uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 16 052 підписників, посідаючи 5 274 місце в категорії Релігія і духовність та 2 238 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 16 052 підписників.

За останніми даними від 30 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 511, а за останні 24 години на 3, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 23.32%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.33% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 742 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 658 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 29.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 31 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

16 052
Підписники
+324 години
+1077 днів
+51130 днів
Архів дописів
በፎቶ ላይ ያሉት ቤተክርስቲያን፤ 1ኛ) #አዲስ አበባ እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም፡፡ ይህች ገዳም ታሪኳ ከታላቁ ገዳማችን ዋልድባ (ገዳመ ዋሊ) ለ2ኛ ጊዜ መሥፋፋት (መመሥረት ጋር) የተያያዘ ታሪክ ያላት ናት፡፡ ይኸውም የሸዋ አባቶች ወደ ዋልድባ በ485 ዓ.ም. በንጉሥ አልአሜዳ ዘመነ መንግሥት ባቀኑ ጊዜ የተሰባሰቡባት ቦታ ናት፡፡ እነዚህም አበው ከመኖሪያ ቀዬቸው (ቡልጋ/ምንጃር/) ሁለት ታቦታትን (ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ዘምሕረት አምባ፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ዘአብየ ገዳምን) ይዘው ነበር፤ በዚህች በተቀደች ቦታ ይዘዋት በመጡት ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ገዳመ ሐመረ ኖኅን መሥረተዋል፡፡ የመድኀኔዓለም ታቦትን ደግሞ በታላቁ ገዳም በዋልድባ አኑረዋል፡፡ ይህች ሐመረ ኖኅ፤ - በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተስፋፍታ ተቋቋመች፡፡ - በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተ ጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡ - በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ - አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ - አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ - በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡ ይህች ቦታ ከታላቁ ገዳም ከዋልድባ ጋር አሁንም ግንኙነቷ እንደጠነከረ ነው፤ ከዋልድባ ያሉ አባቶች በተለያየ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በዋነኛነት የሚያርፉባት ጥንተ ርስታቸውም ናት፡፡ ይህች ቦታ በርካት ቅዱሳን በኪደተ እግር የረገጧት እንደመኾኗ፤ ጸበሏ የአጋንንት ድል መንሻ፤ የብዙ መነኮሳት መጠጊያ፤ የህሙማን መፈወሻ፤ የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎችም አንዷ ናት፡፡ 2ኛ) #ደብረ_መድኀኒት_ዐቢየ_እግዚእ_ኪዳነ ምሕረት፤ . በሃገራችን ኢትዮጵያ የመጻሕፍተ ብሉያት አንድምታ ትርጓሜ ዋና ማስመስከሪያ መካነ አእምሮ (University) የኾነች፤ . ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእ በኪደተ እግር የረገጧት፤ . በአቋቋም በኩልም የላይ ቤት አብነት የኾነች፤ . የታላላቅ ሊቃውንት መፍለቂያና ታላላቅ ሊቃውንት ወንበር አርግተው፥ ጕባኤ አስፋፍተው ያስተማሩባትና በማስተማር ላይ ያሉባት ቦታ ናት፡፡ የምትገኘውም ጎንደር ከተማ ነው፡፡ 3ኛ) ኢየሩሳሌም ደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት፡፡ ሕንፃ ግንባታዋ፤ በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ተጀምራ በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የተጠናቀቀች፡፡ 4ኛ) አዲስ አበባ #ስዕል_ቤት_ኪዳነ_ምሕረት፤ በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ግቢ ውስጥ የምትገኝ፡፡ በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የተሠራች፡፡ 5ኛ) #ራማ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡

#ፍኖተ_ሕይወት_/#የሕይወት_ጕዞ/፤ 30 ቀን (1 ወር ቀረው)፤ #መጋቢት_15/2011ዓ.ም.፡፡ ወደ #ኵሉ_ወይን_ቅድስት_አርሴማ፡፡ **በብዙሃን ዘንድ ዜናው ያልተሰማው፤ 3ት ትላልቅና ሌሎችም ክፍሎች ያሉት፤ ብዙ ንዋያተ ቅድሳት የተገኙበትና በቁፋሮ የተገኘው ጥንታዊ ዋሻ ይጎበኛል፤ **ምክረ አበው በሊቃውንት መምህራን፣ ዝማሬ በዘማርያን ይቀርባል፡፡ **ከሰ/ትቤታችን ምሥረታ ጀምሮ የነበሩና አሁንም ያሉ አባላት በአንድነት የሚሳተፉበት ዐቢይ ጕዞ፡፡ **ለበለጠ መረጃ፤ 0977 30 17 18

