es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 626 suscriptores, ocupando la posición 5 373 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 216 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 626 suscriptores.

Según los últimos datos del 09 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 72, y en las últimas 24 horas de 0, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 8.45%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 4.64% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 1 319 visualizaciones. En el primer día suele acumular 725 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 12.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 10 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 626
Suscriptores
Sin datos24 horas
+907 días
+7230 días
Archivo de publicaciones
የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት የት ሊያከብሩ ዐስበዋል ?? share #በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፺፫ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ (በተለይም በድርብነት ያሉ በዓለ ልደቱን ላያከብሩ ስለሚችሉ ሲሄዱ አጣርተው ይሂዱ ) (ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ አሳውቁን) ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #በአዲስ_አበባ_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፳፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፬. ደብረ ጽላልሽ (ዞረሬ) አቲሣ ተክለ ሃይማኖት፡፡ (#ጻድቁ_የተወለዱበት) አድራሻ፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት፥ ጽላልሽ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. → በደብረ ብርሃን መንገድ አሌልቱ ከተማ ላይ በመታጠፍ ያገኙታል፡፡ ፩ ✣ ጥንታዊው በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋሻ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም) /በአብርሐ ወአጽብሐ ዘመን በ‹‹ሐ›› ቅርጽ በልዩ አሠራር የታነጸ ፍልፍል ዋሻ፤ ከ1600 ዓመታት በላይ ያስቈጠረ፡፡/ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ሾላ (መገናኛ) ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (4 ኪሎ) → ሾላ (መገናኛ) → የካ ሚካኤል → በእግር የ30 ደቂቃ መንገድ፤ ወይም ወደ ኮተቤ በአዲሱ መንገድ ሲሄዱ መንገድ ላይ ወርደው ተራራውን እንደወጡ ያገኙታል፡፡ ፪ ✣ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ /ከዓመት እስከ ዓመት ከበዓለ ሃምሳ ውጭ እንደ ደብረ ሊባኖስ ውሎ ቅዳሴ የሚቀደስበት/ አድራሻ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ መርካቶ ተክለ ሃይማኖት፤ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (ከአውቶቡስ ተራ) → መርካቶ ተክለ ሃይማኖት ፫ ✣ መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል፥ አቡነ ተክለሃይማኖትና ቅድስት አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ በቀጨኔ በአዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ከደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ በላይ ጉብታው ላይ የሚገኝ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → ቀጨኔ(አዲሱ ገበያ) → የ20 ደቂቃ የእግር መንገድ፡፡ ፬ ✣ ሲ.ኤም.ሲ. መካነ ጻድቃን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት ልደታ፤ አድራሻ፤ የካ ክ/ከ፤ ሲ.ኤም.ሲ.፤ መሪ ሎቄ፤ ለገጅጃ ትራንስፖርት፤ ከመገናኛ ሲ.ኤም.