uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 949 підписників, посідаючи 5 314 місце в категорії Релігія і духовність та 2 236 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 949 підписників.

За останніми даними від 20 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 404, а за останні 24 години на 7, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 24.81%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.55% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 957 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 682 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 25.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 21 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 949
Підписники
+724 години
+1617 днів
+40430 днів
Архів дописів
#ዘመነ_አስተርእዮ ፠ “አስተርእዮ” በገሀድ መታየት በይፋ መገለጥ ማለት ነው፡፡ በጽርዕ ቋንቋም ኤጲፋኒ(Epiphany) ይባላል፡፡ ዘመነ አስተርእዮ ከጥምቀት በዓል (ጥር 11) አንስቶ አስከ ጾመ ነነዌ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ አስተርእዮ የተባለበት ምክንያትም የማይታየው የአምላክ አካልና ባሕርይ ከሚታየው የሰው አካልና ባሕርይ ጋር ተዋሕዶ የተገለጠበትና ማንነቱ በገሀድ (በዮርዳኖስ ባሕር) የታወቀበት፥ ምሥጢረ ሥላሴም የተገለጠበት ወቅት ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ዘመን የሚውሉ ማንኛውም በዓላት የአስተርእዮ በዓል ይባላሉ፤ ለምሳሌ ጥር 21 እመቤታችን በዓለ ዕረፍቷ ሆኖ ሳለ ‹‹የአስተርእዮ ማርያም›› ይባላል፡፡ #share #በዓለ_ጥምቀት_የጥምቀት_በዓል ፠ የጥምቀት በዓል በየዓመቱ ጥር 11 ዕለት ይውላል በዓሉ የሚጀምረውም ከጥር 10 ዕለት ጀምሮ ሲሆን፤ ኦሪት ለወንጌል አምሳል፣ መርገፍ እንደሆነች፤ በዘመነ ብሉይ የተሠሩ አጽዋማትና በዓላትም በዘመነ ሐዲስ ለተሠሩ አጽዋማትና በዓላተ አምሳል መርገፍ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያተ በብሉይ ይከበር በነበረው በበዓለ መጸለት(ዳስ በዓል) በዓለ ጥምቀት ገብቶበታል፡፡ ይኸውም እንደምን ነው ቢሉ በመጸለት ቀድሞ ካህናተ ኦሪት ለ7ት ቀናት ታቦት ይዘው ወንዝ ወርደው ድንኳን ተክለው ድባብ አጥልተው ጃንጥላ ጥለው ሕዝቡ እህል አከማችተው አባቶቻችን በኢያሱ መሪነት ውኃውን አቁሞ የዮርዳኖስን ወንዝ አሻገራቸው እያሉ ያስቡበት ነበር፤ በዘመነ ሐዲስ በጥምቀተ በዓልም ካህናተ ወንጌል ታቦት ይዘው፤ ወንዝ ወርደው /ውሃ ከትረው/ ድንኳን ተክለው ድባብ አጥልተው ጃንጥላ ጥለው ጌታችን ወደ ዮርዳኖስ ሄዶ በእደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ ተጠመቀ እያው ያስቡበታልና፡፡ /ዘሌ.23÷39-43፣ ኢያ. 3÷16/ #ለጥምቀት_በዓል_ምዕመናን_የምንይዘው_ዥንጉርጉር_በትር_ምሳሌው፣ ፠ ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳው ሸሽቶ በአጐቱ በላባ ቤት ብዙ ዓመታት ስላገለገለ ለአገልግሎቱ ዥንጉርጉር ሆነው የሚወለዱት በጐች ለያዕቆብ እንዲደረግና ምልክት የሌለባቸውን ለላባ እንዲሰጠው አዘዘው፡፡ ያዕቆብም በጐቹ ምልክት ያለባቸው ሆነው እንዲወለዱ ዥንጉርጉር እንጨት ውኃ በሚጠጡበት ውስጥ ጨምሮ በጐቹም እንደበትሩ ዥንጉርጉር እንደወለዱ እናያለን፡፡ /ዘፍ. 30÷31/ ይህ ምሳሌ ነው፡፡ ፠ በጐቹ የምዕመናን፤ ፠ ውኃው የጥምቀት፤ ፠ አውራዎቹ የመምህራን አንድም የቀሳውስት የሚጸነሱት በትሩን እንጂ አውራውን እንደማይመስሉ ምዕመናንም ሥላሴን ይመስላሉ እንጂ ያስተማራቸውን መምህራንን ቀሳውስትን አይመስሉምና፤ ፠ እንጨቱ ዥንጉርጉር መሆኑ ጌታችን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው /አምላክ ወሰብእ/ ለመሆኑ ምሳሌ፤ ፠ ያዕቆብ የጌታ ላባ የዲያብሎስ ምሳሌ ነው፡፡ ምልክት ያላቸው ለያዕቆብ ምልክት የሌላቸው ለላባ እንደሆኑ ሀብተ ወልድ፥ ሕይወተ ልቡና ያላቸው ለጌታ፤ ሀብተ ወልድና ሕይወተ ልቡና የሌላቸው ለዲያብሎስ የመሆናቸው ምሳሌ ነው፡፡ ምዕመናን ዥንጉርጉር በትር መያዛቸው ሰው የሆነ አምላክ /አምላከ ወሰብእ/ ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ በመሠረተልን ጥምቀት ተጠምቀን ሀብተ ወልድና ሕይወተ ልቡናን አግኝተን የሥላሴ ልጆች መሆናችንን ለማሳየት ነው፡፡ #ጥምቀት_መንከር፣ መድፈቅ፣መዝፈቅ፣ማጥመቅ፣ሲሆን በተገብሮ ደግሞ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጠመቅ፣ መላ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪም አጠማመቅ፣ ጠመቃ፣ የማጥመቅና የመጠመቅ ሥራ፣ኀጽበት በጥሩ ውሃ የሚፈፀም፣ የበዓል ስም፤ ጌታችን የተጠመቀበት ዕለት ማለትም ነው፡፡ በብሉይና በሐዲስ ኪዳን የተለያዩ የጥምቀት ዓይነቶች አሉ እነርሱም፡- #ጥምቀት_በብሉይ_ኪዳን_ (የአይሁድ ጥምቀ፣ የኤሲያንስ ጥምቀትና የዮሐንስ ጥምቀት ነበሩ) #ጥምቀት_በሐዲስ_ኪዳን፤ ፩. #የጌታችን_ጥምቀት፤ #የጥምቀት_መሥራች_ማነው_በምንስ_ተመሠረተ? የጥምቀት መስራቹ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን አመሠራረቱም በትምህርት /ዮሐ.351/፣ በተግባር /ማር.19፣ ማቴ.313/ እና በትዕዛዝ /ማቴ.2813/ ነው፡፡ #ጥንተ_ጥምቀት_ጌታችን_መቼ_ተጠመቀ? ዓለም በተፈጠረ በ5531 ዓመተ ዓለም(በ31 ዓመተ ምሕረት)፤ በዘመነ ሉቃስ፤ በዕለተ ማክሰኞ፤ ጥር 11 ዕለት፤ ሌሊት በ10 ሰዓት ነው፡፡ በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ፍት.