uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 16 041 підписників, посідаючи 5 277 місце в категорії Релігія і духовність та 2 237 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 16 041 підписників.

За останніми даними від 25 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 503, а за останні 24 години на 9, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 24.94%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 9.77% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 4 001 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 567 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 29.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 26 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

16 041
Підписники
+924 години
+987 днів
+50330 днів
Архів дописів
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ገብረ ሕይወት፡፡ እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓለ_ዕረፍት_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ ላሊበላ፥ ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/  ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ተመልሰው ወደ ምድረ ከብድ በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፤ በግብፅ 300ዓመታት፥ በኢትዮጵያ ምድር ላይ 262ዓመታት (በዋነኛነት በምድረ ከብድና በዝቋላ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን ገዘዛ አቦን መጥቀስ ይቻላል) ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባትም ምድረ ከብድ ገዳም ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከባድ/ ትብለሽ ተጠሪ አላት የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ (ሥርዐተ ማኅሌቱን የኢንተርኔት አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች አድርሱልን፤ በተለይም ወደ ምድረ ከብድ፥ ዝቋላና ሌሎች የአባታችን ክብረ በዓል በሚከበርባቸው አድባራትና ገዳማት ያላችሁ አድርሱልን፡፡) /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

ከሰኞ እስከ ዐርብ (ከየካቲት 30 -መጋቢት 4) ማታ ማታ ከ12-1 ሰዐት ስለ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት በሰ/ት/ቤታችነ ን ይካሄዳል። ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ማኅበረ_ሥላሴ_፤ ታላቁ ገዳም፡፡ #ታቦቱ_ሥላሴ፥ #ጻድቁ_ዐምደ_ሥላሴ፥ #የገዳሙ_ስም_ማኅበረ_ሥላሴ፡፡ #በየቀኑ_በሁሉም_ቤክ_በቅዳሴ_ላይ_ስሙ_የሚነሳው_ገናናው_ገዳም (ነገረ ግን ብዙዎች የማያውቁት)፡፡ #የበርካታ_ትምህቶችና_የጥበብ_ማዕክል፤ ፠ ጌታችን ሲወለድ በዕለቱ በሃገራችን ኢትዮጵያ በቶራ አማካይነት ለአንድ ባሕታዊ የተገለጠበት፤ ፠ የበረሃው ውዕየትና ግለት እጅግ የሚያይልበት፤ ፠ አቡነ ዐምደ ሥላሴና ሌሎችም ቅዱሳን (እነ አቡነ ክፍለ ማርያም፥ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘቋራ፥ ፯ቱ ዘሥላሴ በመባል ለሚጠሩ ቅዱሳን፣ አርከ ሥሉስ /የአርኬና የመልክአ ቊርባን ደራሲ/፥ …) የተጋደሉበት፤ ፠ የበቁ ባሕታውያንና ግሑሳን የሚኖሩበት፤ ፠ እንኳን ሰዉ ከብቱ ሥርዐት የሚጠብቅበት፤ (ከብቶቹ ‹‹አጎዶ (ወገን ወገን) ሲባከሉ በጾታ ተለይተው ወዳ ማደሪያቸው የሚሄዱበት) ፠ ብዙ ከብቶች ገዳሙ እያለው ሥጋ ግን የማይበላበት፤ ፠ የላመ የጣመ፥ የጣፈጠ፥ የተዋበ … የማይበላበት፤ ፠ ከዓመት እስከ ዓመት አንድ ዓይነት ምግብ (መኰሪታ) የሚበላበት፤ ፠ ታላላቅ ነገሥታት የገሠገሱበት፤ (*አብርሃ ወአጽብሃ ዳሩ እሳት መሐሉ ገነት ይሁን ብለው የገደሙት፤ *አፄ ቴዎድሮስ የተማሩበት ያደጉበትና ኋላም የተቀበሩበት፤ *አፄ ዮሐንስ ለሃገራቸው ሲሉ መተማ ሄደው ከማረፋቸው በፊት መጥተው የተሣለሙት፤ *ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ብዙ ንዋያት የሰጡት፤ ፠ የበቁ አባቶች የሚኖሩበት፤ (ከብቃታቸው የተነሣ ጣሊያን የገዳሙን የውኃ ገንዳ በአውሮፕላን በቦንብ ብታጋየውም ወዲያው አውሮፕላኗን በጸሎት እዚያው በረሃ ላይ በጸሎት ዶግ አመድ አድርገው ወደ የከሰከሱበት) ፠ የምዕራብ ጎንደርን መልክአ ምድር በማየት አእምሮውን የሚያድሱበት፤ ፠ ………. ፣ ……. ፣ ……. ፨ ፠ በየቀኑም በቅዳሴያችን ቁርባን ሊቆረብ ሲል ይህን ታላቅ ገዳም እንዲህ እያልን እናነሳዋለን፥ እናወድሰዋልን፤ ‹‹ሰላም ለክሙ ጻድቃነ ዛቲ ዕለት ኵልክሙ፤ ዕድ ወአንስት በበአስማቲክሙ፡፡ ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር #ማኅበረ_ሥላሴ አንትሙ፤ ዝክሩነ በጸሎትክሙ በእንተ ማርያም እሙ፤ ተማኅጸነ ለክርስቶስ ሥጋሁ ወደሙ፡፡ ፠ በየካቲት 27ም ጽድቃቸውና ቃልኪዳናቸው እንደ ምድር አሸዋ የበዛው፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት ለመቊጠር የሚያስቸግረው ጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ ልደታቸውም እረፍታቸውም ነው፡፡ ፠ በየካቲት 27ና በሥላሴ ክብረ በዓል ላይ ካልሆነ በቀር ወደ ማኅበረ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት ከግዝት በር ላይ 7ት ቀናት መጠበቅ ይኖርብናል፤  ብፁዕ አባ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ንብረቱ ገዳም ውስተ ሀቌሁ ቅንአቱ ዘአዲም፤ ያስተጋብእ ጽድቀ ዘእምኵሎሙ ቅዱሳን በጾም ወበጸሎት፤ ሀለወ በክብር ወበሰላም፡፡ /መሐረነ አብ/ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/

ዘምኵራብ፡፡ (መዝሙር፤ ምስባክ፣ ምንባባት፣ ወንጌል) መዝሙር ዘምኲራብ፤ቦአ ኢየሱስ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ ቦአ ኢየሱስ ምኲራበ አይሁድ ወመሀረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት፤ አነ ውእቱ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚአ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው፤ ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምሥያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ፤ ቦአ ምኲራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ፤ አንከሩ ምሕሮቶ ሞገሰ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ። ትርጕም፤ ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖትን ቃል አስተማረ፡፡ ከመሥዋዕት