Abu Umer Ibnu Sadik
Відкрити в Telegram
#ቁርአንእናሀዲስ #ቅድሚያ_ለተውሂድ_እና_ለሱና #የሰለፊይ_ኡስታዞች_ሙሀደራዎች ፡ ፡ ፡ ፡ #የተለያዩ_ዲናዊ_ፅሁፎች #የደጋግ_የቀደምቶች_ታሪክ
Показати більше8 264
Підписники
+1024 години
+1657 днів
+58330 днів
Архів дописів
8 264
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ይህ የሚቀጥለው መልእክት የሸይኽ ሙሀመድ አረብ ልጅ ነው አብዱልአዚዝ ይባላል በቆቦ ወረዳ ከሸይኽ ሁሰይን አባስ ወርቄ የሚቀራ ልጃቸው ነው መለክቱን አንብባቺሁ ዱአ አድርጉልት
አሰላሙ አለይኩም ወሰህሙቱሏሂ
ወበረካቱሁ ውድ የኢትዮጲያ ሰለፍዮች በሙሉ
አባቴ ሸይኽ ሙሀመድ ዓረብ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ዱዓ አድርጉለት እና በ16 አመቴ ነው ከቤተሰቦቼ ተለይቼ ወደ ቂርአት የሄድኩት እና ቂርአት ቦታ ላይ 2 አመት ከ4 ወር ቆይቻለሁ እና አባቴ ምን ይለኛል
ልጂ በናፍቅም ቂርአት እስከሆነ ድረስ እችለዋለሁ እና ጠንክርልኝ በእኔ ቦታ እንድትተካልኝ ይለኝ ነበር
አደራ ልጄ በመንሀጀ ሰለፍ አደራህን
እኔ የምፈልገው አንተ ተውሂድንና ሱናን ስታስተምር ማየት ነው ይለኝ ነበር
እና ከአሁን በፊት ወለጋ ልሄድ ስል ልጄ ጠንክር ረመዳን ሲደርስ ትመጣለህ
ፊቂህን ( ቁዱሪይን ) ጨርሰህ ትመጣለህ
አለኝ ረመዳን 3 ወር ከ15 ቀን ሲቀረው
(ቁድሪይን )ልጨርስ 28 ቀን ሲቀረኝ
የአላህ ፍቃድ ሆኖ አባቴጋ ሳንገናኝ ወደ አኼራ ሄደ
إنا لله وإنا اليه راجعون
እና ውድ ወንድሞቼ ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው
አላህ የአባቴን አላማ የማሳካ እንዲያደርገኝ
አባቴ በኔ ምክኒያት አጅር የሚያገኝ እንዲያደርገው እኔንና እናቴን እንዲያሶብረን እንዲሁም ታናሽ ወንድሚንም እህቶቼንም
አላህ ሶብሩን እንዲሰጠን ከልባችሁ ዱዓ አድርጉልን
በየ ቻናሉ ሼር አድርጉልኝ ለሁሉም እንዲዳረስ
ባረከሏሁ ፊኩም
أقول لولَد الشيخ، أعني عبد العزيز الطالب ولأهل الشيخ جميعًا: اصبروا واحتسبوا الأجر عند الله، واعلموا أنَّ لله ما أخذ، وله ما أعطى، وكلُّ شيءٍ عنده بأجلٍ مسمًّى.
فلا تجزعوا، ولا تيأسوا من رحمة الله، بل أحسنوا الظنَّ بربكم، وأكثروا من الدعاء للشيخ، واسألوا الله أن يغفر له ويرحمه، ويرفع درجته في المهديين، ويجعل ما قدَّمه من علمٍ ودعوةٍ وصبرٍ في ميزان حسناته.
نعم فالشيخ قتل مظلوما وله أسوة بسلفنا الصالح
فهذا عمر بن الخطاب رضي الله عنه قُتِل مظلومًا، في الصلاة
وهذا عثمان بن عفان رضي الله عنه قُتِل مظلومًا،
وهذا علي بن أبي طالب رضي الله عنه قُتِل، وكثير من السلف الصالح
ووفقك الله ياعبد العزيز ماتمناه أبوك رحمه الله رحمة واسعة وأسبغ عليك وعلى أهلك صبراجميلا وثبتك الله
على الحق المبين والصراط المستقيم
8 264
👉 ከሸይኻችን ሞት ምን ተማርን ?
ሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ የሚገርሙ ሰው ነበሩ ። በስነምግባራቸው ፣ በመተናነሳቸው ፣ በፈገግታቸው ፣ ሁሉንም በውዴታ አይን በማየታቸው ፣ ለሁሉም በመታዘዛቸው የተለዩ ነበሩ ።
በጣም የሚገርመው ሸይኽ ሙሐመድ በሐሳብ ብቻ ሳይሆነ በተግባርም ጭምር ለሞት የተዘጋጁ ሰው ነበሩ ። ባለፈው አመት ዱና ላይ ከመሻኢኾች ጋር ለመገናነኘት አስፈሪውን የአካባቢው ሁኔታ አቋርጠው ሲመጡ ከፈናቸውን ይዘው ነበር የወጡት ! ቀናቸው አልደረሰም ነበርና ከፈኑን ይዘውት ዱና መጥተው ከመሻኢኾች ጋር ተገናኝተው ይዘውት ተመልሰው ለዛሬ ሆናቸው ! ይህ ማለት ሸይኽ ሙሐመድ ሁሌም ከፈን አብሯቸው ይኖር ነበር ማለት ነው ።
የአላህ ውሳኔ ቅሮት የለውምና ቀኑና ሰአቱ ሲደርስ እሱ በፈለገው ሰበብ ይህችን ምድር ተሰናበቱ ።
ውድ ሰለፍዮች የሱና ዑለሞች ሞት የኡማው ሞት ነው ። ወደ ሱና የሚጣራ ከቢዳኣ የሚያስጠነቀቅ ፣ ወደ ተውሒድ የሚጣራ ከሽርክ የሚያስጠነቅቅ ዓሊም ሲሞት ሲንቀሳቀስባቸውና ዒባዳ ሲያደርግባቸው የነበሩ ቦታዎች ያለቅሳሉ ! ኸይር ስራው ከምድር ወደ ሰማይ ይሄድ ስለነበር ሲቋረጥ ሰማይና ምድር ያለቅሳሉ ! እንደነዚህ አይነት ዑለሞች ለኡማው ብርሃን ናቸውና የሚተካቸው ከሌለ በእነርሱ ብርሃን ሲጓዝ የነበረው ማህበረሰብ ጨለማ ይውጠዋል ። ለዚህ ነው የዑለሞች ሞት የኡማው ሞት ነው የሚባለው ።
ውድ ሰለፍዮች ኒዕማ በመወገዱ እንጂ አይታወቅም እንደሚባለው የዑለሞቻችንን ጥቅም አውቀን በህይወት እያሉ እንጠቀምባቸው ፣ እናክብራቸው ፣ እናግዛቸው ፣ ደረጃቸውን እንወቅላቸው ፣ ከስር ስራቸው እየሄድ ከብርሃናቸው ፍንጣቂ እናጠራቅም እንጂ የቆሻሻ ገንዳ ተሸክመን እየዞርን ድክመታቸውን እየለቀምን አናጠራቅም ። ይህ እነርሱን ባይጎዳም የኛን ዱንያና አኼራ ያበላሻል ። ደካማ ጎን የሌለበት ዓሊም የፈለገ ሰው ከመላኢካ ጋር ሄዶ ይኑር ! ምክንያቱም የሰው ልጅ ሆኖ ደካማ ጎን የሌለበትና የማይሳሳት የለምና ! እንዲህ አይነቱ ተግባር ድንገት ለሚመጣው ሞት መዘጋጀት ካለበት ሰው አይጠበቅም ። ምክንያቱም የሰዎችን ደካማ ጎን የሰበሰቡበት የቆሻሻ ገንዳ ለቀብር ስንቅ የሚሆን የለበትምና ቆሻሻ ገንዳውን ጥለን ራሳችንን በተውበት አፅድተን ለቀብር የሚሆነንን ስንቅ እያጠራቀምን ለቀብራችን መዘጋጀት ይኖርብናል ።
አው ሞት ቀጠሮ የለውም ፣ ሞት እኛ የያዝነውን ፕሮግራም እስክንጨርስ አይጠብቅም ! እኛ ወደርሱ እየሄድን ነው እርሱም ወደኛ እየመጣ ነው የት እንደምንገናኝ አናውቅምና ጉዟችን የታሰበበትና የተዘጋጀንበት መሆን ይኖርበታል ።