ነገሥ.አን.19፣ ድስቅ.29፣ ተረፈ.ቄርሎስ፣ ሉቃ.323/ #ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ_? ሀ. ምሥጢረ ሥላሴን ለመግለጥ ለ. ሰው /አዳም/ በበደል ምክንያት ያጣውን ልጅነት ለመመለስ ሐ. የአዳምና የሔዋንን ዕዳ ደብዳቤ ለመደምሰስ ሠ. ትንቢተ ነቢያትን ለመፈፀም /መዝ.76$16/ ረ. በእርሱ ጥምቀት የእኛን ለመባረክ ሰ. የእግዚአብሔር ልጅ እንድንሆን /ገላ.3$26፣ገላ.4$4፣ሮሜ.8$14፣ዮሐ.1÷13፣1ኛ.ዮሐ.3÷1/ #ጌታችን_ለምን_በዮርዳኖስ_ተጠመቀ? *ትንቢቱን(/መዝ.113$1-8/)፣ *ምሳሌውን(ዮርዳኖስ ከላይ ነቅዑ /ምንጩ/ አንድ ነው ዝቅ ብሎ ለሁለት ‹‹ዮር›› እና ‹‹ዳኖስ›› ተብሎ ይከፈላል፣ ፣ዘፍ.14$14-20፣ መጽሐፈ ነገስት ካልእ 6$1 አንድምታ ና መጽ.ነገሥት ካልዕ 5$16 *ምሥጢሩን (በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የአዳምንና የልጆቹን ደብዳቤ ለመደምሰስ /ቆላ.2$14፣ ኤፌ.2$15፣ ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ቊ.1/፡፡) ለመፈጸም ነው፡፡ #share #ጌታችን_ለምን_በውኃ_ተጠመቀ?  ትንቢቱ፡- ሀ. ‹‹ጥሩ ውሃንም እረጫችኋለሁ እናንተም ከርኵሰታችሁ ትነፃላችሁ›› ጥሩ ውሃ የተባለ የጥምቀት ውሃ ነው፡፡ /ት.ሕዝ.36$25/ ለ. ‹‹አቤቱ ውኖች አዩህ ውኖች አይተው ፈሩ›› /መዝ.76$16/ ሐ. ድሆችና ምስኪኖች ውኃ ይሻሉ /ኢሳ.41$17/ መ. ‹‹ወይቤ ኩሎሙ እለ ጸምዑ ይሑር ኀበ ማይ፣ እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውኃ ሂዱ›› /ት.ኢሳ. 55$1/  ምሳሌው፡- ዘፍ.1$2፣ አክሲማሮስ ዘሐሙስ #ጌታችን_ለምን_ወደ_ዮሐንስ_ሄደ_ለምንስ_በዮሐንስ_እጅ_ተጠመቀ? 1. ትህትናን ለማስተማር፡ 2. ለአብነትና ሥርዐትን ሊደነግልልን፡- #ጌታችን_በማን_ስም_ተጠመቀ? ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ሌላውን ሰው በአንተ ስም፣ በባሕርይ አባትህ በአብ፣ በባሕርይ ሕይወትህ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለሁ አንተን ግን በማን ስም /ምን እያልኩ/ አጠምቅሃለሁ አለው›› ጌታችንም ‹‹ወልዱ ለብሩክ ከሳቴ ብርሃን ተሣሀለነ …፣ እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለን$ ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም፣ እነሆ የዓለምን ሀጢአት የምታስወግድ የእግዚአብሔር በግ /መስዋዕቱ/ እያልክ አጥምቀኝ›› አለው፡፡ /ዮሐ. 1÷30/ #የጥምቀት_ጥቅም_በጥምቀት_የሚገኝ_ጸጋ) ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ እንወለዳለን፡- ድህነትን እናገኛለን፡- የኃጢአት ሥርየትን እናገኛለን፡- #በጥር_11_በጥምቀት_በዓል_የምንረጨውና_የምንጠመቀው_ጥምቀት_ለቡራኬ_ነው፡፡ #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#የጥምቀት_በዓል_አከባበር_በአዲስ_አበባ_ከእንጦጦ_ጋራ_ጥግ_እስከ_ጃንሆይ_ሜዳ_ በአዲስ በአበባ ያሉ ገዳማትና አድባራትም በቦታ ርቀት እስከ ተለያዩበት ቀን ድረስ በእንጦጦ ጋራ ጥግ በአንድ ላይ በመፈናኘት ያድሩ ነበር፤ ኋላ ከቦታ ርቀት በኋላ የተቀሩት በጃንሆይ ሜዳ ማደር ጀምረዋል፡፡ እያደረም ሌሎች ገዳማትና አድባራት ሲመሠረቱ ከጃንሆይ ሜዳ በተጨማሪ ለአጥቢያቸው በሚቀርብ ቦታ ማደር ጀመሩ፡፡ #share ፠ በዓለ ጥምቀት በጃን ሜዳ (ጃንሆይ ሜዳ) መከበር የጀመረው ከ1887 ዓ.ም. አንስቶ መሆኑ ይነገራል፡፡ ስያሜውምና አጀማመሩም ጃንሜዳ የሚለው ጃን፥ ጃኖ ከሚለው ጋራ የተዛመደ ሲሆን ነገሥታት ለመሾም ለመሻር፣ ዳኝነት ለመስጠት፣ ሊቃውንትን ለመሾምና፣ ዐዋጅ ሲያስነግሩ በቤተ መንግሥታቸው አቅራቢያ በሚገኝ ሜዳ ላይ የጃኖ ድንኳን ተክለው ያስነግራሉ፤ ይህም ሜዳ ከጃኖ ጋራ እየተናበበ የቦታ መጠሪያ ሁኗል፡፡ ለምሳሌ፤ ‹‹ጃን ተከል›› በጎንደር ነገሥታት፤ ‹‹ጃን መራቂ›› በላስታ ነገሥታት፤ ‹‹ጃን ተራራ›› በአማራ ሳይንት በአፄ በዕደ ማርያም ‹‹ጃን ሜዳ›› በደብረ ታቦርና በአዲስ አበባ ናቸው፡፡ ፠ አዲስ አበባ መዲና በሆነችበት ሰዓት ‹‹መሐል ሰፋሪ‹‹ የሚባሉ የመኳንንት ጕባኤ በዚሁ በጃንሜዳ በስውር ዐድማ የሚያደርጉበት ሆነ አድማውን ሲያደርጉም በጃን ሜዳ ያለው የጃኖው ድነኳን ከሩቅ እንዳይታይ በማቅ ይሸፈን ነበር፡፡ እቴጌ ጣይቱ ይህን የመሰለ ሜዳ የክፉ ምክር መምከሪያ ሆኖ ከሚኖር ተባርኮ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቢሆን ብለው ለአፄ ምኒልክ ሃሳብ አቀረቡላቸው፤ አፄ ምኒሊክም ማለፊያ ብለው ሐሳባቸውን በመቀበል ጃን ሜዳ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ እንዲሆን አዘዙ፡፡ እንዲሁም የአፄ ምንሊክ አልጋ ወራሻቸው ልጅ ኢያሱ መሆኑን በግንቦት 10 ቀን 1901ዓ.ም. ዐዋጅ ያስነገሩበት፤ ‹‹ንሥረ ተፈሪ›› የተባለው የመጀመሪያው አውሮፕላንም በ12921ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ያረፈውም በዚሁ ሜዳ በመሆኑ ጭምር ስያሜው ጃንሆይ ሜዳ ተባለ፡፡ ፠ በ1887ዓ.