uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 367 підписників, посідаючи 5 600 місце в категорії Релігія і духовність та 2 189 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 367 підписників.

За останніми даними від 26 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 2, а за останні 24 години на 2, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 20.69%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.92% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 180 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 679 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 18.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 27 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 367
Підписники
+224 години
Немає даних7 днів
+230 день
Архів дописів
፭ኛ ዙር ዓመት ፬ኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
+5
፭ኛ ዙር ዓመት ፬ኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

፠ አባታችን አቡነ አረጋዊም የእርጅና ዘመናቸው በደረሠ ጊዜ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይኸውም ‹‹መታሰቢያህን ያደርግ በጸሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላእክት ፊት ሞገስን ቧለሟልነትን እሰጠዋለሁ፤ በእውነተኛ ሀይማኖት ሁሉ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ፤ ያጻፈ፤ የተረጐመ እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፤ ይህ ሁሉ ላደረገም እስከ 14 ትውልድ ድረስ እምርልሀለሁ›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን አልሞተም በዓመቱ "ሞትን የማይቀምሱ አሉ፡፡" ብሎ እንደተናገረው /ማቴ 16 ፥ 28/ ጥቅምት 14 ቀን 558 ዓ/ም #ተሠወረዋል፡፡ ይህም እንዲህ ነው አባታችን አቡነ አረጋዊ ማትያስ ለተባለው ደቀ መዛሙር ጌታችን ተገልጦ የሰጣቸውን ቃል ኪዳንና ይህ መጽሐፍ ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነገሩት፤ (መዝ ፻፲፩/፻፲፪፥፮) ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቶቹ በተሰበስቡበትም ሁሉንም ከአስተማሩ በኋላ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም›› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም በመሪር ኃዘን እግራቸው ሥር ወድቀው አለቀሱ፤ አባታችን አቡነ አረጋዊም አጽኗኗቸው፡፡ ጥቅምት ፲፬ ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በ፺፱ (99) ዓመታቸው ተሰወሩ፤ በዚያም #ከመቋሚያና #ከመስቀል በስተቀር ምንም የተገኘ የለም፡፡ ገድላቸውንም ደቀ መዛሙርታቸው ማትያስ እና ዮሴፍ ጽፈዋል፡፡ ከዚያም አባ ማትያስ ደብረ ደሞን ለማስተዳደር ተሾመዋል፡፡ ከጻድቁ አባት በረከት ይክፈለን፤ በቃልኪዳናቸው ይጠብቀን፤ አሜን፡፡ #_ እግዚአብሔር አምላክህ አንተን መርጦሃልና እንደ ኹለቱ ነቢያት ለተከወነ መሠወርህ ሰላምታ የሚገባህ ደግ አገልጋይና የታመንህ መጋቤ ቤቱ ቅዱስ አረጋዊ ሆይ በዐሥሩ አህጉር ተሹመህ ኀምስቱን መካልይ የተቀበልህ አንተ አይደለህምን?