uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Daily Meditation

Daily Meditation

Відкрити в Telegram

ሂድና በ "ሰሊሆም" መጠመቂያ ታጠብ አለው ትርጓሜውም "የተላከ"ማለት ነው። ስለዚ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ። ዬሀ 9:7 and said to him, "Go,wash in the pool of "SILOAM" (which means "sent"). so he went aweywashed and come back seeing. jon 9:7 ለማንኛዉምሀሳብአስታያየት @yenemrchaeysus 👆👆👆👆

Показати більше
1 097
Підписники
-124 години
-37 днів
-1330 днів
Архів дописів
🩸ይቅርታ!!                 👇👇 🔘 ይቅርታ 👉 የሚኖር ነው ሕይወት ያለው 🔘 ይቅርታ 👉 በመሸነፍ ውስጥ ያለ ማሸነፍ ነው 🔘 ይቅርታ 👉 በዝቅታ ውስጥ ያለ ከፍታ ነው 🔘 ይቅርታ 👉 ራሱ ስኬት ነው 🔘 ይቅርታ 👉 ልብስ ነው የሚለበስ 🔘 ይቅርታ 👉 ተስፋ ነው ነገ ፍሬና ደስታ ያለው "ይቅር በይ ይቅር ትባያለሽ፤ በደል አትቁጠሪ ብዙ የተተወልሽ ነሽና!!" 🐅 በሕይወትሽ ዘመን ሰላም ያለው በረከት የምትሺ ከሆነ በፍፁም ልብሽ የበደሉሽን ይቅር በይ🙋‍♀። ምንም የከፋ በደል ያድርሱብሽ ተይላቸው ይቅር ብለሽ መንገድሽን ቀጥይ ነገሽን ይይዝብሻልና። ⚠️ "ልባም ሴት ይህች ናት በይቅርታ የተሞላ ልብ ያላት ፍሬዋን በይቅርታ የምታበዛ!!"                                

በአንድ ስፍራ በአንድ አደባባይ ሁለት አይነት ግብይት በቤተ መቅደስ እና በቤተክርስቲያን  ዮሐ 2፥12-25    አማኙ በመሰንበቱ አብሮት በመቆየቱ እውነት እውነት የመሰለው የስህተት አደባባዮች አስጨንቀው ከመግዛታቸው የተነሳ ብዙ ብዙ ምንላቸው ዝምታን የተመረጡባቸው ርዕሶች እልፍ ናቸው።   እውነት ለመናገር ትክክል እና ጥቅም ያላቸው የሚመስሉት እነዚህ ጉድፎች ዛሬም የአማኙን ትኩረት እምነት ከልቡ ወደ አይኑ ያዞሩበት ይመስለኛል ።    ልቡንም በጌታ ላይ ከማጣበቅ ይልቅ  የመድረክ ትእይንቶች እምነቱን ሰርስረው  በልተውታል ። በዮሐንስ 2፥14 ላይ እንዲህ የሚል እውነት አለ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ከብቶች በጎችንና ርግቦችን የሚሸጡ እንዲሁም ተቀምጠው የገንዘብ ምንዛሪ የሚያከናውኑ ሰዎችን አገኘ።    በእርግጥ በጊዜው በነበረው ለመስዋዕት አገልግሎት ጠቃሚ ቢሆኑም ስፍራቸው ግን እዚህ አልነበረም።  ስፍራው እነርሱ የሚሰውበት እንጂ የሚገበያዩበት አይደለም ።ለዚህ ነው "የአባቴ ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት !" አላቸው ። ተብሎ የተጻፈልን። ይህ መልእክት ዛሬም ለኛ ዘመኗ ቤተክርስቲያን ⛪ ግልጽ መልእክት አለው። አንዳንድ ነገሮች ጠቃሚ እየመሰሉን ግን መባረር እና መገለባበጥ ያለባቸው ልምዶች ተጣብቀውናል።  መች ወደ ቤታችን እንደገቡ ባናስተውልም አደባባይ እና መድረክ እንደያዙብን ግን በግልጽ እየተመለከትን ነው። የእውቀት ማነስን የመሰለ መንፈሳዊነትን ከእኛ የሚያባርር ነገር የለም። ብዙ በእኛ እይታ ጥሩ የመሰሉን ነገር ግን በቃሉ ሲመዘኑ ቤተክርስቲያን ሳይሆን የንግድ ስፍራ ሆነው ምናገኛቸው እልፍ ናቸው።   ዝርዝራቸውን ለእናንተ ልተው መቼም ዘይት፣ ጨው ፣ውሃ፣ ፎጦና የተለያዩ ጨርቆች እንደምትሉኝ እርግጠኛ ነኝ እንዲሁም ጸሎቶች ደግም በውጭ ምንዛሪ የሚቀርቡ ከሆኑ ሰነባበቱ ደግሞ ያለ መልስ በሁሉም ቤት በተመሳሳይነት መመላለሳቸው እጂጉን አስገራሚ ናቸው። አንዳንድ አስነዋሪነታቸው ከቁጥጥር ውጭ ነው። ከሚያጣጥር ነፍስ ላይ መሆናቸው ደግሞ ምን ያህል ተኩላነትን እንደተላበሱ ግልጽ እውነት ነው።       ስንቱን አፈር እደበላው ምድር ትመስክር የአብዛኛዎቹ የትንቢት ካላደር ገና አመታት ትሮራለህ ተብሎ ዛሬ በህይወት የሌሉ አይቆጠሩም ።  ብቻ ምን አለፍችሁ "ለቤትህ ያለኝ ቅናት ያቃጥለኛል" መዝ 69፥9 የተጻፈው እንደው ትዝ ትዝ ቢለን ቢያቃጥለን በዚህ ዘመን እንዴት ያለ ጤንነት መሰላችሁ !!!    👉  ምን መሰላችሁ መልእክቴን ሳጠቃልል ብቻ አሁን ላይ በኑሮ፣ በስብከት፣ በትምህርት፣ በምክርና በመቃወም ጅራፍ የምናነሳበት ጊዜ እንደሆነ አምናለሁ። ጌታ የምንበረታበትን ጸጋውን ይሰጠናል ዝም ማለታችን ግን በአብሮት ከማበር የማይተናነስ ደረጃ ላይ ነን !!!!    ⭐ ሀሰትን መቃወም እውነትን ያጎላል !!!          ወንድማችሁ ተረከብ ዮሐንስ ነኝ              ተባረኩ ጸጋው ይብዛላችሁ

