uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 369 підписників, посідаючи 5 619 місце в категорії Релігія і духовність та 2 193 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 369 підписників.

За останніми даними від 24 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -18, а за останні 24 години на 1, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 23.10%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 8.16% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 551 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 254 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 22.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 25 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 369
Підписники
+124 години
+477 днів
-1830 день
Архів дописів
ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ። (©ኢኦተቤ ቴቪ የካቲት ፴/፳፻፲፭ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ሕገወጥና ኢቀኖናዊ ድርጊት ምክንያት በሕግ አግባብ የሚፈቱ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ መብት እና የአማኞችን ሁለንተናዊ መብት እንደከበር ያስችል ዘንድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች የጠበቆች ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዮችን በሕግ አግባብ እንዲፈቱ እየጠየቀችና እየተከታተለች እንደሆነ ይታወቃል። በዚህ መሠረት የጠበቆች ቡድኑ ዛሬ የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ/ም በዋለ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ችሎት የሰጠውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በጥልቅ ማብራሪ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም ፍርድቤቱ የቤተ ክርስቲያኗን ሕጋዊ ጥያቄ በሕግ አግባብ መልካም ውሳኔ የሰጠበት መሆኑን ግልጽና ጥልቅ በሆነው ገለጻው ተጠቁሟል። የጠበቆች ቡድኑ በመግጫው ሕገወጦቹ ያቀረቦቻው የመቃወሚያ ጉዳዮች እንደነበሩ አብራርቶ ፍርድቤቱ በውሳኔ ውድ አድርጓቸዋል ብሏል። ፍርድቤቱ ውድቅ ካደረጋቸው መቃወሚያ መከራከሪያ ነጥቦች መካከል ፩. ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ሰውነት ያላት በመሆኑ የመክሰስና የመከሰስ መብት የለት መሆኑንና በጉዳዩ ላይ ክስ መመስረት እንደምትችል። ፪. ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የመብት ጥሰት የንብረት ባለቤትነት ያለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት የሚችል መሆኑ በመጥቀስ የሕገወጡ ቡን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድ አድርጓል። በአጠቃላይ በሕገወጡ ቡድን የቀረቡ መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረግ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጡ ሹመት ላይ በተሳተፉ ፳፮ቱ ግለሰቦች ላይ ክስ እንድትመሠርት ውሳኔ ሰጥቷል። ከዚህ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ በጠየቀችው የሦስት ወር እግድ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤቱ ፵፭ ቀናት ከሦስቱ "አባቶች" በስተቀር ፳፮ (26)ቱም ግለሰቦች ከዚህ ቀደም የገቡበትን መንበረ ጵጵስና እና አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ "የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሏትን ይዞታዎች፣ አህጉረ ስብከት፣ገዳማት እና አድባራት፤ አብያተ ክርስቲያናት ንብረቶቿን፤ ታሪካዊ ቅርሶች፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ መገልገያ እንዳይጠቀሙ፣ ወደ ቅጥሯ እንዳይገቡ፤ ንብረቶቿን እንዳይወስዱ፣ እንዳይገለገሉ፣ ዓርማዋንና ስሟን እንዳይጠቀሙ ይህ ጊዜያዊ የዕግድ ትዕዛዝ ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀናት ብቻ (ከየካቲት ፫/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ድረስ ብቻ ተሰጥቷል"። መባሉን የጠበቆች ቡድን በመግጫው አሳውቋል። ከዚሁ ጋር የኦርዶክሳውያን የእስር ሁኔታ የተነሳ ሲሆን በአብዛኛው እየተፈቱ መሆናቸውን ጠቅሶ በሻሸመኔና በአርሲ ነገሌ አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን እስረኞ ለመጋቢት ፯፳፻፲፭ ዓ/ም ፍርድ ቤት እንደተቀጠሩም ተጠቅሷል። በዚህ ረገድ የሕግ ተርጓሚ አካላት ላይ የሚታየው ፍትሕን የማስፈን ተጠቃሽ ሥራዎችን በመመዘርዘር በፍርድ ቤቶች የሚስተዋለው ፍትሕን የማስፈን መንገድ የሚበረታታና የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሰው የጠበቆች ቡድኑ በአስፈጻሚ አካላት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የታየው የፍረድ ቤቶችን ውሳኔ ያለማስፈጸም ሁኔታዎች በእጅጉ ሊታረሙ እንደሚገባም ገልጿል። በሌላ በኩል "በፓስተር ዮናታን" እና "በፓስተር ኢዩ ጩፋ" የቀረበው ክስ ምን ላይ ደረስ? ለሚለውም በምላሹ ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን እያስኬደው እንደሆነ ተጠቁሟል። በመጨረሻም የጠበቆች ቡድኑ የሕጉን መንገድ ተከትሎ የቤተ ክርስቲያን መብትና ማስጠበቅ ሁነኛ ግቡ መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን ይሁን እንጂ የትኛውም መንገድ ይሁን ድርጊት ከቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ከአባቶች ቃል የማይቀድምና የማይበጥል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የምትከተላቸውን የይቅርታና የስምምነት አቅጣጫዎችን በማክበረ እንደሚቀጥል ገልጿል።