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፮_ (#የሰይጣን_ኀይል_በምን_እንደሚደክም፤ #ሰው_በሰራው_ኀጢአት_ተጠያቂው_ራሱ_እንጂ_ሰይጣን_እንዳልሆነ፤ #ሰይጣን_ሰዎችን_ፈጣሪያቸውን_እንዴት_ባለ_መንገድ_እንደሚያስክዳቸው፤ #አንድን_ኀጢአት_ያለፈን_ሰው_በሌላ_ኀጢአት_እንደሚፈትኑት፤ አባ ጳውሊ፤ ኃይላችሁ በምን ይደክማል? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ #ከፍቅር፥ ከትዕግሥት፥ ከጾም፥ ከጸሎት፥ ከመታዘዝ፥ ከትጋሃ ሌሊትና ከመሳሰሉት ትሩፋቶች ሁሉ ጋር ኃይላችን የሚደክመው #በትሕትና ነው አለው፡፡ እኛ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ጭንቅ የሆነ መከራ ከማምጣት ቸል አንልም አንቦዝንም፡፡ በሚቻለን ሁሉ እንፈትናቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተ እንደምትለኝ ከሆነስ ሰዎች ምንም ኃጢአት የለባቸውም፡፡ ኃጢአትስ የሚሆንባችሁ የክፋትንና የርኵሰትን ሥራ በምታሠሯቸው በአንተና በወገኖችህ ላይ ነው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ እኔ የንግድ ቤቱ ነኝ፡፡ በእኔ ዘንድም ብዙ የሚሸጡ የኃጢአት ዕቃዎች አሉኝ፡፡ የንግድ ቤቱንም በር እከፍታለሁ፡፡ ሁሉም እንደየፍላጎቱ የሚሻውን ይገዛል፡፡ ስለዚህ #ሰው ሁሉ በራሱ ፍላጎት የሚበድል ከሆነ እርሱ በሠራው ኃጢአት እኔ ስለ እርሱ አልጠየቅም፤ ኃጢአትም የለብኝም አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተ የተረገምህ! የንግድ ቤትህ እንዳይከፈት እግዚአብሔር ይቅር አይበልህ፡፡ ፈጽመህም መሸጥ እንዳትችል የንግድ ቤትህ ይዘጋ፤ ይፍረስ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አንተ ክፉ ሽማግሌ ያለ በደሌ ስንት ጊዜ ትረግመኛለህ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ከአንተ ጋር በመሆኔ ሃይሌን አደከምከኝ፤ ሰውነቴንም አሠቃየሃት፡፡ ስለዚህ እሄድ ዘንድ ተወኝ አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲክዱ የምታደርገው በምን መንገድ እንደሆነ እስኪ ዳግመኛ ንገረኝ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ በዚህ ዓለም የማደርገውን ሁሉ ነገርሁህ፡፡ #መጀመሪያ ልጆች የወላጆቻቸውንና የአሳዳጊዎቻቸውን ምክር እንዳይሰሙ፣ ለቃላቸውም እንዳይታዘዙና ከእናንተ ይልቅ በእውቀት እኛ እንበልጣለን፣ እኛ እናውቃለን እንዲሉ እናደርጋቸዋለን፡፡ ##ዳግመኛም ወላጆቻቸውንና በዕድሜ የሚበልጧቸውን እንዲሳደቡ እናደርጋቸዋለን፡፡ /፪ጢሞ.፫:፪/፡፡ በዚህ ምክንያት የቤተሰብ ፍቅር እናሳጣቸዋለን፡፡ በሄዱበት ሁሉ እየተረገሙ ይኖራሉ፡፡ ###ከዚህ በኋላ በዝሙት፥ በክህደት፥ የምንዝር ጌጥን በመውደድ፥ በስካር፥ በስርቆት፥ ነፍስን በመግደል እንዲወድቁ እናደርጋቸዋለን፡፡ በመጨረሻም ተስፋ ቆርጠውና አእምሮ አጥተው ቊጥር የሌለው ኃጢአትን እንዲሠሩ እናደርጋቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ በዕድሜ ያረጀ ዘመኑም የተቃረበና ሥጋውም የደከመ ሽማግሌ ኃይሉ ይደክማልና በምን ትፈትኑታላችሁ? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ እኛ በሽማግሌዎች ብዙ ምክንያት እናገኛለን፡፡ ስንፍና እናመጣባቸዋለን፤ ጾምንና ጸሎትን እንከለክላቸዋለን፡፡ ዘመናቸውን እስኪረግሙና ራሳቸውን እስኪያጠፉ ድረስ የሚያደርስ ጭንቀትና ጥርጣሬን እናመጣባቸዋለን፡፡ ክፉ ሐሳብንና ገንዘብ መውደድንም እናመጣባቸዋለን፡፡ ተስፋ መቁረጥን ሰላም ማጣትን በውስጣቸው እናደርጋለን፡፡ ከልባቸው የኅሊና ጸሎትን፥ ከአንደበታቸው ምስጋናን እናጠፋባቸዋለን፡፡ ለልጆቻቸው፥ ለዘመዶቻቸው፥ ለሚረዷቸው፥ ለሚቀርቧቸው ሁሉ ሁከተኞች እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ዳግመኛ እንዲህ ብሎ ጠየቀው፤ አንተ የተረገምክ ከእናንተ እያንዳንዳችሁ ሰው ሁሉ በፍትወት ተማርኮ ኃጢአትን እንዲሠራ ለማድረግ ሁላችሁም የተሰለፋችሁ አይደለምን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎ ሁላችንም #ሰውን በኃጢአት ምኞት ተማርኮ እንዲወድቅ ለማድረግ የተሰለፍን ነን፡፡ ብዙዎችንም እናስታቸዋለን፤ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እንዲሠሩ እናደርጋቸዋለን፡፡ ዳግመኛም #ከአጠመድነው ወጥመዳችን አምልጦ የወጣውን ሰው በሌላ በታላቅ የኃጢአት ወጥመድ እንዲወድቅ አጥብቀን እንዋጋዋለን አለው፡፡ #ለሰው በሚፈልገው ተመስለው በምትሐት እንደሚገለጹ፤ የሰይጣናት አሳሳች መሆናቸው ለጥቂት ደጋጎች እንጂ (በመጨረሻ በሥራቸው) እንጂ ለሁሉ እንደማይታወቁ፤ በገዳም የሚኖሩትን በምን እንደሚዋጋቸውና እንደሚያሸነፉት፤ ከሰው ልጆች የሚፈራቸውና የማይፈራቸውን .… ክፍል ፯.… ይቀጥላል ነገ ይጠብቁን/ /#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

እንኳን ለእመቤታችን ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል (ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ፤ ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኵሎ፡፡ (ድንግል ሆይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲኦል እሳት ባሰጠመን ነበር፡፡) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሲዖልን ካየች በኋላ ስለኃጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች የካቲት አሥራ ስድስት ቀንም በጎልጎታ ቦታ ቆማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች፡፡ ጸሎትና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ አገልጋይህ የምለምንህን