uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Tula Comprehensive Secondary School

Tula Comprehensive Secondary School

Відкрити в Telegram

Governmental School

Показати більше
1 164
Підписники
+124 години
Немає даних7 днів
+1030 днів
Архів дописів
በዕለታዊ የትምህርት ዕቅድ ዝግጅት የምንጠቀማቸዉየ ፈርጆችና የማሰሪያ ግሶች ውጤታማ ትምህርት የሚጀምረው በትክክል በተቀረጸ ተማሪ-ተኮር ዓላማ ነው። ዓላማው ተማሪው በትምህርቱ መጨረሻ ሊያሳየው የሚገባውን ለውጥ በትክክል የሚለኩ "ተግባራዊ ግሶችን" መያዝ አለበት። እነዚህን ዓላማዎች በሦስት ዋና ዋና ፈርጆች ከፍለን እናያቸዋለን። 1. የእውቀት ፈርጅ (Cognitive Domain) ይህ ፈርጅ የተማሪውን የማሰብ ችሎታ፣ መረጃን የማስታወስና የመተንተን ብቃት የሚለካ ነው። በብሉም ታክሶኖሚ መሠረት ከቀላል ወደ ከባድ በሚከተሉት ደረጃዎች ይከፈላል፦ #ማስታወስ(Remembering): መረጃን ማስታወስና መጥራት። #ማሰሪያ ግሶች፦ ይገልጻል፣ ይዘረዝራል፣ ይጠቅሳል፣ ይስማል፣ ይለያል፣ ያዛምዳል። #መረዳት(Understanding): ሃሳቡን በራስ ቋንቋ መግለጽና ትርጉም መስጠት። #ማሰሪያ ግሶች፦ ያብራራል፣ ይተረጉማል፣ በምሳሌ ያስረዳል፣ ያጠቃልላል፣ ይፈርጃል። #መተግበር(Applying): የተማሩትን እውቀት በአዲስ ሁኔታ ላይ በተግባር ማዋል። #ማሰሪያ ግሶች፦ ያሰላል፣ ያሳያል፣ ይጠቀማል፣ ይሠራል፣ ይተገብራል። #መተንተን(Analyzing): መረጃን በክፍል በክፍል በመከፋፈል ግንኙነታቸውን መረዳት። #ማሰሪያ ግሶች፦ ያወዳድራል፣ ይለያል (Differentiate)፣ ይተነትናል፣ ይመርምራል። #መገምገም(Evaluating): በምክንያት ላይ ተመስርቶ ውሳኔ ወይም ፍርድ መስጠት። #ማሰሪያ ግሶች፦ ይሞግታል፣ ይደግፋል፣ ይገመግማል፣ ያረጋግጣል፣ ይመርጣል። #መፍጠር(Creating): ነባር እውቀቶችን በማቀናጀት አዲስ ነገር መሥራት ወይም ሃሳብ ማመንጨት። #ማሰሪያ ግሶች፦ ያዘጋጃል፣ ይነድፋል (Design)፣ ይፈጥራል፣ ያደራጃል። 2. የክህሎት/ተግባር ፈርጅ (Psychomotor Domain) ይህ ፈርጅ የአካል እንቅስቃሴን፣ የእጅ ጥበብንና በተግባር የሚታዩ ክህሎቶችን ያጠቃልላል። #መመልከት(Observation): አንድን ተግባር ሲከናወን በትኩረት መከታተል። #ማሰሪያ ግሶች፦ ይከታተላል፣ ይለያል፣ ይመርጣል። #መኮረጅ(Imitation): የታየውን ድርጊት ደረጃ በደረጃ ለመድገም መሞከር። #ማሰሪያ ግሶች፦ ይደግማል፣ ይከተላል፣ ይለማመዳል። #መልመድ(Manipulation): ያለ ሰው እርዳታ መመሪያን ተከትሎ መሥራት። #ማሰሪያ ግሶች፦ ይሠራል፣ ያከናውናል፣ ይገጥማል፣ ይስላል። #ማጥራት(Precision): ድርጊቱን በከፍተኛ ጥራት፣ ፍጥነትና ያለ ስህተት ማከናወን። #ማሰሪያ ግሶች፦ በትክክል ይሠራል፣ ያሳምራል፣ ይቆጣጠራል። 3. የስሜት/አመለካከት ፈርጅ (Affective Domain) ይህ ፈርጅ ተማሪው ለትምህርቱ ወይም ለጉዳዩ የሚያሳየውን ስሜት፣ እሴትና የአመለካከት ለውጥ የሚለካ ነው። #መቀበል(Receiving): ለመማር ፈቃደኛ መሆንና ትኩረት መስጠት። #ማሰሪያ ግሶች፦ ያደምጣል፣ ይጠይቃል፣ ይከታተላል። #ምላሽ_መስጠት (Responding): በትምህርቱ ሂደት በንቃት መሳተፍ። #ማሰሪያ ግሶች፦ ይመልሳል፣ ይሳተፋል፣ ያወያያል። #እሴት_መስጠት (Valuing): ለተማረው ቁምነገር ዋጋ መስጠትና አቋም መያዝ። #ማሰሪያ ግሶች፦ ያደንቃል፣ ያከብራል፣ ይደግፋል፣ ተቃውሞውን ይገልጻል። #ባህሪ_ማድረግ (Characterizing): እሴቱን የዕለት ተዕለት የሕይወት መመሪያ ማድረግ። #ማሰሪያ ግሶች፦ ይተገብራል፣ ይጠብቃል፣ ይለማመዳል። #ማሳሰቢያ ለመምህራን፦ ዓላማ ሲቀረጽ "ያውቃል" ወይም "ይረዳል" የሚሉ ግሶችን መጠቀም አይመከርም። ምክንያቱም እነዚህ ግሶች ተማሪው በትክክል ማወቁን ለመለካት(Measure ለማድረግ) ስለማያስችል ነዉ። ይልቁንም ተማሪዉ ማወቁን በተግባር የሚያሳይባቸዉ ግሶች(ለምሳሌ፦ ይገልጻል፣ ያወዳድራል፣ ያሰላል፣ ወዘተ) መጠቀም ተገቢ ነዉ።

ለ2ኛ ደረጃ ር/መህራን 12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያስተምሩ መምህራን ነግ 13/02/2019 ዓ.ም 2፡00 ስዓት ስልጥና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ስለምስጥ በስዓቱ እንድገኙ እንዲደረግ እናሳሰባለን።

ማስታወቂያ :በዲፕሎማ እና ዲግሪ በመምህርነት ሙያ ተቀጥራችሁ መስራት ለምትፈልጉ በሙሉ የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም አዲስ የመምህራንን ቅጥር በዲጂታል ቴክኖሎጂ መምህራንን በመመልመል
+1
ማስታወቂያ :በዲፕሎማ እና ዲግሪ በመምህርነት ሙያ ተቀጥራችሁ መስራት ለምትፈልጉ በሙሉ የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም አዲስ የመምህራንን ቅጥር በዲጂታል ቴክኖሎጂ መምህራንን በመመልመል ለመቅጠር ይፈልጋል ።ስለሆነም ከታች በተዘረዘሩ ክፍት መደቦች በማስታወቂያ ላይ በተገለጸው ቀናት "tmis.sreb.gov.et" "new vacancies" ሊንክ መሠረት በመጠቀም ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን እንድትሞሉና እንድትወዳድሩ እናሳውቃለን ።

photo content

photo content

NEW
NEW

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content