#የሚዳሰሰው_መጽሐፍ ፤ በዓላት ምን ? ለምን ? እንዴት ? #የመጽሐፉ_ይዘት ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለምታከብራቸው በዓላትና ምክንያት፣ ስለ በዓላት ምንነትና የት መጣነት፣
#የሚዳሰሰው_መጽሐፍ ፤ በዓላት ምን ? ለምን ? እንዴት ? #የመጽሐፉ_ይዘት ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለምታከብራቸው በዓላትና ምክንያት፣ ስለ በዓላት ምንነትና የት መጣነት፣ በበዓላት ላይ ስለሚነሱ ጥያቄዎች ለተሳሳቱ አረዳዶች በማስረጃና በአመክንዮ የሚያቀርብ መጽሐፍ ነው ። #ሐሙስ የካቲት 30 ምሽት 12 ፡ 30 #Orthodox_Book_Review

መረጃ! በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት መቀመጫ አሰላ ከተማ መንበረ ጵጵስናው በሚገኝበት ደብረ ምጽላል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የዛሬ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ሥርዓተ ቅዳሴ ታጉሏል። ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው ለዚህ ምክንያቱ ለሀገረ ስብከቱ ተሹሜያለሁ ያለው ግለሰብ ከሌሎች ሦስት ተሿሚዎች ጋር በመሆን በ5 ፓትሮል መኪና የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች ታጅቦ ቤተ ክርስቲያኗን ለመውረር እየሞከረ በመሆኑና ውጥረት በመንገሱ ነው። በትናንትናው ዕለት የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በሕገ ወጥ መንገድ “ኤጲስ ቆጶስነት” ከተሾሙት ግለሰቦች መካከል አንዱ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነኝ በማለት ወደ ሀገረ ስብከቱ መምጣታቸው ተገልጿል፡፡ የግለሰቡን ወደ ሀገረ ስብከቱ መግባት ተከትሎ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውጭ አንቀበልም በማለት ከአገልግሎት ቦታቸው ሳይገኙ ቀርተዋል። ይህንን መነሻ በማድረግ ሕገ ወጥ ተሿሚው ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሥራ እንድትገቡ የሚል የማስጠንቀቂያ መልእክት የተጻፈላቸው ሲሆን ማስጠንቀቂያውም የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ የአርሲ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በሚል በሕግ ዕውቅና የሌለው ማኅተም የተጻፈ ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ውስጥ በጋራ ሃገራዊ እና ማኅበረሳባዊ ጉዳዮች ላይ በአንድነት ይሰራል ተብሎ ከሚታመንበት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ውስጥ በጋራ ሃገራዊ እና ማኅበረሳባዊ ጉዳዮች ላይ በአንድነት ይሰራል ተብሎ ከሚታመንበት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት በዚህ መልኩ ለማበላሸት በመሪዎቹ አማካይነት ለሰራው ሕገወጥ ሥራ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል። tmc

