Our Side of the Story
Відкрити в Telegram
"To those who hurt and hunger” Since Oct 14, 2019 Here to help @DebbieTesfaye
Показати більше1 682
Підписники
Немає даних24 години
+177 днів
+430 день
Архів дописів
There’s a box of gifts (cards) I’ve received over the years, my people know me well so it’s basically filled with bracelets and some more ኮተትs. I no longer wear most of them, ሳያቸው ደስ ይለኛል. I lost a valuable recently, the only tangible reminder of the person and I can’t seem to move on from it. Is there a means of recovery to this madness or do I just sit with it?
ከጊቢ ቤት ስመጣ በጣም የሚከብደኝ ፀጥታው ነው...it’s a deafening silence. As if there’s no life or chaos around.
እዛ
በቀን ውስጥ በጣም በትንሹ ከ አስራ ምናምን ሰው ጋር interact አደርጋለሁ...ያወራሉ...አወራለሁ...ብዙ exchanges of voices happen.
እዚህ
"ደህና አደርሽ"
"ደህና ዋላችሁ"
"ደህና እደሩ"
የመድሀኒያለም ያለ...ተዓምራቱ አያልቅ ፀጥታን ጠላሁ ኑ ረብሹኝ እያልኩ መሆኑ ነው::
Who would’ve thought?
ወይኔ🤭 ለምን ይሆን ልብ ወለድ ላይ እንዳሉት characters, real life lovers እውይ! እሺ ከዛስ...what’s your story የማያስብሉኝ?
ምናልባት እውነትም ልብ ወለድ እና አለሙን እዚሁ እኛው ጋር ማግኘት possible እንደማይሆን ቀድመን ስላመንን? ምናልባት::
ብቻላችሁ ታክሲ ውስጥ ቅድም ልሞት ምን ቀረኝ...ገና በትውውቅ ላይ ናቸው መሰል both of them try to catch pieces of each other from their conversations. ይሄን እወዳለሁ...እኔ ደግሞ ይሄን stage ላይ ናቸው:: ለምን ታክሲ ውስጥ ያለው ህዝብ ከነጆሮው ገደል አይገባም ግዳቸው አልነበረም...እኔ አጠገባቸው ተቀምጬ በ cringe አለቅሁ እንጂ::
Cute እኮ ናቸው...ያሳዝናሉ (እንፋቀራለን የሚል ሰው ሳይ ማዘን ይቀናኛል እንጃ እኔ why)
ግን ደግሞ እኛ ተሳፋሪዎቹስ?
ይሄንኑ ታሪክ ወይ አሌክስ ወይ አለማየሁ ወይ አዳም ቢፅፉት እኮ ተንገብግቤ አንብቤው ይሆናል...ምፅ ሰው ከንቱ😅
አንዱ የመረረው መች ለት ስለ ባህርዳር እያለቃቀስኩ የሰራሗት ቪዲዮ ላይ ነፍሴን አወጣት..."አሽቃበጥሽ...እኛ አናቀውም እንዴ ያን ጊቢ እና ህዝብ"...ብቻ ብዙ አለ:: ወይ ስለ ትምህርቱ አላወራው ወይ ስለ ህዝቡ ፀባይ አላወራው...እንዴት ብትደፍሪ ነው ደስተኛ ሆነሽ የምትመረቂው ይሁን ምኑን አውቄው...ብሶት ያለበት ሰው ግን ያሳዝናል በእውነት...ጭራሽ የቲክቶክ ቪዲዮ ብቅል ሆኖላችሁ አረፈው🤭
ስታመም አልወድም...የሚያንዘፈዝፍ ጥላቻ ነው ያለብኝ...ብዙ ነገር የሚያመልጠኝ ነው የሚመስለኝ:: በተለይ ጥርስ ህመም...ሆድ ቁርጠት እና ጉንፋን የተባሉ ነገሮች::
Repost from አማዶን
የሰው ልጅ ሰላም መደፍረስ የሚያቆመው ፥ ሲሞት ይመስለኛል።
ከዚያ በፊት ግን?
ከዚያ በፊት ግን... በሩጫ ውጤት፣ ገብስ ገብስ በሚል ቡና፣ በማይጣፍጥ ሽሮ፣ አልከፈት በሚል የታክሲ መስኮት፣ በሚኮረሸም ፎርጂድ ባናና ማስቲካ፣ በረፋድ በሚያልቅ የሞባይል ባትሪ፣ ብብቷ በሚሸት የካፌ አስተናጋጅ፣ ነፃ ባልተገኘ የሊስትሮ ወንበር፣ ሁለት ሶስቴ ተነግሮት በማይገባው የበሽተኛ አስታማሚ፣ ጨው በሚያንሰው እርጥብ፣ ለጊዜው አገልግሎት በማይሰጥ ATM ወይም 200 ብር አዘውት በቂ ገንዘብ የለኝም በሚል ATM፣ ታጥቦ ባልደረቀ ጋወን፣ የት እንደጠፋ በማይታወቅ የዶርም ቁልፍ፣ ማለቁ ጠዋት በተስታወሰ ላይፍ ቦይ ሳሙና፣ ቆንጆ ቆንጆ ሆና ስለ ቃና ቲቪ ትርጉም ድራማ በምታወራ ሴት፣ በችኮላ በተጠበሰ በቆሎ፣ የለኝም ቢሏቸው በማይሰሙ ለማኝ ህፃናት፣ 30 ብር የገዙትን በቆሎ እየጋጡ ሲሄዱ ‘በቆሎ ስጠኝ’ በሚሉ ለማኝ ህፃናት እና የመሳሰሉ ምክንያቶች ሰላም ይደፈርሳል። ምን ማድረግ ይቻላል?
በጣም ወረኛ የምባል ሰው ነኝ...የእውነት የእውነት ግን አንዳንድ ሰው ይደክመኛል...እኔም እንዲህ ነው የሰው ልብ የማወርደው? ወይ ጉድ🤣
መቼ ስለ ጊዜ weird መሆን ማውራት እንደማቆም በእውነት I genuinely don’t know. ብዙ ነገር...so many things I held close to my heart, so many things I thought would never end, something’s I thought I’d never get over ደብዛቸውም የለም:: Blame የሚደረግ አካል ቢኖር እንዴት ደስ ባለኝ...ወፍ ነዋ blame. በቃ life :)
Second year, I swear እንደ ትላንት ነው ትዝ የሚለኝ But it’s not ትላንት, I’ve changed so much. It’s end of an era after two weeks, I don’t know how to deal with it.
እዚህች ሰማያዊ አጎበር ውስጥ ራሱ ስንት ትዝታ አለኝ መሰላችሁ🤣
እያንዳንዱ የዚህ ጊቢ ጥጋጥግ እና አስፓልት ላይ ብዙ ሳቅ...ለቅሶ እና heart to heart conversations አሉኝ...በቃ ይቀመጡ? ይቅሩ? ይሄንም ጊዜ እንደሌላው ወይ ካምፓስ ብዬ ነው የማወራው?
ምግብ ለብቻዬ እንዴት ነው የምበላው? ጫጫታ ሊናፍቀኝ እኮ ሆነ ጎበዝ::
ወይ ጊዜ...የዛሬ አመት አድርሶን ደግሞ ስለየትኛው ጊዜ እፅፍ ይሆን? ምፅ
የእኛ ሰው እና ለቅሶ አንድ ላይ ሲነሱ ደስ ከማይለኝ ጥምረት ዋነኛው ነው::
ማስተዛዘኑን የሚችለው እነዛ unbearable first few days እስኪያልፉ ድረስ ነው...ስራ ማገዙ...ወደዛ ወደዚህ ማለቱን በጣም ነው የምወደው...grateful ነኝ::
እናፅናና ብለው ማውራት ሲጀምሩ ነው ችግሩ...እውነት የሰው መኖር ከምንም በላይ ያፅናናል...ወሬው ምን ያደርጋል?
Regarding Zerithu’s loss I was reading lots of comments እና ኤጭ አልኩ በቃ...ለምን እግዚአብሔር ይመስገን አለች ነው መሰለኝ...በሀዘን ጊዜ ደንቡ እግዚአብሔርን ማማረር ነዋ...ጥንካሬዋ ሰዉን ረብሾታል::
ሀዘን ቤቷ በደንብ እንደገባ ሰው "እግዚአብሔር የወደደውን አደረገ...እግዚአብሔር ይመስገን...ምን እንላለን እንግዲህ" ያልኩት ሳላዝን ቀርቼ...my heartbreak ሳያሰክረኝ ቀርቶ አይደለም...ግን እግዚአብሔር ይበልጣል...በደንብ ስላየሁ...ስላስተማረኝ::
ህመሟን እየካደችው አይደለም እግዚአብሔርን ተመስገን ያለችው...why is it that hard to believe?
ደግሞ ልክ እንደ አዋቂ እግዚአብሔር ይርዳት ትክክል አይደለችም ይባላል😅
Grief’ን experience በማድረግ ውስጥ ማንም ያወጣው ህግ የለም...ሁሉም በግሉ መታመም ያለበት ከእግዚአብሔርም ከእራሱም ጋር deal ማድረግ ያለበት ትልቅ ህመም ነው...በአሽሙር አንስተው የሚጥሉት የ አንድ የሁለት ቀን ሀሜት አይደለም!
ሀዘኑን ይዛችሁ ስትቆዩ "ኧረ እግዚአብሔርም አይወደው"
የእግዚአብሔር ትልቅነት በምንም ሁኔታ ውስጥ እንደሚቀጥል ገብቷቹ "እግዚአብሔር ይመስገን" ስትሉ ትችቱ...የጉድ ሀገር::
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