ይህ ነው፡፡ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ፣ አብያተ ክርስቲያኔን ለሚሠሩ፣ ወይም ለታረዙ ለሚያለብሱ፣ ለተራቡ ለሚያጠግቡ፣ የተጠማውንም የሚያጠጡ(በስሜ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጡ) ፣ የታመመውንም የሚጎበኝ፣ ያዘነውንም የሚያረጋጉ፣ የተከዘውንም ደስ የሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ፣ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም፣ በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ በዓይን ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን በጎ ዋጋ ስጣቸው፡፡ በአማላጅነቴም የሚተማመኑትን ሁሉ ከሲዖል ነፃ አድርጋቸው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረሃብና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽን ቃልኪዳን እንዳይታበይ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘየካቲት_16፤ #በዓለ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡ በሃገራችን በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመው፤ የ3ት ዐበይት አድባራት አብነት ነው፡፡ እነዚህም፤ 1ኛ) የላይ ቤት፤ የደብረ መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት 2ኛ) የታች ቤት አብነት፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ 3ኛ) የደፈጫ ኪዳነ ምሕረት አብነት ናቸው፡፡ እኛም ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ የዐቢየ እግዚእንና የበዓታን ይትበሃል አንድ ላይ በቅደም ተከተል አድረገን አዘጋጅተንላችኋል፤ የደፈጫ ከላይ ከተጠቀሱት ከ2ቱ በጥቂት ቀለም ብቻ የሚለይ በመኾኑ አላካተትነውም፡፡ ስለዚህ እንደ የደብራችሁ ይተበሃል የላይ ቤት ከኾነ ‹‹ዘዐቢየ እግዚእ›› የሚለውን፤ የታች ቤት ከኾነ ‹‹ዘበዓታ) የሚለውን እንድትጠቀሙ እናሳስባልን፡፡ መልካም ማኅሌት፡፡

(ሃገረ ስብከቱ ደብዳቤውን ለሚመለከታቸው አካላት (ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ ለሀገረ ስበከቱ የተለያዩ ክፍሎች፣ ለወረዳውና ለክልሉ አስተዳደር አካላት፣ ጸጥታ አካላትና ለሚዲያ አካላት) ግልባጭ ድርጎ ጽፏል፡፡) (የለጠፍናቸው ደብዳቤዎች፤ ሀገረ ስብከቱ የገዳሙን ሀብትና ንብረት በአግባቡ መዝግበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ለአባ ዮሐንስ የጻፈውን፤ ሀገረ ስብከቱ ለፀረ ሙስና ኮሚሽን የጻፈውንና አባ ዮሐንስን ያገደበት ደብዳቤዎች ናቸው፡፡)

#እንወያይበት፡፡ #በእንተ_አባ_ዮሐንስ_ተስፋ_ማርያም_ /ጽሑፉን ሳታነቡ አስተያየት ባትሰጡ ይመከራል፡፡/ ያያችሁትን፥ የሰማችሁትንና የምታውቁትን ብትጽፉም እንዲሁ ይመከራል፥ ውይይታችን ሁሉ እውነቱን እውነት፥ ሐሰቱን ሐሰት በማለት ይሁን እንጂ፤ በጭፍን ድጋፍና ጥላቻ አይሁን!!!፡፡/ እኛ ግን ባየነው ደብዳቤ (የደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት የደራ ወረዳ ቤተ ክህነትን የጻፈለትንና መነሻ በማድረግና ራሱ ሀገረ ስብከቱም የጻፋቸውን ደብዳቤዎች)፤ እንዲሁም በሰመናውና ባየነው ቪዲዮ (አባ ዮሐንስ በታጣቂ ገበሬዎች ታጅበው የሰጡትን የቪዲዮ ንግግር) መነሻ አድርገን ይሄን ጽፈናል፡፡ #ጥር_3/2011ዓ.ም. #የደቡብ_ጎንደር_ሃገረ_ስብከት_በጻፈው_ደብዳቤ፤ *ገዳሙ የሚገኝበት የደራ ሐሙሲትና የአፈር ውኃ እናት ወረዳ ቤተ ክህነት ጥምር ኮሚቴ በነሐሴ 18/2010ዓ.ም. በቊጥር ደ/ወ/ቤ/ክ/340/2010 ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እንዲከበርና የገዳሙ ሀብት ንብረት እንዲመለስ መመሪያ ቢሰጥም ምላሽ ባለመሰጠቱና ከ2004ዓ.ም. ጀምሮ ሃገረ ስብከቱ ለአባ ዮሐንስ በሥርዐተ ገዳም እንዲመሩ በተደጋጋሚ መመሪያ ቢሰጣቸውም እርሳቸው ግን በዚሁ በአበው ሥርዐተ ገዳም ሊመሩ ባለመፈለጋቸውና ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምሕሮና ከሥርዐተ ገዳም ውጭ ራሳቸውን ከቅዱሳን በላይ በማድረጋቸው ደብዳቤውን እንደጻፈ ይገልጻል፤ *ሃገረ ስብከቱም በኅዳር 7/2011ዓ.ም. በቊጥር ደጎ/ሀስ/464/2011 የገዳሙን ሀብት ንብረት እንዲያስመዘግቡ ቢታዘዙም ማንም አያዘኝም በማለት ሪፖርት ሳያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይህንንም ለማስተካከል ይቻል ዘንድ በታኅሣሥ 17/2011ዓ.ም. ወደ ሃገረ ስብከቱ ሲጠሩ ጠበልተኞችን ሰብስቦ በማምጣት የሰላም ችግር በመፍጠርና፤ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የሚመሩትን ስብሰባ በመርገጣቸው፤ የሃገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጕባኤ በታኅሣሥ 24/2011ዓ.ም. ተሰብስቦ ባጠፉት የዶግማና ቀኖና ጥሰት እንዲሁም የገዳሙን ሀብትና ንብረት በግለሰቦች ስም በማድረጋቸው እንዲጠየቁ ወስኗል፡፡ አስተዳዳር ጕባኤውም ይህንን ለሚመለከታቸው አካላት፣ ለአባ ዮሐንስና ለገዳሙ በደብዳቤ አሳውቋል፤ ነገር ግን አሁንም አባ ዮሐንስ በሀገረ ስብከቱ ላይ በመዛትና በማስፈራራት ሁከት እየፈጠሩ እንዲሁም አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሽፋን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በአባ ዮሐንስ ላይ እንዲጣራባቸው የአስተዳደር ጕባኤው የወሰናቸው ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው፤ #በመስቀል ላይ ከሚቀረጸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ(ኢ.