uk
Feedback
𝑻𝒓𝒆𝒆𝒑𝒍

𝑻𝒓𝒆𝒆𝒑𝒍

Відкрити в Telegram

መማር ከፈለክ ቀኖች ሁሉ አስተማሪ ናቸው። https://t.me/treeplh2 ለጥያቄና ለአስተያየት @yisakor24

Показати більше
986
Підписники
-124 години
+67 днів
+530 днів

Триває завантаження даних...

Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
жовт '26
жовтень '26
+11
в 0 каналах
вересень '26
+34
в 0 каналах
Get PRO
серпень '26
+19
в 0 каналах
Get PRO
липень '26
+53
в 1 каналах
Get PRO
червень '26
+26
в 0 каналах
Get PRO
травень '26
+38
в 0 каналах
Get PRO
квітень '26
+37
в 0 каналах
Get PRO
березень '26
+38
в 0 каналах
Get PRO
лютий '26
+12
в 0 каналах
Get PRO
січень '26
+15
в 0 каналах
Get PRO
грудень '25
+38
в 0 каналах
Get PRO
листопад '25
+36
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '25
+35
в 0 каналах
Get PRO
вересень '25
+40
в 1 каналах
Get PRO
серпень '25
+54
в 1 каналах
Get PRO
липень '25
+41
в 2 каналах
Get PRO
червень '25
+36
в 2 каналах
Get PRO
травень '25
+46
в 1 каналах
Get PRO
квітень '25
+34
в 0 каналах
Get PRO
березень '25
+38
в 0 каналах
Get PRO
лютий '25
+46
в 1 каналах
Get PRO
січень '25
+68
в 1 каналах
Get PRO
грудень '24
+88
в 1 каналах
Get PRO
листопад '24
+61
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '24
+56
в 0 каналах
Get PRO
вересень '24
+54
в 0 каналах
Get PRO
серпень '24
+114
в 0 каналах
Get PRO
липень '24
+96
в 0 каналах
Get PRO
червень '24
+88
в 0 каналах
Get PRO
травень '24
+76
в 1 каналах
Get PRO
квітень '24
+93
в 1 каналах
Get PRO
березень '24
+98
в 0 каналах
Get PRO
лютий '24
+112
в 0 каналах
Get PRO
січень '24
+96
в 0 каналах
Get PRO
грудень '23
+272
в 0 каналах
Get PRO
листопад '23
+200
в 1 каналах
Get PRO
жовтень '23
+319
в 0 каналах
Дата
Залучення підписників
