cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

cheffie primary school 2013

በዚህ ቻናል በጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ የሚከናወኑ ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎች ለመምህሩ ለተማሪው ለወላጆችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እንዲደርሳቸው የሚደረግበት ነው።

Більше
Рекламні дописи
748
Підписники
+224 години
+27 днів
+2830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
⭐️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!✅ ======================== ⭐️ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው:: ⭐️ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:- ------------------------------------------------ ✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ✅ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።  ✅ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።  ቻናሉን ለወዳጅዎ 🌟Share ያድርጉ ቻናላችን ይህ ነው 👇👇👇👇👇👇 ✅✅✅✅✅ https://t.me/dam76
Показати все...
👍 3 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሠላም ዋላችሁ? ለነበረን ከፍተኛ ርብርብ እና ተጋድሎ እስከ መጨረሻው ስዓት ለድል ስለበቃን ክብር ይገባችዋል !!! እንኳን ደስ አለን!!ድል እና ውጤት ለለሚ ኩራቨየዘርፉ ላላችሁ ጀግኖች 🏆🏆🏆ለ3 ተከታታይ አመታት 1ኛነቱን ሳይለቅ ድሉን ማስቀጠል የቻለው ትምህርት ፅ/ቤት🏆🏆🏆 የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በከተማ ደረጃ በተካሄደው ዘጠነኛው የሳይንስ ፈጠራ ስራዎች ውድድር የአሁኑን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ አመታት ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች 1ኛ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ። በዘንድሮ አመትም በጠቅላላው 11 ዋንጫዎችን በመውሰድ አሸናፊነታቸውን አረጋግጠዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ የዋንጫ እርክክብ ላይ ሽልማት የስራ ውጤት ነው። ይህንን ሽልማት ያመጣችው በየደረጃው ያላችው የትምህርት ማህበረሰብ ሁሉ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስም ክብር ይስጥልን ሲሉ በቀጣይ ውጤቱ ተጨማሪ ስራ በመስራት የተማሪዎች የፈተና ውጤት ላይ በትኩረት እንድትሰጡ እና አዱሱ ትውልድ በዕውቀት እና በስነ ምግባር የታነፁ እንዲሆኑ የተለመደው ጥረታችሁን እንድትቀጥሉ አደራ ማለት እፈልጋለው ብለዋል። ይህን ጣፋጭ ድል አስመለክቶ የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት ያስተላለፉት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዩ በየነ ይህ ውጤት እንዲመጣ ትልቁን ሚና የተጫወቱት ርዕሰ መምህራን፣መምህራን፣ተማሪዎች እንዲሁም በዘርፉ ላሉ አካላት ሁሉ የእንኳን ደስ አለን ደስ አላቹ መልዕክት ያስተላለፉት አሁን የመጣው ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው በየደረጃ ያለነው አካላት ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን ግንቦት 18/2016 ዓ.ም
Показати все...
9👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉ የሰላም የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ይሁንልን መልካም የፋሲካ በዓል ይሁን ስለፋሲካ በዓል አከባበር ሳነብ ያገኘሗቸው መረጃዎችን ነፃ ስትሆኑ ብታነቡት አይከፋም ብየ እንደሚከተለው ለጠፍሁት። ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳዔ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው። በፋሲካ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳን፤ ማለትም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋዬን ቆርሼ ደሜን አፍስሼ አድንሀለሁ ባለው ቃል መሰረት፤ ወደዚህ አለም ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆኖ አዳምን ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ሊያወጣው፤ የአዳምን በደል እርሱ ሊክስ የተሰቀለበት ጊዜ ይታሰብበታል። ፋሲካ በአል አከባበር በተለያዩ ሃገራት ስዊድን፦ በስዊድን በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ በአላት መካከል ፋሲካ/Easter/ አንዱ ነው ፡፡ በአሉ ከሶስት ቀን አስቀድሞ አካባቢን ዋና ዋና ጎዳናዎችና አደባባዮችን በማስዋብ ማክበር ይጀመራል፡፡ በፋሲካ እለትም ህጻናት ረዘም ያለ ቀሚስ ለብሰው፤ራሳቸው ላይም በተለያዩ ቀለማት ያሸበረቁ ኮፍያችዎን በማድረግና ስእሎችን በመያዝ ተሰባስበው ጎረቤቶቻቸውን እንኳን አደረሳችሁ ይላሉ፡፡ በህጻናቱ እንኳን አደረሳችሁ መልእክተ የደረሳቸው ነዋሪዎችም ህጻናቱን ተቀብለው ቤት ያፈራውን በማቃመሰ ይሸኟቸዋል፡፡ ጣፋጭ ምግቦችን በማዘጋጀት በአሉን በድምቀት ያከብራሉ፡፡ ሃንጋሪ፦በሃንጋሪ የፋሲካ በአል በተለያዩ ባህላዊ ክንውኖች ያደምቁታል፡፡ ስፕሪንክሊንግ በመባል የሚታወቅ የውሃ ዳር ጨዋታ በፋሲካ በአል የሚጫወቱት ነው፡፡ ወጣቶች በውሃ ዳር ይሆኑና በመረጫጨት ያከብሩታል፡፡ይህም ውሃ ንጹህ ነው ሁሉንም ነገር ያጸዳልናል ከሚል ባህል እንደሚያከብሩትም ነው የሚነገረው፡፡ በወጣት ሴቶች ትክሻ ላይ ውሃ በመድፋትም የወደዳት ወንድ የፍቅር ጥያቄ እንደሚያቀርብላትም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ግሪክ፦ የግሪክ ሃይማኖቶች ከጥንታዊው የአምልእኮ ስርአት እስከ ክርስትና በድምቀት የሚከበሩ ናቸው፡፡ የግሪክስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቤዛንታይን የቀን መቁጠሪያ የምትከተል በመሆኗ ከአውሮፓውያን በተለየ ቀን ላይ ነው ፋሲካን የምታከብረው፡፡ ግሪክ ውስጥ በድምቀት ከሚከበሩ በአላት መካከል ፋሲካ ዋነኛው ተጠቃሽ ነው፡፡ አቴንስ ከስቅለት በአሉ ጀምሮ በተለያዩ አበቦችና ማስጌጫዎች ታሸበርቃለች፡፡ የስቅለት አርብ የክርስቶስ መቃብር በከተማዋ ውስጥም እንዲታሰብ ይደረጋል፡፡ ለፋሲካ ዋዜማም እኩለ ሌሊት ላይ ወደ ቤተክርስቲያን የሄዱ ምእመናን ሻማዎቻቸውን ይዘው /Christos Anesti/ ክርስቶስ ተነስቷል/ ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ/ Alithos Anesti/ እርሱ በእርግጥ ተነስቷል እያሉ ይዘምራሉ፡፡ የሻማ ብርሃኑ ታዲያ የሚለኮሰው ከእሩሳሌም ክርስቶስ ተቀብሮ ተነስቶበታል ተብሎ ከሚታመንበት ዋሻ በመጣ እሳት ነው፡፡ ዕለተ ፋሲካንም የስጋ ጥብስ፤ በቀለማት ያሸበረቁ እንቁላሎችና ድግስ አድማቂ የምግብ አይነቶችን አዘጋጅተው በደማቅ ያከብሩታል ፡፡ በሃገሪቱ ኦርቶዶክስ ባህል መሰረት የጎረቤት በርን በእንቁላል መቆርቆር የተለመደ ሲሆን ይህም በጎ እጣ ፈንታን ያመጣል የሚል አምልኮ አላቸው፡፡ ፈረንሳይ፦ የቤተ ክርስቲያን ደወሎች ፈረንሳይ ውስጥ አመቱን ሙሉ ሰኣታትን እየጠበቁ የሚደውሉ ሲሆን በፋሲካ ሶስት ቀናት ውስጥ ግን ድምጻቸውን አጥፍተው ይቆያሉ፡፡ ትውፊታቸው እንደሚያስረዳው ከሆነ የቤተክርስቲያናቱ ደወሎች ተቀድሰው ለመምጣት ወደ ሮም ይሄዳሉ፡፡ በፋሲካ እሁድም በከተማው ውስጥ በሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች ቼኮሌቶችን፡እንቁላሎችን፡ዶሮዎችንና ሌሎች የሃገሪቱ የበአል የሚሆኑ ምግቦችን ሰርተው በአሉን ያደምቃሉ፡፡ ሃዋክስ በተባለች የሃገሪቱ ከተማም 4ሺ 500 እንቁላሎች የገቡበት ኦምሌትም በመስራት በእንዱ ኦምሌት ከ1ሺ ሰው በላይ በመመገብ የፋሲካ በአልን በማድመቅ በአለም አስደናቂነትን ቦታ ይዘዋል፡፡ ስፔን፦ በስፔን በህብረት ከሚከበሩ በአላት መካከል ፋሲካ አንዱ ነው፡፡ የፋሲካ ክብረ በአል በዋናነት ከሆሳእና እሁድ/Domingo de Ramas/ የሚጀምር ሲሆን/Lunes de Pascua/ የፋሲካ ዋናው በአል እሁድ ይሆንና ሰኞ ድረስ ይቆያል፡፡ በእነዚ ቀናት ሃገሪቱ በጡሩንባዎችና ከበሮዎች አድማቂነት የካርኒቫል ስሜት ውስጥ የምትሆንበት ጊዜም ነው፡፡ በአንዳሉሽያ ውስጥ የምትገኘው ሴቬሌ ይምትባል ግዛት የፋሲካ ክብረ በአልን በደማቁ በማክበር የምትታወቅ አካባቢ ናት፡፡ በስፔን የፋሲካ ቅዱስ ሳምንታት ህመሙና ስቅለቱ የሚታሰቡበት ጊዜያት ሲሆን በፋሲካውም ማድሪድን ጨምሮ ሁሉም አካባቢዎች በአበባዎች ፤በመንገድ ላይ ጭፈራዎችና ጣፋጭ ኬኮች በደማቁ ይከበራል፡፡ ጀርመን፦ ፋሲካ በጀርመን ውስጥ በሥጦታ ቅርጫቶች ይበልጥ ይደምቃል፡፡ ልጆች በቤተሰቦቻቸው ከሚዘጋጁላቸው የስጦታ ቅርጫት ውስጥ ቼኮሌት እንቁላል አሻንጉሊቶችና ሌሎችም ስጦታዎችን በጉጉት ይጠብቁታል፡፡ እናም የፋሲካ በአል በጀርሞኖች ዘንድ ለዘመድ ለጓደኛ ለልጅ ለፍቅረኛና ለወዳጆች የሚሆኑ ስጦታዎችን በመለዋወጥ ያከብሩታል፡፡ ሊባኖስ፦ሊባኖስ ክርስቲያኖች በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም ሳቢ የሆነ ልዩ የፋሲካ በአል አከባበር ባህል አላቸው፡፡ ለሊባኖሳውያን የተለየ የሚሆነው የአከባበር ስርአት በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚካሄደው በሪቫኖች ያሸበረቁ ሻማዎችና አበባዎች ለልጆች ከተሰጡ በኋላ ቤተክርስቲያኑን እንዲዞሩ የሚደረገው ነው፡፡ ማሙል የተባለው የሃገሪቱ ልዩ የሆነ ጣፋጭ ምግብም በፋሲካ በአል የሚቀርብ ነው፡፡ ስኮትላንድ፦በስኮትላንዳውያን ፋሲካ በህብረት የሚከበርና በምግቦች ተሞላ ከመሆኑ በተጨማሪ በተለየ በልጆች ዘንድ በፈንጠዝያ የሚከበር በአል መሆኑ ነው የሚነገረው፡፡ በስኮትላንድ በልጆች በሚደረግ ፈንጠዝያ ከእንቁላል ጋር የተያያዘ ነው፡፡እንቁላሎችን ከቀቀሉና በተለያየ ቀለማት እንዲያሸበርቁ ካደረጉ በኋል በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ኮረብታማ ስፍራዎች በመውሰድ በፋሲካ እለት ቁልቁል ያንከባልሏቸዋል፡፡ ለልጆች እንደአስደሳች የጨዋታ ጊዜ ቢቆጥሩትም ክንውኑ ፍጹም ትእምርታዊ/ምሳሌያዊ/ ነው፡;፡ እንቁላል ከተራራ ላይ ማንከባለል የክርስቶስ መቃብር የተከደነበትን ድንጋይ እንደማንከባለል ይቆጥሩታል፡፡ይህም ትንሳኤውን እንደማገዝ ማለት ነው ይላሉ፡፡ አሜሪካ፦ አሜሪካውያን ንጹህ በመልበስና ቤተክርስቲያን በመሄድ የፋሲካ በአል ሳምንትን ማክበር ይጀምሩታል፡፡ የተለያዩ ከረሜላዎችና ቼኮሌቶችም የበአሉ ማድመቂያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ምግቦች በብዛት የሚበሉበት ሰሞን ነው፡፡ የፋሲካ በአልን ጠብቀው የተለያዩ ዝነኛ የጣፋጭ ምርቶች በብዛት ይለቀቃሉ ፡፡ ሌላው በዋሽንግተን ዲሲ ህጻናት እንቁላሎችን በማንከባለል ይጫወታሉ፡፡ መረጃወቸ እንደሚያሳዩት ከሆነም የኋይትሃውስ ቤተ መንግስት ከፊል ቦታዎች ክፍት ተደርገው ህጻናት እንቁላል እያንከባለሉ እንዲጫወቱ የሚደረግበት አግባብ አለ፡፡ በአሜሪካ ይህ ባህል እንደአውሮፓውያኖቹ ከ1978 አመተ ምህረት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ መቀጠሉ ነው የሚነገረው፡፡ ከተለያዩ ሃገራት የፋሲካ በአል አከባበር የምንረዳው ሁሉም ሃገራት በአሉን ሲያከብሩ ጎረቤት ለጎረቤት ተጠያይቀው በሰላም በፌሽታ በመዋደድ በመቻቻል በይቅር መባባልና በመረዳዳት ነው። በድጋሚ መልካም የፋሲካ በዓል ሚያዚያ 26/2016ዓም
Показати все...
🥰 1
በቀን 18/08/2024 የጨፌ ቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከ6ኛ/7ኛ/8ኛክፍል አንደኛ የወጡ ተማሪዎች በኢትዮጵያአየር መንገድ ያደረጉት ጉብኝት ይህንን ።
Показати все...