Geta ras adrgogn“አምላኬ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤ እስከ ዛሬም ተአምራትህን እነግራለሁ።” — መዝሙር 71፥17

እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው። ያዕቆብ 4:17 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው።" 1ኛ የዮሐንስ 3:4

ትንቢተ ኢሳይያስ 43:16 •••••••••• ¹⁶ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፤     @About_Jesus

ለኛም ቀን ይመጣል ጌታ ቀን ያመጥልናል

“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡”

ይህንን ድንቅ ምክር እዩማ "ጠላት ሰይጣን ሁልጊዜ፦ 'አንተ ገና ወጣት ነህ፤ ዛሬ በሕይወትህ ተደሰትና ነገ ንስሐ ትገባለህ' ሊልህ ይወዳል። ነገር ግን አስታውስ፤ እግዚአብሔር ንስሐ ለሚገቡት ምሕረትን ቃል ቢገባም፣ለሚያዘገዩት ግን 'ነገን' ቃል አልገባቸውም።ያላችሁ ብቸኛና እርግጠኛ ሰዓት 'አሁን' ብቻ ነው።"

ከ አምላኬ  የራኩ ቀን ፍሩኝ! አለኝ የምለው ጥቂት መልካም ነገር  እንኳን ያለኝ ከሱ የተነሳ  ብቻ ነው:: 😔

ዓለም የምታምረው በሳሎኗ እንጂ በጓዳዋ አይደለም፡፡ የዓለም ጨለማና ክፋት በታየህ ቁጥር ከደጉ ጌታ ጋር የምትገናኝበት ቀን ይናፍቅሃል፡፡ ዓለምን በእኔ ካላየሁ አትበል አክብራ ባዋረደቻቸው ስማ በነከሰቻቸው በእነዚያ ሰዎች ተመልከታት ዓለም ማለት መልከአ ምድሩ ሳይሆን አስተሳሰብ ነውና ምናልባት ይህች ዓለም በውስጥህ እንዳትኖር ተጠንቀቅ፡፡ ምክኒያቱም ክርስትና ከዓለም መውጣት ሳይሆን ዓለምን ከአንተ ውስጥ ማስወጣት ነውና፡፡

♦️መፍትሄ አለው…❗️                  👇👇 የሰው ልጅ ድብቅ🤔 ነው ብዙ ጉዳዬችን ብዙም ሚስጥራትን በውስጡ ይይዛል፣ ይደብቃል ይሸሽጋልም ለሌላ ሰው አንደበቱን🗣 ከፍቶ የውስጡን ማውጋት፣ ግልፅ ሆኖ የተሰማውን ያለበትንም ሁኔታ ማስረዳት ማጫወት ይከብደዋል🤷‍♂ ውስጡ በሃዘን ተሞልቶ ደስተኛ ለመምሰል መፍጨርጨር፣ የውስጡን ህመም በውጫዊው ነገርም ለመሸፈንም ይንቀሳቀሳል😰 ታዲያ ግን ይህ አካሄዱ ለራሱ ለገባበት፣ በውስጡም ላውጠነጠነው ጉዳይ ለደበቀውም ነገር መፍትሄን ይዞለት ሲመጣ ብዙ ጊዜ አይስተዋልም‼️ ለሰው መናገር የውስጡን ሃሳብ መግለፅ እያለበት🤔 ግን ገድቦ ካስቀረው መጨረሻው ጥሩ አይሆንም ቀን ጠብቆም ይጎዳዋል😔 ለዚህም አንዱ መፍትሄው👉 መነጋገር፣ ሃሳብን በግልፅ መግለፅ፣ ውስጥን  ማውራት ነው ።  ለሚቀርባችሁ ሰው ልትናገሩ ይገባል፤ በውስጣችሁ አምቃችሁት አታስቀሩ እርሱ መፍትሄ አይሆናችሁምና🙅‍♂ ብዙ ሰዎች ውስጣቻው በጭንቀት ተሞልቶ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ራሱ በማያውቁበት🤦‍♂ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ያሉበትን ነገር መናገር አይፈልጉም ይህ በጭራሽ ትክክል አይደለም❌ ⚠️ ስታወሩ ሰው ምረጡ #መንፈሳዊ ሕይወቱ ጥሩ የሆነ ፣ #የሚያበረታችሁ ሸክማችሁን #የሚሸከም፣ የልቡን ሳይሆን #የእግዚአብሔርን መልካም ሃሳብ አስቀድሞ የሚመክራችሁ ሰው ይሁን🙏 ዛሬ ምን ይሆን ያስጨነቃችሁ ውስጣችሁንስ በሃሳብ ያቆሰለው⁉️ የእውነት ዝም ያላችሁት መፍትሄ የለውም ብላችሁ ነው🤔⁉️ ግድ የለም አውሩ ለዛ ሰው የሚቀልላችሁ ነገር አለ።  በየትኛውም #ሃጥያት ውስጥ ውደቁ #ምንም አድርጉ #የቱም ነገር ያስጨንቃችሁ  ውስጣችሁ ግን አታስቀሩ አውሩት። መፍትሄው እርሱ ስለሆነ ስለዚህ ጊዜ አትስጡት ነገ የሚጠብቃችሁ ሌላ ህይወት ስላለ🙏

ኢየሱስን ምከተለው ስለሞላልኝ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን የምከተለው ስለጎደለብኝም ጭምር ነው ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን በህይወታችሁ እግዚአብሔር ለማመስገን ስትነሱ ስለተደረገላችሁ ብቻ ሳይሆን ስላልተደረገላችሁም ነገር እግዚአብሔር አመስግኑት ስላጣው አመሰግንሀለው ስለጎደለኝ አመሰግንሀለው ስለተቸገርኩ አመሰግንሀለው ስለጠማኝ አመሰግንሀለው ስለወደኩ አመሰግንሀለው ስለተንገጫገጭኩ አመሰግንሀለው ጠይቄ ስላልተመለሰልኝ አመሰግንሀለው ስለ ሁሉ የኔ ጌታ ተመስገን ስለ ሁሉ ከፍ በል የኔ አባት @behayluminilu @behayluminilu @behayluminilu

አንድ ወጣት ሁል ጊዜ ለመጠጥነት የተጠቀመበትን የውሃ ሃይላድ ከበሩ ደጃፍ ላይ አውጥቶ #ይጥላል በንጋታው ሲነሳ ከስፍራው ያጣዋል ለብዙ ጊዜያት ይህ ከሆነ ቡሃላ አንድ ቀን🤔 "ለምን ማልጄ ተነስቼ ማን እንደሚወስደው አላይም!" ይልና ማልዶም ይሳልና። ታዲያ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ #ሽማግሌ ከደጃፉ ላይ ሲያነሱም ይመለከታል "አባት ለምንድን ነው የሚወስዱት ቆሻሻ ነው እኮ እኔ ተጠቅሜ #ያበቃለትን #የወደቀ #የቆሸሸ ስልምን ፈለጉት" ይላቸዋል እርሳቸው ግን ምንም ሳይመልሱ በዝምታ ያልፉታል🤫 ታዲያ አንድ ቀን  "ለምን ተከትያቸው ይህን ቆሻሻ ምን እንደሚያደርጉት አልመለከትም❗️" ይልና አንድ ቀን ይከተላቸዋል ታዲያ እኚህ ሽማግሌ እጅግ #ውብ የሆነ ቤት ውስጥ ሲገቡም ያያል ይገረምና ሄዱ በሩን #ያንኳኳል እርሳቸውም #ይከፍቱለትና ወደ ቤት እንዲገባ #ይጋብዙታል ከዚያም ወጣቱ "አባት ይህን የመሰለ ውብ መኖሪያ ይዘው ስለምን ቆሻሻ ሲለቅሙ ይገኛሉ #ለዚያውም የማይጠቅም❗️" ሲል ይጠይቃቸዋል እርሳቸው ዝም ብለው ያዩትና "እስቲ ተመልከት ልጄ ቤቱ ውብ አይደል🤔 ይህን ከምን የሰራሁት ይመስልሃል⁉️ አንተው ከጣልከው ቆሻሻ ነው ካልከው ሃይላንድ አይደል!" ሲሉት እንዴት ቢላቸው ጊዜ 👉 "አየህ ልጅ አጠቃቀሙን ስለማውቅ ነው" 👈 ብለው መለሱለት ይባላል🙏 #ወድቄያለው፣ #አብቅቶልኛል፣ #ከንቱ ነኝ #ከዚህ ቡሃላማ እንዴታ🤷‍♂⁉️ የምትሉ ልብ በሉኝ "የወደቀ #አይነሳም የሳተስ #አይመለስም" አየሽ ያ ሃይላንድ እንኳ ጥቅም ላይ ከዋለ ለማጌጫነት ካገለገለ አንቺማ እንዴታ⁉️ ሰው ነሽ እኮ ጌታ በአምሳሉ #የፈጠረሽ ስለ አንቺ #ግድ የሚለው ዳግም የሚያነሳ #እንደገና ከወደቅሽበት ስፍራ አንስቶ #የክብር እቃ፣ የከበረ ሰው #ውብ የሚያደርግሽ ክርስቶስ አለ✝ አበቃልኝ አትበይ ሰይጣን ውሸቱን ነውና። ስለዚህ ቀና በይ ውድቀትሽን  ለሚያወራልሽ ጠላት #ጆሮና #ልብ አትስጪው  #ዳግም ውብ መሆን አለና‼️ "በጌታ ዘንድ ሁሌም ተስፋ አለ እርሱ በሰው ተስፋ አይቆርጥምና!"                 

ኢየሱስ ይመጣል

🩸ትህትና! 💁‍♀                  👇👇 ትህትናን መጫሚያዋ👟 ትህትናን ካባዋ🧥 ያደረገሽ ሴት እርሱ ልቧሟና አስተዋዯ ናት👍 በሄደችበት ስፍራ ሁሉ በረከት፣ እግሯ በረገጠበት ቦታ መብዛት፣እጇ የነካው ሁሉም ፈውስ ይሆናልና😳 🔹"ትህትና ራስሽን ዝቅ ዝቅ በማድረግ ከፍ ከፍ የምትይበት መሰላል ነው"🐆 🔹"ዝቅ በይ ታዛዥ ሁኚ ቀና ብለሽ ለመሄድ ድፍረት ይሆንሻልና"🐆 🔹"ታላቅሽን አክብሪ ለታናሽሽም ታዘዢ በእግዚያብሄር ዘንድ ተቀባይነት ታገኛለሽና"🐆 🔹"ትህትናን ልበሺ አጥብቀሽም እሺው መልካም ፍሬ አለውና"🐆 ልብሽ በማንም ላይ ክፋ አያስብ❌ ይልቅስ ለሚጠሉሽ ለሚገፉሽ ይበልጥኑ ትሁት ሁኚ😇 ከአንዲት ልባም ሴት ባህሪዎች ውስጥ አንዱ ትሁት መሆኗ ነው ዝቅታን መላበሷ😲 ትሁት መሆን ዝቅም ማለት የበታችነትን የሚገልፅ አይደለም የበላይነትን እንጂ💪 ልብ በይ ይህንንም ነገር ሁሌም አስተውይ ትህትና የበላይሽ ይሁን!🙏                              

ድል የሚቀናው ቶሎ የጀመረውን ሳይሆን፣ እስከ መጨረሻው የጸናውን ነው።

👋 👋 ወርቅ የከበረም አልማዝ በቤቱ ውስጥ ያኖረ ያስቀመጠም ሰው 1⃣ #ትኩረት እርሱ ላይ ቢሆን 2⃣ #ሌቦችም ደጁን ደግመው ደጋግመው ቢያጤኑ አያስገርምም፤ በቤቱ ያስቀመጠው #ውድ ነገር አለና።  ማድረግ የሚችለው አንድ ነገር 👇 "ቤቱን #መጠበቅ ውዱን ንብረትም #ደህንነቱ በሚጠበቅበት ስፍራም ማስቀመጥ መጠበቅ።" 🔘 #በቅድስና ስትመላለሺ፣ #ፈሪያ እግዚአብሔር ሲኖርሽ፣ አካሄድሽ #በቅን #በእውነት #በጽድቅ ሲሆን ፈላጊሽ ብዙ ነውና ተጠንቀቂ⚠️ 🔘 ልብሽን #ከሰዎች፣ #ከሁኔታዎች #ከራስሽም ክፉ ብሎም መልካም ከሚመስል ሃሳብ ጠብቂ።  🙏 🔘 በቅድስና ሕይወትሽ #አትደራደሪ ዛሬ ጌታን #ፈርተሽ የኖርሽው ሕይወት ነገ #ቀን ጠብቆ ይከፍልሻልና። 🍇 🔘 #አስተዋይ #ንቁ #ብልህ #ጥበበኛ ሴት ሁኚ ዙሪያሽን በደንብ ተመልከቺ። 🙏 "ፈላጊሽ ብዙ ነውና አጥብቀሽ ጌታን መፈለግሽን አታቁሚ!!"                              

Photo እና video ዝም ብለሽ አትፓስቺ 😳🙄 "ለክርስቲያን" ሴቶች በየ social media በየ Instagram በየ Facebook የምትለቂው photo እና video አላማው ምንድነው..? እይታ እና አድናቂ አገኘው ብለሽ የምትፓስቺው ነገር በኅላ የማትወጪው ነገር ውስጥ ሊያስገባሽ ይችላል.😳🥺 ስለዚህ ምን አይነት መልህክት እያስተላለፍኩ ነው..? አለባበሴ፣እንቅስቃሴዬ እግዚአብሔርን ያከብራል ወይ..? የሚለው ሀሳብ ላይ ትኩረት ይኑርሽ.. የምታደርጊውን ሁሉ በማስተዋል አድርጊ. ከዛ እመኚኝ እህቴ ብዙ ታተርፊያለሽ 🙌 ውድ እህቴ🥰 ለሰዎች የመሰናከያ ምክንያት ሳይሆን የመታነጻቸው ምክንያት ለመሆን እራስሽ ላይ ስሪ🙌🥰

ያዕቆብ መልዕክት ይህ ጥናት አማኞች እምነታቸው በዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ተግባራዊ እንዲሆን፣ በፈተና ጊዜ የማይናወጥ ጽናት እንዲኖራቸው እና የክርስቶስን መልክ በባህሪያቸው እንዲያንጸባርቁ የሚያበረታታ መፅሐፍ ነው

👋 👋 ወርቅ የከበረም አልማዝ በቤቱ ውስጥ ያኖረ ያስቀመጠም ሰው 1⃣ #ትኩረት እርሱ ላይ ቢሆን 2⃣ #ሌቦችም ደጁን ደግመው ደጋግመው ቢያጤኑ አያስገርምም፤ በቤቱ ያስቀመጠው #ውድ ነገር አለና።  ማድረግ የሚችለው አንድ ነገር 👇 "ቤቱን #መጠበቅ ውዱን ንብረትም #ደህንነቱ በሚጠበቅበት ስፍራም ማስቀመጥ መጠበቅ።" 🔘 #በቅድስና ስትመላለሺ፣ #ፈሪያ እግዚአብሔር ሲኖርሽ፣ አካሄድሽ #በቅን #በእውነት #በጽድቅ ሲሆን ፈላጊሽ ብዙ ነውና ተጠንቀቂ⚠️ 🔘 ልብሽን #ከሰዎች፣ #ከሁኔታዎች #ከራስሽም ክፉ ብሎም መልካም ከሚመስል ሃሳብ ጠብቂ።  🙏 🔘 በቅድስና ሕይወትሽ #አትደራደሪ ዛሬ ጌታን #ፈርተሽ የኖርሽው ሕይወት ነገ #ቀን ጠብቆ ይከፍልሻልና። 🍇 🔘 #አስተዋይ #ንቁ #ብልህ #ጥበበኛ ሴት ሁኚ ዙሪያሽን በደንብ ተመልከቺ። 🙏 "ፈላጊሽ ብዙ ነውና አጥብቀሽ ጌታን መፈለግሽን አታቁሚ!!"