፡፡ _# #መልክአ አቡነ አረጋዊ ፨#ቅዱስ ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር በዓለ #ዕረፍታቸው_፡፡(ታቦታቸው በቀጨኔ ደብረሰላም ያለ) ታሪኩ ከሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስና ከቅዱስ ቶማስ ዘቶርማቅ ጋር ተመሳሳይ የሆነው(ቅዱስ ያሬድ ለእመቤታቸን ( ትዕግሥትኪ ፈድፈደ እምትዕግሥተ ኢዮብ ጻድቅ ፤ወእማርቆስ #ዘቶርማቅ ፤ ወገብረ ክርስቶስ መርዓዊ ተወካፌ ሕማም መጽዕቅ፡፡ ) ብሎ እንደጻፈው ቅዱስ ቶማስ ዘቶማርቅ እንደ ኢዮብ ታጋሽ የሆነ ጻድቅ ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ሰው የተባለ ትዕግሥኛው ቅዱስ ሙሴ ዕረፍቱ ነው፡፡ ፠፠ ፠፠፠ ፠፠፠ ፠ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#ጥቅምት_14 አቡነ #_ አረጋዊ የተሰወሩበት፤ ቅዱስ #_ ገብረክርሰቶስ በዓለ እረፍት፤ ቅዱስ #_ ሙሴ_እግዚአብሔር በዓለ ዕረፍታቸው ነው፡፡(ታቦታቸው በቀጨኔ ደብረሰላም ያለ) በጋዛ ምድር ኢትዮጵያዊውን ጃንረባ ባኮስን ያጠመቀው ረድኡ ሐዋርያ ቅዱስ #_ ፊሊጶስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ጥቅምት 14 ፤ አቡነ አረጋዊ ( ዘሚካኤል ) ወቅዱስ ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር #አቡነ_አረጋዊ (#ዘሚካኤል) ፠ ከእንጦንስ ከመቃርስ እና ከጳኵሚስ የምንኵስና ሐረግ አራተኛ ትውልድ ናቸው፣ ፠ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም 6 ሺህ የደረሱ ናቸው፣ ፠ ከቅዱስ ያሬድ ጋር እጅግ ይዋደዱ የነበሩ ፣ ዝማሬውንም ለመስማት ከጐንደር ለመጣ ሲል በጸጋ አይተው ደብረ ዳሞ ላይ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ሰብሰበው ይጠብቁ የነበሩ ፡፤ ፠ ታላላቅ የኢትዮጵያ ነገሥታትን ለባረኩ ይመጠላቸው የነበረ .. ፠ አጼ ገብረ መስቀል በተመስጦ የቅዱስ ያሬድን እግር በጦር በወጋው ጊዜ ታለቅ ግብዣን አድርገ የዛኔም አቡነ አረጋዊ ቀድሰዋል፣ ቅዱስ ያሬድም ዘምሯል ፤ ታላቅ ሥርዓትንም አስጀምረዋል፡፡ ___________ ፠ ትውልዳቸው ሮም ሲሆን እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከአባታቸው #ይስሐቅና ከእናቸው #እድና የተገኙ የቅዱሳን ፍሬ ናቸው ፤ ወንድሞቹም #ቴዎድሮስ እና #ገብረ አምላክ ይባላሉ፡፡ ፠ የቀድሞው ስማቸው #ዘሚካኤል ነበር፡፡ “አረጋዊ” የተባሉት ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ነው፡፡ በእድሜ ልጅ ሲሆኑ በመንፈሳዊ ሕይወታቸውና ሥራቸው አዋቂ ስለነበሩ አረጋዊ ብለዋቸዋል፡፡ ፠ወላጆቻቸው ቅዱሳት መጻሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፤ እሱም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እየጸናና እየበረታ ሄደ፡፡ ዕለት ዕለት ጧትና ማታም ወደቤተክርስቲያን እየሄደ ጸሎት ከመጸለይ አያቋርጥም ነበር፡፡እድሜውም ለጋብቻ ሲደርስ አባትና አናቱ ያገባ ዘንድ ሚስት አጩለት፡፡ እሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ እየተቃኘ የምንኵስና ሕይወትን ለመኖር ፈልጓልና፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ የምንኵንስና ሕይወትን ለመኖር ወደ አባ ጳኵሚስ ዘንድ ሄደ፤ ወደ ገዳሙም በገባ ጊዜ አንድ መነኵሴ አገኙትና ‹‹ልጄ ሆይ ከወዴት መጥተሃል እነሆ አንተ ሕፃን እንደሆንክ እመለከታለሁና›› አሉት፡፡ እሱም አመጣጡ ከሮም እንደሆነና ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ የሚፈልገው ነገር እንዳለ ነገራቸው፡፡ እሳቸውም ነገሩን ከሰሙ በኋላ ወደ አባ ጳኩሚስ ዘንድ ወሰዱት፡፡አባ ጳኩሚስም በአየው ጊዜ ከመንበሩ ተነስቶ በፍፁም ፍቅር አቅፎ ሳመው የእግዚአብሔር ጸጋ በእሱ ላይ አድሯልና፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ስለምን ጉዳይ ወደ እሱ እንደመጣ ጠየቀው፡፡ አባ ዘሚካኤልም ‹‹እንደአንተ እንደ አባቴ መነኵሴ እሆን ዘንድ መጥቻለሁ›› አለው፡፡ አባ ጳኩሚስም ‹‹ልጄ ሆይ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደመሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኵሰህ ለመኖር እንደምን ይቻልሃል?