uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 622 підписників, посідаючи 5 362 місце в категорії Релігія і духовність та 2 204 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 622 підписників.

За останніми даними від 08 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 67, а за останні 24 години на 14, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 8.25%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 4.62% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 1 288 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 721 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 12.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 09 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 622
Підписники
+1424 години
+867 днів
+6730 днів
Архів дописів
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጅማ መቆየት አይችሉም ተብለው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርጓል። © ማኅበረ ቅዱሳን

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጂማ ከተማ በፀጥታ አካላት ተወስደዋል። በነገው ዕለት አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በጂማ ከተማ ለማስመረቅ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመምሪያ ኃላፊዎች ጋራ ዛሬ ጠዋት ለመሄድ አዲስ አበባ አየር መንገድ ተገኝተው ነበር። ከእነዚህም መካከል ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሲገኙ ሌሎች እንግዶች ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ፣ ሊቀ ትጉሃን እስክንድር ገ/ክርስቶስ ይገኙበታል። አየር መንገድ ሲደርሱም የሀገረ ስብከቱ አባት ይበቃሉ በማለት ቀሲስ ታጋይ አብረው እንዲሄዱ በመፍቀድ ሌሎች አባቶችና እንግዶችን ከጉዞ መልሰዋቸዋል። ጂማ ከተማ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ አካላት የተያዙ ሲሆን የያዟቸው አካላትም ከክልል የደረሰን አቅጣጫ ነው ማለታቸው ተሰምቷል። በተመሳሳይ ዜና ሕገ ወጡን ሹመት ትተው ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱት መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ታፍነው መወሰዳቸው ተገልጿል። ©ማኅበረ ቅዱሳን

እንኳን አደረሳቹሁ #ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_(ለሶልያና ) #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡ ፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው ----›እርሱን እዚህ ያንብቡ ----›https://t.me/medihanaelem/6840፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››ረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ #ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ *የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡ *እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡ **ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል:: /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts #Our_mother_Virgin_mary #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...

“ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።” — መኃልየ. 2፥15 ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶስ በቀድሞ ስማቸው "አባ"ሳዊሮስ ፣ "አባ" ኤዎስጣቴዎስና ፣ "አባ" ዜና ማርቆስን ከዲቁና - ጵጵስና ያላቸውን ሥልጣነ ክህነት ሙሉ በሙሉ በመሻር በቀድሞ የዓለም ስማቸው "አቶ" ተብለው እንዲጠሩና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባልነት እንዲለዩ ወሰነ !

ከሐሙስ እስከ ቅዳሜ የሚቆይ የጸሎት መርኀ-ግብር ። #ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለ3 ቀናት የሚቆይ #ጸሎት_አወጀች፡፡ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን
ከሐሙስ እስከ ቅዳሜ የሚቆይ የጸሎት መርኀ-ግብር ። #ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለ3 ቀናት የሚቆይ #ጸሎት_አወጀች፡፡ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ከተጠናቀቀነ በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ እንዲሆን አዋጅ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል፡፡ #_#_#_#_#_#_#_ #በዚህም መሠረት ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከነገ #ሐሙስ (18/05/2015) ጀምሮ እስከ #ቅዳሜ(20/05/2015) የሚቆይ #የመሐረነ_አብ የጸሎት መርኀ-ግብር ስላዘጋጀ ሁላችንም #ከ11:30 ጀምሮ በመገኘት የጸሎቱ ተሣታፊ እንድሆን ይሁን ።

ከሐሙስ እስከ ቅዳሜ የሚቆይ የጸሎት መርኀ-ግብር ። #ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለ3 ቀናት የሚቆይ #ጸሎት_አወጀች፡፡ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ከተጠናቀቀነ በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ እንዲሆን አዋጅ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል፡፡ #_#_#_#_#_#_#_ #በዚህም መሠረት ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከነገ #ሐሙስ (18/05/2015) ጀምሮ እስከ #ቅዳሜ(20/05/2015) የሚቆይ #የመሐረነ_አብ የጸሎት መርኀ-ግብር ስላዘጋጀ ሁላችንም #ከ11:30 ጀምሮ በመገኘት የጸሎቱ ተሣታፊ እንድሆን ይሁን ።

ሰበር ዜና መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ ! ተ.ሚ.ማ መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ ! ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ። መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው የይቅርታ ደብዳቤያቸውን የተቀበሉ ሲሆን የቅዱስ ሲኖዶስን ምላሽ እንዲጠብቁ ምክር ለግሰዋል።

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት - Статистика та аналітика Telegram каналу @finotehiwott