ሲ. ፭ ✣ ኮልፌ ፊሊዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ፥ ፊሊዶሮ፤ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ → መርካቶ → ኮልፌ አጣና ተራ /ፊሊዶሮ/፡፡ ፮ ✣ ፍኖተ ሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤ (በድርብነት ይከብራል) አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ፥ ብርጭቆ ኮንዶሚንየም ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ አረዳ → ብርጭቆ ፯ ✣ (ጀሞ) ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ → ጀሞ ፰ ✣ ደብረ ቢታንያ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ፥ 5 ቊጥር (2 ቊጥር) ማዞርያ ትራንስፖርት፤ ከፒያሰ (መርካቶ)→ ሜክሲኮ → ንፋስ ስልክ ፱ ✣ ቦሌ ቡልቡላ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ሥላሴ ገዳም፤ (አስደናቂ ጠበል ያለበት) አድራሻ፤ ቤሌ ክ/ከ፥ ቡልቡላ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (ከመገናኛ) → ሳሪስ አቦ → ቡልቡላ መድኀኔዓለም ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #እንዲሁም_በአንድነት_፤ ፲ ✣ መጠሊ ደብረ አሮን ፍልፍል ዋሻ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ገላን ጉራ ገበሬ ማኅበር፥ መጠሊ፤ ታክሲ፤ ከቃሊቲ → ገላን፡፡ ፲፩ ✣ (ቀበና) ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ሀብተ ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ሲግናል ዐደባባይ → ዐድዋ ድልድይ → ኮንጎ ሰፈር (ከበአታ ቤ/ን ፊት ለፊት)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ካዛንቺስ (22) /በአዋሬ በኩል በሚሄዱት)፡፡ ፲፪ ✣ ቱሉዲምቱ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ፤ አድራሻ ፤አቃቂ ቃቲ ክፍለ ከተማ፥ ቱሊ ዲምቱ አደባባይ ወደ አለም ባንክ መንገድ ላይ ነዳይ ማደያ ጋር፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → ቱሉ ዲምቱ → ዐደባባይ አለም ባንክ፡፡ ወይም ከቃሊቲ → ቱሊዲምቱ (አለም ባንል,ክ ነዳጅ ማደያው ጋር) ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #እንዲሁም_በድርብነት_፤ ፲፫ ✣ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል፥ 24ቱ ካህናተ ሰማይና ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → የካ አባዶ፡፡ ፲፬ ✣ ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ/ክ አድራሻ፤ ቤሌ ክ/ከ፥ ቡልቡላ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (ከመገናኛ)→ ሳሪስ አቦ → ቡልቡላ መድኀኔዓለም ፲፭ ✣ ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም (እናትና ልጇ) ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ፈረንሳይ፤ ታክሲ፤ ከ4(6) ኪሎ → ፈረንሳይ፡፡ ፲፮ ✣ ቤላ መጥምቀ መለከት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ቤላ ፈረንሳይ ፓርክ፤ ታክሲ፤ ከ4 (6 ኪሎ) → ቤላ (ፈረንሳይ) ፲፯ ✣ ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ፥ ሰርጢ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (ከመገናኛ) (ከመርካቶ)→ አቃቂ ፲፰ ✣ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. አድራሻ፤ ኮለረፌ ቀራንዮ ክ/ከ፥ ቤተል ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → ቤተል/ዓለም ባንክ/ ፲፱ ✣ ኤ(የ)ረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤልና ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ጎሮ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ (ቦሌ) → ኤረር በር (ጎሮ)፡፡ ፳. ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤልና ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ሩፋኤል፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (ጴጥሮስ ዐደባባይ) → ሩፋኤል፡፡ ወይም ከአዲሱ ገበያ/ቶታል/ → በእግር ፳፩ ✣ ገዳመ ኢየሱስ፤ አድራሻ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ሆላንድ ኤምባሲ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ኮልፌ አጠና ተራ፡፡ ወይም ከጦር ኀይሎች → ኮልፌ (ቀለበት መንገዱ ላይ) ፳፪ ✣መሪ አያት ምሥራቀ ፀሐይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክ/ከ፥ መሪ አያት ትራንስፖርት፤ ከመገናኛ → መሪ አያት ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ http://www.finotehiwotsundayschool.com