ምጽዋትን እወዳለሁ አላቸው፡፡ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባትዋ እኔ ነኝ አላቸው፡፡ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ፤ ቤቴ የጸሎት ቤት ነው (ይባላል)፡፡ ምኵራብ ገብቶ ተቆጣቸው፤ ዝም ይሉ ዘንድ ትምህርቱን የቃሉን መሰማት (ሞገስ) የነገሩን መወደድ የአፉን ለዛ አደነቁ፡፡ ምንባባት ቈላስይስ ፪፥፲፮-ፍጻሜው ያዕ. ፪፥፲፬-ፍጻሜው የሐዋ. ፲፥፩-፱ ꕥꕥꕥ ፨፨፨ ꕥꕥꕥ ምስባክ፤ መዝ. ፷፰፥፱ እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዓኒ፤ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትኤየሩከ ወድቀ ላዕሌየ፤ ወቀጻእክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡ (ትርጕም፤ የቤትህ ቅናት በልቶኛል፤ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ላይ ወደቀ፤ ነፍሴን በጾም ቀጣኋት፡፡) ꕥꕥꕥ ፨፨፨ ꕥꕥꕥ ወንጌል፤ ዮሐ.፪፥፲፪-ፍጻሜው ꕥꕥꕥ ፨፨፨ ꕥꕥꕥ ቅዳሴ፤ ቅዳሴ እግዚእ (ነአኵተከ) ꕥꕥꕥ ፨፨፨ ꕥꕥꕥ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

ምኵራብ፤ ሦስተኛው ሳምንት ሦስተኛ ሳምንት ምኵራብ ይባላል፡፡ ጌታ በምኵራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት ሳምንት ሲሆን ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምኵራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ በብሉይ ዘመን ቢያንስ ዐስር የጎለመሱ ወንዶች (የቤተሰብ ኃላፊዎች) በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመስራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ዋናው ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ብቻ ነበር፡፡ በምኵራብ ውስጥም የኦሪት የሕግ መጻሕፍትና በቅዱሳን ነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር፡፡ በኦሪቱ ምኵራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ፤ በመግረፍ ወይም ከምኵራብ በማስወጣት ሊቀጡ ስልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡ በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፤ በአምልኮታቸው ውስጥም ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡ በዚህ በምኩራብ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፤ ሕሙማንን ፋውሷል፡፡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ምዕራፍ ፷፩ን አንብቧል፡፡ በዚህ በዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ምኵራብ) የሚታሰበውም ይህ ነው፡፡ ፨ ‹‹ወደ አደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሳ፡፡›› ሉቃ. 4፥16 ፨ ‹‹ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር፡፡›› ማቴ. 13፥52 ፨ ‹‹ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፡፡››ማር 6፥1 ፨ በዕለቱ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡ ምንባባትም፤ ጌታችን ቤተ መቅደሱን የንግድ ማዕከል ያደረጉትን ዓይቶና አዝኖ ነጋዴዎቹን ከነመንጋቸው በጅራፍ እንዳስወጣቸውና ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን እኔ እሠራዋለሁ፡፡›› ብሎ ስለመ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ማስተማሩን የሚገልጽ ነው፡፡ ፨፨፨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፨፨፨ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

*ለታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ የብር ጸናጽል፣ መቋሚያና መስቀል አበርክተዋል፤ እነዚህም ንዋያተ ቅድሳት በገዳሙ ቤተ መዘክር (Museum) ተቀምጠው በዕይታ ላይ ይገኛሉ፡፡ *ላደጉባት ለጋን ማርያም የተለያዩ ንዋየተ ቅድሳትን አበርክተዋል፤ እንዲሁም በአቅራቢያው ለሚገኘው የሰገን ሚካኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን አሠርተዋል፡፡ አሁን እንኳን በቅርቡ በየካቲት ወር እንኳን መጎናጸፊያ፣ ሞጣሕት፣ ሽቱ፣ ከነሻንጣው ጭምር በስጦታ አበርክተዋል፡፡ *ለታላቁና ባለ 13ት ቤተ መቅደሱ ሞላሌ ዳግማዊ ቤተልሔም አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ገዳም የብራና ግብረ ሕማማትና የተለያዩ ንዋያተ ቅድሳት አብርክተዋል፡፡ *ለእንሳሮ የትኖራ ቅዱስ ሚካኤል የተለያዩ ንዋየተ ቅድሳት አበርክተዋል፡፡ አባታችን አባ ቆሞስ ተክለ ወልድ በዚህች ምድር ላይ ከልጅነት እስከ ዕርግና በቤተ ክርስቲያን አድገውና ኖረው፤ ተምረውና አገልግለው ያለደዌ ፥ ያለሕማም እኁድ የካቲት 22/2012 ዓ.ም. ጠዋት ቁርሳቸውን ዳቦ በሰሊጥና በማር አድርገው ተመግበው እንዳበቁ በተወለዱ በ83 ዓመታቸው በሰላም የቅዱሳንን ዓይነት ዕረፍት አረፉ፡፡ ሥርዐተ ግብዐተ መሬታቸው ደግሞ ከፍትሐት ጭምር በታላቁ ገዳም ዕፁብ በሚያሰኝ ሁኔታ በደብረ ደብረ ሊባኖስ የካቲት 23/2012 ዓ.ም. ተፈጽሟል፡፡ የቃል አስረጂዎች፤ *ቀሲስ ተስፋዬ፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም አገልጋይና የቆሞስ አባ ተክለ ወልድ የንስሐ አባት፡፡ *የአባ ተክለ ወልድ የእኅት ልጆች *ወ/ሮ ዐሥራት (ፍሬሕይወት) ተክለ አረጋዊ፤ ኄኖክ ጌታቸው፤ ቄስ……. አብረው በአንድ ግቢ የሚኖሩ፡፡ *ዲያቆን ዮናስ፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም አገልጋይና ከቆሞስ አባ ተክለ ወልድ አንዳንድ ጥያቄዎችን የጠየቀ፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል_፡፡›› ሲራክ 38፥26 (እያለቀስን ጻፍንላችሁ) ደብራችንን ለ26 ዓመታት በነጻ በክህነት ያገለገሉን አባት #ቆሞስ_አባ_ተክለ_ወልድና በተለያዩ የማስተባበር አገልግሎቶች የሚያገለግለው ወንድማችንን #አቡዬን (#ዮሴፍ_አለምሸትን) በአንድ ቀን አጣች፡፡ የ2ቱንም አጭር ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ #የቆሞስ_አባ_ተክለ_ወልድ_መኮንን_ታሪክ፤ ፠ ‹‹ግርማት ኃይላ›› ብለው የሚጠሯት የእመቤታችን ስዕል ዘንድሮን እንዳማላፍ ነግራኛለች ብለው ተናግረው ያረፉ፤ ፠ በታላቁ ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም 3ት ስውራን አባቶች መኖራቸውን የተናሩና ደብሩን ለ26 ዓመታት በነጻ ያገለገሉ፤ ፠ አኗኗራቸው ልክ እንደ ገዳም አባቶች የሆኑት፤ ፠ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም የሃገራችንንና የቅዱሳንን ታሪክ በቃላቸው የሚያውቁ፤ ፠ ድምፃቸው እጅግ በጣም የሚማርከው፤…… አባታቸውን ቆሞስ አባ ተክለ ወልድ የካቲት 23 ዐረፉ፡፡ ሥርዐተ ግብዐተ መሬታቸውም በታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ ተፈጸመ፡፡ ግንቦት 24/1929 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ እነዋሪ ሞረት አውራጃ ልዩ ስሙ ሰገድ ሚካኤል (ጋን ማርያም) አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ መኮንንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ተወለዱ፡፡ የተወለዱበት ወቅቱ ጣሊያን ኢትዮጵያን በጠላትነት የወረረችበት ወቅት በመሆኑ ገና ልጅ ሳሉ ቤተሰቦቻቸው ይዘዋቸው ወደ ዋሻ ገቡ፤ ቢሆንም ግን ጠላት ጣሊያን ደርሶ በአካላቸው ላይ ጉዳት አደረሰባቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በሞት ገና ብዙ ሥራን የሚሠራባቸው በመሆኑ ሕይወታቸው ተረፈ፡፡ ቤተ ሰቦቻቸውም ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ ይደግ ብለው በአቅራቢያቸው ለምትገኘው ጋን ማርያም ሰጧቸው፤ እርሳቸው በዚህችው ቤተ ክርስቲያን በልጅነታቸው እያገለገሉ ቆይተዋል፡፡ 7ት ዓመት ሲሞላቸው ወደ ታላቁ ገዳም ደብር ዜና ማርቆስ ገብተው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከተለያዩ መምህራን በሚገባ ቀስመዋል፡፡ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ወደ አዲ አበባ ረጲ መድኀኔ ዓለም አምጥተዋቸው በዚሁ ደብር ከሚገኙ መምህራን ተጨማሪ ትምህርቶችን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ፡፡ እቴጌ መነን አ.አ. ኮልፌ ላይ የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅን ከፍተው የሚማሩ ተማሪዎችን በሚያሰባስቡበት ጊዜ በቢትወደድ መኮንን እንዳልክቻው አቅራቢነት ወደ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው ተምረዋል፡፡ ለተማሪነትም እንደተመረጡ ከገጠር ለብሰዋት የመጡት ነጠላ ነበረች፤ ይህች ነጠላ አልቃ ነበርና አውልቋት ተባሉ፤ እርሳቸው ግን ከገጠር ስወጣ ለብሼያት የወጣኋት የእናቴ ነጠላ ነችና አላወልቃትም አሉ፤ እቴጌ መነን ይህን ሲሰሙ ልባቸው ተነክቶ በነጠላቸው ላይ የሚለብሱትን ሌሎች ልብስ ወዲያውኑ ሰጥተው ትምህርታቸው እንዲማሩ አደረጓቸው፡፡ በዜማ ትምህርት የተደነቁ በመሆናቸው በሃገር ፍቅር በዜማ ክፍል ተቀጥረው ለመሥራት ፍላጎቱም ስለነበራቸው የመንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁና የሃገር ፍቅር የዜማ ክፍል አስተባባሪ ኢዩኤል የተባሉ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ለመቀጠር ተመዝገቡ፤ ነገር ግን ቀጠሮ ስለበዛባቸው፤ ወደ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመልሰው ከቆዩ በኋላ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገብተዋል፡፡ የ23 ዓመት ዕድሜ ላይ ሳሉም በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ መንኵሰዋል፤ ኋላም ቆይተው በ1957 ዓ.ም. ቁምስና ተቀብለዋል፡፡ በቋንቋ በኩልም አማርኛ፣ ግእዝ፣ ዐረብኛና ሱዳንኛን አዋቂ ነበሩ፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነትም የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ረድዕ በመሆን ሲያገለግሉ ቆተዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም እጅግ በጣም ይወዷቸው ስለነበር ኋላ አሜሪካ ከሄዱ በኋላ ልብስና ገንዘብ ይልኩላቸው ነበር፡፡ በደሴ ይኖሩ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ጋርም አብረው ኖረዋል፡፡ በመቀጠልም ወደ አሥመራና አሰብ ለአገልግሎት ተልከዋል፤ ምጽዋንና ደብረ ቢዘንንም አገልግለዋል፡፡ በመቀጠልም ግብጽ ለተወሰኑ ጊዜያት ከቆዩ በኋላ፤ የሱዳን ካርቱም ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው ተመድበው በትጋት አገልግለዋል፡፡ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በጠቅላይ ቤተ ክህነትና በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም በተያዩ የአገልግሎት ዘርፎች እያገለገሉ መኖሪያቸውንም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ አድርገው ቆይተዋል፡፡ ከ26 ዓመታት በፊት በ1986 ዓ.ም. የመድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንን በጣም ይወዱ ስለነበር ከጠቅላ ቤተ ክህነትና ከቅድስት ማርያም ወደ ታላቁ ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም መጥተው አቶ አማረ የተባሉ አባት የመቃብር ቤት ሰጥተዋቸው ደብራችንን በቅስና አገልግሎት በነጻ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በመቃብር ቤት ሕይወታቸውም በቀጨኔ ደብ ሰላም 3ት ስውራን አባቶች (1ኛው መነኰስ ሺኖዳ ዘግብፅ የሚባሉ) መኖራቸ ተገልጾላቸዋል፤ ይህንንም ነገር በጣም የቅርብና የልብ ወዳጃቸው ለሆኑ ሰዎች ብቻ ተናግረዋል፡፡ በ2000 ዓ.ም. ላይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ በመቃብር ቤት የሚኖሩ አገልጋዮች ቤቶቹን እንዲለቁ በተደረገበት ወቅት ለደብራችን ብዙ ታላላቅ አስተዋጽዖ ካደረጉት ግንባር ቀደም የሆኑት የአቶ ደርቤ አበበ ባለቤት ወ/ሮ ዐሥራት (ፍሬሕይወት) ተክለ አረጋይ በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ውስጥ አንድ ክፍል ሰጥተዋቸዋል፡፡ እንዲያም ሁኖ የሚወዱት ደብራችንን ሌሊት፣ ጠዋትና ማታና ሳይለዩ፤ ሌሊት በሰዓታትና በኪዳን፤ ጠዋት(ከሰዐት) በቅዳሴ፣ ማታ በጸሎት አይለዩም ነበር፡፡ በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ አብረው ይዘዋት የሚሄዷትና የማይለይዋት ስዕለ እግዝዕትነ ማርያም ‹‹ግርማት ኃይላ›› (ፎቶውን ይመልከቱ) ብለው የሰየሟት ዘንድሮ እንደማላልፍ ነግራኛለች ይሉ እንደነበር አብረው የሚኖሩ አባቶች ነግረውናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን፣ ታሪክን በተለይም የሃገራችንንና የቅዱሳንን ታሪክ እጅግ በጣም ከማወቃቸው የተነሣ ለሚጠይቃቸው ሁሉ በቃላቸው አስፈላጊውን መልስ ይሰጡ ነበር፤ በዚህም ሊቅነታቸው የማይደነቅባቸው ሰው አልነበረም፡፡ በዜማ በኩልም ቅዳሴ በጣም አዋቂና ድምፃቸው እጅግ የሚመስጠው ቆሞስ አባ ተክለ ወልድ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ ድምፃቸው ባለመለወጡና ቅዳሴ በጣም ስለሚወዱ የቅዳሴ አገልግሎት የሚያገለግሉት አብዛኛውን ጊዜ በዲቁና ነው፡፡ እኒህ አባት የማላስተምረውና የማልመክረው፤ የማልጠይቀውና የማልጎበኘውን የንስሐ ልጅ አልይዝም ብለው አንድም የንስሐ ልጅ አልያዙም ነበር፡፡ አኗኗራቸውም ልክ በገዳም እንዳሉ አባቶች ሲሆን፡፡ ይኸውም፤ *በአብዛኛው ጊዜ የሚለብሱት ወይባ (ቢጫ) ልብስ ነው፤ *የሚተኙት መሬት ላይ ያለምንም ፍራሽ ነው፤ (ፎቶውን ይመልከቱ) *የሚበሉት ዳቦ በሰሊጥና በማር ነው፤ ምንም እንኳን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስንም ጨምሮ ከውጭ ሃገር ጭምር የሚያውቋቸው ሰዎች ገንዘብ ቢልኳላቸውም እርሳቸው ግን በመጠን የሚኖሩ ስለሆነ፤ ገንዘቡን ለተለያዩ ገዳማትና አድባራት በጥሬ ገንዘብና አስፈላጊውን ንዋያተ ቅድሳት እየገዙ ይሰጡ ነበር፡፡ ለአብነትም ያህል፤ *ለደብራችን ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም 4ት የእጅ መስቀሎች (1ዱ ከኢየሩሳሌም የመጣ)፣ 1ድ የአንገት መስቀል፣ ልዩ የሆነ ትልቅ መቁጠሪያ፣ ይታጠቁበት የነበሩ 2ት የመነኰሳት መታጠቂያዎች (1ዱ ከኢየሩሳሌም የመጣ ከቆዳ የተሠራና ስማቸው ያለበት ነው)፣ እንዲሁም 3ት የመነኰሳት ቀሚስ (1ዱ ላይ የእመቤታችን ስዕል በጥልፍ የተቀመጠበትን) አበርክተዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ስጦታዎችም በቤተ መዘክር (Museum) ተቀምጠው ተቀምጠው በዕይታ ላይ ይገኛሉ፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ)

፠ #ዓድዋ፥ #ሶሎዳ(በፎቶ ላይ የምትመለከቱትና ከዓድዋ ተራሮች ዋነኛው)፡፡ #ዓድዋ #፬ት #ታላላቅ_ነገሮችን_አስተባብራ_የያዘች_የኢትዮጵያ_ሕያው_ምስክር። 1ኛ) ከ1500 ዓመትት በፊት ዓድዋ (ዖድዋ
+1
፠ #ዓድዋ፥ #ሶሎዳ(በፎቶ ላይ የምትመለከቱትና ከዓድዋ ተራሮች ዋነኛው)፡፡ #ዓድዋ #፬ት #ታላላቅ_ነገሮችን_አስተባብራ_የያዘች_የኢትዮጵያ_ሕያው_ምስክር። 1ኛ) ከ1500 ዓመትት በፊት ዓድዋ (ዖድዋ፥ ዖድዋ) ብለው የሰየምዋትንና ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸውን #የእንዳአባ_ገሪማን ገዳም የያዘች፤ 2ኛ) በዓለም #ከ1500 #ዓመታት_በላይ ረዥም ዕድሜን ያስቆጠረውን የእንዳአባ ገሪማን #የብራና_ወንጌል ጠብቃ ያቆየች፤ 3ኛ) ከዓድዋ በፊት በጥር 1878 ጣሊያንን ዶጋሊ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰው፡፡ የታላቁ አርበኛ #ራስ_አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ በክብር ያሸለበባት፤ 4ኛ) ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገበትን #ሶሎዳ_ተራራና ሌሎችንም ተራሮች በጉያዋ ያቀፈች ናት፤ ዓድዋ። ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

፠ #ዓድዋ፥ #ሶሎዳ (በፎቶ ላይ የምትመለከቱትና ከዓድዋ ተራሮች ዋነኛው)፡፡ #ዓድዋ #፬ት #ታላላቅ_ነገሮችን_አስተባብራ_የያዘች_የኢትዮጵያ_ሕያው_ምስክር። 1ኛ) ከ1500 ዓመትት በፊት ዓድዋ (ዖድዋ፥ ዖድዋ) ብለው የሰየምዋትንና ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸውን የእንዳአባ ገሪማን ገዳም የያዘች፤ 2ኛ) በዓለም ከ1500 ዓመታት በላይ ረዥም ዕድሜን ያስቆጠረውን የእንዳአባ ገሪማን የብራና ወንጌል ጠብቃ ያቆየች፤ 3ኛ) ከዓድዋ በፊት በጥር 1878 ጣሊያንን #ዶጋሊ_ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰው፡፡ የታላቁ አርበኛ ራስ አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ በክብር ያሸለበባት፤ 4ኛ) ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገበትን ሶሎዳ ተራራና ሌሎችንም ተራሮች በጉያዋ ያቀፈች ናት፤ ዓድዋ። ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ዜና_ዕረፍት ****ያገለገለህን ሰው ሞት ቸል አትበል። ፠ ደብራችንን በተለያዩ አገልግሎቶች ለበርካታ ዘመናት ያገለገሉን #ቆሞስ_አባ_ተክለወልድ እና ፠ በመስቀል ደመራ፣ በጥምቀትና በተለያዩ የደብራ
+1
#ዜና_ዕረፍት ****ያገለገለህን ሰው ሞት ቸል አትበል። ፠ ደብራችንን በተለያዩ አገልግሎቶች ለበርካታ ዘመናት ያገለገሉን #ቆሞስ_አባ_ተክለወልድ እና ፠ በመስቀል ደመራ፣ በጥምቀትና በተለያዩ የደብራችን አገልግሎት ግንባር ቀደም አገልጋያችን #ዮሴፍ_አለምሸት (#አቡዬ) በድንገት ስላረፉ፤ ሥርዐተ ግብዓተ መሬታቸው የሚፈጸመው፤ * ሰኞ የካቲት 23 ጠዋት የአባ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሽኝት * የአቡዬ ደግሞ በ8 ሰዐት በደብራችን ላይ ይፈጸማል።