EECSF
Відкрити в Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Показати більше508
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
508
❌❌
ውድ ተከታታዮቻችን ዛሬ ትልቅ የኔትዎርክ እና ሌሎችም ችግሮች ምክንያት ሙሉ ፕሮግራማችንን ማድረግ አልቻልንም። በመሆኑም ከነገ ወድያ እሮብ የምናደርግ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር እናሳውቃለን
508
1ኛ ዮሐንስ ምዕ.3 ማጠቃለያ
"Vertical and horizontal Love"
📌 የገባንበትን ፍቅር ስናውቀው እና ስንረዳው ለሌላው ማካፈል እንጀምራለን፣ የተትረፈረፈ ህይወት ይባላል
📌 የአዲስ ኪዳን የሕግ ማጠቃለያ እግዚአብሔርን መውደድ እና ባልንጀራችንን መውደድ ነው
📌 በእግዚአብሄር የተወደድነው ከእርሱ የመወለዳችን እና የእግዚአብሄር ልጆች የመባላችን ምስጢር ነው
📌 የተቀበልነው ፍቅር 👇👇
👉 በትልቁ የተትረፈረፈ ፍቅር ፈሶልናል
👉 ይህም የእግ/ር ልጆች አስብሎናል
👉 እውነተኛ የሆነው የክርስቶስ ህይወት(ከአለም system ተቃራኒ የሆነ)
👉 ይህን ህይወት መኖር ስንጀምር ከአለም መለየታችን በግልፅ መታወቅ ይጀምራል
👉 ይህም በአለማዊያን ዘንድ እንድንጠላ እና እንድንገፋ ሊያደርገን ይችላል
📌ስለ ኃጥያት እናውራ ቁ.(4-10)
👉 ኃጥያትን define ለማድረግ የመጀመሪያው የሰው ልጅ ኃጥያት ምን እንደሆነ መመልከት አለብን
👉 አዳም በእግ/ር ኪዳን ውስጥ ይኖር ነበር። ኪዳኑም በሁሉም ነገር ገዢ እንዲሆን እና በእግ/ር ትዕዛዝ ውስጥ ብቻ እንዲመላለስ ነበር (ዘፍ 2: 16) ።
ክፉውን እና መልካሙን የምትለየው ያች ፍሬ የመቀመጥዋ ትልቁ ምክንያት ፦ ሰው እውነት በእግዚያብሄር ትዕዛዝ ይመላለሳል ወይስ የራሱን ስሜት እና ፈቃድ ይፈፅማል የሚለውን ለመለየት ነው። ሰይጣንም ለመጀመሪያ ጊዜ ሀሳቡን ማስፈፀሚያ እንዲሆን ያን እንሰሳ እባብን ተጠቀመ።
📌 እስኪ እቺን conversation እንያት
👩🦳 አዳም.....አዳም
👱♂ ወዬ እማ
👩🦳 እንካ ሚበላ ነገር? የሚያምር 🍎
👱♂ እሺ እሺ
እሺ??? Seriously???