Згадування
Канали
06 жовтня0
05 жовтня+1
04 жовтня+1
03 жовтня+4
02 жовтня+2
01 жовтня+3
Дописи каналу
ደና አመሻችሁ 😊 ስለ ንጉሱ ላወራ አይደለም ነገር ግን የህይወት እውነታን በሱ አንተርሼ ልንገራችሁ እናንተም ሀሳባችሁን አካፍሉኝ ። በህይወትህ የስኬት ጫፍ ላይ ስትሆን ጉልበትህ እና ተሰጥኦህ ጎል
ደና አመሻችሁ 😊 ስለ ንጉሱ ላወራ አይደለም ነገር ግን የህይወት እውነታን በሱ አንተርሼ ልንገራችሁ እናንተም ሀሳባችሁን አካፍሉኝ ። በህይወትህ የስኬት ጫፍ ላይ ስትሆን ጉልበትህ እና ተሰጥኦህ ጎልቶ ሲታይ የሁሉም ሰው ቀዳሚ ምርጫ ትሆናለህ። ወዳጅህ ይበዛል፣ ቤተሰብ ይከብሃል፤ ሁሉም ሰው በአንተ ብርሃን መሞቅ ይፈልጋል። ነገር ግን ጊዜ፣ እርጅና፣ ወይም የአቅም መገደብ ሲመጣ የሰዎች እይታ በቅፅበት ይቀየራል። ትላንት ያለሱ አይሆንም ይሉ የነበሩ ሰዎች ዛሬ እንደ ተራ ሰው መቁጠር ይጀምራሉ። አብዛኛው የዓለማችን ግንኙነት የተገነባው በአቋም እና በውጤት ላይ ነው። ህይወት በቆንጆ መስመር ላይ የምትጓዘው አንተ ጠንካራ ሆነህ ፍሬ እስካፈራህ ድረስ ብቻ ነው። ካያችሁ በመንገድ የተጣለ ፈረስ ዘመኑን ሙሉ ሲያገለግል የነበር ጉልበቱ ሲክዳው እና እርጅና ሲጫነው ያለፈ ውለታው አይታሰብም፤ ፈረሰኛው ሌላ ብርቱ ፈረስ ይፈልግና ይሄን ይጥለዋል፤ ሰወችም እንዲሁ ናቸው።አገልግሎትህን ስትጨርስ የትላንት ገድልህ ታሪክ ሆኖ፣ የዛሬው አቅም ማጣትህ ብቻ መነጋገሪያ ይሆናል። እናም የሰዎች ጭብጨባ ጊዜያዊ፣ የራስህ ማንነት ግን ዘላቂ ነው። ስለዚህ ጉልበት ሳለ፣ አቅምህ ጠንካራ በሆነበት ጊዜ ለራስህ ስራ፣ ለራስህ ሩጥ፣ የራስህን አለም ገንባ። መድረኩ ሲዘጋና ተመልካቹ ሲበተን፣ ባዶ መድረክ ላይ አብሮህ የሚቀረው ራስህ ብቻ ነህ።🚶‍♂ ሰላም እደሩልኝ❤️ @treeplh2 @treeplh2

2
በዚህ ዓለም ሰዎች የራሳቸውን ነውርና ጉድለት መሸከም ሲከብዳቸው ያንን ባህሪ በሌሎች ላይ ያንፀባርቁታል፤ የሌላውን ሰው ስህተት አጉልቶ የሚያሳይ መነፅር ማጥለቅ ይቀላቸዋል፤ ምክንያቱም የራሳቸውን እ
በዚህ ዓለም ሰዎች የራሳቸውን ነውርና ጉድለት መሸከም ሲከብዳቸው ያንን ባህሪ በሌሎች ላይ ያንፀባርቁታል፤  የሌላውን ሰው ስህተት አጉልቶ የሚያሳይ መነፅር ማጥለቅ ይቀላቸዋል፤ ምክንያቱም የራሳቸውን እውነተኛ ማንነት የሚያሳየውን መስተዋት ፊት ለፊት መጋፈጥ ከባድ ድፍረትን ይጠይቃልና። የሌሎችን ጉድለት የሚያወሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በውስጣቸው ትልቅ የባዶነት እና የፍርሃት ጩኸት አለ። የራሳቸውን ቁስል፣ ስህተት እና ነውር ላለማየት ሲሉ፣ የሌሎችን ስህተት በመፈለግ አእምሯቸውን ያዘናጋሉ። የሰውን ውድቀት መቁጠር ለራሳቸው ያልተፈወሰ የህሊና ህመም ማስታገሻ  አድርገው ይወስዱታል። ሰዎችን በመኮነን እና በመፍረድ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ የከፍታ ስሜት አለ። እሱ እንዲህ ነው፣ እሷ እንዲህ ናት በማለት ራሳቸውን ንፁህ እና ፍፁም አድርገው ለመሳል ይሞክራሉ። ነገር ግን ከሌሎች ሰዎች ጉድለት ላይ ቆመው የገነቡት የፅድቅ ማማ በትንሽ የህሊና ነፋስ የሚፈርስ በአሸዋ ላያ የተገነባ ቤት ነው። እውነተኛ ጥበብ የሚጀምረው አይንን ከውጭ ወደ ውስጥ በመመለስ ነው። የራሱን ጥላ በድፍረት ማየት የቻለ ሰው፣ የሰዎችን ድካም በክፋት እና በነቀፋ ሳይሆን በርህራሄ ይመለከታል። ምክንያቱም የሰው ልጅ ሁሉ ጎደሎ እና ተሳሳች መሆኑን ከራሱ ህይወት ተምሯልና። ዓለምን ለማየት መነፅርህን ፤ ራስህን ለማየት መስተዋትህን አንሳ። የተሻለ ሰው መሆን የሚቻለው የሰውን ነውር በማውራት ሳይሆን፣ የራስን ነውር በማረም ብቻ ነው። @treeplh2 @treeplh2   @treeplh2
116
3
አንዳንድ ምዕራፎች ሳይዘጉ ያበቃሉ ፤ ይቅርታ ፣ ማብራሪያ ወይም የሚገባውን ስንብት አያገኙም። 🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2
አንዳንድ ምዕራፎች ሳይዘጉ ያበቃሉ ፤ ይቅርታ ፣ ማብራሪያ ወይም የሚገባውን ስንብት አያገኙም። 🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2
139
4
አጋጣሚዎች የሰወችን ትክክለኛ ባህሪ ባያሳዩን ኖሮ ብዙ ምርጫዎቻችን እውነት መስለውን ነበር 🚶‍♂!! @treeplh2 @treeplh2
    አጋጣሚዎች የሰወችን ትክክለኛ ባህሪ ባያሳዩን ኖሮ ብዙ ምርጫዎቻችን እውነት መስለውን ነበር 🚶‍♂!! @treeplh2 @treeplh2
164
5
አይንህን የሚስበውን ሳይሆን ልብህን የሚስበውን ሰው ፈልግ! ካህሊል ጂብራን @treeplh2 @treeplh2
አይንህን የሚስበውን ሳይሆን ልብህን  የሚስበውን ሰው ፈልግ! ካህሊል ጂብራን @treeplh2 @treeplh2
216
6
የህይወት ጉዟችን የብርሃን እና የጨለማ ትግል ነው። ብርሃን የሚወክለው እውነተኛነትን፣ መተማመንን እና ሰዎችን ወደ ከፍታ የሚያወጣ ንፁህ ወዳጅነትን ነው። ጨለማ ደግሞ በሹክሹክታ የሚዘራ ጥል፣ በማባበል የሚመጣ ጥፋት እና በፈገግታ የተሸፈነ ተንኮልን ይወክላል። በዚህች ምድር ላይ ስትኖር፣ ልብህን ክፍት አድርገህ መኖር መልካም ቢሆንም፣ የልብህን ደጅ መጠበቅ የግድ ነው ፤ ምክንያቱም ሁሉም ፈገግታ ወዳጅነትን ሁሉም መሳም ፍቅርን አይገልጽም ። እንደ ጴጥሮስ ፈገግ ብሎ የሚክድ ፣ እንደ ይሁዳ ስሞ የሚሸጥ እንዳለ ታላቁ መፅሐፍ ያስተምረናል። ሁሉም ማባበል ወደ ሰላም መንገድ አይመራም። እውነተኛ ወዳጅነት ነፃነትን ሲሰጥ፣ የተንኮለኞች ማባበል ግን በብልሃት የተሰራ እስር ቤት ነው። በህይወትህ ያሉ ሰወችን ማንነት አጥርተህ እወቅ። ቃላትህን ከሚያጣምሙ፣ ጥርጣሬን በመዝራት ግንኙነትህን ከሚያፈርሱ፣ እና በውሸት ወደ ጨለማ ከሚመሩህ ሰዎች ራስህን ጠብቅ። ምክንያቱም ንፁህ ልብ አለህ ማለት ጅል ነህ ማለት አይደለም። የዋህ እንደ ርግብ፣ ብልህ እንደ እባብ መሆን የህይወት ትልቁ ጥበብ ነው!!! መልካም የመስቀል በዓል❤️🙏 @treeplh2 @treeplh2
251
7
