💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Відкрити в Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Показати більше9 047
Підписники
-1024 години
+157 днів
-6830 день
Архів дописів
ሀቂቃ ይደመጥ !
አሊሞችን በእዉቀታቸዉ እንጠቀምባቸዉ። እንቅራባቸዉ፦እንከባከባቸዉ፦እናክብራቸዉ።
በየፕሮግራሙ የግሩፕ መክፈቻ የሳንቲም መሠብሠቢያ አናድርጋቸዉ።
~
🟢🎧🎤አዲስ ሙሀደራ
በሸይኽ ኢማም ሰይድ (حفظه الله)🕌🟢☑️ በደሴ ከተማ አረብ ገንዳ መስጅድ የተደረገ ⚙💬💬 ርዕስ:–ዒልምን በመፈለግ ላይ መጠንከር(መትጋት) https://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ሃብት እና ትዳር
~
ለትዳር ሃብት ያለውን ወይም ያላትን መምረጥ ምንም የሚያስወቅስ ነገር የለውም። የሚያስወቅሰው ሃብትን ብቻ በማየት የማይሆን ሰው ማግባት ነው። "ባለ ዲኗን ምረጥ" የሚለው ሐዲሥ መልእክቱ ከዚህ አንፃር የሚታይ ነው።
ስለዚህ ሴቷ ተውሒድ ያለው፣ ሶላት የሚሰግድ፣ አላህን የሚፈራ እስከሆነ ድረስ ሃብት ያለውን ብትመርጥ ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰነችው። ሃብት አይታ ሄደች ተብላ የምትወቀስበት ምንም አይነት ውሃ የሚያነሳ ምክንያት የለም።
ወንዱም ላይ ተመሳሳይ ነገር ማለት ይቻላል። የእውነት ትዳር ፈላጊ እስከሆነ ድረስ ገንዘቤን ፈልጎ ሊሆን ይችላል የመጣው እያልሽ አትመልሺ። ወይም ከገባሽ በኋላ ትዳርሽን በአጉል ስሜት አትበጥብጪ። ሃብትሽ ለትዳርሽ ፈተና አይሁንብሽ። ትዳር ጌጥ ነው። ትዳር መከበሪያ ነው። ትዳር ዱንያ ብቻ ሳይሆን ዲንም ነው። እንዲያውም አላህ ሃብት ሰጥቶሽ ከሆነ ሁነኛ ሰው አፈላልገሽ ጥሩ ትዳር ለመመሰረት ተጠቀሚበት። "በሃብቷ ልትጫነኝ ትፈልጋለች" የሚል ስሜት አድሮበት ሳይሳቀቅ ቤቴ ብሎ ዘና ብሎ በርትቶ ስራ ላይ እንዲሰማራ አድርጊው። የኸዲጃን - ረዲየላሁ ዐንሃ - ታሪክ አስታውሺ። በሃብታቸው ጥሩ ትዳር የመሰረቱ ብልጥ ሴቶችን እናውቃለን። ሃብታቸው ፈተና ሆኖባቸው ምን የመሰለ ትዳራቸውን አፍርሰው የተፀፀቱ ሴቶችንም እናውቃለን።
በሌላ በኩል ከገንዘብ ውጭ ለትዳር ቦታ የሌለው፣ ስግብግብ ወንድም ያጋጥማል። ሰው እንደ አገዳ ተነክሶ አይለይም። አስተውሎ፣ ሰው አማክሮ ዲኑ እና ስነ ምግባሩ ያማረ የሆነውን መምረጥ፣ ዱዓእ ማድረግ፣ በአላህ ላይ መውወከል፣ በራስ በኩል ያለን ኃላፊነት እስከ ጥግ መወጣት ለዘላቂ ትዳር ሁነኛ ሰበቦች ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🌺 أَحَسِبَ النَّاسُ أَن يُترَكوا أَن
يَقولوا آمَنَّا وَهُم لا يُفتَنونَ🌺
~አንዲት ሴት ጠየቀች !
ያ ሸይኽ
ባሌ ምንም ስራ የለውም።
የማስተዳድረው እኔ ነኝ
ወላሂ ሁለተኛ አገባለሁ አለኝ ምን ላድርግ አለቻቸው?
ሼኹ:- ሁለት ቤት ማስተዳደር አልችልም በይው--¡
منقول
#የጂኑ_ታሪክና_የ"አየቱል_ኩርሲይ"_ትሩፋት
🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
t.me/abu_reyyis_arreyyis
t.me/abu_reyyis_arreyyis
🔖ሼኸ ሷሊህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።
አንድ ሙስሊም ከሌሊት ሶላት ቁጥሩ
ቢያንስም እንኳን ሁሌም የሚዘወትርበት የሆነ የተወሰነ ድርሻ ሊኖረው ይገባል።
📚الملخص الفقهي(صـ ٩٣)
=
t.me/https_Asselfya🔖ወሳኝ መልእክት ለሴቶች
ብዙ ሴቶች ካገባሁ በኋላ ኢማኔ ደከመ፣ የኢባዳ ጥፍጥና አጣሁ… ሌላም ይላሉ።
ሚስጥሩ ወዲህ ነው። እሱም የባልሽ ሀቅ ስላልተወጣሽ ነው ሚሆነው። ባልሽ የማታከብሬ ፣ ትእዛዙን የምትጥሺ፣ አዛ ምታደርጊውና አሳንሰሽ ምትመለከቺው ከሆነ እንኳን የኢማን ጥፍጥና ማጣት ሌላም ነገር ይፈራልሻል።
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል።
(ሴት ልጅ የኢማን ጥፍጥና አታገኝም የባሏን ሀቅ በትክክል እስክታደርስ ድረስ።)
=Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ደርስ
~
* ኪታቡ፦ አልአርበዑነ ነውዊየህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር
* ቦታ፦ በአሸዋ ሜዳ፣ ዘህራ መስጂድ (ኮንደሚኒየም አጠገብ)
* ጊዜ፦ ሰኞ እና ማክሰኞ
* ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የምትችሉ ኪታቡን ገዝታችሁ ያዙ። የማትችሉ pdf ፋይል በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፦ https://t.me/IbnuMunewor/7390
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🔴 የመጀመሪያው ፕሮግራም
ተ
ጀ
መ
ረ
☑️ በኡስታዝ አቡ ረያን
ርዕስ :
"አል'ኢኽዋኑ አል'ሙስሊሙን"
https://t.me/dawaharaketema?videochat=590b95e29bd607dc51
አይ አሕባሾች! ግን ምን አይነት ፍጡሮች ናችሁ?
እንደሚታወቀው በተለያዩ ጊዜ በንፅፅር ዳዕዋ ላይ በተሰማሩ ኡስታዞችና ዳዒዎች አማካይነት ብዙዎች ወደ ኢስላም እየሰለሙ እንደሆነ ይታወቃል። ካፊሮች ወደ ትክክለኛው መንገድ ወደ ኢስላም እንድመሩ ለሂዳያ ሰበብ የሆኑና እየሆኑ ያሉ ኡስታዞቻችንን ዳዒዎቻችንን ልናግዛቸውና በምንችለው ሁሉ ከጎናቸው ልንቆም ይገባናል።አሏህ ለሁሉም ሰው የሂዳያ ሰበብ እንዲያደርጋቸውና አምሳያዎቻቸውን እንዲያበዛ ዱዓ እናድርግ።!
ይሁን እንጂ ለእንዲህና መሰል ለኸይር ስራ ያልታደሉት አሕባሾች ደግሞ ይህን ኸይር ስራ ለማደናቀፍና እንቅፋት ለመሆን ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል።ድሮም የአሕባሽ ስራ መበጥበጥና ሁከት መፍጠር ነው።ይህ አዲስ ነገር አይደለም። በተለይ ደግሞ የመጅሊስን ስልጣን ከተነጠቁ ወዲህ ጤናቸውም ትክክል አይመስለኝም።
ዶክተር ተብዬው ስለ የሚሰልሙ ሰዎች ተጠይቆ መጀመሪያ ከነበሩበት እምነት የስም ለውጥ አደረጉ እንጂ ምንም ያው እዛው ኩፍር ውስጥ ናቸው።ምንም ልዩነት የለውም። ነሷራ እያለ አባታችን ሆይ! በሰመያት የምትኖር ይል ነበር! ሰለመ ካሉ በኋላ አባታችን አትበል ይሉታል። ያው ተጅሲም ነው የሚያመልከው አለ ፈትዋ መሆኑ ነው! ድንቄም ፈትዋ!
ለነገሩ አሕባሾቹ እነ
ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ ዶክተር ተብዬው አቡበክር፣ ሐሰን ታጁ፣ዑመር ኮምቦልቻና ሌሎችም የአሕባሽ ግልገሎች አይደለም ከኢስላም ውጪ ያለን ሰው በንፅፅር ዳዕዋ አድርገው ወደ ኢስላም ልያመጡ ቀርቶ ኢስልምና ውስጥ ያለውንም ሰው ሺርክያት ወደ ቀብር አምልኮ፣የቀብር አፈር ወደ መብላት፣ወደ ጫት መቃምና በመንዙማ ነብዩን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን እናወድሳቸዋለን በሚል ሴትና ወንድ አደባልቆ ወደ መጨፈርና መዝለል ነው ጥሪ የሚያደርጉት።ስራቸው ይሀው ነው። ከዛም ይህ ነው ነባሩ እስልምና ይሉሃል።! ነባሩ ማለት የጥንት የጧቱ የሷሓቦቹ?! ድንቄም ነባሩ እስልምና!!
ኢንሻ አሏህ ዳግም ወደ መጅሊስማ አትመለሱም!! ህዝበ ሙስሊሙን ልታሳስሩ፣ልታስደበድቡ፣ልታስገድሉ፣መስጂዶችን ከቂርኣት፣ከዳዕዋና ከዒባዳ ባዶ አድርጋችሁ ጫት መቃሚያ መጨፈሪያ ድቤ መደብደብያ ልታደርጉት አሏህም አያሳካላችሁም ኢንሻ አሏህ!!
✍ወንድማችሁ:- አቡ መርየም
የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ሼርም ያድርጉ።
👉http://t.me/AbuMeryemNeja 👈
"በቀልድም እንኳ ቢሆን ጓደኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን ከመናገር ተቆጠብ --- ወዳጅነት ውድ ነው!
~
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