›› ሲል መለሰለት፡፡ አባ ዘሚካኤል ግን የምድር መንግሥት ኀላፊ ጠፊ እንደሆነ ያውቃልና ከዓለም ንግሥና ይልቅ ዘለዓለማዊ መንግሥትን ይወርስ ዘንድ እንደሚሻ ያመነኵሰውም ዘንድ አጥብቆ ጠየቀው፡፡ አባ ጳኩሚስም ፈተናን ፈትኖት መቋቋም የሚችል ከሆነ እንደሚያስገባው ነግሮ የተለያዩ ፈተናዎችን ፈትነው፡፡ አባ ዘሚካኤልም የተባለውን የታዘዘውን ሁሉ በትጋት ፈጸመ፡፡ አባ ጳኵሚስም ስለሃይማኖቱ ጽናት ስለጠባይና ስለቅንነቱ እጅግ አድርጐ ወደደው፡፡ ከዚያም አስኬማው ወይም ቆቡ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ አመነኰሰው፤ ስሙንም ዘሚካኤል ብሎ ጠራው፤ በዚህ ጊዜ #እድሜው 14 ዓመት ነበር፡፡ ፠አባ ዘሚካኤል አስኬማ ካደረገ በኋላም በታላቅ ትጋቱ በጸሎቱና በጾሙ አባ ጳኵሚስ ተደነቀ፡፡ ስለሱም ዝናው በየሀገሩ ሁሉ እስከ አባቱ አገር ሮም ድረስ ተሰማ፡፡ አባ ዘሚካኤል ገና በሕፃንነቱ የምንኵስና ማዕረግ መቀበሉን ከሰሙ በኋላ ወደ እሱም 8 ቅዱሳን የመጡ ነበሩ፡፡ እነሱም፦ አባ #_ ሊቃኖስ ከቁስጥንጥንያ(ገዳማቸው በአኵሱም የሚገኝ )፣ አባ #_ ይምዓታ (ገዳማቸው በኃውዜን የሚገኝ (ትግራይ) ከሀገረ ቁስያ፣ አባ #_ ገሪማ ከሮም(ገዳማቸው በአኵሱም የሚገኝ ፣ ከአንፆኪያ አባ #_ ድሕማ፣ ከቂልቅያ አባ #_ ጉባ፣ ከእስያ አባ #_ አፍጼ፣ ከሮሚያ አባ #_ ጴንጠሌዎንከሮም(ገዳማቸው በአኵሱም የሚገኝ ) ፣ ከቂሳርያ አባ አሌፍ ነበሩ፡፡ እነሱም አባ ጳኵሚስ የምንኵስናውን አፅፍ አጐናፀፏቸውና አመነኮሷቸው፡፡ ለእያንዳንዳቸውም ስማቸውን ሰየሟቸው፡፡ እኒህም አባቶች ስለትዕግስት፣ አርምሞ፣ ትህትና፣ ስለሥርዐተ ማኀበር አመሠራረት ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ ተማሩ፡፡ ፠ ከዚህ በኋላ በዚያ ገዳም ለብዙ ዓመታት በፍቅር በአንድነት ከአባ ቴዎድሮስ ጋር ተቀመጡ፡፡ በዚህን ጊዜ ግን አባ ጳኩሚስ አርፈው አባ ቴዎድሮስ ተተክተው ነበር፡፡ እነዚህም አባቶች ወደየሃገራቸው ሄደው ማስተማርና ሃይማኖትንማስፋፋት እንዳለባቸው ተስማምተው ወደየሀገራቸው ተመለሡ፡፡ አባ ዘሚካኤል ግን በዚያው ቆየ፡፡ እሱ ልቡን የነካችዉ ዜናዋንም የሰማላት ሃገር ነበረችና፡፡ ይህቺውም ሃገራችን #ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ እሱም ማንም ሰው ሳያውቅና ሳያየው ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው መጥተው ጐብኝተዋታል፡፡ ያለመምህራንና ያለአስተማሪ ያመነች የዚህችን ሀገረ እምነቷንና ሥነስርዐቷን ተመልክቶ ተደነቀ፡፡ እነዚያን 8 መነኰሳትም ከያሉበት ስለሃገሪቷ እየነገረ ጠራቸው የሚገርመው ግን እነሱም ስለዚህች ሀገር እንደሰሙ ያለምንም ማመንታት መጥተዋል፡፡ እነሱም ሕዝቡን እንደሰሙት አገኙት፡፡ አባ ዘሚካኤል አቡነ አረጋዊ የሚለውን ስያሜ ያገኙት ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ትህትናቸውና ታዛዥነታቸው እሳቸውሲመነኩሱ ገና ሕፃን ነበሩ ስራቸው ግን የአረጋውያን ነበርና አንተስ ሐፃን አይደለህም የልጅ አዋቂ ነህ ሲሉ #አረጋዊ አሏቸው፡፡ አባታችን አቡነ አረጋዊ ወደ ኢትዮጵያ የገቡበትም ቀን ጥቅምት 11 ነበር ፡፡ አቡነ አረጋዊ በኢትዮጵያ ሲኖሩ በሄዱበት ስፍራ ብቻቸውን የሚፀልዩበትን ቦታ ሁል ጊዜ ይፈልጉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም በመንገድ እየሄዱ ሳሉ ትልቅ ተራራን (ደብረ ዳሞን) ተመለከቱ፤ ከሦስተኛው ቀን በኃላም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ‹‹አንተ እግዚአብሔር ያከበረህ ቅዱስ ሆይ ምን ያስጨንቀሃል›› አለው፡፡ አባታችንም አቡነ አረጋዊም ‹‹ከዚህች ተራራ ላይ ወጥቼ ስለኃጥያቴ እናዘዝና እለማመን ስለበደሌም ይቅርታን እጠይቅ ዘንድ እወዳለሁ›› አለው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም እንዲፀልይና ታላቅ ዘንዶም ወደርሱ እንደሚላክለት ነገረው፡፡ በሦስት ሰዓትም ዘንዶው መጣ፤ አባታችንም የዘንዶውን ጅራት ይዘው ወደ ላይ ወጡ ብቻቸውን አልነበሩም ፡፡ ዘንዶው እንዳያስደነግጣቸውና እንዳይጐዳቸው ሰይፍን ይዞ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቃቸው ነበር እንጂ፡፡ ቢዚያችም ሰዓት ተራራዋ ደብረ ታቦርን መስላ ነበር:: በዚህችም ላይ ንጉሥ አጼ ገብረ መስቀል ቤ/ክ ከአነጹ በኃላ የቅዳሴ ቤቱ ዕለት አቡነ አረጋዊ ቀድስው ንጉሡም ሠራዊትም ሕዝቡም ጳጳሳቱም ጭምር ሥጋ ወደሙን ተቀብለዋል፡፡ ንጉሡም በረከተን ከአባታችን ተቀብሉ ወደ አኵሱም ተመልሷል፡፡ ሲመለስም ሰርቶት የነበረውን ድልድላይ ላፍረሰው ወይ ሲላቸው ዳሕምሞ ብለውታል ትርጕሙም ‹‹የሰራኸውን ደረጃ ናደው ፥ አፍርሰው እንጂ አትተወው›› ፡፡ ከዚ በመነሳት ዳሞ ተብላለች፡፡ እግዚአብሔርም ሰማያዊ ኅብስት ትሁነህ ብሎ ደብረ ዳሞን ስጥቶዋቸዋል ይህም በመንፈስ ለሚወለዱት ልጆቹ እስከ ዘለዓለም ማርፍያ እንድትሆን ነው ፡፡

አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ----- ጥቅምት 9 --› ጽላቶችን የተቀበሉበት ዕለት በዓሉ ከሚከበሩባቸው ቦታዎች ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ( ፈዋሽ ፀበል ያለበት እና አጽመ ቅዱሳንን የያዘ ዋሻ ያለበት ገዳም) ከሳሪስ --› ቦሌ ቡልቡላ (ኮንዶሚኒየም) (የ30 ደቂቃ መንገድ) ---- አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለትተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ "ስብሐት ለአብ: ስብሐት ለወልድ : ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ" ብለውአመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ "የአብ : የወልድ : የመንፈስ ቅዱስእስትንፋስ" : አንድም "የክርስቶስ እስትንፋስ" ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቦናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍትቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡ በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴንጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክመጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት : ለአባቶች መነኰሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳንበማውጣት አገልግለዋል፡፡ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊትከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንናግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያንአገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል፡፡አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችንከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ጌታንም በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላመልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ ሁሉንም የኢትዮጵያንቅዱሳት ገዳማትንም ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያስነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡ ጻድቁ ወደ ደብረ አስጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ፡፡ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አስጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ ኢየሱስ ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔ ዓለምንየሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት "ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም" ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር ግን መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ ጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ታህሳስ 9 ቀን ተወልደው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን የተቀበሉበት ዕለትም ጥቀምት 9 ይከበራል በዓሉ ከሚከበሩባቸው ቦታዎች ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ( ፈዋሽ ፀበል ያለበት እና አጽመ ቅዱሳንን የያዘ ዋሻ ያለበት ገዳም) ከሳሪስ --› ቦሌ ቡልቡላ (ኮንዶሚኒየም) (የ30 ደቂቃ መንገድ) ሌሎች ይህ በዓለ የሚከብረባቸውን አድባራት ኮሜንት ላይ ያስቀምቱጡ ገዳማቸው ደብረ አሰጋጅ ቀርሜሎስ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገዳም ሰሜን ወሎ ዳውንት ይገኛል። /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like