ና.ን.አ) ስም ይልቅ የአባ ዮሐንስ ስም እየተቀረጸበት እየተሸጠ በመገኘቱ፤ (የጽሑፉ አዘጋጆች ልዩ ምልከታ፤ ማንኛውም ምዕመን የአንገት መስቀሉ ላይ /በተለይ ወደ አኵሱም የሚሄድ ምዕመን/ የራሱን ስም ማስቀረጽ ሥርዐተ ቤ.ክ. አይደለም!!! መስቀል ላይ ሊጻፍ የሚገባው ስም ኢ.ና.ን.አ. የሚለው የአምላካችን ስም ነው፡፡!!) #በስዕለ አድኅኖ ፈንታ የአባ ዮሐንስ ፎቶ ግራፍ የገዳሙ ማኅተም እየታተመበት በ50 ብር እየተሸጠ መገኘቱ፤ #ሥርዐተ ገዳም በማይፈቅደው ሁኔታ በገዳሙ ውስጥ መኖር የማይገባቸውን ሰዎች እንዲኖሩ በማድረጋቸው፡፡ #ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጋደለው 7 ዓመታት ነው፤ እኔ የገተጋደልኩት 30 ዓመት ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ያጠመቀው ጌታችንን ብቻ ነው፤ እኔ ግን ያጠመኩት ዓለምን ሁሉ ነው፡፡ ስለዚህ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፥ ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እኔ እበልጣለሁ በማለት እያስተማሩ መሆናቸው፡፡ #ስግደት የሚገባው ለቅዱሳን ስዕላትና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቢሆንም በቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ የአባ ዮሐንስ ፎቶ ተደርጎ እየተሰገደለት በመሆኑ፡፡ #መስከረም 1 ቀን የአባ ዮሐንስ ልደት በሚል ሰበብ ከ5ት በላይ በሬ እየታረደ የገዳሙ ሀብትና ንብረት እየባከነ መሆኑ፡፡ (የጽሑፉ አዘጋጆች ልዩ ምልከታ፤ ሲጀመር ልደትን ያለቅጥ ማክበር የክርስቲያን ወይስ የአሕዛብ ጠባይ ነው!!!????) #በቤተ ክርስቲያን ሁል ቀንም፥ ሁል ጊዜም፤ የፈውስ ቀን፥ የበረከት ቀን ቢሆንም፤ የፈውስ ቀን በሚል የቤተ ክርስቲያንን የፈውስ ቀን በጥቂት ቀናት እንዲወሰኑ ማድረጋቸው፡፡ #የገዳሙ ጥሬ ገንዘብ በማን ስም እንዳለና ንብረቶቹ በዝርዝር የማይታወቁ በመሆናቸው #በሃገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና ሠራተኞች ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እያደረሱ በመሆናቸው ምክንያት ሃገረ ስብከቱ ደብዳቤውን ለሚመለከታቸው አካላት (ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ ለወረዳውና ለክልሉ ጸጥታ አካላትና ለሚዲያ አካላት) ግልባጭ አድርጎ ጽፏል፨ #ስለ_አባ_ዮሐንስ_መታገድና_ከአስተዳዳሪነት_መነሣትን_በተመለከተ #የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በየካቲት 07/2011ዓ.ም. ባካሄደው የአስተዳደር ጠቅላላ ጕባኤ የደራ ወረዳ ቤተ ክህነት አባ ዮሐንስን አግዶ እገዳው ይጽናልኝ ሲል የጻፈውን የይታገድልኝ ደብዳቤ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቋል፡፡ የማገጃ ደብዳቤውም የሚከተሉትን ነጥቦች አካቷል፤ **የከተማውን ሕዝበ ክርስቲያን በመከፋፈል ከፍተኛ የሆነ ችግር እየፈጠሩ ስለሚገኙ፤ **በቅዳሴ ጊዜ ጠቅጥቀው(ረግጠው) በመግባት ለምዕመናን እንቅፋት በመሆንና ራስዎትን እንደ መላእክት በመቊጠር ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በማፍለስ፤ ከቅዱሳን በላይ ነኝ እያሉ ሕዝበ ክርስቲያኑን በማደናገርዎ፤ **እኔ ከቅዱሳን እበልጣለሁ እያሉ ለምሳሌ ‹‹መጥምቁ ዮሐንስ ያጠመቀው ጌታን ብቻ በዮርዳኖስ /ነው/፤ እኔ ግን ዓለም ዞሬ አጠመኩ፤ ስለዚህ እኔ እበልጣለሁ በማለት ከሥርዐተ ቤተ ክርቲያን ውጭ ትምህርት በማስተላለፍዎ፤ **ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የፈውስ ሥርዐት በማለት ምዕመናኑን እያደናገሩና ግራ እያጋቡ መሆንዎት፤ **መስቀል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሁኖ ያዳነበት ሲሆን፤ እርስዎ ግን ከክርስቶስ መስቀል ላይ ስምዎትን በማስቀረጽና የእርስዎን ፎቶ እንደ ስዕለ አድኅኖ በገዳሙ ማኅተም በማስደገፍ እየሸጡ ምዕመናንንበማደናገርና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እያፋለሱ በመገኘትዎ፡፡ **ቃለ ዐዋዲው ከሚያዘው ሥርዐት ውጭ በመሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብትና ንብረት ጉዳዩ የማይመለከታቸውን ግለሰቦች በመሰብሰብ ንብረቱን እያባከኑና አላግባብ የልደት ቀን በማለት ገንዘቡን እያባከኑ መገኘትዎ፤ **የቤተ ክርስቲያኒቱ ቃለ ዐዋዲ ከመቶ ሃያ ፐርሰንት ለወረዳ ቤተ ክህነት እንዲከፈል ቢያዝም፤ እርስዎ ግን ከቃለ ዐዋዲው መመሪያ ውጭ በመሆንዎና በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊም ሆነ ማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ጠቅሶ የደራ ወረዳ ቤተ ክህነት በቊጥር 62/20011ዓ.ም. በቀን 03/04/2011ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ መሠረት ሃገረ ስብከቱ እርስዎ እየፈጸሙ ያሉት ድርጊት የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት፣ የገዳመ ሀብትና ንብረት ብክነትና ለማይመለከታቸው የገዳሙን ቋሚ ሀብትና ንብረትን መስጠት #ካጣራ_በኋላ_የአስተዳደር_ጕባኤው_ባደረገው_ስብሰባ_በሙሉ_ድምፅ_እግዳውን_አጽንቷል፤ ስለዚህ በእጅዎ ያሉትን የገዳሙን ማንኛውም ንብረት እንዲያስረከቡ በጥብቅ እየገለጽን፤ የደራ ወረዳ ቤተ ክህነት ርክክቡን እንዲያስፈጽም፤ /በሀገረ ስብከቱ/ ሊቀ ጳጳስ ደብሩን በቋሚነት የሚመራ አስተዳዳሪ እስኪመደብ ድረስ፤ ደብሩን በአግባቡ የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ወክሎ እንዲያቀርብ በዚህ ደብዳቤ (በየካቲት 07/2011ዓ.ም. በቊጥር ደጎ/ሀስ/831/2011) የታዘዘ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