በዚህች ምድር ላይ የምንፈጥራቸው እያንዳንዱ ግንኙነቶች አስደናቂ የህይወት ቴአትሮች ናቸው። በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ የህይወትን ጨዋታ አክብረህ ህጎቿን ተከትለህ በጥበብና በውበት ተጫወተው። ነገር ግን የቱንም ያህል በብቃት ብትጫወት ማብቂያው ጨዋታ መሆኑን አትዘንጋ። ከውጤቱ ጋር አትጣበቅ፤ ማሸነፍና መሸነፍን ማግኘትና ማጣትን በፀጋ ተቀበል እንጂ ራስህን የትኛውም ትዕይንት እስረኛ አታድርግ። በዚህች አጭር ጉዞህ ምንም ነገር ከልክ በላይ አክብደህ አትውሰድ። ሰዎች ሲመጡ በደስታ ተቀበል፣ ሲሄዱም መንገዳቸውን መርቀህ በሰላም አሰናብት። በልብህ ውስጥ ሁሌም የማይነጥፍ የደስታ እና የሳቅ ዜማ ይኑር። ለቃላትህና ለድርጊትህ ታማኝ ሁን፣ ጥልቅ አፍቃሪም ሁን፤ ነገር ግን የህይወትን ሸክም የሚያከብድ ደረቅ እና ከመጠን ያለፈ ቁምነገረኛ ባህሪ አይያዝህ። ወደዚች ምድር የመጣኸው ልትከብድ ሳይሆን ልትበር ፤ ልትጨነቅ ሳይሆን ልታጣጥም ነው። ስለዚህ ትላንትን እና ነገን ለቀህ በዛሬ ውስጥ እረፍ። ቀላል ሁን፤ እንደ ንፋስ እለፍ። እንደ ወራጅ ውሃም የገጠመህን ተፈጥሮ ሁሉ እያስተናገድክ ተጓዝ እንጂ፣ በየትኛውም ቦታ ላይ ቆመህ አትቅር። እውነተኛው የህይወት ነፃነት እና ብስለት መኖርን በሙሉ ልብ ማጣጣም፣ ነገር ግን ከምንም ነገር ጋር አለመጣበቅ ነው!🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2
309
8
ለተደረገልኝ ደግነት ሁሌም አመስጋኝ ነኝ፤ ነገር ግን ያ ደግነት እናንተን ለማቆየት፣ ክብሬን ለመንካት፣ መጥፎ ፀባያችሁን እንድሸከም እና እኔን እንደፈለጋችሁ ለማድረግ የመግቢያ ትኬት ሊሆናችሁ አይች
ለተደረገልኝ ደግነት ሁሌም አመስጋኝ ነኝ፤ ነገር ግን ያ ደግነት እናንተን ለማቆየት፣ ክብሬን ለመንካት፣ መጥፎ ፀባያችሁን እንድሸከም እና እኔን እንደፈለጋችሁ ለማድረግ የመግቢያ ትኬት ሊሆናችሁ አይችልም። ልቤ ምን ግዜም ለምስጋና ክፍት ነው፣ በሬ ግን ለትዕቢታችሁ ዝግ ነው!። እኔ ህይወት ላይ ማንም ሰው ተሳፋሪ እንጂ ሹፌር አይደለም። ፌርማታህ ሲደርስ ትወርዳታለህ።🚶 @treeplh2 @treeplh2
357
9
ሰዎች "ለምን ቸልተኛ ሆንክ?" ሲሉህ፣ ያልገባቸው ነገር ቢኖር አንተ ቸልተኛ የሆንከው በሰዎች ላይ ሳይሆን፣ ዳግም ልብህ እንዳይጎዳ እየጠበከው ስለሆነ ነው። ዓመታት የፈጀ ወዳጅነት በአንዲት ጀንበር እና በትንሽ ምክንያት ሲፈርስ ስታይ ሰው ማለት አላፊ እንግዳ መሆኑን ትማራለህ። ስለዚህ መራቅህ ሰውን መጥላት ሳይሆን፣ በሰው ላይ ያለህን ከመጠን ያለፈ ጥገኝነት ማቆምህ ነው። ረጅም ጊዜ የገነባኸው ወዳጅነት ያለምክንያት ሲፈርስ፣ ሰዎችን በልብህ ዙፋን ላይ ማስቀመጥ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ስታይ፣ ዙፋኑን ለራስህ ሰላም ብቻ ትተወዋለህ። አሁን የሰው ልጅን የምታየው እንደ ቋሚ የህይወትህ ማገር ሳይሆን፣ አብሮህ መንገድ እንደጀመረ እና መውረጃው ሲደርስ እንደሚወርድ ተጓዥ መንገደኛ ነው። ለአዳዲስ ሰዎች የምትሰጠው ሌላ አዲስ እና የዋህ ልብ የለህም። ያለህ ያው የተሰፋ፣ የትላንት ጠባሳ ያለበት፣ ነገር ግን የበለጠ ጠቢብ የሆነ ልብ ነው። አዲስ ሰወችን ስትቀበል ያለ ቅድመ-ሁኔታ ተቀበላቸው፣ ግን አትደገፍባቸው፦ አብረውህ እስካሉ ድረስ ጊዜውን አጣጥም፣ አክብራቸው፣ ውደዳቸው፤ ግን "ለዘላለም አብረውኝ ይኖራሉ" የሚል የውሸት ተስፋ አትሰንቅ። የልብህን በር ከፊል ክፈት ወደ ህይወትህ እንዲገቡ ፍቀድላቸው፣ ነገር ግን የደስታህ እና የህልውናህ ቁልፍ አትስጣቸው።   ማንነታቸውን አክብር አንዳንዴ አዳዲስ ሰዎች የሚመጡት የድሮዎቹን ቦታ ለመተካት ሳይሆን፣ የራሳቸውን አጭር ምዕራፍ ጽፈው ለማለፍ ሊሆን ይችላል። በስተመጨረሻም ሰው አትፈልግም ለሚሉህ ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሰዎችን አልጠላሁም፤ ሰዎችን መፈለግም አላቆምኩም። ነገር ግን በገነባሁት ልክ መፍረስን ስለደጋገምኩ፣ አሁን ግንበኛ መሆን አቁሜ ተመልካች ሆኛለሁ። ለአዲሶቹ የምሰጠው ንፁህ እና ያልቆሰለ ልብ የለኝም፤ ያለኝ የትላንት ጠባሳውን የሚያከብር እና ነገ ዳግም ላለመሰበር የሚጠነቀቅ ብልህ ልብ ብቻ ነው። የሚመጣን በፍቅር እቀበላለሁ፣ የሚሄድን ባላየ ባልሰማ ሙድ ዝም እለዋለሁ።🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2   @treeplh2
191
10
ሰዎች በድብቅ ይጠሉኛል፤ እኔ በግልጽ ችላ እላቸዋለሁ...!!🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2
ሰዎች በድብቅ ይጠሉኛል፤ እኔ በግልጽ ችላ እላቸዋለሁ...!!🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2
212
11
የምሽቱን መንገድ ዝናብ የቀላቀለ ካፊያና ከየስራው ወደቤቱ የሚገሰግስ  የመኪና ጋጋታ ሞልቶታል።  ይሳቅ በካፌው ጥግ ባለው ወንበር ላይ ተቀምጦ፣ ከፊት ለፊቱ ፊቷን በእጆቿ ደግፋ በመስኮት ወደ ውጭ የምትመለከተውን ማህሌትን በዝምታ ይመለከታል። ፊቷ ላይ ያለው ሰላም እና እርጋታ ያስቀናል። የይሳቅ ልብ ግን በሃሳብ ይናወጣል። ባለፉት ጊዜ ያጠፋቸውን ጥፋቶች፣ በብስጭት የተናገራቸውን አስቀያሚ ቃላት፣ የዋሻቸውኝ እውነታዎች እና ያመከነውን ጊዜ እያሰበ ራሱን ይወቅሳል። እንዴት ከነዚህ ሁሉ ጉድለቶቼ ልትወደኝ ቻለች? ብሎ በልቡ ራሱን ጠየቀ። ማንነቱን፣ የውስጡን እድፍ፣ ውድቀቱን እና ድካሙን ከማንም በላይ ጠንቅቆ ያውቀዋል። አንዳንዴ እሱ ራሱ ራሱን መሸከም ሲከብደውና ራሱን ሲጠላ፣ እሷ ግን ምንም ሳትል፣ ሳትፈርድበት፣ በዚያች በማይነጥፍ ፈገግታዋ እና ርህራሄዋ ታቅፈዋለች። ይህ እኮ ለእኔ አይገባኝም... እሷ ከዚህ የተሻለ፣ ንፁህ የሆነ ሰው ይገባታል... የሚለው ሐሳብ ዘወትር አእምሮውን ይሞግተዋል። ከሀሳቡ ነቅቶ ቀስ ብሎ ጉንጮቿ የተደገፋንን እጇን ወደ ራሱ ሳበው እና ያዘው። ከምትመለከተው ግርግር አይኖቿን ወደ እርሱ መልሳ ፈገግ እያለች ጣቶቹን አጥብቃ ጨበጠች። ምን ሆንክብኝ የኔ ጌታ? በሀሳብ ርቀህ ሄድክ እኮ? አለችው የካፌውን ጫጫታ በሚያሸንፍ ለስላሳ ድምፅ። ምንም... ዝም ብዬ እያየሁሽ ነው። አንቺ ግን...  