Atleast መምን እንደሆነ መጠየቅ ነበረበት፤ የእግ/ርን ትዕዛዝ ችላ ብሏል ሰይጣን በድክመቱ ቢጠቀምም
📌 የሀጥያትን ትርጉም ከዚህ እናገኛለን
👉 ከእግዚአብሄር ትዕዛዝ ውጭ የሆነውን ነገር ማድረግ
👉 ከእግ/ር በላይ እራስን መውደድ
👉 ይህ ነው በእግዚያብሄር ላይ ማመፅ የሚባለው
👉 ሀጥያት ፦ የሚለው ቃል በግሪክ "ሃመርሺያ" ማለት ነው ፤ ትርጓሜውም "ኢላማን መሳት" ማለት ነው
📌 እና በአዲስ ኪዳን ሀጥያትና ሀጥያተኛ የሚያደርገው የዲያብሎስን ስራ ለማፍረስ ክርስቶስ ተገልጧል
📌 እኛም በእግዚያብሄር ትዕዛዝ እና በፅድቁ ስንመላለስ ከኢየሱስ ጋርፀእንተባበራለን
📌 ሀጥያትን ማድረግ እግዚአብሔርን ካለማወቅ ጋር ይያያዛል። ስለዚህ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ማወቅ እና ወደ መምሰል ማደግ የህይወታችን ዘይቤ መሆን አለበት
📌 እርስ በእርስ መዋደድ (Horizontal)
👉 ፍቅር ከእግዚአብሔር ነው፤ በፍቅር ውስጥ የሚኖር በእግዚያብሔር ውስጥ እየኖረ ነው
👉 የፍቅርን ትርጉም ያልተረዳ ወይም ምን ያህል እንደተወደደና ይቅር እንደተባለ ያልገባው ሰው Already በጨለማ ውስጥ ነው ፤ መውደድ አይችልምና ይቅር ማለትም አይችልምና
👉 እርሱ ህይወቱን አሳልፎ ሰጥቶአልና፤ የፍቅር ትርጉምም ይህ ነው
👉 ወንድምን መውደድ ማለት ስለወንድምህ ክራስህን አሳልፎ መስጠት ማለት ነው
👉 እራስን በመስጠት ውስጥ ብዙ ነገሮችን እናገኛለን ፦ ገንዘብን፣ እንክብካቤን፣ ገንዘብን....
👉 1ኛ ዮሐንስ 3 (አዲሱ መ.ት)
¹⁴ ወንድሞቻችንን ስለምንወድ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ፍቅር የሌለው ሁሉ በሞት ይኖራል።
…
²³ ትእዛዙም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናምንና እርሱ እንዳዘዘንም እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።
508
🙌 የዛሬ ፕሮግራሞቻችን 🙌
1⃣ የ1ኛ ዮሐንስ መልዕክት ም.3 ማጠቃለያ 📖
2⃣ የዝማሬ ግብዣ ከ @AdadisSongs 🎶
3⃣ ከዚህ ቀደም በዚህ ህብረት የነበሩ ተማሪዎች ከተነሷቸው ምስሎች መካከል የተወሰኑትን 📸
4⃣ የቃለ መጠይቅ እና ልምድ የማካፈል ጊዜ 🎤🤹♂
5⃣ የመፀሀፍ ግብዣ 📚
6⃣ ይመልሱ፣ ይሸለሙ 🗣 💸
#StayHome
#StayTuned
508
🕚🕛 ደቂቃዎች ብቻ ቀሩት!!
🎤🎤ዕለተ ሰኞ በዚህ ሰዓት የሚቀርበው #መልካም ሰኞ ሾው ሊጀምር ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀሩት 👏👏
🏅Package የሚያሸልሙ ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ናቸው
❤️ አስተማሪ,አዝናኝ እንዲሁም አሳታፊ የሆነው ዝግጅታችን ደቂቃዎችን ብቻ ይቆጥራል👏😍😍
🎭 አዘጋጅ እና አቅራቢ አማኑኤል 🎧 ከ ቴክኒሻን ካሌብ ጋር🙈
508
Are you ready for tonight's show😱😱
anonymous poll
Yes – 16
👍👍👍👍👍👍👍 100%
No
▫️ 0%
👥 16 people voted so far.
508
#Chain_prayer(Chain48)_update
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
📌 3ተኛ ሳምንት
ርዕስ - በፍቅር መመላለስ 1 ዮሐ 3፥ 1-24
ቀን 1
📌በምናውቀው የተፈጥሮ ሕግ ሳይሆን በፍቅሩ ልጆቹ ስላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና
📌በአይናችን ከምናየው ልጅነት ይልቅ እውነት የሆነው በማመናችን የሆነው ልጅነት የበለጠ እንዲበራልን ልመና
📌 ለወላጅ የልጁ እርሱን መምሰል እጅግ እንደሚያስደስተው ሁሉ እግዚአብሔር በኛ ልጅነት መልኩን እንዲገልጥ ፀጋ እንዲበዛልን
⭕️ በቃል የሚጠና ጥቅስ፦ ❝የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።❞
—ሮሜ 8: 16
**************************
የሕንፃ ኮሌጅ(EiABC) ወንጌላውያን ክርስቲያን ዎች ተማሪ
2012 ዓ. ም.
Join and share:
@EECSF