#ጀግናውና_የቅኔው_አዝመራ_አለቃ_መርሻ_ወልደ_ማርያም ከዚህ በታች የቀረበውን ግጥማዊ ቅኔ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ሊገድሏቸው የመጡትን ጣልያኖች አብዛኛውን ፈጅተው በሐምሌ 12/1928ዓ.ም. በሰማዕትነት ያረፉት የ70 አዛውንቱ ጀግናና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከመሞታቸው ከ8 ቀን ቀድመው እንዲህ ብለው ተቀኙ፡፡ ተምሮ ተምሮ ካልሰበሰቡት፤ እንዴት ያሳዝናል ሲባክን ዕውቀት፡፡ ሂጅ ተመለሽ ግቢ አገርሽ ቅኔ፤ ወንዶች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡ ለጀግንነታቸውም መታሰቢያ የሚቀጥለው ግጥማዌ ቅኔ ቀረበላቸው፤ አለቃ መርሻ አይፈራም እጁ፤ ጠላት ሲጋበዝ እንደ ወዳጁ፤ ገሥግሠው ሄደው እንደ ጐመጁ፤ በሽጉጥ ጠርሙስ ፩ድ ፩ዱን ፈጁ፡፡ መርሻ ቢያጠጣው የሽጉጥ ጠላን፤ ወዲያው ወደቀ ግብዙ ጣሊያን፡፡ /ቢያነቧቸው ስለ የካቲት 12ና ስለ 5ቱ ዓመት የመከራ ዘመን በርካታ ቁም ነገርን ያስጨብትዎታል፤/ #አምስቱ የመከራ ዘመናት፣ ቅጽ 1፤ 44 የተመዘበሩ. የተቃጠሉና የጠፉ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ፣ እርቅይሁን በላይ፣ 2007 #“The Massacre of Debre Libanos, Ethiopia 1937” (“የደብረ ሊባኖስ እልቂት)፣ ኢያን ካምፕቤል፣ # "ሕይወቴ(ግለ ታሪክ)" ተመስገን ገብሬ፤ #የሸንቁጥ ልጆች፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ #"Yekatit" 12 Revisited: new light on the strike against Graziani Author(s): Ian Campbell Source: Journal of Ethiopian Studies, Vol. 40, No. 1/2, Festschrift Dedicated in Honour of Prof. Richard Pankhurst & Mrs. Rita Pankhurst (June-December 2007), pp. 135-154 /ታሪኩን ከመጻሕፍት አገላብጦና ምሁራንን ጠይቆ ላቀረበልን አምላከ ኢትዮጵያ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በእድሜ በጤና ይጠብቅልን፡፡/

ዐጤ ኀይለ ሥላሴም ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በኋላ በ6 ኪሎ ለሰማዕታቱ ሐውልት ቆመ መጀመሪያ የተሠራው አነስተኛ በመሆኑ ኋላ አሁን ያለው ትልቅ ተደርጎ ተሠርቷል፡፡ ቀኑ እንዳይረሳም ቤተ ሳይዳ ተብሎ ይጠራ የነበረው የካቲት 12 ሆስፒታል ተባለ፡፡ ከ8 ዓመት በኋላም የሰማዕታቱንም ዐፅም ሰብሰብሰበውና አፍልሰው በ4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክብር እንዲያርፍና መቃብር ቤት እንዲሠራለት ተደረገ፡፡ በሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍና ግጥም እንዲህ ይነበባል፤ #‹‹ዝንቱ ውእቱ ምዕራፈ አዕጽምቲሆሙ ለብዙኃን ኢትዮጵያውያን እለ ተቀትሉ በግፍዕ በእደዊሆሙ ለሕዝበ ኢጣሊያ ፋሽስታውያን አመ ፲ወ፪ ለየካቲት በ፲ወ፱፻፳ወ፱ ዓ.ም.፤ ወተቀትሎቶሙኒ ኮኑ በውግረተ አእባን ወበአብትር፥ በመክርይ ወበመስኤ፥ በመሕፄ ወበዕፀው፥ በመብረቀ ሐፂን ወበፀዓዕ፥ ወበውዕየተ እሳት ውስተ ቤቶሙ፡፡ ወበራብዕ ዓመት እምዘኮነ ዝንቱ ነገረ ግፍዕ ተመይጠ እግዚእነ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እም ሀገረ ብሪታንያ በግርማ መዊዕ፤ ወአቲዎ ብሔሮሙ ሠረዎሙ ለጸላእትነ ወአቀመ ትእምርተ ግዕዛንነ፡፡ ወእምድኅረዝ አዘዞሙ ለኅሩያኒሁ ከመ ያስተጋብኡ አዕጽምቲሆሙ ለእሉ እለ ተቀትሉ በግፍዕ ወያንብርዎሙ ውስተ ዝንቱ መካን ቅዱስ ዘሕኑፅ ለዝክረ ነገር ወለዝክረ ስሙ፤ ወኮነ በዓለ ፍልሰቶሙ ወተጋብኦቶሙ ለእሙንቱ አዕጽምተ ምውታን በ፲ወ፬ ዓመተ በዓለ ንግሡ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትየጵያ አመ ፳ወ፫ ለጥቅምት በዕለተ ኀሙስ በ፲ወ፱፻፴ወ፯ዓ.ም.፡፡›› #ራስን ካንገት ላይ ቈራርጦ እየጣለ፤ በችንካር ቸንክሮ ሰው እየገደለ፤ ሰውን ከነቤቱ አብሮ እያቃጠለ፤ ማነው እንደ ፋሽስት በሰው ግፍ የዋለ?፡፡ ሥጋችንን ገድለው ሳይቀብሩ እየጣሉ፤ ስማችንን ገድለው ሊቀብሩት ከጀሉ፡፡ በዚህ ያልነበሩ ሐሰት እንዳይሉ፤ እሊህ አስከሬኖች ይመሰክራሉ፡፡ ይህን ታላቅ ስቃይ መከራና ግፍ፤ ሲያስታውስ ይኖራል የታሪክ መጽሐፍ፡፡ አትርሱት አንርሳው ያስታውሰው ዘራችን፤ ኢጣሊያ መሆኗን መርዛም ጠላታችን፡፡ እናንት አእጽምቶች ዕድለኞች ናችሁ፤ በኃይለ ሥላሴ ትንሣኤ አገኛችሁ፡፡

የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች የሆኑት አርበኞችም፤ ጎራዴ መዝዘው ነፍጥ ይዘው በተለያዩ ቦታዎች እምቢ ለሃገሬ በማለት ሸፈቱ፤ በጎጃም ዱር ቤቴ ያሉት ለጣሊያን ፋታ አልሰጥ አሉት፡፡ ራስ አበበ አረጋይ ግንቦት 6/1928ዓ.ም. ጅሩ ገብተው የአርበኝነት ተግባራቸውን ሲጀምሩ ሌሎች ጀግኖች አርበኞችም እርስ በእርሳቸውም ተባበሩ፡፡ ለአብነትም ዋና ዋናዎቹ ከፊት መሪዎቹና አስተባባሪዎቹ ፊታውራሪ ዘውዱ አባ ኮራን፣ ዳዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ደጃዝማች ፍቅረ ማርያም ናደው፣ ፊታውራሪ በለው ቸርነት፣ ልጅ ኃይለ ማርያም ማሞ፣ ግራዝማች ዘውዱ አስፋው፣ ባሻ ወልደ ጻድቅ ሲሆኑ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በጎጃም ታላቁቅ የጅግንነት ጀብዱ ከፈጸመው ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ጋር ሕብረት ፈጠሩ፡፡ ይህ ሕብረትም ለጣሊያን ፋታ ሲያሳጣው፤ በሌሎች ቦታ ላሉ ኢትዮጵያውያኝ ፈር ቀዳጅ በመሆኑ ሁሉም ይተባባርና እምቢ ለሃገሬ ይል ጀመር፡፡ ለምሳሌም፤ ሰኔ 1928ዓ.ም. የሆለታ የጦር አካዳሚ ምሩቃን(ዶ.ር ያለም ወርቅ በየነን ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጦ)ና በውጭ ሃገር የተሰማሪ ሲቪሎች በመተባበር የመሠረቱት ‹‹‹ጥቁር አንበሳ›› አንዱ ነው፡፡ ‹‹ጥቁር አንበሳ›› ራስ እምሩን መሪው በማድረግ ብዙ ጀብዱዎችን ፈጽሟል፤ ጣሊያን ደቡብ ኢትዮጵያን ለመያዝ ካቶሊካዊውን ደጃዝማች ሀብተ ማርያምን በመጠቀም ቦንጋ አውሮፕላኖቿን ስታሳርፍ የጥቁር አንበሳ ማኅበርም በቦንጋ አውሮፕላን ማረፊያ የሰራው ጀብዱ ግን ከሁሉም የላቀና የማይረሳ ነው፡፡ ስለ ታላቁ አርበኛ ልጅ ኃይለ ማርያም ማሞ እንዲሁም ለጃዝማች ኃይሉ እንዲህ ተብሎ ተገጥሞላቸዋል፤ እውነተኛው ጀግና ኃይለ ማርያም፤ ስሙ እንዳይረሳ ጻፈልን በደም፡፡ እንዲህ ያለው ጀግና እንዲህ ያለ ወንድ፤ ጌጥ ይሆናቸዋል ለታሪኮች ዐምድ፡፡ የተባለለት የደጃዝማች ኃይሉ እጁ ውድ ናት፤ የቀመሱ ሁሉ ሲያመሰግኗት፡፡ ሌላው ፋሽስትን በተባበረና ስልታዊ በሆነ መልኩ በሐምሌ 21/1928ዓ.ም. በአዲስ አበባ መቀመጫና መቆሚያ ያሳጡት የሸዋ አርበኞች ሲሆኑ አሰላለፋቸውም፤ በሰሜን አዲስ አበባ ወንድማማቾቹ ደጃዝማች አበራ ካሣና ወንድወሰን ካሣ የሚመሩት ሲሆን በውስጡ ሰማዕት የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ያካተተ ነው፡፡ በሰሜን ምሥራቅ አዲስ አበባ፤ በራስ አበበ አረጋይ የሚመራ፡፡ በምሥራቅ አዲስ አበባ፤ በደጃዝማች ፍቅረ ማርያም ናደው (አባ ተጫን)ና ነጋድራስ ቦጋለ የሚመራ፡፡ በደቡብ አዲስ አበባ፤ በደጃዘማች ባልቻ አባ ነፍሶ የሚመራ ሠራዊት ተጀምሯል፡፡ነገር ግን ወቅቱ ክረምት በመሆኑና ወንዞች በመሙላታቸው አርበኞች ተቀናጅተው እንዳይዋጉና ሕዝቡንም እንዳይቀሰቅሱ ትልቅ እክል ሁኖባቸው ነበር፡፡ በዚህም ሙሉ አዲስ አበባ ላይ አደጋ ጥሎ ጣሊያንን የማስለቀቁ ተግባር የታለመለትን ያክል ባየሳካም በጠቂት አቅጣጫዎች ጀግኖች አርበኞች ተዋግተዋል፡፡ የተወሰኑትም ወደ ፍቼ ሸሽተዋል፤ ታላቁ አባት ብፁዕ ጴጥሮስም የታያዙት በዚሁ ወቅት ነበር፡፡ ጀግኖቹም ጣሊያንን እምቢ ለሃገገሬ በማለት እስከ የካቲት 12/1929ዓ.ም. የጉያ ረመጥ ሁነውበታል፡፡ ከ1927-1934 ዓ.ም. ለ7ት ዓመታት ጣሊያን በሀጋረችን ላይ ያደረሰችው ጥፋት፤ *በኢትዮጵያ ሰሜንና ደቡብ በየቀለቡና በማደሪያው ከዘመተው የሞቱ፤ *ጠላት አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ዓረቦችና ዓርመኖች ግሪኮች ተዘርፈናል በማለታቸው ምክንያት የሞቱ፤ **የካቲት ሚካኤል (የካቲት 12) ዕለት በአካፋ በዱላ በእሳት ያለቁ የሞቱ፤ *በአርበኝነት በየጊዜው በጠላት እጅ የሞቱ፤ *በደኅንነት አገር ቤት ላይ ሳሉ ሳያስቡት በጠላት እጅ የሞቱ፤ *ወደ ስደት ሲሄዱ በችግር ምክንያት በየመንገዱ የሞቱ፤ *በፌርማቶሪ አመልካችነት በየቀኑ የሞቱ፤ *ጠላት ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በተደረገው ጦርነት የሞቱ፤ *ከጠላት ወገን ሆነው (ባንዳዎች) ሆነው ከተዋጉ ባንዳ የሞቱ፡፡ *ሞሶሎኒ ባነሳው ጦርነት በየቀኑ በሚደረገው የግፍ ሥራ ያላግባብ የሞቱ (በሆለታ ተማሪ ቤት የነበሩ ወጣቶች፣ #የካቲት_12/1929ዓ.ም. (#የሰማዕታት_ቀን) ግራዚያኒ በናፖሊ መስፍን አልጋ ወራሹ ኡምቤርቶ ወራሽ በማግኘቱ ምክንያት ዐርብ የካቲት 12/1929ዓ.ም. በአዲስ አበባ የሚገኙ ድሃዎችንና ነዳያንን እንዲሰበሰቡ አደረገ፡፡ በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ቀትር ላይም ንግግር ማድረግ ሲጀምር በወቅቱ የተገኙትና የጣሊያን ፋሽስትነት ያንገፈገፋቸው አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ሰባት ቦንብ በግራዚያኑ ላይ ወረወሩ፤ በጥቃቱም ግራዚያኑ 365 ቦታዎች ላይ ቆሰለ /በይበልጥ እግሩ ቆሰለ/፣ 3ት ኢጣሊያናውያን ሞቱ፣ 50 ቆሰሉ፣ በተለይም የጦር አዛዡ አውራሊያ ሊአታ ከን ዓይኑ ጠፋ፡፡ በዚህም አንድም ኢትዮጵያዊ እንዳያመልጥህ ግደል በመታዘዙ በፋሽስት ኢጣሊያ በመትረየስ፣ .... በአካፋ ጭምር ሊረዳ የመጣውን ድሃና ነዳይን ጨምሮ 30 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሰዕትነት አረፈ፡፡ ይህ ግድያ ወደ ታላላቆቹ ገዳማትና አድባራትም በመዛመት በደብረ ሊባኖስ ያሉ 2200፤በዝቋላ ገዳምም 120 መነኰሳትና ምዕመናን ተረሸኑ፡፡ አስከሬናቸውንም ክብር ባለመስጠት በአካፋ በማንሳት አሰቃዩት፡፡ እንዲሁም 350 የሚጠጉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ሮምና ሞቃድሾ እስር ቤት ተላኩ፤ ከ2500 በላይ ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው እንዲማቅቁ ተደረጉ፡፡ በእስረኞችና በምርኮኞች ላይም አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡ ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጋዎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገድልና ዱር አላገኝ ስትል ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460 770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746 800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤ 300ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤ 2000 አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣ በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡ ለአብነትም ካቃጠለቻቸው ገዳማትና አድባራት መካከል፤ *ይደመቆ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን /ሰሜን ሸዋ/ *አፈር ባይኔ ተክለ ሃይማኖት ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/ *አክርሚት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/ *ጎበጥ አገር ገብርኤል ቤ.