ቃላቶች ጉሮሮው ላይ እየተሰባበረ ...ከነጥፋቴ፣ ከነድካሜ እንዴት ልትወጂኝ ቻለሽ? እንዴት አልሰለችሽም?" አላት፣ ዝግ ባለ ድምፅ። አይኑን በፍቅር እያየች እጁን ይበልጥ አጥብቃ ያዘችው እና፣ ፍቅር ማለት እኮ ንፁህ እና ያልተበላሸ ገፅ ላይ አንድ ነገር መፃፍ ብቻ አይደለም ። ፍቅር ማለት የተበላሸውን ገፅ አብሮ ማስተካከል፣ የወደቀውን ማንሳት፣ የቆሸሸውን ማጠብ ነው። እኔ ያንተን ጥፋት ሳይሆን፣ በጥፋትህ ጀርባ ያለውን ደጉን እና የተሰበረውን ልብህን ነው የማየው፣ አለችው። ከነድካምህ ሰው ሲወድህ ፣ እንዴት ደስ ይላል? ከነ ሀጢአትህ  ከነጥፋትህ ፣ ሰው ሲያፈቅርህ፣እንዴት ደስ የሚል ስሜት አለው? ማንነትህን አይተህ ይህ እኮ ለእኔ አይገባኝም??...... እያልክ ፣ ግን ምንም  ሳይል ፣ ዝም ብሎ ሚወድህ ሰው ስታገኝ ፣ ከዚህ በላይ ምን መታደል  አለ?      ሰናይ ለሊት❤️ @treeplh2 @treeplh2
312
12
የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታው ሲጨምር ጓደኛ ይቀንሳል!! በስነ-ልቦናው ዓለም አንድ ታዋቂ አባባል አለ፦ ትልልቅ አእምሮዎች ስለ ሀሳብ ይወያያሉ፣ መካከለኛ አእምሮዎች ስለ ድርጊት ይወያያሉ፣ ትናንሽ አእ
የሰው ልጅ የማሰብ  ችሎታው ሲጨምር ጓደኛ ይቀንሳል!! በስነ-ልቦናው ዓለም አንድ ታዋቂ አባባል አለ፦ ትልልቅ አእምሮዎች ስለ ሀሳብ ይወያያሉ፣ መካከለኛ አእምሮዎች ስለ ድርጊት ይወያያሉ፣ ትናንሽ አእምሮዎች ደግሞ ስለ ሰው ይወያያሉ። አንድ ሰው የማሰብ አቅሙ ሲጨምር፤ ለሐሜት፣ ለሰዎች የግል ህይወት ትንተና፣ እና ለትርጉም አልባ ጭቅጭቆች ያለው ትዕግስት እጅግ በጣም ይቀንሳል። በመሆኑም እነዚህን ነገሮች ከሚያዘወትሩ ሰዎች ራሱን እያገለለ ይመጣል። @treeplh2 @treeplh2
413
13
መጽሐፈ ምሳሌ 26:20-24 (NASV) •••••••••• ²⁰ ዕንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ አሾክሻኪ ከሌለም ጠብ ይበርዳል። ²¹ ከሰል ፍምን፣ ዕንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ አዋኪ ሰውም ጠብን ያባብሳል። ²² የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጕርሻ ነው፤ ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል። ²³ ክፋትን በልብ ቋጥሮ ለስላሳ ቃል የሚናገር ከንፈር፣ በብር ፈሳሽ እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው። ²⁴ ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤ በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል። ከሀሜተኛ ይሰውረን🚶‍♂❤️ @treeplh2 @treeplh2
