Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 601 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 374,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 203 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 601 名订阅者。
根据 06 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 52,过去 24 小时变化为 74,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 6.93%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.35% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 081 次浏览,首日通常累积 679 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 601
订阅者
+7424 小时
+697 天
+5230 天
帖子存档
፥ የተግባባ በመሆኑ “ማርቆስ አባታችን ፥ እስክንድርያ እናታችን” ማለት በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ የተለመደ ነበር፥ ታሪክ ነውና ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያናችን ሙሉ በሙሉ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ተላቃ በኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ብትመራም ይህ እውነታ ግን የሚዘነጋ አይደለም፡፡
---------------
፠ በፎቶ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤
* ሰላ ድንጋይ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአፄ ምኒልክና የተሠራና የአቡነ ማቴዎስ መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ በልዩ አሠራር በ42 ቆመ ብእሲ (ዐምድ) የታነጸ፡፡
* መናገሻ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአቡነ ማቴዎስ የተሠራና መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ ውጭው ክብ ውስጡ ግን ከሌሎች ክብ አብያተ ክርስቲያናት ልዩና ድንቅ በሆነ አሠራርና ሥዕላት የተሞላ፡፡ቀ
* ጎጃም ደብረ ማርቆስ፤
* መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ፤ አፄ ኀይለ ሥላሴ ከቤተ መንግሥታቸው ላይ ቦታ ቀንሰው ያነጹት ቤ.ክ.፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ_ሚያዝያ_፴
ማርቆስ የሚለው ስም 3ት ፍቺዎች አሉት ንብ፣ አንበሳና ካህን::
ሀ) *ንብ የሚለው ፍቺ የተሰጠው ንብ አበባ ካለው ተክል ሁሉ ቀስማ ማር እንድትሠራ እርሱም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከጌታ የተማርኩት ይበቃኛል ሳይል ከሐዋርያት ተምሮ ደገኛይቱን ወንጌልን በማስተማሩና በመጻፉ ነው፤
ለ) *አንበሳ መባሉ አንበሳ እንስሳት አራዊትን በክርኑ እንዲሰብር፤ በግብጽ ይመለኩ የነበሩ በእንስሳ አምሳል የተሠሩ ጣዖታትን በወንጌል ቃል ኃይልነት በማጥፋቱ ነው፡፡
ሐ. *ካህን የሚለው ትርጕም ደግሞ በሐዋ. 14፥13 “ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ” ተብሎ ከተመዘገበው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ የተወረሰ ነው::
፠ ማርቆስ ከመባሉ በፊት ዮሐንስ ይባል የነበረ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት ነው፤ ሐዋ. 12፥12፡፡ አባቱ አርስጦቦሎስ እናቱ ማርያም ይባላሉ፡፡ እናቱ ማርያም በጌታ ትምህርት አምነው ሲከተሉትና ሲያገለግሉት ከነበሩት
ደጋግ ሴቶች አንዷ ስትሆን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ቤቷን ለወንጌል አገልግሎት ሰጥታ ሐዋርያት በዚያ ተሰብስበው ለጸሎት ይተጉ ነበር፥ ጌታ ባረገ በ10ኛው ቀን (በተነሣ በ50ኛው ቀን) ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በአንድነት ሳሉ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉትም በዚሁ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሐዋ. 2፥1 ፤ 12፥12፡፡
፠ የራሱን ሀገረ ስብከት ይዞ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያትን እየተከተለ ይማር ፥ በተልእኮም ይራዳቸው ነበር:: ከቅዱስ ጳውሎስ መጠራት በኋላ ጳውሎስንና አጎቱ በርናባስን ተከትሎ በአንጾኪያ ፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትሎ በሮም አስተምሯል፤ እነርሱም በመልእክቶቻቸው “ማርቆስ ሰላም ይላችኋል” እያሉ አንስተውታል:: ሐዋ. 12፥25፣ ቈላ. 4፥10፣ 1ኛ ጴጥ. 5፥13
፠ በሮም ተልእኮው ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ ከፍጹምነት መድረሱን ዐውቆ ጵጵስና ሾሞ ከሀገረ ስብከቱ ግብጽን ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው፡፡ እርሱም ሊያስተምር ሄዶ ወደከተማ ሊገባ ሲቃረብ የጫማው ጠፍር ተበጥሶበት አንያኖስ ወደሚባል ጫማ ሰፊ ሄደና ስፋልኝ ብሎ ሰጠው። አንያኖስ ጫማውን ተቀብሎ ሲሰፋ መስፊያው እጁን ወግቶት “ኢስ ታኦስ” ብሎ ጮኸ “አሐዱ እግዚአብሔር” ማለት ነው፤ የጠራኸውን ታውቀዋለህን? አለው፥ ሲሉ ሰምቼ እንጂ ያስተማረኝስ የለም አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ፈቃደኛነቱን አይቶ አስተማረው አንያኖስም ከነቤተሰቦቹ አምኖ ተጠመቀ::
፠ ከዚህ በኋላ አንያኖስን አስከትሎ በከተማ እየተዘዋወረ ያስተምር ጀመረ፤ ሕዝቡም ትምህርቱን ሰምተው ፥ ተአምራቱን አይተው አመኑ፥ ተጠመቁ፤ አብያተ ጣዖታቱንም አፈራርሰው አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የጣዖታቱ አገልጋዮች የለመዱት ቢቀርባቸው በጠላትነት ተነሡበት:: ምእመናኑ ተሰብስበው አባታችን እንድትለየን አንሻም፤ ነገር ግን ገነውተ ጣዖታቱ በጠላትነት ተነሥተውብሀልና ቁጣቸው እስኪበርድ ጥቂት ጊዜ ወደ ሌላ ሥፍራ ሄደህ ቆይ አሉት:: አንያኖስን ኤጲስቆጶስ ልጆቹን ቄስና ዲያቆን አድርጎ ሾሞላቸው፤ በባርቃና በሌሎች 5 አውራጃዎች እየሰበከ ቅዱስ ጴጥሮስን ለመጠየቅ ወደሮም ሄደ፤ በዚያ ሆኖ በስብከቱ ያመኑ የእስክንድርያ ምእመናን የተማሩትን እንዳይዘነጉ የማርቆስ ወንጌል ተብሎ የሚታወቀውን ወንጌል በሮማይስጥ ቋንቋ ጽፎ ልኮላቸዋል:: ዘመኑ ጌታ ካረገ 11ኛው ሲፈጸም 12ኛው ሲጀመር ፥ ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሠ በ4ኛው ዓመት /45-46ዓ.ም. ባለው ጊዜ/ ነው::
፠ ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ግብጽ ተመለሰ፥ ምእመናኑ በቊጥር በዝተው፥ በእምነት ጐልምሰው አግኝቷተቸው ደስ ብሎት እያስተማራቸው አብሯቸው ጥቂት ጊዜ ቆየ:: በዓለ ትንሣኤን በሚያከብሩበት ቀን አምልኮ ጣዖት ከስሞ አምልኮተ እግዚአብሔር
በመስፋፋቱ ምቀኝነት ያደረባቸው ጣዖታውያን ሊጣሉት መጡ፤ ምእመናኑ አባታችን ሽሽ አሉት፤ እንግዲህስ በጌታዬና በአምላኬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ወንጌል ክብር መከራ ልቀበል እንጂ ልሸሽ አይገባኝም፥ አልሸሽም አለ፡፡ እንደ ላም በአንገቱ ገመድ አስረው በረሀ ለበረሀ ሲጐትቱት ዋሉ ፥ ሥጋው በእሾህ በጋሬጣ ተቀረደደ፡፡ ወደጌታ ቢያመለክት፤ ስለተቀበልኸው መከራ ክብርህን ከ12ቱ ደቀመዛሙርቴ ክብር አንድ አድርጌልሀለሁ፤ በስምህ የተማፀነኝንም እምርልሀለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለት ነፍሱን በቃለ አቅርንት፥ በይባቤ መላእክት አሳርጓታል:: በሞቱ ያልረኩት ጣዖታውያኑ ከሞተም በኋላ ሥጋውን ለማቃጠል ሽተው እንጨት ሰበሰቡ የሚያቀጣጥልላቸውን ዝፍትም በከመሩት እንጨት ላይ አርከፈከፉ፤ ጌታ ግን ይህን እንዲያደርጉ ዕድል አልሰጣቸውም ድንገት ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ፥ የተከማቹበት ሥፍራ ተናወጸ፥ የፀሐይም ብርሃን ተሠወረባቸው፤ በዚህ ጊዜ ምን መጣብን ብለው ማቃጠሉን ትተው ሸሽተዋል፡፡ ኋላ ግን ምእመናን በመብረቅ ጸዳል ተከብቦ አግኝተው በክብር ሥጋውን በአሌክሳንድርያ ቀብረውታል::
፠ በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 ዓ.ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት፤ በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር።
ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም የሮማው ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ፤ ቅዱሱ ባረፈ በ1900 ፥ በተወሰደ በ1140 ዓመት አጽሙ ሰኔ 17 ቀን 1960 ዓ.ም.