ክ ሰሜን ሸዋ እም ምሕረት/ *አንኮበር ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. *ደረፎ ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. /ሰሜን ሸዋ ደረፎ/ *ጎንቻ መድኃኔ ዓለም ገዳም /ምሥራቅ ጎጃም/ *አንኮበር ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ. ይገኙበታል፡፡ (ምንም እንኳን አልፎ አልፎ እንደ ማኅበረ ሥላሴ ያሉ ገዳማት አባቶች በጸሎታቸው አውሮፕላናቸውን እንዲከሰከሱ ቢያደርጉባቸውም) ኢጣሊያ ላደረሰችው ጥፋት 326 ቢሊዮን ሊሬ ቢወሰንባትም የሰጠችው ግን 105 ቢሊዮን ሊሬ ብቻ ነው፡፡ (እንደ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ዘገባ ደግሞ 175 ሚሊዮን ስተርሊንግ ተወስኖባት የከፈለችው 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው)፡፡ በከፈለችው ገንዘብም የቆቃ ግድብ ብቻ ተሠርቶበታል፡፡

/ከትናንቱ የቀጠለ……/ #ለየካቲት_12_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_ማስታወሻ የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ኢትዮጵያን ልትቀራመት ወሰኑ፡፡ ለዚህም ውሳኔ ያደረሳቸው ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላው አባ ማስያስን(የጣሊያ ንጉሥ የቪክቶሪ ንስሐ አባትን ቀድሞ በትንሹ ራስ ዐሊ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው) በአፄ ቴዎድሮስ ተባሮ፤ እንደገና በአፄ ዮሐንስ ዘመን ወደ ሃገራችን ገብቶ ነበር፤ አሁንም መልሰው አፄ ዮሐንስ ሲያብርሩት ለጣሊያን መንግሥት የኢትዮጵያን ልዩ መልክአ ምድሮችና በዓለም ላይ ልዩ ሃገር መሆኗን 2ት መጻሕፍት ጽፎ ለጣሊያን መንግሥት በማስረከቡ በዚሁ መሠረት ጣሊያኖች በመቋመጣቸው ነው፡፡ #የመጀመሪያው_ወረራና_ጦርነት መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ(እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘ በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡ ከኤርትራ ሲሻገሩ መጀመሪያ ጦርነት ያደረጉት በ1887ዓ.ም. በወርኃ ጥር በዶጋሊ ከአጼ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና ከሐማሴኑ ባላባት ከጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋ ጋር ነው፡፡ ጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋም ጠላትን ድል በማድረግ ወደ ምጽዋ መልሰውታል፡፡ ለራስ አሉላ አባ ነጋም እንዲህ ተብሎ ተግጠሞላቸዋል፡፡ ‹‹የአሉላ ፈረስ የረገጣቸው፤ እስካሁን ድረስ አለ ቊስላቸው፡፡ የአሉላ ፈረስ ተስቦ ወርዶ፤ ያንን ነጭ ገብስ አረገው ነዶ፡፡›› ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በማድረግ በየካቲት 1885ዓ.ም. ዐጤ ምኒልክ የውጫሌ ውል እንደማይሠራ ለአውሮፓ መንግሥታት ደብዳቤ ጻፉ፡፡ በዶጋሊ የተሸነፉትና በውጫሌ ውል አልሆን ያላቸው ጣሊያን በኅዳር 29/1888ዓ.ም. ጦርነት ከፈቱ ጀግኖች ኢትዮጵያኖችም ሻለቃ ቶዘሊንና ሌሎች ፋሽስቶችን እንደ ነፋስ ትቢያ አድርጎ በተናቸው፡፡ ቀጥለውም በየካቲት 23/1888ዓ.ም. ጠዋት 12 ሰዐት አመሻሽ 12 ሰዐት ባለቀው፤ እንኳን ለኢትዮጵያውይን ይቅርና ለአፍሪካውያን ኩራትና የጀግንነት ተምሳሌት የሆነው የአድዋ /የሶሎዳ ተራራ/ ጦርነት በጀግናው መሪ በዐጤ ምኒልክ ድል አድራጊት ተጠናቀቀ፤ ጣሊያንም የሽነፈት ጽዋዋን ጠጥታ ተመለሰች፡፡፡ዐጤ ምኒልክም ሚያዝያ 15/1889ዓ.ም. ወደ መናገሻ ከተማቸው ሲመለሱ የማረኳቸወን ጣሊያኖች ዛሬ ‹‹ጣሊያን ሰፈር›› በሚባለው ቦታ አኖሯቸው፡፡ ‹‹የአዲስ አበባ ውል›› ተብሎ በሚጠራው በኢትዮጵያና በጣሊያን በተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ ምርኮኞቹን እንድትፈታ፤ የውጫሌ ውል መሠረዙና፣ ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ ጣልቅ እንዳትገባ፤ የኤርትራ ድበር እስኪከለል ጣሊያን ከጦርነቱ በፊት ባለችበት እንድትረጋ በሚል ተከናወነ፡፡ #ሁለተኛው_ወረራና_ጦርነት ሁለተኛው ጦርነት ከ1929ዓ.ም.-1933ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ (ለዚህ ጦርነት ደግሞ መሠረቱ ጣሊያን የቀድሞ ሽንፈቷ ቂም በመያዟ ነው)፡፡ የተጀመረውም በኅዳር 26/1927ዓ.