ም. በዓለ ጥምቀትን ለመጀመሪያ ጊዜ በጃን ሜዳ በሕብረት ያከበሩት የመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን፣ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነበሩ፡፡ ፠ እስከ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ መን ድረስ ግን ታቦታቱ ወደ ቀበና ወንዝ (አፈ ንጉሥ ጥላሁን ሰፈር፤ ከፈረንሳይ ኤምባሲ በታች) ከከተራው አንስቶ አድረው በጥምቀት ዕለት ወደ ጃንሜዳ ይመለሱ ነበር፡፡ ሌሎችም በየሰበካቸው በሚገኝ አምች ቦታ ሲያከብሩ ቆይተው በ1939ዓ.ም. ከንሜዳ እጅግ በጣም ብዙ ያልራቁት (የካ ሚካኤልና ቅዱስ ዑራኤል) በንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደርጎ ወደ ጃናሜዳ እንዲመጡ ተደርጎ ነበር፤ ሆኖም ሕዝብ እየበዛ ስላስቸገረ በየአቅራቢያቸው እንዲያድሩ ተድርጓል፡፡ ፠ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኀይለ ሥላሴ በ1936 ዓ.ም በስፍራው የውኃ ቧንቧ እንዲዘረጋ፣ ባሕረ ጥምቀት ገንዳ በግንብ እንዲሰራ፣ የኤሌክትረክ መብራት በቦታው እንዲገባ አድርገዋል፡፡ ዙሪያውን በግንብ ተሰርቶ በቧንቧ የብረት ማገር ውብ ሆኖ እንዲታጠርና በዐፀድና በአበባዎች እንዲያጌጥ አድርገዋል፡፡ ይህ ቦታ ኋላ በ1994ዓ.ም. እድሳት ተደርጎለታል፡፡ ፠ እስከ ቅርብ ጊዜያትም ድረስ ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱ ታቦታት ከነድርባቸው ነበር፤ ለምሳሌ ቀቀጨኔ ደብረ ሰላም ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነበረ፤ ኋላ ግን ድርብ ታቦታት ቀርተው ዋናውን ይዘው የሚወርዱ ሆኗል፡፡ በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ውስጥ እስከ 2010ዓ.ም ድረስ ….. ባሕረ ጥምቀት (አብሕርተ አጥማቃት) አሉ፡፡ ፠ እስከ 1958ዓ.ም. በምስካየ ኅዙናን ተምሮ ማስተማር ማኅበርና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የታሪክ ድርሰትና ስብከት ክፍል አስተባባሪነት ከኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ሐዋርያዊ ድርጅት፣ ከሊቃውንትና ከመምህራን፣ ከሰዋስወ ብርሃንና ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተውጣጡ መምህራን በባሕረ ጥምቀቱ የስብከተ ወንጌልና፣ የመዝሙርና የድራማ መርሐ ግብር ያቀርቡ ነበር፡፡ በ1959ዓ.ም. አካባቢ ጥቂት ሰንበት ት/ቤቶች የደንብ ልብስና ነጠላ በማድረግ ታቦታቱን አጅበው አውጥውና አጅበው በመመለስ የበዓሉ ድምቀት እየሆኑ መጡ፡፡ በአሁኑ ወቅት በጃንሜዳ የሚያድሩ ታቦታት 12 ናቸው እነርሱም፤ 1ኛ. መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤ 2ኛ. ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም፤ 3ኛ. መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፤ 4ኛ. መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ.፤ 5ኛ. ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.፤ (የምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ታቦተ ወደ ጥምቀተ ባሕር ስለማይወጣ ሕዝቡና ሰ/ት/ቤቱ አብሮ ነው የሚያከብረው) 6ኛ. መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም 7ኛ. ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ.፤ 8ኛ. መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (አብሮም ቅዱስ ሚካኤል ይወርዳል)፤ 9ኛ. ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ.ክ.፤ 10ኛ. ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ.ክ.፤ 11ኛ. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ 12ኛ. ፈለገ ሰላም ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና አቡተ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ (ቀበና 18 ፓርክ አጠገብ)፡፡ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት / #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#የጥምቀት_በዓል_አከባበር_በአዲስ_አበባ_ከእንጦጦ_ጋራ_ጥግ_እስከ_ጃንሆይ_ሜዳ በአዲስ በአበባ ያሉ ገዳማትና አድባራትም በቦታ ርቀት እስከ ተለያዩበት ቀን ድረስ በእንጦጦ ጋራ ጥግ በአንድ ላይ በመፈናኘት ያድሩ ነበር፤ ኋላ ከቦታ ርቀት በኋላ የተቀሩት በጃንሆይ ሜዳ ማደር ጀምረዋል፡፡ እያደረም ሌሎች ገዳማትና አድባራት ሲመሠረቱ ከጃንሆይ ሜዳ በተጨማሪ ለአጥቢያቸው በሚቀርብ ቦታ ማደር ጀመሩ፡፡ በዓለ ጥምቀት በጃን ሜዳ (ጃንሆይ ሜዳ) መከበር የጀመረው ከ1887 ዓ.