ፈልሶ ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ፡፡ ሲመለስም ጃንሆይም በስፍራው ተገኝተዋል፡፡
ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ሲያርፍ የ70 ዓመት አረጋዊ ነበረ፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ በዘለቀ መዋዕለ ስብከቱ ለዓለም ሁሉ የምስራች የሚሆን የወንጌልን ቃል ከመጻፉ ባሻገር ከሐዋርያዊ ተልዕኳቸው የተነሣ ብርሃናተ ዓለም ከተባሉ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በብዙ አህጉረ ስብከት ተዘዋውሮ በማስተማሩና ይልቁንም የጥንት ግሪክ ሥልጣኔ ተስፋፍቶባትና የሮማ ሥርወ መንግሥት ቁልፍ የፓለቲካና የንግድ መዲና በነበረችው እስክንድርያ በሰማዕትነት እስካረፈባት ቅጽበት ድረስ በአንደበቱም በሕይወቱም በክብሩና በመከራው ሁሉ
በማስተማር አይሁድን ከይሁዲነት ወደ ክርስቲያንነት ፥ አረማውያንን ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የመለሰ እንዲሁም በጸሎታቸው የሚጠብቁ፥ በትሩፋታቸው የጽድቅን ዋጋ የሚያሰጡ የባሕታውያን አባት አባ ጳውሊን፣ የመነኰሳት አባት አባ እንጦንስን፣ አባ ጳኩሚስ እና አባ ሰራብዮንን፤ መናፍቃንን ተከራክረው የረቱ ፥ ሃይማኖትን ያቀኑ ቅዱስ እለእስክንድሮስን ፥ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊን ፥ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያን፥ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትና ቅዱስ ዲዮስቆሮስን የመሳሰሉ ኦሮቶዶክሳውያን ሊቃውንትንና እስከ
ዛሬም መከራ ሳይበግራቸው፥ ሞትና ግርፋታቸውን እንደ ክብር ቈጥረው፥ በሃይማኖታቸው ፀንተው የሚኖሩ የጸኑ ምእመናንን ያፈራች አንፀባራቂ ስም ያላት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ያቋቋመ ሐዋርያ በመሆኑ ዳግመኛም ከ4ኛ ክ/ዘ/ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እስከ አቡነ ቄርሎስ 20ኛ ክ/ዘ/ ድረስ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በክህነት የመገቡ 111 ጳጳሳት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ያቋቋማት የዚህችው ቤተክርስቲያን ፍሬዎች በመሆናቸውና ትምህርታችን ከትምህርታቸው ፥ ሥርዐታችን ከሥርዓታቸው የተስማማ
ሥርዓተ ቀብራቸው ከ 4 - 5 ነው ።
+ የአባታችን የመጋቤ ሐብታት ታደሰ መልካሙ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለ 53 ዓመታት ባገለገሉበት በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነገ ሐሙስ ከ 5 እስከ 6 ይፈጸማል ።
+ ዛሬ ከምሽቱ ዠምሮ በማሕሌት በሰዓታት እና በጸሎተ ፍትሐት በቁመት ይታደራል።
#ከአባታችን በረከት ያሳታፈን ።
#ዜና_ዕረፍት
መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ
ከ1937 - 2015 ዓ.ም በአገልግሎት
‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ ፥ 38
* የደብራችን ታላቅ አገልጋይ ሊቀ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ፡፡
* ሥርዓተ ግብዓተ መሬታቸው የሚፈጸምበትን ዕለት እና ሰዓት እናሳውቃን።
፨፨
መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ በመናገሻ አውራጃ በአዳ በርጋ ልዩ ስሙ ደብረ ጽሙና ገዳም ከአባታቸው ከአቶ መልካሙ ባሻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ጥሩነሽ የለሙ ሰኔ 12 ቀን 1937 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም በዛው በደብረ ጽሙና ገዳም የንባብ መምህር ከነበሩት ከየኔታ ወልደ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የንባብ ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረው አጠናቅቀዋል፡፡ በመቀጠልም የዜማ መምህር ከነበሩት መምህር መንበሩ ገብረ ሕይወት ጋር በመሄድ የዜማ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በደብረ ጽሙና ገዳም የቅዳሴ መምህር ከነበሩት ከአባ ንዋይ ወልደ ማርያም የቅዳሴ ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ በ1953 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ ሚያዝያ 29 ቀን 1959 ዓ.