ም. በወልወል (የኢትዮጵያ ሶማሌ ክፍለ ሃገር በኦጋዴን ውስጥ በዋርዴር አውራጃ አካባቢ የምትገኝ ወረዳ ስትሆን ንጹሕ የከርሠ ምድር ውኃ የሚገኝባትም ነች፤ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ 350 ጥልቅ የውኃ ጕድጓድ አስቆፍረውላታል) ላይ ጣሊያን ባንዲራዋን በመትከሏ ምክንያት ነው፡፡ በዚሁም ምክንያጥ የአውራጃው ገዢ ፋውራሪ ዓለማየሁ ከጣሊያኑ ጦር አዛዥ ካፒቴን ችማሩታ ጋር ጦርነት ገጠመዋል፤ በጦርነቱም ጀግናው ፊታውራሪ ዓለማየሁ በፋሽስታዊ ታንክ ነጂ በገዛ ታንኩ ላይ ላይ ተወርውረው በመውጣት ሰይፈውታል፤ ብዙ የጀግንንት ሥራንም አከናውነዋል፤ ቆይቶ ግን ለሃገራቸው በጀግንነት እየተዋጉ ሣለ ከሌሎች 107 ኢትዮጵያውያን ጋር አርፈዋል፡፡ በዚህ ውጊያ ላይ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ባንዳ በመሆን ለሃገራችን ጠላት ቢሆኑም (ለምሳሌ ሡልጣን ኢብራሂም አሰብን ለሮማ ልዑካን ሸጥኩላቸው የሚለውና፣ የአዳል ባላባት የራሄታ ሡልጣን ሐሰን ሙሐመድለሮማ ሚስዮናውያን የኢትዮጵያን ወደቦች እነሸጣለን ብሎ የመከረ)፤ ለሃገራቸው ሲሉ የተዋጉ የሙስሊም አርበኞችም ነበሩ፤ ዋነኞቹም ኑር ሑሴንና ደጃዝማች ዑመር ሰመትር ይጠቀሳሉ፡፡ በዚሁም ጣሊያን ‹‹ጅራፍ ረሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል›› እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዜጎቹን ገድላብኛለችና 200 ሺህ ሊሬ ካሳ ትክፈለን ብለው ለመንግሥታቱ ማኅበር ከሰሱ፡፡ ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ በድርድር ያልቃል ብላ ስትጠብቅ በጎን ግን ኢጣሊያ ለጦርነት ስትዘጋጅ ቆየች፤ በኅዳር 1927ዓ.ም የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስቴር ፒየር ላቫል ኢጣሊያ ከጀርመን ሂትለር ጎን እንዳትሰለፍ በማሰብ ኢትዮጵያን ብትወርር እንደማትቃወም አሳወቅ፤ ጦርነቱን የተቃመወችው ሩሲያ ብቻ ነበረች፡፡በመስከረም 22/1928ዓ.ም. ኢጣሊያ የመረብን ወንዝ ተሸግራ ጦሯን በ3ት መስመር አሰልፋ ወደ ኢትዮጵያ ምድር ገባች፡፡ ያገኘችውንም እያጠፋች እንትጮንና አዲግራትን በያዝ ዓድዋ ደረሰች፤ ለዚሁም አስተዋጽዖ ያደረጉላት ለግል ጥቅማቸው ያደሩ የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑ ባንዳዎች ነበሩ ለአብነትም ዋነኞቹ (ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ፣ ደጃዝማች ሀብተ ማርያም፣ ደጃዝማች እጅጉ አያሌው) ናቸው፡፡ ባንዳ ደጃዝማች እጅጉ አያሌው የጎንደርን ሕዝብ አሳምኖ ለኢጣሊያ ተገዢ ለማድረግ መንቀሳቀሱን ጀግናው አርበኛ ደጃዝማች ታደሰ ይማም ወንድይራድ ሲሰማ ያለበት ድረስ ደርሶ ድባቅ መትቶታል፤ ባንዳው እጅጉ በጣና ሐይቅ በታንኳ ተሸግሮ አምልጦ ወሎ ተደበቀ፤ ይህንንም ታላቁ አርበኛ ደጃዝማች ታደሰ ወሎ ድረስ ዘምቶና ከበባ አድርጎ ሃገሩን ለሸጠ ምሕረት አይገባውምና እንደ በግ አርደውታል፡፡ ጣሊያኖች በባንዳዎች በመታገዝ ጭምር በመርዝ ጋዝ ታግዘው በየካቲት 27 ከራስ ሙሉጌታ ጋር በተደረገው ውጊያ የራስ ሙሉጌታ ጦርን በመደምሰሳቸው በሐበሾች ዘንድ የሞራል ውደቀት አስከትሏል፡፡ ነገር ግን ጀግኖች አርበኞች እምቢ ለሃገሬ በማለት በተንቤን፣ በእንደርታ፣ በሽሬ፣ በአሸንጌ ላይ ተዋጉ፡፡ በአሸንጌው ጦርነት ጠላት ጣሊያን ከላይ በአውሮፕላን ጠላት ባንዳ ደግሞ ከታች በመሆን 8ሺህ የሚጠጉ አርበኞቻችን ላይ ጉዳት አደረሱ፡፡ በመጋቢት 24 ለ13 ሰዐታት በተካሄደው የማይቸው ጦርነት ላይ ኢትዮጵያውያን ድል አድረገው ጦርነቱ ማብቂያ ላይ የመርዝ ጋዝና የቦንብ ውርጅብኝ ከአውሮፕላን ላይ በማዝነብ ጀግኖች አርበኞቻችን አብዛኞች አለቁ፤ ከማይጨው የተረፉና በአሸንጌ ላይ የነበሩትን ጀግኖች አርበኞችን 150አውሮፕላን ደርሰው ደብደቡት በመትረየስም ፈጁት፡፡ (ጣሊያኖች ዚሁ ወረራቸው በሰሜን 300፣ በደቡብ 150 አውሮፕላን አዝምተዋል፡፡) በአምባ አራዶም 50 ሺህ፣ በሽሬና በተንቤን 15 ሺህ ሰው ሙቶ 200 ሺህ ሰው ቆስሏል፡፡ በሚያዝያ 24/1928 ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ለተባበሩት መንግሥታት አቤቱታ ሊያቀርቡ ወደ ጄኔቫ ሄዱ፤ በሃገሪቱ ንጉሠ ነገሥቱ አለመኖሩን ጣሊያኖ ሲያውቁ በ3 ቀናት በመገስገስ በሚያዝያ 27 አዲስ አበባን ተቈጣጠሩ፡፡ በእነዚህ 3ት ቀናት ውስጥም ሽብር ዘረፈና ግድያ በአዲስ አበባ እጅጉን በርቶቶ ነበር፡፡

‹‹#የአካፋው_ሚካኤል››፤ #የካቲት_12 ለሁለተኛ ጊዜ ሃገራችንን ልተውርር በመጣችው የጣሊያን የጦር ሹም የነበረውን ብራዚያኒን ለመግደል ጀግኖቹ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በጣሉት አደጋ ግራዚያኒ በመቁሰሉና አመራሮቹ በመሞታቸው የተቆጣው የጣሊያን ጦር በአዲስ አባባ በየካቲት 12/1929ዓ.ም. ለቅዱስ ሚካኤል ወርኋዊ በዓል በየቤተ ክርስቲያኑ የተገኙትን (ለምጽዋት የተሰበሰቡትን ጨምሮ)ና በየቤቱ በመግባት 30 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ በአካፋ ጭምር እንደ ቅጠል አረገፏቸው፤ 30ሺህ ሰማዕታት በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ከጥቂት ናት በኋላም የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኰሳትን አርበኞችን ደብቃችኋል በሚል በተቀደሰው ስፍራ ተረሸኑ፡፡ በዚህም ምክንያት ጣሊያን ይህን አሰቃቂ ግፍ ስትሠራና የሰማዕታቱን የከበረ አካል በአካፋ በመሰብሰቧ ‹‹የአካፋው ሚካኤል›› በሚል መጠሪያ ይጠራል፡፡ በተለይም በ6 ኪሎ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ የቅዱስ ሚካኤል ታቦተ ሕግ ወጥቶ በልዩ ጁኔታ ይከበራል፡፡ (እናት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም ቢሆን የሃገርና የቤተ ክርስቲያን ባለውለታዎችን አትዘነጋምና!!!!) (እናቶቻችንና አባቶቻችን እንደነገሩን በቀጨኔ የሚገኙ አያቶቻችን የተሠዉና ግማሾቹም ይህንን ዜና ሲሰሙ ወደ 6 ኪሎ ከመኄድ ተመለሱ እንዳሉ ልብ ይሏል፡፡) /ክፍል ሁለትን ለነገ ይጠብቁ፡፡/