ም. አንስቶ መሆኑ ይነገራል፡፡ ስያሜውምና አጀማመሩም ጃንሜዳ የሚለው ጃን፥ ጃኖ ከሚለው ጋራ የተዛመደ ሲሆን ነገሥታት ለመሾም ለመሻር፣ ዳኝነት ለመስጠት፣ ሊቃውንትን ለመሾምና፣ ዐዋጅ ሲያስነግሩ በቤተ መንግሥታቸው አቅራቢያ በሚገኝ ሜዳ ላይ የጃኖ ድንኳን ተክለው ያስነግራሉ፤ ይህም ሜዳ ከጃኖ ጋራ እየተናበበ የቦታ መጠሪያ ሁኗል፡፡ ለምሳሌ፤ ‹‹ጃን ተከል›› በጎንደር ነገሥታት፤ ‹‹ጃን መራቂ›› በላስታ ነገሥታት፤ ‹‹ጃን ተራራ›› በአማራ ሳይንት በአፄ በዕደ ማርያም ‹‹ጃን ሜዳ›› በደብረ ታቦርና በአዲስ አበባ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ መዲና በሆነችበት ሰዓት ‹‹መሐል ሰፋሪ‹‹ የሚባሉ የመኳንንት ጕባኤ በዚሁ በጃንሜዳ በስውር ዐድማ የሚያደርጉበት ሆነ አድማውን ሲያደርጉም በጃን ሜዳ ያለው የጃኖው ድነኳን ከሩቅ እንዳይታይ በማቅ ይሸፈን ነበር፡፡ እቴጌ ጣይቱ ይህን የመሰለ ሜዳ የክፉ ምክር መምከሪያ ሆኖ ከሚኖር ተባርኮ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቢሆን ብለው ለአፄ ምኒልክ ሃሳብ አቀረቡላቸው፤ አፄ ምኒሊክም ማለፊያ ብለው ሐሳባቸውን በመቀበል ጃን ሜዳ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ እንዲሆን አዘዙ፡፡ እንዲሁም የአፄ ምንሊክ አልጋ ወራሻቸው ልጅ ኢያሱ መሆኑን በግንቦት 10 ቀን 1901ዓ.ም. ዐዋጅ ያስነገሩበት፤ ‹‹ንሥረ ተፈሪ›› የተባለው የመጀመሪያው አውሮፕላንም በ12921ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ያረፈውም በዚሁ ሜዳ በመሆኑ ጭምር ስያሜው ጃንሆይ ሜዳ ተባለ፡፡ በ1887ዓ.ም. በዓለ ጥምቀትን ለመጀመሪያ ጊዜ በጃን ሜዳ በሕብረት ያከበሩት የመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን፣ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነበሩ፡፡ እስከ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ መን ድረስ ግን ታቦታቱ ወደ ቀበና ወንዝ (አፈ ንጉሥ ጥላሁን ሰፈር፤ ከፈረንሳይ ኤምባሲ በታች) ከከተራው አንስቶ አድረው በጥምቀት ዕለት ወደ ጃንሜዳ ይመለሱ ነበር፡፡ ሌሎችም በየሰበካቸው በሚገኝ አምች ቦታ ሲያከብሩ ቆይተው በ1939ዓ.ም. ከንሜዳ እጅግ በጣም ብዙ ያልራቁት (የካ ሚካኤልና ቅዱስ ዑራኤል) በንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደርጎ ወደ ጃናሜዳ እንዲመጡ ተደርጎ ነበር፤ ሆኖም ሕዝብ እየበዛ ስላስቸገረ በየአቅራቢያቸው እንዲያድሩ ተድርጓል፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኀይለ ሥላሴ በ1936 ዓ.ም በስፍራው የውኃ ቧንቧ እንዲዘረጋ፣ ባሕረ ጥምቀት ገንዳ በግንብ እንዲሰራ፣ የኤሌክትረክ መብራት በቦታው እንዲገባ አድርገዋል፡፡ ዙሪያውን በግንብ ተሰርቶ በቧንቧ የብረት ማገር ውብ ሆኖ እንዲታጠርና በዐፀድና በአበባዎች እንዲያጌጥ አድርገዋል፡፡ ይህ ቦታ ኋላ በ1994ዓ.ም. እድሳት ተደርጎለታል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜያትም ድረስ ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱ ታቦታት ከነድርባቸው ነበር፤ ለምሳሌ ቀቀጨኔ ደብረ ሰላም ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነበረ፤ ኋላ ግን ድርብ ታቦታት ቀርተው ዋናውን ይዘው የሚወርዱ ሆኗል፡፡ በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ውስጥ እስከ 2010ዓ.ም ድረስ ….. ባሕረ ጥምቀት (አብሕርተ አጥማቃት) አሉ፡፡ እስከ 1958ዓ.ም. በምስካየ ኅዙናን ተምሮ ማስተማር ማኅበርና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የታሪክ ድርሰትና ስብከት ክፍል አስተባባሪነት ከኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ሐዋርያዊ ድርጅት፣ ከሊቃውንትና ከመምህራን፣ ከሰዋስወ ብርሃንና ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተውጣጡ መምህራን በባሕረ ጥምቀቱ የስብከተ ወንጌልና፣ የመዝሙርና የድራማ መርሐ ግብር ያቀርቡ ነበር፡፡ በ1959ዓ.ም. አካባቢ ጥቂት ሰንበት ት/ቤቶች የደንብ ልብስና ነጠላ በማድረግ ታቦታቱን አጅበው አውጥውና አጅበው በመመለስ የበዓሉ ድምቀት እየሆኑ መጡ፡፡ በአሁኑ ወቅት በጃንሜዳ የሚያድሩ ታቦታት 11 ናቸው እነርሱም፤ 1)#መካነ_ሥላሴ_ቅዱስ_በዓለ_ወልድ(አሁን #መንበረ_ጸባዖት_ቅድስት_ሥላሴ_የሚል ስም የተጨመረለት) 2)#መናገሻ_ገነተ_ጽጌ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ 3)#መንበረ_መንግሥት_ቅዱስ_ገብርኤል 4)#ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም 5)#ታዕካ_ነገሥት_በዓታ_ለማርያም 6)#ደብረ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስ 7)#መንበረ_ፓትርያርክ_ቅድስት_ማርያም 8)#አንቀጸ_ምሕረት_ቅዱስ_ሚካኤል 9)#ፈረንሳይ_አቦ 10)#መንበረ_ልዑል_ቅዱስ_ማርቆስ(ቅዱስ ሚካኤልም በድርብ አብሮ ይወጣል) 11)#ፈረንሳይ_ኢየሱስ፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ጥምቀት_በኢትዮጵያ፤ #share #like ፠ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠመቀው የንግሥት ሕንደኬ በጅሮንድ አቤላክ(ባኮስ) ‹‹እነሆ ውኃ አለ፣ ታድያ መጠመቅን ማን ይከለክለኛል?›› /የሐዋ. ፷፥፳፱-፴፮/ ብሎ በሐዋርያው ፊልጶስ በተጠመቀ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ሥርዐት ግን ተስፋፍቶ የቀጠለው በነገሥታቱ በአብርሃ ወአጽብሐ (315-351ዓ.ም.) የቤተ መንግሥቱ ጃንደረባ በነበረውና ኋላ ጳጳስ በሆነው በፍሬምናጦስ(አባ ሰላማ) ዘመን ነው፡፡ በዓሉ ግን አሁን በምናከብረው ዓይነት ስዕላዊ በሆነ መልኩ መከበር የጀመረው ከማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድ ዜማ መስፋፋት ጋራ በአፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (530-544ዓ.