ከሸይኻችን ሞት ሁሌም ለሞት መዘጋጀትን ነው የተማርነው ። እሳቸውን አላህ በእዝነቱ ይቀበላቸው ። ከወደዳቸው ባሮቹ ጋር ያኑራቸው ። የሳቸው መጨረሻ ያማረ ለመሆኑ አላህ ምልክቶች አሳይቶናል ። በዱንያ ፣ በጥቅም ሳይሸነገሉ ለሱና እየታገሉ እያሉ ወደ አኼራ ሄደዋል ። አሟሟታቸው ደግሞ ሸሃዳ የሚያስከጅልላቸው ነው ።
ማናችንም መጨረሻችንን አናውቅም ። ነገ ካለንበት ሐቅ እናፈንግጥ ወይም እንፅና የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው ። አንድ ሰው መጨረሻው አማረ የሚባለው በሐቅ ላይ ሆኖ ሳይቀየርና ሳይቀይር እቺን ምድር ሲሰናበት ነው ። ታዲያ የኛ ሁኔታ ምን ይሆን የሚለው የሁላችንም ፍርሃት ሊሆን ይገባል ።
በሀገራችን ዙሪያ ያሉ ሰለፍዮች ሸይኻችንን ለመቅበር አካባቢው ያለበት ሁኔታ ስለማይፈቅድ ውስጣችን እየታመመ የምንችለው ዱዓእ ማድረግ ብቻ ሆነ ። በአቅራቢያና አካባቢ ያላችሁ ሸይኻችንን መቅበር የምትችሉ ሰለፍዮች በሙሉ ሶላተል ጀናዛ ሰግዳችሁ እንድትቀብሯቸው አደራ እንላለን ። ክስተቱ ከባድ ቢሆንም ዘመድ አዝማድ ሶብር አድርጎ ከአላህ ምህረትን እየለመነላቸው ጀናዛቸው አላህን በሚያስደስት መልኩ መሸኘት አለበት ። በህይወት እያሉ የኖሩትን ሱና ዛሬ በሰው እጅ የገባው ጀናዛቸው ሊያጣው አይገባም ።
ውድ የቱሉ ጋና ሰለፍዮች ሆይ አላህ ፅናቱን ይስጣችሁ አደራ ሸይኻችንን በሱና ሸኟቸው ። የትኛውንም እንቅስቃሴ በሱና እንዲሆን የበኩላችሁን አድርጉ ። ቤተሰባቸውን በማፅናናት ከመቀበራቸው በፊት እዳ ካለባቸው ማጣራት ምናልባት ያስቀየሙት ካለ አውፍ እንዲላቸው በማድረግ መልካም አሻራ አኑሩ ።
በማንኛውም የሚያስፈልግ ነገር መላው ሰለፍይ ከጎናችሁ ነውና አብሽሩ ። በተለይ እዳ ካለባቸው አጣርታችሁ ቶሎ ከመቀበራቸው በፊት ንገሩን በአላህ ፈቃድ ለመክፈል ዝግጁ ነን ።
አላህ የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን ።
8 264
ሸይካችን ሙሀመድ ዐረብ አላህ ይረሀመቸውና በዘንድሮ #በዱናው ፕሮግራም ላይ #ከፈናቸውን ይዘው መጥተው አስለቅሰውን ነበር አሁን ግዜው ደርሶ ወደ አኼራ ሄዱ😪😪😪
8 264
Rabbiin Subhaanahu Wata'aalaa hojii gaarii Sheikh Mohammad
Arab qindeessaa fi fudhatee, qabrii isaanii jannata keessaa bakka
taasisaf. Akkaataa sunnaa irratti jiraatan sanaan jannata keessatti
isaan haa gammachiisuu, badii isaaniif dhiisee Jannatul Alfirdaws
keessa isaan haa qubsiisu.