360
14
ቡናዋን በዝግታ እያማሰለች መስኮት አሻግራ ትመለከታለች፤ ከውጪ የሚዘንበው ዝናብ የመንገዱን እንቅስቃሴ አቁሞታል። የኔ ትኩረት ግን ሙሉ በሙሉ እሷ ላይ ብቻ ነበር። የተገናኘንበትን ጉዳይ በስሱ ማውራት ጀመርኩኝ በጭራሽ አትገመትም፣ ታደርገዋለች ብሎ ማሰብ ዘበት እስኪመስል ድረስ ሀሳቧና ፍላጎቷ አይታወቅም፤ በውስጤ እያሰላሰልኩ ትኩር ብዬ ተመለከትኳት። አብሬያት የቆየሁባቸውን ጊዜያት ወደ ኋላ መለስ ብዬ ሳስብ፣ ገፆቿ ያልተፃፉባት መፅሐፍ ሆና ነው የምትታየኝ። የሰው ልጅ በባህሪው ሲቀረብ ሚስጥሩ ይገረጣል፤ በርሷ ዘንድ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ያወቅኋት የመሰለኝ ቀን፣ አለማወቄ ይጎላል፤ ዛሬ አንድ እርምጃ ወደ ልቧ የተጠጋሁ ሲመስለኝ፣ ነገ በማይታይ የርቀት ግድግዳ ታጥረቀኛለች። እንደ ሌላው ሰው በድንገተኛ ነገሮች አትደነግጥም፣ በደስታ አትቦርቅም፣ በሀዘንም አትሰበርም። ዓይኖቿ ውስጥ ጥልቅ የሆነ እርጋታ እና ለመፍታት የሚያዳግት ዝምታ ብቻ ነው ያለው። ከዚህ በፊት ህይወትን የኖረችው ይመስል ብዙም ነገሮች አይገርሟትም። ምን ያህል ህይወት ቢገባት ነው እንዲህ ደመ-ቀዝቃዛ የሆነችው?!" ስል ራሴን ጠየቅሁ። የዓለምን ጫጫታ ሁሉ አልፋ፣ የሰውን ልጅ ስሜት ሁሉ አሟጥጣ የጨረሰች እና ወደ ሌላ የመንፈስ ከፍታ የወጣች ትመስላለች። ዝምታው በመሀከላችን ሲረዝም፣ ዞር ብላ አየችኝ። ከንፈሯን በስሱ እንደመሳቅ ለጠጠችው። ወሬ ለማስቀጠል ያህል፣ ሀሳቧ ከኔ ጋር የነበረ ለማስመሰል፤ "ይገርማል..." አለችኝ። እኔ ግን የልቧን ምት አውቀዋለሁ። አስባበት እና አሰላስላ እንጂ ተሰምቷት እንዳልሆነ ጠንቅቄ አውቃለሁ። የሷ ፈገግታ የውስጥ ደስታ መግለጫ ሳይሆን፣ ለእኔ ስትል የለገሰችኝ ምላሽ ነበረች። ያቺ ሰው ሰራሽ ፈገግታዋ እና የዓይኗ እርጋታ ተዳምረው ሊሸውዱኝ አልቻሉም፤ አጠገቤ ተቀምጣ ሳለ፣ የርቀቷ ልክ ተሰማኝ። በምሽት በቀስታ እንደሚነፍስ ነፋስ አይነት ቅዝቃዜ በአጥንቴ ሰርፆ ገባ። ይህች ሴት የራሷ የተለየች ዓለም አላት። እኔ ደግሞ በዚያች ዓለም ደጃፍ ላይ የቆምኩ፣ መቼም ቢሆን ወደ ውስጥ ገብቼ እውነተኛ ማንነቷን ማግኘት የማልችል ምፃተኛ መሆኔን ተረዳሁ፤ ነገር ግን ደግሞ ትቻት መሄድ ያቃተኝ የራሴ እስረኛ ነኝ። የነፍሷን ጥልቅ ባህር እንደ ሙሴ በትር ከፍዬ ለመረዳት መሞከር፣ በሬ ይወልዳል ብሎ እንደመጠበቅ ሆነብኝ........ @treeplh2 @treeplh2
372
15
የውስጣችንን ስሜት ሁሉ አውጥተን ብንዘረግፈው ዙሪያችንን እንደ እሳት ያቃጥላል ፤ አምቀን ዝም ብንል ደግሞ የገዛ የራሳችንን አንጀት ይበላል። መናገር የውጭ ጦርነት ነው፤ ዝምታ ደግሞ የውስጥ ጦርነት
የውስጣችንን ስሜት ሁሉ አውጥተን ብንዘረግፈው ዙሪያችንን እንደ እሳት ያቃጥላል ፤ አምቀን ዝም ብንል ደግሞ የገዛ የራሳችንን አንጀት ይበላል። መናገር የውጭ ጦርነት ነው፤ ዝምታ ደግሞ የውስጥ ጦርነት። የሕይወት ትልቁ ጥበብ፣ ራስን በማያደማ ዝምታ እና ሌላውን በማያቆስል እውነት መሀል መንገድ መፈለግ ነው። አንዳንዴ ለዚህ መፍትሄው ለሁሉም ሰው ከመናገር ይልቅ፣ ሀሳባችንን ያለፍርድ ለሚሰማን ለአንድ እውነተኛ ወዳጅ ማካፈል፣ ወይም ደግሞ ስሜታችንን በወረቀት ላይ መፃፍ የውስጥን ሸክም ያቀላል። @treeplh2 @treeplh2