ም ከ ወ/ሮ ትምክህተ ታደሰ ጋር በህገ ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ ተክሊል ጋብቻን በተማሩበት በደብረ ጽሙና ገዳም ፈጽመዋል ከጋብቻውም አንድ የልጅ ፍሬ አግኝተዋል፡፡ ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ በመስከረም 25 ቀን 1960 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ቅስናን ተቀብለዋል፡፡
በትውልድ አካባቢያቸው በቅስና ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ቆይተው መጋቢት 5 ቀን 1962 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ከመምሬ መኮንን ወልደ ሥላሴ ጋር በመምጣት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም በዲቁና ተቀጥረው ማገልገል ጀመሩ፡፡ ነገር ግን የመንግስት ለውጥን ተከትሎ መሬታቸው በመወረሱ ምክንያት እን በወቅቱ ይከፈላቸው የነበረው በዓመት 15 ብር የድጎማ ገንዘብ ቤተሰብ ለማስተዳደር በቂ ባለመሆኑ ከአገልግሎቱ ጎን ለጎን በመንግስት መስሪያ ቤት የፍትህ ሚኒስቴር በመቀጠር ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 1971 ዓ.ም በደብሩ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በወቅቱ የነበሩት የአጥቢያው ሽማግሌዎች ልጆቻችን ይመለሱ በማለታቸው ከተመለሱትና ዳግመኛ የሙሉ ሰዓት አገልግሎታቸውን ከጀመሩት አገልጋዮች መካከል የያን ጊዜው ሊቀ ዲያቆን የአሁኑ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ አንዱ ናቸው፡፡
መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ በደብሩ በሊቀ ዲቁና፤ በዳቦ ቤት ሽያጭ፤ በዳቦ ቤት ተቆጣጣሪነት፤ በደብሩ ገንዘብ ያዢነት፤ ደመወዝ ከፋይነት፤ በቄሰ ገበዝነት ለሁለት ጊዜ፤ በሰበካ ጉባኤ ተወካይነት፤ በልማት ኮሚቴነት፤ እንዲሁም በአሁን ሰዓት በስርዓተ ጋብቻ አስፈጻሚነት ተመድበው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ የንስሃ ልጆቻቸውን እና በጎ አድራጊ ምዕመናንን በማስተባበር ለቤተ ክርስቲያኑ አስፈላጊ የሆኑ ንዋየ ቅድሳትን በማሟላት ለተከታታይ 52 ዓመታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል፤
የአባታችንን ነፍስ ፥ አምላካችን መድኀኔዓለም ከደጋጎቹ አባት ከአብርሃም ከይስሓቅ ጋር ይደምርልን !
#የሥርዓተ ቀብር ሰዓቱን የምናሳውቅ ይኾናል ።
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ።
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
፪ኛው ዙር ፥ ዝክረ አበው ዘደብረሰላም
2015 ዓ.ም
ዓርብ ጠዋት ፤ ሚያዝያ 27 ።
✞ #እሑድ፤ #ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
‹‹ይትነሣእ እግዚአብሔር ወይዘረው ፀሩ
ወይጕየዩ ጸላዕቱ እምቅድመ ገጽ
ከመ የሐልቅ ጢስ ከማሁ የሐልቁ ››
መዝ ፷፯፥፩
እንኳን ለበዓለ ዳግም ትንሣኤ እና #ሚያዝያ_23_በዓለ_ክላሌሁ_ለሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰላም አደረሳቹህ
#ሥርዓተ_ማኀሌቱን ሰሙነ ፋሲካ ስለሆን እንደ #የደብሩ_ይትባህል እያጣቀሳቹህ እንድጠጠቀሙ የበዓለ #ትንሣኤን እና #የቅዱስ_ጊዮርጊስን ሥርዓተ ማኀሌት እነሆ ብለናን፡፡ #እስከ_ዳግም_ትንሣዔ_ድረስ_መልክ_አይደረስም!