እንኳን አደረሳችኁ በዓለ_ልደቱ_ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታኅሣሥ 24 1196 ዓም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ እቲሣ ተወልደው በአጠገቡ በምትገኛዋ ደብረ አጋዕዚት ክርስትና_ተነሡ፡፡ #አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘአብና እናታቸው ቅድስት እግዚእ ኀረያ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው በአካባቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻንና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡ #በ7ት ዓመታቸው ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ ከዮዲት ጉዲት በኋላ ሃገራችን ሰሜኑና ደቡቡ ተቆራርጧል፤ የሐሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ሐዲስ ሐዋርያ ያስፈልግ ነበርና አምላካችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ጠራ፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው በሸዋና በዳሞት በስብከተ ወንጌል አገለገሉ፡፡ ከዚያም፤ #በመጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ላይ ገዳማቸውን ደብረ ጎል ገድመው ወደሚገኙት ታላቁና ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወደኾኑት ጻድቅ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ዐሥር ሁለት ዓመታት በትምህርትና በሥራ (በአርድእትነት) አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡ #በ1216 ዓ.ም. አካባቢ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገሳም ገብተዋል፤ በዚሁ ገዳምም ከመመንኰሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኰሱም በኋላ ሦስት ዓመት በድምሩ ለ10 ዓመታት በትምህርት፣ በእደ ጥበብ ሥራ፣ በአገልግሎትና ሥርዓተ ምንኩስናን እያጠኑ ቆይተዋል፡፡ #ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዐተ ምንኩስናና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ በየገዳሙ አበምኔት ከሆኑት ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት ፣ ሥርዐተ ምንኩስናና ጥበበ እድ ሲማሩ ለ12 ዓመታት ቆዩ ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡ #በደብረ ዳሞ የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው በገመድ ሲወርዱ ሰይጣን በቅንዐት መጥቶ ገመዱን በጠሰባቸው እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወቅት የሚበሩበትን እንደ መላእክት ክንፍ ሰጣቸው፡፡ #ለአምስት ዓመታት #አኵስምን_ዋልድባን እንዲሁም ሎሎች የትግራይ ገዳማትን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆዩ #ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት (እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን) ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ #ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለዐሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኩስና፣ ትምህርትና ሥራ፡፡ መነኮሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡ #ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፋፍተው ካደላደሉ በኋላ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡ #አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ 24 ቀን 1297 ዓ.ም. በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡ ✤✤ #እቲሣ_ገዳም_ #በቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተ፤ ሲመሠረትም በታቦተ ኢየሱስና አርባዕቱ እንስሳ ነው፤ #ሊቀ ካህናት አበይድላ ከአኵስም 300 ታቦታትና 300ካህናት ይዞ መጥቶ በጽላልሽ የተቀመጠባት ናት፤ #ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱባት (የተወለዱባት ጠፍጣፋ ደንጊያ አሁንም በቦታው አለች)፣ #አባታቸውና ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእኀረያ የተወለዱበት፤ ኋላም ክብሩ አጽማቸው ያረፈበት ነው፡፡ #ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ቅዱስ ላሊበላ 7 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ተሰዓቱ ቅዱሳን 20 ዓመት የጸለዩበት፤ #ሐርቤ በሚባለው ቦታ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 7 ዓመት ጸልየውበታል፤ #ታቦተ ጽዮን 12 ዓመት (ከ9ሺህ ሕዝብ) ጋር መጥታ ኖራበታለች፤ #በአምሳለ ሲዖል የተሠራ አስደናቂ የጨለማ ዋሻ ያለበት ነው፤ #ብዙ የታሪክ ቅርስ ያለበት ነው፤ #በቅዱስ ሚካኤልና ጸጋ ዘአብ ቤተ ክርቲያን ውስጥ ካየን በኋላ፤ እዚሁ ቦታ በሚገኘው ፈዋሽ ጠበል ተጠምቀንና ጠጥተን ጕዟችንን ወደ ቦታው ከአ.