ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

Tula Comprehensive Secondary School

Tula Comprehensive Secondary School

前往频道在 Telegram

Governmental School

显示更多
1 155
订阅者
-124 小时
-47 天
-1430 天
帖子存档
Grade 10 New
Grade 10 New

Teacher Cr 1.docx0.29 KB

የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የሲቪል ሰርቫንት ሰራተኞች ማረጋገጫ ስራን በተመለከተ እስካሁን ከ88000 በላይ ሰራተኞች መመዝገባቸውንና በቀጣይ እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ብቻ የሰራኞች ማረጋገጫ ስራ የማጠናቀቅ ስራ እንደሚሰራ ገልፆ በተጠቀሰው ጊዜ በመገኘት መረጃቸውን ባላሟሉትና ሀላፊነታቸውን ባልተወጡት ላይ ከቀጣይ ወር ጀምሮ የደመወዝና ማንኛውም ዓይነት የመብት ጥያቄዎች እንደማይስተናገዱ ቢሮው አሳውቋል።

‼️ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አደረገ ​ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በ2019 ዓ.ም በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በዕጩ መምህርነት ለመሰልጠን ለሚወዳደሩ አመልካቾች የመወዳደሪያ የመቁረጫ ነጥብ በይፋ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ለሁሉም ክልሎችና ለከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች በላከው ይፋዊ ደብዳቤ፣ የመቁረጫ ነጥቡ የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታና የ2018 ዓ.ም የፈተና ውጤት ባገናዘበ መልኩ የተወሰነ መሆኑን ገልጿል። ​በዚህም መሠረት በዲፕሎማ (12+2) እና በሰርተፊኬት (12+1) የሙያ ስልጠናዎች መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ እንደሚከተለው ተወስኗል፦ ​1. ለዲፕሎማ (12+2) ፕሮግራም፦ ⊙ ​​ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች፦ 215 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች፦ 205 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች፦ 185 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ተፈታኞች፦ 185 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​አካል ጉዳት ያለባቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች፦ 185 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች፦ 150 እና ከዚያ በላይ ​2. ለሰርተፊኬት (12+1) ፕሮግራም፦ ⊙ ​​ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች፦ 210 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች፦ 195 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች፦ 180 እና ከዚያ በላይ ⊙ ​​ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ተፈታኞች፦ 180 እና ከዚያ በላይ ​ይህ የመቁረጫ ነጥብ የሚያገለግለው በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለወሰዱ እና በ2019 ዓ.ም በዕጩ መምህርነት ለሚወዳደሩ አመልካቾች ብቻ ሲሆን፤ ሌሎች መስፈርቶች በዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ መመሪያ መሠረት ተፈጻሚ የሚደረጉ ይሆናል።

‎📢 ማስታወቂያ ‎ለትምህርት ቤታችን መምህራን በሙሉ ‎በቀን 22/01/2019 ዓ.ም. (ዓርብ) ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በትክክል የሚጀመረው የሥልጠና መርሃ ግብር ስለሚኖር፣ ሁሉም መምህራን በተጠቀሰው ሰዓት በቦታው እንድትገኙ ትምህርት ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል። ‎በተጨማሪም፣ ቅዳሜ 23/01/2019 ዓ.ም. የWelcome Program (የአቀባበል መርሃ ግብር) የሚካሄድ ሲሆን፣ ተጋባዥ እንግዶችም የሚገኙበት መርሃ ግብር ነው። ስለሆነም ሰዓትን መጠበቅ የሥራ ባህላችን እንዲሆን ትምህርት ቤቱ ያሳስባል። ‎⚠️ ማሳሰቢያ ‎በተጠቀሰው ሰዓት ሳይገኙ ዘግይተው የሚመጡ መምህራን፣ የሥልጠናውን የጊዜ አጠባበቅና ውጤታማነት ሊያስተጓጉሉ ስለሚችሉ፣ የመገኘት ሁኔታቸው በትምህርት ቤቱ የሚከታተል ይሆናል። ‎ስለሆነም ሁሉም መምህራን በሰዓቱ በመገኘት ለሥልጠናውና ለመርሃ ግብሩ ስኬት የድርሻችንን እንወጣ። ‎ትምህርት ቤቱ!