https://t.me/medihanaelem/6274
#ሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ፡፡
※እናቱ ቴዎብስታ ስትባል አባቱ እንጣስዮስ ይባላል፡፡ አባቱ ባረፈ ጊዜ መስፋን ነበርና የእርሱን ሹመትን ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ሄደ፤ ሰዎችን ጣዖት አቁም በግድ እንደሚየስመልክ ባየ ጊዜ ፤ ባሮቹን ነጻ አውጥቶ ገንዘቡንም ለምስኪኖችና ለድኀች ሰጠ
ንጉሡም ከእርሱ ጋር እንዲተባብር ቢያባብለው እና ቃል ኪዳን ቢገባለት ቅዱስ ጊየርጊስ አልተቀበለውም ፡፡
※ለመስማት የሚያስጨንቅ መከራን እና ስቃይን አደረሰበት ጌታችን ግን መልሶ ያጸናዋል ቊስሉንም ያድንለት ነበር ፡፡
※ጌታችን ለቅዱስ ጊየርጊስ 3 ጊዜ እንደሚሞት እርሱም እንደሚያስነሳው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው ፤ ስሙ በዓለም ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ በተጋድሎና መከራ በመቀበልም ጽኑዕ በሆነ ሥቃይም ሰባት ዓመት እንደሚኖር
መላእክትም እንደሚያገለግሉት ነገርው ፤ ቃል ኪዳንንም ሰጠው ፡፡
※ ንጉሡ አትናስዮስ በሚባል ታላቅ ሥረየኛ መርዘ አስበጥብጦ እና ክፉ አስማትን አስርቶ ቢሰጠው ቅዱስ ጊያርጊስን ምንም ሳያገኝው ቀረ ፤ ሥርየኛውም ይህን አይቶ በኢየሱስ ክርስቶስ አሞኖ ሰማዕትነትን ተቀብሎ ሞቷል፡፡ከእርሱም ጋር #ሠላሳ ሺህ የሚሆኑ
ሰዎች አብረው የሕይወት አክሊልን ተቀብለው በሰማዕትነትን ዐረፈዋል፡፡
※ በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ የተቀመጡባቸውን የእንጨት ወንበሮች እንዲአብቡና እንዲበቅሉ አድርግ ቢሉት በጾሎቱ አድርጎ አሳያችው ይህንንም አይተው እጅግ ብዙ አህዛብ በአምላካችን አምነዋል፡፡
※ ብዙ መከራንም አደረሱበት በጐድጓዳ በረት ምጣድ ውስጥ አኑርው አበሰሉት ፤ እቃ ጥለው አሳርረው ሥጋውንና ዐጥንቱን ፈጭተው አመድ አድረገው በተኑት ፡፡ ጌታችንም ነፍሱን ከሥጋው መልሶ ዳግም አስነሳው ወደ እነርሱም ተመልሶ በጌታችን ስም ሰበካቸው ይህንንም አይተው
ቁጥር የሌላቸው አሕዛብ በጌታችን አምነው ሰማዕታት ሆኑ፡፡
※ ነገሥታቱም ሙታኖችን ብታስነሳ በአምላክህ እናምናለን አሉ ፤በጸሎቱ ሙታኖችም አስነሳላቸው በጌታቸንም ስም አምነው በእርሱ ስም አስተማሩ ጥምቀትንም ተቀበሉ ፡፡የቀሩት ነገሥታት ግን ሰይጣናትን ነው ያሳየኸን ብለው ተከራከሩ ፡፡
※ ከአንዲት እምበለት ቤት ተቀምጦ ምግብ ልትፈልግለት ሄዳ በተመለሰች ጊዜ ቤቷ ላይ ተአምር አየች ፤ የክርስቲያኖች አምላክ በሰው ተመስሎ እኔ ጋር መጣ ብትል ቅዱስ ጊየርጊስም #_እኔ_አምላክ_አይደለሁም_የአምላክ_ባርያ_ነኝ እነጂ አላት፡፡ የአምላክ
አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ እለምናለሁ አለችው ልጇንም በመስቀል ምልክት አማትቦበት ከዕውርነት አድኖታል ፡
※ ንጉሡም ተአምር ማድረጉን በሰማ ጊዜ በመንኰራኵርም ፈጨው ከከተማ ውጪ ወስደው ጣሉት ከሞትም ተነሣ ተመለሶም ወደ ነገሥታቱ ሄደ ፡፡ንጉሡም አድንቆ ይለምንው ጀመር በመንግሥቱ ላይ ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስ
እየዘበት ነገ ጠዋት ለአማልክቶች እሰዋለሁ ብሎት አደረ ፡፡ በሚጸልይበትም ጊዜ የንጉሡ ሚስት ሰምታ ጠየቀችው እርሱም ስለ ጌታችን አስተምራት አመነች ፡፡ በማግሥቱም ንጉሡ ሰውን ሰብስቦ እንደሚጠብቀውና እውነት መስሎ በታያት ጊዜ አዘነች ፡፡እርሱም
ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዚያም ወደ አጵሎን (ጣዖቱ) ሂድ ወደ እኔም እንዲመጣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እዘዘው አለው ፡፡ ልጁም ድኖ ቅዱሱ እንዳለው ሄዶ አዘዘው ፡፡ በጣዖቱም የነበረው እርኩስ መንፈስ ወጥቶ እኔ ሰውን የማስት