ሸይኻችንን አላህ የጀነት ያድርግልን
በህይወት ያሉ ሰለፊይ ኡለሞችንም አላህ ረጅም እድሜ ከጤና እና ከፅናት ጋር ይስጣቸው!! አሚን ያረብ
8 264
▫️ ሸይኽ መሀመድ አረብ ረሂመሁሏሁ
♦️በአል_ወሰጢያ መድረሳ አለም ባንክ በእንግድነት ተገኝተዉ ከመግሪብ በኋላ ያደረጉት ሙሀዷራ
ርዕስ:- የአላህ መልክተኛ ያመጣላቹሁን ነገር ያዙ የከለከላቹሁን ነገር ተከልከሉ ከሚለዉን በመነሳት ተዉሂድን እና ሽርክን የዳሰሱበት አጠር ያለ መሳጭና ጣፋጭ ምክር
ሼር ሼር አርጉት ሁሉም ሰለፍይ ጋር እንዲዳረስ አላህ አጅራቸዉን ከፍያድርግላቸዉ የጥሩ ስራቸዉን ቀጣይነቱን ያብዛዉ ማረፍያቸዉን በጀነት ያድርግላቸዉ
http://T.me/Abuabdellah_As_Selefiy
8 264
Repost from አቡ ሙዓዝ (Abu muaz)
ወንድማችን ሸይኽ ሙሐመድ ጨረብ ወለጋ ወደ አኺራ ሂደዋል በዓለም ላይ ያላቹህ ሙስሊሞች ዱዓ አድርጉላቸው
ማረፊያቸውን ፊርደውስ አሏህ ያርግላቸው ልባችን ቢያዝንም አሏህ የማይወደውን አንናገርም
إن لله ما أخذ وله ما أعطى وكل شيء عنده بأجل مسمى
8 264
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ለአራተኛ ዙር የኪታብ ደርሳችንን ትምርት በዛሬው እለት ይጀመራል! 📚
ውድ የዳሩ አል-ሙእሚን ቤተሰቦች፤ በቁርአንና በሐዲስ እውቀት ላይ የተመሰረተውን የትምህርት ፕሮግራማችንን አጠናክረን ቀጥለናል!
በአሁኑ ዙር የምንጀምረው ታላቁን ኪታብ «አደርሱ አል-ሙሂማህ ሊአምቲል-ኡማህ» (ለኡማው ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶች)
🍀በሰለፍይ ኡስታዛችን :-
በኡስታዝ ኢብኑ ሙደሲር ይቀርባል
⏰ ሰዓት፦ ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ!
እውቀትን መቅሰም ለሁሉም ግለሠብ ግዴታ ነውና ቤተሰብና ጓደኞቻችሁን በመጋበዝ የኸይር ስራው ተካፋይ ይሁኑ።
🔗 የቻናላችን ሊንክ፦
Sher 👇👇Sher join join
https://t.me/Duru_al_muimin_Menhaj_Aselefiy
8 264
☄አመታት ወይም ቀናት ሊወስዱ ይችላል ነገር
ግን አሏህ ሲፈቅድ ሁሉም ነገር ቦታውን ይይዛል ።
እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነዉ ምንም ነገር ሰዓቱንና ጊዜውን ጠብቆ ነዉ ሚመጣው እስከዚያ ሰብር🤌
8 264
🌿🤍 ሰውን በሀብትህ አትመዝን፣ በውበቱም አትፍረድ፤ እውነተኛ ውበት በልብ ንጽሕና፣ በአንደበት ጥራትና በባህሪ መልካምነት ይታያል። ✨
8 264
ከሙመይዓና ከአስተሳሰቧ ማስጠንቀቅ!!
———
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ
“የሙመይዓን ተጣሪዎች ተጠንቀቃቸው፣ ሌሎችንም ከቢድዐህ ባለቤቶች ጋር መቀማመጥን፣ መተባበርንና የቢድዐህ ባለቤትን ማወደስን የሚያቃልሉትን (ተጠንቀቅ)፣ ከአንበሳ እንደምትሸሸው ሽሻቸው!።
ሙመይዓዎች ሰለፊዮችን የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመከተላቸው ምክንያት በአጥባቂነት ይወርፏቸዋል።” [አት-ተመሱኩ ቢሱነቲ ነጃት ገፅ 9]
#join ↘️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
8 264
Repost from N/a
🕐🆕ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም🎁
🗓የሚቀርብበት ጊዜ -
ጥቅምት 14 ቅዳሜ ምሽት
➡️ተጋባዥ መሻኢኾች:-
1⃣ሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን(🇧🇼)
🎧🔖በዲን ላይ መፅናት🔖
⏰️ሰአት:- በኢትዮ. አቆጣጠር 3:00
2⃣ሸይኽ አቡዘር ሐሰን (🇧🇼)
🎧🔖በሰለፍዮች መካከል መከባበርና መተዛዘን🔖
⏰️ሰአት:- በኢትዮ. አቆጣጠር 4:00
➡️ይህ ብርቅዬ ፕሮግራም እንዳያመልጥዎ::
👈👥ለሌሎችም ሸር በማድረግ ከቤተሰብዎ ጋር ይከታተሉ ይሳተፉ‼️
🌐 ቻናሎቻችን
⤵️
🎙️https://t.me/bilalmesji
💭https://s.imoim.net/tBLAMO?from=copy_link