309
16
ለሁለት ነገሮች አልታገልም....... 1 ለእውነተኛ ፍቅር 2 ለእውነተኛ ጓደኞች በሕይወታችን ውስጥ በላብ፣ በድካም እና በግዴታ ልናገኛቸው የማንችላቸው ውድ ነገሮች ቢኖሩ የልብ ትስስሮች ናቸው። እነ
ለሁለት ነገሮች አልታገልም....... 1 ለእውነተኛ ፍቅር 2 ለእውነተኛ ጓደኞች በሕይወታችን ውስጥ በላብ፣ በድካም እና በግዴታ ልናገኛቸው የማንችላቸው ውድ ነገሮች ቢኖሩ የልብ ትስስሮች ናቸው። እነዚህ ሁለት ፀጋዎች ልክ እንደ ንጋት ፀሀይ በራሳቸው ጊዜ ፈንጥቀው የሚወጡ እንጂ፣ ታግለን የምናመጣቸው አይደሉም። @treeplh2 @treeplh2
334
17
የህይወት ጎዳናህ የአንተ እና የአንተ ብቻ ነው። በጉዞህ ላይ ሰዎች አብረውህ ሊጓዙ መንገድህን ሊያደምቁት ወይም ድካምህን ሊያካፍሉህ ይችላሉ፤ ነገር ግን ማንም ያንተን ጫማ አጥልቆ ላንተ ሊራመድልህ፣
የህይወት ጎዳናህ የአንተ እና የአንተ ብቻ ነው። በጉዞህ ላይ ሰዎች አብረውህ ሊጓዙ መንገድህን ሊያደምቁት ወይም ድካምህን ሊያካፍሉህ ይችላሉ፤ ነገር ግን ማንም ያንተን ጫማ አጥልቆ ላንተ ሊራመድልህ፣ ወይም ህይወትህን ተክቶ ሊኖርልህ አይችልም። የእርምጃውም ሆነ የመድረሻው ባለቤት አንተው ራስህ ነህ። @treeplh2 @treeplh2
411
18
አንዳንዴ ወደ ህይወትህ ዳግም እንዲመለሱ ሳትፈልግ ያሳለፋችሁትን ጊዜ መናፈቅህ አንዳችም ክፋት የለውም። አብራችሁ የፈጠራችኋቸውን ውብ ትዝታዎች ወደኋላ መለስ ብለህ እያሰብክ ብትናፍቅም ተፈጥሯዊ ነው። ዛሬ ላይ አጠገብህ ሊሆኑ የማይችሉበትን እውነተኛ ምክንያት ስታስታውስ፣ ልብህ በሀዘን ቢከበድም አሁንም ችግር የለውም። አብራችሁ ያሳለፋችሁት ያ ቆንጆ ጊዜ ስላመለጠህ ወይም ትዝታው ስላንሰፈሰፈህ፣ ያንን ሰው ዛሬም በህይወትህ ዳግም ትፈልገዋለህ ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ የምንናፍቀው ሰዎቹን ሳይሆን፣ ከእነሱ ጋር የነበረንን ያንን ጣፋጭ ጊዜ ነው። ስለዚህ ያለፈውን ማሰብ፣ መናፈቅ እና ማዘን የሰው ልጅ ጤናማ ስሜት እንጂ፣ ወደተዘጋ በር የመመለስ ፍላጎት አይደለም። @treeplh2 @treeplh2
404
19
ከህይወት አንድ ነገር ተምሬያለሁ ፥ ለአንድ ሰው አስፈላጊ መሆን ትችላለህ ነገር ግን ለራሱ ጥቅም ሲሆን ብቻ ነው ።🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2
ከህይወት አንድ ነገር ተምሬያለሁ ፥ ለአንድ ሰው አስፈላጊ መሆን ትችላለህ ነገር ግን ለራሱ ጥቅም ሲሆን ብቻ ነው ።🚶‍♂ @treeplh2 @treeplh2
507
20
ሰዎች በአንተ ውስጥ ምንም መልካም ነገር ማየት እንደማይችሉ ሲናገሩ፤ እቅፍ አድርገህ ሕይወት ለዓይነ ስውራን አስቸጋሪ እንደሆነች ንገራቸው።😁 @treeplh2
447