ም.) እንደሆነ ይነገራል፡፡ ፠ ገዳማቱና አድባራቱም በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የውኃ ምንጮች በተናጥል በመውረድ በዓለ ጥምቀትን ያከብሩ ነበር፡፡ ተቀራርበው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታቸውን በአንድ ቦታ እንዲያሳድሩ ዐዋጅ የታወጀው፥ ትእዛዝ የተላለፈው በጻድቁና በጠቢቡ ንጉሥ ላልይብላ(1140-1180ዓ.ም.) ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ በዚሁ ዘመን የነበሩት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአኵሱም በመቀለና በመርጡለ ማርያም ያሉ ጥምቀተ ባሕሮችን ባርከዋል፤ በአፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን ደግሞ በአቡነ ተክለሃይማኖት አሳሳቢነት ሥርዐተ ጥምቀቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዐዋጅ ታውጇል፡፡ እስከ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ድረስም ታቦታቱ ዕለቱን ጠዋት ወጥተው ማታ መለሱ ነበር፤ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግን ታቦታቱ በዋዜማው ጥር 10 ከሰዐት በኋላ ወደ ትምቀተ ባሕር ወርደው እንዲያድሩ፤ አገሩንም በኪደተ እግር እንዲባርኩ፤ በሄዱበት መንገድም እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ቀጥሎም አፄ ናዖድ ሕዝቡ ታቦታቱን አጅቦ ወደ ጥምቀተ ባሕር እንዲሄድ በዐዋጅ አስነገሩ፡፡ ይህ ሥርዐትም እስካሁን ከኛ ዘንድ ደርሷል፡፡ በዘመናት ውስጥም የጥምቀት በዓል ሲከበርባቸው ከነበሩ ቦታዎች ዐበይቶቹን ለመጥቀስ ያህል፤ #በአኵሱም_የንግሥተ_ሳባ_መዋኛ_ ‹‹#ማይ_ሹም›› #በጎንደር_የአፄ_ፋሲል_መዋኛ_ገንዳ #በቅዱስ_ላሊበላ_የዮርዳኖስ_ወንዝ #በሸዋ_የአፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ_ፍርድ_መስጫ_አደባባይ #44ት #ታቦታት_የሚያድሩበት_የሸንኮራ_ሜዳ ‹‹#ኢራንቡቴ_ጥምቀተ_ባሕር›› #በአዲስ_አበባ_የጃንሆይ_ሜዳ_ (ጃንሜዳ) #በአዲስ_አበባ_የእንጦጦ_ማርያምና_ቅዱስ_ራጕኤል_ታቦት_ማደሪያ #ኀሙስ_ገበያ_ሜዳ ዐበይቶቹ ናቸው፡፡ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

ወይሴብሑ ለስሙ በትፍሥሕት፡፡ (#ስሙን_በደስታ_ያመሰግናሉ_፡፡) መዝሙረ ዳዊት ፻፵፱፥፫ (ለታቦታቱ ምንጣፍ በማንጠፍና መንገዶቹን በመጥረግ የሚያገለግሉ ወንድሞችና እኅቶች) እንዲሁም
+5
ወይሴብሑ ለስሙ በትፍሥሕት፡፡ (#ስሙን_በደስታ_ያመሰግናሉ_፡፡) መዝሙረ ዳዊት ፻፵፱፥፫ (ለታቦታቱ ምንጣፍ በማንጠፍና መንገዶቹን በመጥረግ የሚያገለግሉ ወንድሞችና እኅቶች) እንዲሁም

የተለያዩ አድባራት ሰንበት ትምህርት ቤት በዝማሬ ላይ፡፡ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በመዝሙር፡፡ #እግዚአብሔርን_በመዝሙር_አመስግኑት፡፡ መዝሙረ ዳዊት ፻፶ ይከተሉን Facebook https://www.fac
+6
የተለያዩ አድባራት ሰንበት ትምህርት ቤት በዝማሬ ላይ፡፡ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በመዝሙር፡፡ #እግዚአብሔርን_በመዝሙር_አመስግኑት፡፡ መዝሙረ ዳዊት ፻፶ ይከተሉን Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

ወይሴብሑ ለስሙ በትፍሥሕት፡፡ (#ስሙን_በደስታ_ያመሰግናሉ_፡፡) መዝሙረ ዳዊት ፻፵፱፥፫ (ለታቦታቱ ምንጣፍ በማንጠፍና መንገዶቹን በመጥረግ የሚያገለግሉ ወንድሞችና እኅቶች) እንዲሁም የተለያዩ አድባራት ሰንበት ትምህርት ቤት በዝማሬ ላይ፡፡ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በመዝሙር፡፡ #እግዚአብሔርን_በመዝሙር_አመስግኑት፡፡ መዝሙረ ዳዊት ፻፶ ይከተሉን Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

፠ በዓለ ጥምቀት ሰንበት (ቅዳሜና እሑድ ላይ) ካልዋለ የሚታረሰው መሬት ረድኤት በረከት ስለሚገኝበት ገበሬው አንድ ሁለት ፈር ያርሳል፡፡ ፠ በዓለ ጥምቀት ዐቢይ በዓል ስለሆነ የጥሉላት (የፍስክ) ምግብም ጭምር ስለምንመገብበት ዘንድሮ ማክሰኞ ስለሚውል ዋይዜማውን ሰኞ የጋድ ጾም (ከጥሉላት መባልዕት) እንጾማለን፡፡ የሚቈርብ ሰው ግን አክፍሎ ያድራል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ከተራና_ባሕረ_ጥምቀት_ጥምቀተ_ባሕር #ታቦታት_ለምን_ከመንበራቸው_ወጥተው_ያድራሉ? #በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት #ሥርዐተ_ከተራ ……. (#ያንብቡ) #ከተራ_፤ ከተረ (ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡ #ከተራ_ለምን_ተባለ? በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ #ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ #አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ #አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ ፠ውኃ የሚከተርበት ቦታ ‹‹#ባሕረ_ጥምቀት(#ጥምቀተ_ባሕር_››) (#የታቦት_ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡ #ሥርዐተ_ከተራ ፠ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡ ፠ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤ *ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡ *የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን፤ *መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡ *እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ *ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡ *የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ *ሕዝቡም ደግሞ ‹‹#ለጥምቀት_ያልሆነ_ቀሚስ_ይበጣጠስ›› እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ የጀብዱነት ሽልማት ያለው በሽልማቱ አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡ **ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡ ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ #ተረኛ_ደብር (#የምራት_ባለተረኛ) “#ወረደ_ወልድ_እምሰማያት_ውስተ_ምጥምቃት_፤ #በፍሥሓ_ወበሰላም” (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው #ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹#አንሺዎች_›› ይባላሉ፡፡ የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት(ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ)፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ 7-9 ሰዐት ነው፡፡ በዚያን ዕለት ምሽት ፈቃደኛ የሆኑ ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ ባልቴቶችና ኮረዳዎች ሕፃናትም ጭምር እዚያው በጥምቀተ ባሕሩ ዙሪያ ስለሚያድሩ እንደ የዕድሜ ደረጃቸው ማለትም በልጅነት ዕድሜ ላይ ያሉት በሀገር ባህል ዜማ ሲያመሰግኑ ፥ እናቶችም ታቦቱን የሚያሞግስ ግጥም እየገጠሙ ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ በከተሞች ደግሞ ስበከተ ወንጌልና መዝሙር ሲዘመር ያድራል፡፡ #በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት_አላቸው_እነዚሁም_፤ #ታቦቱ_የጌታችን ምሳሌ #ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ምሳሌ #ባሕረ_ጥምቀቱ_የዮርዳኖስ_ወንዝ_ምሳሌ #ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን_ወደ_ቅዱስ_ዮሐንስ_እየመጡ_የንስሐ_ጥምቀት_ሲጠመቁ_የነበሩ_ሰዎች_ምሳሌ #ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው_መድኀኔ_ዓለም_ክርስቶስ_በእደ_ዮሐንስ_በፈለገ_ዮርዳኖስ_ለመጠመቅ_ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ_ከማታው_ጀምሮ_መውረዱንና_ተራውን_ሲጠብቅ_አድሮ_መጠመቁን_ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡›› /ማቴ፡ 3፥13/ #ጥምቀቱ_የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡፡

የቀደሙ የጥምቀት በዓል አገልግሎቶች እና ካሕናት ፤ ከፍቶ ማሕደራችን
+8
የቀደሙ የጥምቀት በዓል አገልግሎቶች እና ካሕናት ፤ ከፍቶ ማሕደራችን

የቀደሙ የጥምቀት አገልግሎቶች እና ጥምቀት 2012 ዓ.ም፤ የአጫብር አገልግሎት በ ፍኖተ ሕይወት እና በፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት አገልጋዮች ፤ ከፍቶ ማሕደራችን
+9
የቀደሙ የጥምቀት አገልግሎቶች እና ጥምቀት 2012 ዓ.ም፤ የአጫብር አገልግሎት በ ፍኖተ ሕይወት እና በፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት አገልጋዮች ፤ ከፍቶ ማሕደራችን

፠ ፠ ፠ #አቃቂ_ቃሊቲ_ክፍለ_ከተማ_ (9ኝ ጥምቀተ ባሕር) #፵፰ኛ) #ወረዳ_1 #አቃቂ_በሰቃ_ወንዝ 1ኛ. ቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3ኛ. ጃቲ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት 4ኛ. ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም 5ኛ. አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኀኔ ዓለም 6ኛ. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል 7ኛ. ፈንታ ደ/ጽ/ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት አርሴማ 8ኛ. ቀርሣ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ልደታ ለማርያም #፵፱ኛ) #ወረዳ_5 #ከቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ 1ኛ. ቃሊቲ ደብረ ቊስቋም ማርያምና ቅዱስ ሚካኤል #፶ኛ) #ወረዳ_4 #ሰርቲ_መድኀኔ_ዓለም_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ 1ኛ. ሰርቲ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም #፶፩ኛ) #ወረዳ_9 #ገብረ_መንፈስ ቅዱስ_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ 1ኛ. ኮዬ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #፶፪ኛ) #ቃሊቲ_አካባቢ 1ኛ. ሠፈረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል #፶፫ኛ) #ወረዳ_9 #ሥላሴ_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ 1ኛ. ቂሊንጦ ቅድስት ሥላሴ #፶፬ኛ) #ወረዳ_10 #ገላን_ጉራራ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ 1ኛ. ገላን ጉራራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል #፶፭ኛ) #ወረዳ_11 #ገላን_ኢዶሮ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ 1ኛ. ገላን ኢዶሮ ቅዱስ ገብርኤል #፶፮ኛ) #መጠሊ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ 1ኛ. መጠሊ ደ/አ/ቅዱስ ገብርኤል ፠ ፠ ፠ #ቦሌ_ክፍለ_ከተማ_ (19ኝ ጥምቀተ ባሕር) #፶፯ኛ) #ጉምሩክ_ወረዳ_3 1ኛ. ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኀኔ ዓለም ወመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ #፶፰ኛ) #ወረዳ_23 #አየር_መንገድ 1ኛ. ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ክርስቶስ ሰምራ #፶፱ኛ) #ወረዳ_06 #መገናኛ 1ኛ. መገናኛ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ #፷ኛ) #ወረዳ_02 #ሩዋንዳ_አካባቢ 1ኛ. ቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል 2ኛ. ቦሌ አየር ማረፊያ መንበረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ #፷፩ኛ) #ወረዳ_13 #አድዋ_ፓርክ 1ኛ. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም 2ኛ. ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ 3ኛ. ኤ(የ)ረር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑርኤል #፷፪ኛ) #ወረዳ_9 #ሰሚት_አደባባይ 1ኛ. ቦሌ ሰሚት መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም 2ኛ. ቦሌ ሰሚት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3ኛ. ቦሌ ሰሚት ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት 4ኛ. በሻሌ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም #፷፫ኛ) #ወረዳ_12 #ቡልቡላ 1ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም 2ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ወቅዱ አማኑኤል 3ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም #፷፬ኛ) #ወረዳ_9 #ጎሮ_ሰፈር_ባሕረ_ጥምቀት 1ኛ. ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብኤል 2ኛ. ኤረር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ 3ኛ. ኤረር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል #፷፭ኛ) #ወረዳ_13 #አያት_አደባባይ_ #4_ኪሎ_ሰፈር 1ኛ. አያት መ/ሕ/መድኀኔ ዓለም #፷፮ኛ) #ወረዳ_13 #መሪ_አያት 1ኛ. መሪ ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 2ኛ. አያት ጌቴ ሴማኒ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት 3ኛ. መሪ ቅዱስ ፋኑኤል 4ኛ. መሪ ቅድስት ሥላሴ #፷፯ኛ) #በሻሌ 1ኛ. ቦሌ በሻሌ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ እስጢፋኖስ 2ኛ. የቃጥላ ደብረ ፀሐይ ቅድሰት ማርያም #፷፰ኛ) #ወቄ_አካባቢ 1ኛ. ወረገኑ ቅዱስ ሚካኤል #፷፱ኛ) #አያት_ጨፌ 1ኛ. አያት ጨፌ ደብረ ኢያሪኮ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ #፸ኛ) #ወረዳ_11 #ለሚ_ኮንዶሚኒየም 1ኛ. ቦሌ ሰሚት ቅዱስ ሩፋኤልና ኤዎስጣቴዎስ #፸፩ኛ) #ወረዳ_11 #አራብሳ 1ኛ. አራብሳ ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. ዋሻው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #፸፪ኛ) #ለሚ 1ኛ. ቦሌ ለሚ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2ኛ. ቦሌ ለሚ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #፸፫ኛ) #አያት_ኮንዶሚኒየም 1ኛ. አያት ጨፌ ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. አያት ፈለገ ሕይወት ቅዱስ ዮሐንስ #፸፬ኛ) #ቦሌ_ቡኒ 1ኛ. ቦሌ ቡኒ ደብረ ቤቴል ቅዱስ እግዚአብሔር አብ #፸፮ኛ) #ሪፈንቲ 1ኛ. ሪፈንቲ ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. ቦሌ ሰሚት መካነ ሕያዋን ዋሻው ቅዱስ ገብርኤል /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት / #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