እንጅ አምላክ አይደለሁም አለው ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ምድር ትውጠው ዘንድ አዘዛት ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋር አጠፋቸውን ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር አፈረ፡፡
※ ንጉሡም ሚስቱ በጌታችን እንዳመነች ባወቀ ጊዜ በመጋዝ አሰነጠቃት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች፡፡
※ ነገሥታቱ ኀፍረት እንዳይጨመርባቸው ለንጉሡ በሰይፋ እንቁረጠው ብለው ጻፉለት እርሱም አዘዘ ፡፡ ድል አድራጊው ጊዮርጊስም ከሰማይ እሳት ወርዶ ሰባውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገኖች ጸጥ ይል ዘንድ ለመነ ፤ አሣቱም መጥቶ
ወዲያውኑ አጠፋቸው፡፡
※ጌታችን ተገልጾለት እጅግ ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጠው ፤ መታሰቢያህን የሚያደርግ ኃጢያቱን እደመስሳለሁ በመከራ ውስጥም ያለ በባሕርም ሆነ በየብስ በደዌም ሆነ በሕማም ያለ በስምህ የሚለምነኘን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለው ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፡፡
※ በስተ መጨረሻም ራሱን ዘንበል አድርጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም አክሊላትን ተቀበለ ፡፡ አገልጋዮቹም የቀረውን ሥጋውን ወስደው በልብስ ጠቀልልው ወደ ሀገሩ ልዳ ወሰዱት ፡፡ ቤተ ክርስቲያንንም ሰርተው በውስጥዋ አኖሩት ከእርሱም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎዋች ተአምራቶች ተገለጡ፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ምልጃ አይለየን
———
#ኮከበ ክብር፥
*ሊቀ ሰማዕታት፥
*መክብበ ሰማዕታት፥
*የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥
*የልዳ ፀሐይ፥
*የኢትዮጵያ ገበዝ፥
*ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥
*፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥
*በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ በዕረፍቱ ክርስቶስን የሰበከ፥ ከዕረፍቱ በኋላ ዛሬን ጨምሮ ፈጥኖ የሚራዳ፥
*፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥
*፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤
*እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር የተባበረ እንዲኾን ያደረገችለት፤
#ኀያል መስተጋድል
ኀያል ኮከበ ክብር፤
ኀያል ገባሬ ተአምር፤
ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር፡፡
#በእንተ ጊዮርጊስ ፍቁርከ (ሰማዕትከ፥ ምዕመንከ)፤
ምህላነ ስማዕ በዕዝንከ፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
——
✞ የሰሙነ ፋሲካ የመዠመርያው #ዐርብ፤ #ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በክርስቶስ ደም ተዋጅታ በተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያ በመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዐርብ «ቤተ ክርስቲያን» ተብላ ትጠራለች፡፡
ማቴ. 26 ÷ 26-29
የሐ. ሥራ. 20-28
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.
www.finotehiwotsundayschool.com
