𝑻𝒓𝒆𝒆𝒑𝒍
Відкрити в Telegram
መማር ከፈለክ ቀኖች ሁሉ አስተማሪ ናቸው። https://t.me/treeplh2 ለጥያቄና ለአስተያየት @yisakor24
Показати більше966
Підписники
+124 години
Немає даних7 днів
-1130 день
Архів дописів
965
ብዙ ጊዜ በሕይወታችን ስንወድቅ ወይም መድረስ ያለብን ቦታ አልደረስንም ብለን ስንቆጭ ራሳችንን የምንቀጣው፣ ፍጹም ለመሆን ስለምንሞክር ነው። መላእክትን እንኳ ሳይቀር ስንፍና እንደሚከሳቸው በቅዱስ ቃሉ ተጽፏል፤ ፍጹም እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ይህንን እውነት ሲገባን ራሳችንን ከማይቻል የጭንቀት ቀንበር ነፃ እናወጣለን። መሳሳትና መውደቅ የሰው ልጅ ተፈጥሮ አካል መሆኑን ስንቀበልም፣ ውድቀትን እንደ መጨረሻ ሳይሆን እንደ መማሪያ ክፍል ማየት እንጀምራለን።
ሰውን እውነተኛ ሰው የሚያደርገው ይህ ነው፤ እንደ እንስሳ ፍጹም ጨካኝና ሕሊና ቢስ አይደለም፣ እንደ መላእክትም ፍጹም ረቂቅ አይደለም። ሰው ማለት መውደቅና መነሳት የሚችል፣ ከስህተቱ በንስሐና በጸጸት ታጥቦ የሚቀደስ ድንቅ ፍጡር ነው።
ውድቀት በራሱ ጨለማ ቢሆንም፣ ከጀርባው ግን “ተነስ! ገና ሰዓት አለህ፤ የጀመርከው ሕልም አለህ!”የሚል የፈጣሪ የቸርነት ሹክሹክታ አለ። ያንን ድምፅ ሰምቶ፣ አቧራውን አራግፎ መነሳት መቻል እሱ ነው የብልሆችና የጽኑዓን ሰዎች ትልቁ ጥበብ።🚶♂
@treeplh2
@treeplh2
965
አንዳንዶች በሰዎች አስተያየት፣ ክህደት ወይም መለወጥ ምክንያት ተስፋ ሲቆርጡና ሕይወታቸውን ሲያጨልሙ ማየት በእውነት ያስገርማል።
ትላንት ወደ ሕይወትህ የመጣ፣ ታሪክህን የማያውቅ ባዕድ ሰው ዛሬ እንዴት ሙሉ ሕይወትህን የመወሰን፣ የመቆጣጠር ሥልጣን ይኖረዋል?
በዚህች ምድር ላይ ሁሉም ነገር "ኮንትራት" ነው። ማንም ሰውና ምንም ነገር ለዘለዓለም አብሮህ እንዲኖር አልተፈጠረም። ከእናትህ ማኅፀን ጀምሮ አብሮ የተወለደ የለም፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ሕይወትህ የሚመጣው ለተወሰነ ምዕራፍ፣ ለአንድ የተለየ ምክንያትና ለጊዜያዊ ኮንትራት ብቻ ነው። ጊዜው ሲያበቃ ደግሞ ጥሎህ መሄዱ የማይቀር ሀቅ ነው።
የወደደህ አብሮህ ይቀጥላል ፤ የደበረው ደግሞ ይሄዳል።
ስለዚህ በሰዎች መምጣትና መሄድ ውስጥ ልብህን አታስጨንቅ። ራስህን ቻል፤ በገዛ እግርህ ላይ ብቻ ቁም። ማንም ሰው ያንተን ሰላም እንዲሰርቅህ አትፍቀድ። የሕይወትህ ድልድይ የሚሠራው በላብህና በጥረትህ እንጂ በሰዎች ቃልኪዳን አይደለም።
አንተ ሹፌሩ ነህ ሌላው ተሳፋሪ ነው ፤ በጉዞ ላይ ደግሞ ተሳፋሪም ወራጅም አለ ሹፌሩ ከነተሳፋሪው ቤቱ ገብቶ አያውቅም።🚶♂
ሰላም እደሩልኝ❤️
@treeplh2
@treeplh2
965
የአሪስጣጣሊስ የጓደኝነት ደረጃዎች
ታላቁ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ ጓደኝነትን በሦስት ይከፍለዋል፦
1 የጥቅም ጓደኝነት (Utility) ለሥራ ወይም ለጉዳይ የሚደረግ።
2 የደስታ ጓደኝነት (Pleasure) ፈታ ለማለት ለጨዋታ ብቻ የሚሆን።
3 የመልካምነት ጓደኝነት (Virtue) ይህኛው "እውነተኛው" ጓደኝነት ነው። እዚህ ጋር ጓደኛህን የምትወደው ስላለው ነገር ሳይሆን ስለ ማንነቱ ነው። አብሮ መማርና መስራት ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎች መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ ሦስተኛው ደረጃ ላይ አያደርሱም።
አብረህ ስለዋልክ ጓደኛ አትባልም፤ አብሮ መማርም ሆነ መስራት የቦታ እና የጊዜ መገጣጠም እንጂ የልብ መገጣጠም አይደለም። ጓደኝነት ከሁኔታዎች በላይ የሆነ በጥቅም የማይለካ በጊዜ የማይሻር የነፍስ ትስስር ነው።
ብዙ ሰው መንገደኛ ሆኖ ሳለ ጓደኛ ይመስላል። ልዩነቱ የሚታወቀው ግን መንገዱ ሲያልቅና ጥቅሙ ሲቆም ነው። እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁኔታዎች ሲቀየሩ አብሮ የማይቀየር፣ ትላንት በነበረህ ማንነት ዛሬም የሚያከብርህ የነፍስህ መስታወት ነው።
* አብሮ መኖር ቅርበት ነው፤ ጓደኝነት ግን የልብ ትርታን ማድመጥ ነው።
* ስራና ትምህርት ሰዎችን ያገናኛሉ፤ ጓደኝነት ግን ሰዎችን አንድ ያደርጋል።
* ብዙዎች አብረውህ ይጓዛሉ፤ ጥቂቶች ግን አብረውህ ይቆማሉ።🚶♂
እደሩልኝ❤️
@treeplh2
@treeplh2
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