፠ ፠ ፠ #ኮልፌ_ቀራንዮ_ክፍለ_ከተማ_(9ኝ ጥምቀተ ባሕር) #፳፮ኛ) #መድኀኔ_ዓለም_ከፍተኛ_መሠናዶ_ትምህርት_ቤት_(ራስ ኀይሉ ሜዳ) 1ኛ. መርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል 2ኛ. ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል 3ኛ. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል 4ኛ. ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ 5ኛ. ጠሮ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ #፳፯ኛ) #ሳንሱሲ_መናፈሻ_አጠገብ 1ኛ. አስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. አስኮ ደብረ መንክራት ቅዱስ ጊዮርጊስ 3ኛ. መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4ኛ. ፍኖተ ሎዛ ብርጭቆ ማርያም #፳፰ኛ) #ወረዳ_15_(አርሴማ ጠበል /አወልያ ትምህርት ቤት ጋር/) 1ኛ. ቃሎ ተራራ አቡነ ሀብተ ማርያም #፳፱ኛ) #ገዳመ_ኢየሱስ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅጽር_ግቢ_ውስጥ 1ኛ. ደብረ ቀራንዮ መድኀኔ ዓለም 2ኛ. ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ 3ኛ. ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ 4ኛ. ወይብላ ደብረ ጽዮን ማርያም 5ኛ. ፊሊዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 6ኛ. መርካቶ ደብረ ገሊላ አማኑኤል 7ኛ. ገዳመ ኢየሱስ #፴ኛ) #ወረዳ_5_ #ጻድቃኔ_አካባቢ_ታቦት_ማደርያ 1ኛ. ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ 2ኛ. ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3ኛ. አውግስታ ደብረ ጽዮን ማርያም 4ኛ. ጻድቃኔ ማርያም 5ኛ. ፈለገ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት 6ኛ. ወይራ ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማና ዕጨጌ ዮሐንስ #፴፩ኛ) #ወረዳ_4_ #አየር_ጤና_ኪዳነ_ምሕረት_ቤተ_ክርስቲያን_አጠገብ 1ኛ. አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት 2ኛ. ጀሞ ፈለገ ኮሬብ ቅድስት ሥላሴና ቅድስት ማርያም 3ኛ. ዓለም ባንክ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል #፴፪ኛ) #ወረዳ_1_ #በቴል_አጠገብ_(ኳስ ሜዳ) 1ኛ. ቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል 2ኛ. አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑር(ራ)ኤል #፴፫ኛ) #በላፍቶ_ክፍለ_ከተማ_ወረዳ_4 #ገብርኤል_ጠበል 1ኛ. ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ #፴፬ኛ) #ወረዳ_2_ #ሮል_ሳሙና_ፋብሪካ_ፊት_ለፊት 1ኛ. ረጲ ደብረ ጎልጎታ መድኀኔ ዓለም 2ኛ. ካራ ቆሬ ቅዱስ ሩፋኤል 3ኛ. ደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል 4ኛ. ግራር ደ/አ/ቅድስት አርሴማ 5ኛ. ወይብላ ደብረ ጽዮን ማርያም ፠ ፠ ፠ #ነፋስ_ስልክ_ላፍቶ_ክፍለ_ከተማ_ (13ት ጥምቀተ ባሕር) #፴፭ኛ) #ደብረ_ኢያሪኮ_መድኀኔ_ዓለም_ቤተ_ክርስቲያን_አጠገብ 1ኛ. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል 2ኛ. ፉሪ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ማርያም 3ኛ. ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለም 4ኛ. ደብረ ወርቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት 5ኛ. ፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ 6ኛ. ፉሪ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል #፴፮ኛ) #ጎፋ_ሠፈር 1ኛ. ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. ቤዛ ብዙኃን ኪዳነ ምሕረት 3ኛ. ቄራ መብራት ኀይል ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስና ዮሐንስ መጥምቅ #፴፯ኛ) #ጀሞ_መድኀኔ_ዓለም 1ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል #፴፰ኛ) #ቻይና_ካምፕ 1ኛ. ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት ማርያም #፴፱ኛ) #ጀሞ_ቊጥር_3_አደባባይ 1ኛ. ጀሞ ቊጥር 3 ቅዱስ ገብርኤል #፵ኛ) #ቶታል_አደባባይ 1ኛ. ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. መካኒሳ ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #፵፩ኛ) #መካኒሳ_ኮንዶሚንየም 1ኛ. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል #፵፪ኛ) #ዮሴፍ_አካባቢ 1ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 2ኛ. ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ 3ኛ. ብሔረ ጽጌ ቅድስት ማርያም 4ኛ. አዲስ አምባ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት 5ኛ. ሐመረ ወርቅ ቅድስት ማርያም #፵፫ኛ) #ብሥራተ_ወንጌል 1ኛ. ደብረ ቢ/ያ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #፵፬ኛ) #ደብረ_ዕንቊ_ቅዱስ_ገብርኤል 1ኛ. ደብረ ዕንቊ ቅዱስ ገብርኤል #፵፭ኛ) #ፉሪ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም 1ኛ. ፉሪ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም #፵፮ኛ) #ፉሪ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ዑር(ራ)ኤል 1ኛ. ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል #፵፯ኛ) #ቡልቡላ_ ኤምባሲ_አጠገብ 1ኛ. ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል 2ኛ. ለቡ በዓለ ወልድ