Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 622 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 362,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 204 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 622 名订阅者。
根据 08 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 67,过去 24 小时变化为 14,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 8.25%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.62% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 288 次浏览,首日通常累积 721 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 12。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 09 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 622
订阅者
+1424 小时
+867 天
+6730 天
帖子存档
#Orthodox_Quotes
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጅማ መቆየት አይችሉም ተብለው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርጓል።
© ማኅበረ ቅዱሳን
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጂማ ከተማ በፀጥታ አካላት ተወስደዋል።
በነገው ዕለት አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በጂማ ከተማ ለማስመረቅ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመምሪያ ኃላፊዎች ጋራ ዛሬ ጠዋት ለመሄድ አዲስ አበባ አየር መንገድ ተገኝተው ነበር።
ከእነዚህም መካከል ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሲገኙ ሌሎች እንግዶች ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ፣ ሊቀ ትጉሃን እስክንድር ገ/ክርስቶስ ይገኙበታል።
አየር መንገድ ሲደርሱም የሀገረ ስብከቱ አባት ይበቃሉ በማለት ቀሲስ ታጋይ አብረው እንዲሄዱ በመፍቀድ ሌሎች አባቶችና እንግዶችን ከጉዞ መልሰዋቸዋል።
ጂማ ከተማ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ አካላት የተያዙ ሲሆን የያዟቸው አካላትም ከክልል የደረሰን አቅጣጫ ነው ማለታቸው ተሰምቷል።
በተመሳሳይ ዜና ሕገ ወጡን ሹመት ትተው ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱት መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ታፍነው መወሰዳቸው ተገልጿል።
©ማኅበረ ቅዱሳን
እንኳን አደረሳቹሁ
#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_(ለሶልያና )
#እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡
#ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤
#ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤
#ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡
፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው ----›እርሱን እዚህ ያንብቡ ----›https://t.me/medihanaelem/6840፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››ረፍታ ለሶልያና(ለማርያም)
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡
#ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡
*የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡
*እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡
**ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል::
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts
#Our_mother_Virgin_mary #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም
https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...
#Orthodox_Quotes
“ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።”
— መኃልየ. 2፥15
ሰበር ዜና
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀድሞ ስማቸው "አባ"ሳዊሮስ ፣ "አባ" ኤዎስጣቴዎስና ፣ "አባ" ዜና ማርቆስን ከዲቁና - ጵጵስና ያላቸውን ሥልጣነ ክህነት ሙሉ በሙሉ በመሻር በቀድሞ የዓለም ስማቸው "አቶ" ተብለው እንዲጠሩና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባልነት እንዲለዩ ወሰነ !
ከሐሙስ እስከ ቅዳሜ የሚቆይ የጸሎት መርኀ-ግብር ።
#ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለ3 ቀናት የሚቆይ #ጸሎት_አወጀች፡፡
በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ከተጠናቀቀነ በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ እንዲሆን አዋጅ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል፡፡
#_#_#_#_#_#_#_
#በዚህም መሠረት ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከነገ
#ሐሙስ (18/05/2015) ጀምሮ እስከ #ቅዳሜ(20/05/2015) የሚቆይ
#የመሐረነ_አብ የጸሎት መርኀ-ግብር ስላዘጋጀ ሁላችንም #ከ11:30 ጀምሮ በመገኘት የጸሎቱ ተሣታፊ እንድሆን ይሁን ።
ከሐሙስ እስከ ቅዳሜ የሚቆይ የጸሎት መርኀ-ግብር ።
#ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለ3 ቀናት የሚቆይ #ጸሎት_አወጀች፡፡
በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ከተጠናቀቀነ በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ እንዲሆን አዋጅ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል፡፡
#_#_#_#_#_#_#_
#በዚህም መሠረት ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከነገ
#ሐሙስ (18/05/2015) ጀምሮ እስከ #ቅዳሜ(20/05/2015) የሚቆይ
#የመሐረነ_አብ የጸሎት መርኀ-ግብር ስላዘጋጀ ሁላችንም #ከ11:30 ጀምሮ በመገኘት የጸሎቱ ተሣታፊ እንድሆን ይሁን ።
ሰበር ዜና
መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ !
ተ.ሚ.ማ
መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ !
ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ።
መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር አቅርበዋል።
ብፁዕነታቸው የይቅርታ ደብዳቤያቸውን የተቀበሉ ሲሆን የቅዱስ ሲኖዶስን ምላሽ እንዲጠብቁ ምክር ለግሰዋል።