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደረ ገጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መረጃዎችን በይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና ተቋማዊ የመረጃ ፍሰትን ለመተግበር አዲስ ድረ ገጽ ከፍታለች፤ ድረ ገጹ በተለይም በውጭ አገራት የሚገኙ ምዕመናንን በእጅጉ የሚጠቅም ስለሆነ በማስተዋወቅ እንድትተባበሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።ሁላችሁም ሼር አድርጉት። ድረ ገጹ https://eotceth.org ድረ ገጻችንhttp://www.finotehiwotsundayschool.com

መረጃ! በሻሸመኔ ከተማ ከአርባ በላይ ኦርቶዶክሳውያን በጸጥታ አካላት እንዲገደሉ ያደረገው ሕገ ወጡ ቡድን በዚህ ሰዓት የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን በመውረር ጸሎተ ምሕላ እ
መረጃ! በሻሸመኔ ከተማ ከአርባ በላይ ኦርቶዶክሳውያን በጸጥታ አካላት እንዲገደሉ ያደረገው ሕገ ወጡ ቡድን በዚህ ሰዓት የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን በመውረር ጸሎተ ምሕላ እያደረሰ ይገኛል። እንደ መረጃ አድራሾቻችን ገለጻ ይህ ድርጊት በጊዜ መፍትሔ ካልተሰጠው ተጨማሪ እልቂት መፈጠሩ የማይቀር ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

#ምኵራብ ፤ ሦስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ምንት ሦስተኛው ሳምንት ምኵራብ ይባላል፡፡ ጌታ በምኵራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት ሳምንት ሲሆን ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምኵራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ በብሉይ ዘመን ቢያንስ ዐስር የጎለመሱ ወንዶች (የቤተሰብ ኃላፊዎች) በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመስራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ዋናው ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ብቻ ነበር፡፡በምኵራብ ውስጥም የኦሪት የሕግ መጻሕፍትና በቅዱሳን ነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር፡፡ በኦሪቱ ምኵራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ፤ በመግረፍ ወይም ከምኵራብ በማስወጣት ሊቀጡ ስልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡ በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፤ በአምልኮታቸው ውስጥም ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡ በዚህ በምኩራብ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፤ ሕሙማንን ፋውሷል፡፡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ምዕራፍ ፷፩ን አንብቧል፡፡ በዚህ በዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ምኵራብ) የሚታሰበውም ይህ ነው፡፡ ፨ ‹‹ወደ አደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሳ፡፡›› ሉቃ. 4፥16 ፨ ‹‹ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር፡፡›› ማቴ. 13፥52 ፨ ‹‹ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፡፡››ማር 6፥1 ፨ በዕለቱ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡ ምንባባትም፤ ጌታችን ቤተ መቅደሱን የንግድ ማዕከል ያደረጉትን ዓይቶና አዝኖ ነጋዴዎቹን ከነመንጋቸው በጅራፍ እንዳስወጣቸውና ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን እኔ እሠራዋለሁ፡፡›› ብሎ ስለመ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ማስተማሩን የሚገልጽ ነው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/finotehiwotee

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ይገኛል። ቅዱስነታቸው የካቲት ፳፭/፳፻
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ይገኛል። ቅዱስነታቸው የካቲት ፳፭/፳፻፲፬ ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፉ ይታወቃል።

በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ባለበት ሰዓት ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ የበዓሉ ስነ ሥርዓት ሳይጠነቀቅ ታቦታተ ህጉ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል። በተወረወረው አስለቃሽ ጭስም በርካታ ምዕመናን ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን በቦታው የተገኙ የተ.ሚ.ማ ሪፖርተር ገልጸውልናል። ተሚማ