንደተለመደው ክላሱን መፈናፈኛ አሳጥተን ሞልተናል ስምንት ሰዓት ላይ ነበር ክፍሉ የጀመረው በሚወብቅ ሙቀት እንቅልፍ እንቅልፍ በሚል ድባብ የማትስ ውስብስብ ቁጥሮች እሹሩሩ እያሉ አንድ በአንድ እያስተኙት ነው። እኔ ማልተኛበት ትልቅ ምክንያት አለኝ እሷም ዮዲት ናት! "ዮዲት ጉዲት" እላታለው እኔ በምግባር ከዮዲት ጉዲት ጋር ብትፃረርም ልቤን ጉድ ያረገች የፍቅርዋ ምርኮኛ ነኝ፣ውብ ናት ውብ መልክ ታድላ ሰው እሱን ትቶ ስለ ውብ ፀባይዋ ሚያወራላት እፁብ ድንቅ ወዳታለው እሱን ማውቀው ደግሞ ማትስን በፍቅር ስማር ነው የሰው ልጅ የማይወደውን ነገር በሚወደው ነገር በኩል ሲያሻግሩለት በደስታ እንደሚቀበለው ያወኩት ዬዲትን እያየው ማትስ ማትስ ሳይለኝ መጨረሴን ሳይ ነው ። ግን ሙቀቱ በብርታቱ አልቀጠለም በሀይል ለመጣው ንፍስና መብረቅ ቦታውን ቀስ እያለ ለቀቀ በምትኩ ፍጡር ሚቋቋመው ማይመስል ዝናብ በመብረቅ ታጅቦ እንደ ጉድ ወረደ መምህራችንም አብርሃም "ኦኦ ከበድ ያለ ነው!" ብሎ ዝናቡ ሲበረታ በሩ ጋር ወዳለችው መቀመጫው አቀና ደግነቱ ትንሽ ነበር የቀረን 9:40 አካባቢ ነው ዝናቡ የበረታው መውጫችን ደግሞ አስር ሰዓት ሁሉም ተማሪ ግልግል ባለ ፊት መንጠራራት እና ፊቱን ከተኛበት መቀስቀስ ጀመረ ። "ዣንጥላ መያዜ በጀኝ እንጂማ ጉዴ ነበር" አለች ውጪ ውጪውን በነዛ ውብ አይኖች አሻግራ እያየች " እርግጠኛ ነኝ ቅድም ከቤት ስትወጪ ለፀሐይ ብለሽ ነው ይዘሽ የወጣችዋ ? " አልኳት መልኮችዋን እያየው "አዎ አይገርምም አሁን ደግሞ ለዝናብ ሆነ" "ህይወት እንደዚህ ናት! ለፀሐይ የታሰበ መከላከያ ከዝናብም ያወጣል እውነተኛ ወዳጅም እንደዚሁ ነው ወቅት ሳይመርጥ የሚሆን ጥላ " ብዬ ንግግሬን እንዳበቃው የሆነ ነገር እንደገባት ለማሳየት አንገትዋን ነቀነቀች እኔም ዣንጥላዋ መሆንን እንደዛ ቀን ናፍቄ አላውቅም ከሁሉም ነገር ልከልላት እሷ ላይ የመጣ ዶፍና ሀሩር እኔን አጊንቶ እንዲመለስ . . . . .
Показати все...
👍 4
- እንደ ሀገር የወደቅነው በቁልቁለት ፍጥነት ዳገቱን ለመውጣት የሞከርን ቀን ነው ! ( ካሊድ አቅሉ)
Показати все...