አ በቅርብ ርቀት በደብረ ብርሃን መንገድ አሌልቱ ከተማ ላይ በመታጠፍ ይገኛል፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌቱን እንደየደብራችሁ ይትበሃል እንድትጠቀሙበት (በላይ ቤትና በታች ቤት) (#ዘአባጃሌ_ተክለ_ሃይማኖትና_ዘአደባባይ_ተክለሃይማኖት) አዘጋጅተነዋል፡፡ ጸሎትና በረከታቸው ፤ ረድኤትና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ኢትዮጵያውያን_ቅዱሳን

#ታኅሣሥ 22 (በዓለ ደቅስዮስ ) ብሥራተ ገብርኤል በዚህችም ዕለት እመቤታችንን ድንግል ማርያምን የከበረ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በአበሠራት መሠረት ደቅስዮስ በዓልን አደረገ፡፡ ደቅስዮስ የተባለው ኤጲስ ቆጶስ ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ የተአምራቷን መጽሐፍ ሰብስቦ ያዘጋጀ ነው፡፡ መጽሐፉን ስለጻፍክ ብላ እመቤታቸን ደስ መሰኝቷን ነግራው ተሰውራለች ፡፡ ይህንን በራዕይ ባየ ጊዜ የእርሷን ክብረ አብዝቶ ይጨምር ዘንድ አሰበ ፡፡ ሰዎችም አስበውት የማያውቁትን የቅዱሰ ገብርኤል ብሥራት በዓሏን አከበረ ሰዎችም እጅግ ተደሰው በዓሉን በታላቅ ድምቀት አከበሩት ፡፡ይህችም በዓል በጵጵስናው ዘመን ተሰራታ እስከ አሁን ትኖራለች፡፡ እመቤታችን ለቅዱስ ደቅስዮስ ዳግመኛ በተገለጸችበት ጊዜ የከበረ ልብስ ይዛ ፤ ደቅስዮስ ሆይ ስለ አከበርከኝ ደስ አለኝ እኔም ዋጋህን ልከፍኽ መጣሁ ይህችን ልብስ ልበስ በላዩም ትቀመጥ ዘንድ ወንበር አመጣሁልህ ከሰው ወገን ይህን ልብስ ሊለብስ እና እዚህ ወንበር ላይ ሊቀመጥ ከቶ የሚችል የለም ፡፡ ደቅስዮስም ከአረፈ በኃላ ሊለብሱ እና ሊቀመጡ የነበሩ በመሞታችው ዛ ፤ በዙሃን የእመቤታችንን ተአምር አይተው አደነቁ ፡፡ #የብሥራቱም ነገር እንዲህ ነው ፡፡ እመቤታችንን ያን የተጠማ ውሻ ውኃ ባጠጣችው ጊዜ ፤ በዚህ ዘመን አምላክ ከድንግል ይወለዳል ያላት ካንቺ ይሆን እያሉ ይዘባበቱባት ነበር ፡፡ ወዲውኑ ከኃላዋ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ትጸንሲ አላት ፡፡ ዞር ብትል አጣቸው አባቴ አዳምን እና እናቴ ሔዋንን ያሳተ ጠላት ይሆናል ብላ ዝም ብላ ሄደች ፡፡ ዳግመኛም ቤት ከደረሰች በኃላ ትጸንሲ አላት ፡፤ ይህ ነገር ተደጋገመ ብላ ወደ ቤተ መቅደስ ነገሩን ልትረዳ ሄደች ፡፡ በወርቅ ወንበራ ተቀምጣ ከደናግለ እሥራኤል ጋር የተካፈለችውን ሐር እና ወርቅ እያስማማች ስትፈትል ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾ ‹‹ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ ›› ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበለሽ አላት ፡፡ ይህን ሰምታ በደነገጠችም ጊዜ ‹‹ኢትፍርሂ ማርያም እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር ›› በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻል አትፍሪ እነሆ ትጸንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ እግዚአብሔርም የአባቱን የዳዊት ዙፋን ይሰጠዋል አለቸው ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም አላት ፡፡ ……ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል አለችው ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ወኃይለ ልዑል ይጼልለኪ›› መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል ብሎ የተቀመጠችበትን የወንበሩን እጀታ አለምልሞ ይህን ማን አደረገው ቢላት እግዚአብሔር አለችው፡፡ ይህንንም የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው ‹‹አስመ አልቦ ዘይሰአኖ የሚሳነው የለምና ኤልሳቤጥ እንኳን ጸነሰች ይህ ስድስተኛው ወር ነው አላት ፡፡ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ ‹‹ እንደቃልህ ይሁንልኝ ይደረግልኝ ›› አለችው፡፡ ይህን ቃሏን ምክንያት አድርጎ ወልድ ዋህድ እግዚአብሔር በማኀፀኗ አደረ ፡፡ ይህ የሆነው መጋቢት 29 ቀን ነው ታኅሣሥ 22 እንዲከበር ያደረገው ግን ከላይ እንደገለጽነው ኤጲስ ቆጶሱ ቅዱስ ደቅስዮስ ነው ፡፡ መጋቢት 29 በጾም ምክንያት በሚገባ አይገበርም ነበርና ከበዓለ ልደቱ ሰባት ቀን አስቀድሞ ታኅሣሥ 22 በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ የእመቤታችን ምልጃዋ አይለየን አሜን! /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Angeles #ቅዱሳን_መላእክት #ክብረ_በዓላት #Feasts #Our_mother_Virgin_mary #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም