uk
Feedback
ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

Відкрити в Telegram

ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ቻናል ነው 👉👉ለጠቅላላ @weldwahid 👉👉ለአብነት እና ግእዝ ቋንቋ ትምህርት @weldwahidabinet 👉👉 ለቤተ መጻሕፍት አገልግሎት @Abaiyesuslib 👉👉ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @mels_asteyayet

Показати більше
2 125
Підписники
-324 години
-27 днів
+930 днів
Архів дописів
በጌታ በኢየሱስ የትኛውንም ትእዛዝ እንደሰጥናችሁ ታውቃላችሁና ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና ከዝሙት እንድትርቁ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብበፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን እቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁ እንደመሰከርንላቹ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነው። ተሰ 4፥3
 ✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨ 💿💿💿💿💿💿💿💿💿💿💿 🌹ሳምንታዊ ረቡዕ ጉባኤ በዚህ ሳምንት በቤታችን በአካል መገኘት ላልቻሉ ሁሉ🌹 በመምህር ዲ/ን አንተነህ በ20/01/2019 ዓ/ም በ #ረቡዕ_ጉባኤ በወልድ ዋሕድ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ የተላለፈ ቃለ እግዚአብሔር 17.2MB ብቻ

እንኳን #የእናታች_የእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም (ለብዙኃን ማርያም)፣ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል #በግሸን_በመስቀለኛው_ተራራ ላይ ገብቶ ለተቀመጠበት፣ #ሊቃ
+1
እንኳን #የእናታች_የእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም (ለብዙኃን ማርያም)፣ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል #በግሸን_በመስቀለኛው_ተራራ ላይ ገብቶ ለተቀመጠበት፣ #ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ሃይማኖታዊ_ውሳኔ ለመወሰን፤ #በኒቅያ_ጉባኤ_አርዮስን_ለማውገዝ ከሩቅ #ለተሰባሰቡበት_ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️

"በህይወትህ እግዚአብሔርን የመጀመሪያው ቦታ ላይ ስታስቀምጠው ሌላው ነገር ሁሉ ቦታውን አውቆ ይይዛል ።"      አውግስጢኖስ

ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ              🗓 ዛሬ 🕕ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ                  ሁላችኹም ከዚህ መልካም መዓድ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እንድትቋደሱ ተጋብዛችኋል!                    

እግዚአብሔር ሆይ 🙏 "ይህ ብርቱ ጠላቴን፣ እንደሚያገሣ አንበሣ የሚመላለሰው፣ ይህን ተንኰለኛ ጠላቴን በእኔ ጥበብና ዕውቀት ማሸነፍ አይቻለኝምና ከአንተ ማዳንን እፈልጋለሁ ።እኔም የምችለውን ያህል አደርጋለሁ ፣ ከእሱም የሆነውን ሀሳብ እንዳውቅ ፣ በእሱ ላይ ጥንቃቄ እንዳደርግ ሁሌም አንተ ከእኔ ጋር ሁን ፣እኔ አቅሜ በሚፈቅድልኝ መጠን እታገላለሁ ፣አንተ ግን ወደ ድል መንሳት ምራኝ"     አቡነ ሺኖዳ

"በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥በተኛሁ ጊዜ። መቼ እነሣለሁ? እላለሁ።ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፤ዘመኔ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኵላል፥ ሕይወቴ እስትንፋስ እንደ ሆነ አስብ፤የሚያየኝ ሰው ዓይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥ስለዚህም አፌን አልከለክልም፤ ጠባቂ ታስነሣብኝ ዘንድ፥ እኔም። አልጋዬ ያጽናናኛል፥ አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ነፍሴም ከአጥንቴ ይልቅ ሕይወቴን ናቅኋት፤ ለዘላለም ልኖር አልወድድም።ሰው ምንድር ነው ታከብረው ዘንድ፥ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥የማትተወኝ እስከ መቼ ነው?ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ ምን ላድርግልህ?ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም?"     መጽሐፈ ኢዮብ 7

ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ ዐይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው ? ታዲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘላለም ሲወድቁ እንድምን እጃችን የበለጠ አይዘረጋም? ወገኖቼ! በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰው ስታዩ " የእኔ ሥራ አይደለም፣ የቀሳውስቱና የመነኮሳት ሥራ እንጂ።" አትበሉ። አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሱት አይደለምን? ይህ ወደ ዘላለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትደግፉት። (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ-ሰማዕትነት አያምልጣችሁ)

‛‛የተቸገረ ወንድማችሁን ንቃችሁቤተክርስቲያንን አታስጊጡእርሱ ከሁሉ የተቀደሰ ቤተመቅደስ ነውና።’’        ✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

" ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ፤ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። " (ትንቢተ ኤርምያስ 15:16) ኦርቶዶክሳዊያንን በማስመዝገብ የቤተክር
" ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ፤ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። " (ትንቢተ ኤርምያስ 15:16)
ኦርቶዶክሳዊያንን በማስመዝገብ የቤተክርስቲያን ልጅነቶን ኃላፊነት ይወጡ። ለመመዝገብ 👉https://weldwahid.netlify.app/ 👉 @Gebremedhin27 #ሼር

Contact Center Representative
Contact Center Representative

“የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች፤”                    ✍️ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

"ነገሮች ሁሉ አንተ እንደምትፈልጋቸው እንዲሆኑ አትመኝ ፣ እግዚአብሔርን እንደሚያስደስቱት እንጂ  እንደዚህ ከሆነ የማትታ ወክና በጸሎትህም የምታመሰግን ትሆናለህ ።"         አባ ኄሌስ

"ቁጥር የሌላቸው ታላላቆችን መመርመር የሌለባቸውን የተደነቁ የከበሩ ሥራዎችን ይሠራል።ሥራው ከአየነው ይልቅ ዕጹብ ነው ኃይሉም ከሰማነው ይልቅ ድንቅ ነው ጌትነቱም ከነገሩን ይልቅ ድንቅ ነው።" ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ "የክርስቶስ መስቀል ታላቅ በረከትንና ድኅነትን እንድናገኝ ምክንያት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡ የክርስቶስ መስቀል ስናስበው ሐዘንና ምሬት ነው ነገር ግን እውነታው ደስታና ሐሴትን የሚሞላ ነው፡፡ መስቀል ለቤተ-ክርስቲያን ድኅነት ነው መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያ ነው መስቀል የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበሩት የታረቁበትና ኃጢአን ወደ ክርስቶስ የቀረቡበት ነው፡፡ በመስቀል ከጠላትነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ተሸጋግረናል በመስቀል ከዲያብሎስ ቀንበር ወጥተናል ከሞት ወደ ሕይወት መጥተናል፡፡ ስለ መስቀል የማንሰብክ ከሆነ አሁንም በሞትና በፍዳ እንደ ተያዝን ነው ማለት ነው፡፡             ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

☦️መስቀል ይህ ነው በእውነት የጨነቀ ነገርን ያቀላል በኃይል ጽናት በበጎ ምግባር በዕፀ መስቀሉ ኃጢአትን ያስተሠርያል። ጻድቃን ከልዑል ተራራ ላይ ሆነው ጮኹ ኃጥአንም በሥቃይ መካከል ሆነው ጮኹ። ለ
☦️መስቀል ይህ ነው በእውነት የጨነቀ ነገርን ያቀላል በኃይል ጽናት በበጎ ምግባር በዕፀ መስቀሉ ኃጢአትን ያስተሠርያል። ጻድቃን ከልዑል ተራራ ላይ ሆነው ጮኹ ኃጥአንም በሥቃይ መካከል ሆነው ጮኹ። ለእናታችን ጽዮን ማዕበል ቆመ በዕለተ ሰንበት ባሕርን ገሠፃት የእስራኤል ልጆች በእግር ተሻገሩ እኛም ረድኤቱንና ኃይሉን እናምናለን። መስቀል በጠላት መካከል ጽናችን ቤዛችን ነው። ይህ መስቀል ኃይላችን ፀወናችን ሞገሳችን ነው።☦️ መዝሙር ዘሰንበት

እምነት ለጋስ እና ብርቱ ነፍስ ያስፈልገዋል ከአእምሮም በላይ የሆነ፤የሰውንም የአስተሳሰብ ድካም የሚያልፍ።ራስን ከዓለም ከተለመዱት ልማዶች በላይ ከፍ ማድረግ ካልተቻለ በቀር አማኝ መሆን አይቻልምና። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

«አእምሮህ እንደ ንብ እንጂ እንደ ዝንብ አይሁን! ዝንብ ውብና መዓዛ ባለው አትክልት ቦታ ውስጥ እንኳን ብትገኝ አበቦቹን ትታ ቆሻሻ ፍለጋ ትሄዳለች። ንብ ግን ቆሻሻ ቦታ እንኳን ብትገኝ ቆሻሻውን ትታ ንጹህ ቦታ አንዲት ትንሽ አበባ ፈልጋ በማረፍ ማር ትሠራበታለች። እኛም እንዲሁ በሰዎችና በሁኔታዎች ውስጥ ሁልጊዜ ክፉውን ከመፈለግ ይልቅ በጎውንና መልካሙን ነገር ብቻ ማየት እንልመድ። የአእምሯችን ሰላምና የልባችን እረፍት የሚወሰነው በምናስተናግደው አሳብ መጠን ነውና።» (ቅዱስ ፓይስዮስ ዘደብረ አቶስ)

"ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልዕኮ ጸሎት ናት።"                       አረጋዊ መንፈሳዊ

"ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ሌሊትና ቀን የተገለጡ ይሁኑ።" 1ኛ ነገ 8፥29 🕯ሳምንታዊው የአርብ ጸሎት🕯 👉
"ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ሌሊትና ቀን የተገለጡ ይሁኑ።" 1ኛ ነገ 8፥29
🕯ሳምንታዊው የአርብ ጸሎት🕯 👉 ውዳሴ ማርያም 👉 መሐረነ አብ 👉ስንክሳር 📆አርብ 15/01/2019 ዓ.ም 🕰12:00 በወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