👍 32 9💯 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 40 11💯 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የደመቁ ገፆች . . . . . . እንዲህ ስትልም ተጠምደሃል ፦ አንዳንዴ መስኪድ የምሔደው ለማንቀላፋት ነው " " ከፈጣሪ ጋር በሠላም የሚኖር ብቻ ነው በስግደት ላይ እያለ እንቅልፍ የሚወስደው ። " ቃዲው ቢገርመውም ዑመር ተበርታትቶ ቀጠለ ፦ " ተአምኖን እንደ አንዳንዶች ፣ የፍርድና የፍርሀት ጉዳይ አድርጌ አልቆጥረውም ። እነሆ የኔ ፀሎት ፦ ፅጌሪዳዋን ማድነቅ ፣ ክዋክብትን መቁጠር - ማስላት ፣ የፍጥረት - ዐለሙን ትንግርት መዘከር . . . ስለ ሰብአዊ ፍጡር - ስለዚህ ድንቅ የአምላክ ቁራጭ ፍጡር - መገረም ነው። አእምሮውን ዕውቀት፣ ልብን ፍቅር የሚጠማው . . . የህዋሳቱስ ንቃትና እርካታ ! . . . ድንቅ ዘድንቅ ፍጡር!" " አድምጠኝ ወጣቱ ጓዴ ሆይ ፣ ሀያሉ እግዜአብሔር ለሰው ልጅ የሚለግሳቸው ውድ ነገሮች ሁሉ ተለግሰውሃል ። አእምሮ ፣ አንደበት ፣ ጤና ፣ መልክ ፣ የዕውቀት ፣ ጥማትና የሕይወት ጉጉት ። የሰው አድናቆትና እንዲሁም - አይጠረጠርም - የሴቶች አፍቅሮት ። የአርምሞ ክሂሎት እንዳልነፈገህም እተማመናለሁ። ያለ አርምሞ ፣ ያለ ዝምታ ከላይ የዘረዘርኳቸው ሁሉ አይጠቅሙም ። " " እንዴ! የማስበውን ሁሉ መናገር እንድችል እስከ እርጅና መጠበቅ አለብኝ ?" " ያሰብከውን ሁሉ መናገር እስክትችል የልጅ ልጆችህ ያረጃሉ ። የምንኖርበት ዘመን የምስጢር መያያዝና የመፈራራት ዘመን ነው። ሁለት ፊት ያሻሃል። አንዱን ለሰፊው ህዝብ የምታሳየው ፣ አንዱን ለራስህና ለፈጣሪ የምትይዘው። ዓይኖችህን ፣ ምላስህንም ጭምር ሳታጣ እንድትኖር ከፈለግህ እንደሌሉህ አርገህ ቁጠራቸው ። " ----------------------------------- ዑመር ኻህያም እንደፃፈው ረ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ እንደተረጎሙልን ።
Показати все...
👍 21👏 7
አፌን እየያዘች ልነግራት ስል ሀቁን መች ተገነዘበች? መኖርዋን ስጠብቅ መኖሬ ማለቁን ! (ካሊድ አቅሉ)
Показати все...
የሚስጥሮች ሚስጥር ( ፍቅር!) ካሊድ አቅሉ ከኢልሃም ጋር ሰባ ደረጃን ወደ ታች ጥለን ወደ አራት ኪሎ እያዘገምን ነው ። ጭር ያለ ድባብ ሰማዩ ላይ ሰፍንዋል ውር ውር ሚሉት መኪኖች ከምሽት ጋር ጥል ያለባቸው ይመስል መንገዱን ለቀዋል ስንራመድ ኮቴያችን ማጀቢያ ድምፅ ሆኖ ንግግራችንን ይከተላል። ድሮ የተራመደ ሁሉ የሄደ ይመስለኝ ነበር ስሩ የገባኝ መድረሻዬን አጥርቼ ሳልወስን ብዙ ተራምጄ መጨረሻዬ ቀርፋፋ የሆነበትን ዘመን ሳስታውስ ነው፣ብቻ እየተራመድን ነው እርምጃ አጋር ይመርጣል እንጂ ቶሎ ለማለቅ ማን ብሎት ሰፈራቸው ስንደርስ ሁለታችንም ቆምንና የመሰናበቻ ንግግርዋን ጀመረች " እኔ ምልህ ካሉ አንድ ነገር ልንገርህ ወደ ጆሮዬ ጠጋ በል" እለችኝ ትዕዛዝ ባዘለ ድምፀት " "ማንም የለም እኮ እንደዚሁ ንገሪኝ " አልኳት ግራ ቀኙን ባይኔ እያማተርኩኝ ዝም ብላ በጭንቅላትዋ እንድጠጋት በምልክት ነገረችኝ ምን ልትነግረኝ ይሁን በሚል ጉጉት ጆርዋ ውስጥ ተወሸኩኝ በለስላሳ ድምፅዋ በሚያስተጋባ ቃል አጣጣል "እወድሃለው" አለችኝ ደነቀኝ መውደድዋን በሚስጥር እቃ አሽሞንሙና እኔ ጋር ስታደርሰው ከበፊቱ በላይ ክብደቱ ገዘፈብኝ ። ተናግራ እንደ ጨረሰች በዝግታ ከጆሮዋ ዋሻ ወጣው፣እኔን በተራዬ ከጆሮዋ ግርጌ ሄጄ መልስ በቃል አልሰጠዋትም ግን ቃላትን በሚገዳደር ሀይል አቅፌ ስሬ አስገባዋት ። አያያዙ ያማረ ሚስጥር ተንደርድሮ ተራ ወይንም ወረትን መሳይ አልባሌ ነገርን አይመስልም እንዳይጨማደድ በወጉ ያጠፍነው ፍቅር በመተዛዘን ካውያ እየተኮስነው እንደተዋበ አለ እራሱን ነገ በሌላ ውብ ሚስጥር ለመግለፅ እየተዘገጃጀ . . . . . .
Показати все...
21👍 4😁 2🔥 1