የአገልጋይ ብርሃኑ ገጽ
Відкрити в Telegram
ይህ የአገልጋይ ብርሃኑ ገፅ ነው። 👉መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶች 👉የጽሞና መልእክቶች 👉መዝሙር 👉የጥያቄ መልሶች በዚህ ገጽ ይቀርባሉ። በማንበብና ሼር በማድረግ ከአገልግሎቴ ጎን ይቁሙ።
Показати більше1 529
Підписники
+224 години
Немає даних7 днів
+230 днів
Завантажуємо дані
Схожі канали
Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
жовтень '26жовт '26
жовтень '26
+1 055
в 0 каналах
вересень '260
в 0 каналах
Get PRO
серпень '260
в 0 каналах
Get PRO
липень '260
в 1 каналах
Get PRO
червень '260
в 2 каналах
Get PRO
травень '260
в 0 каналах
Get PRO
квітень '260
в 0 каналах
Get PRO
березень '260
в 1 каналах
Get PRO
лютий '260
в 0 каналах
Get PRO
січень '260
в 0 каналах
Get PRO
грудень '250
в 0 каналах
Get PRO
листопад '250
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '250
в 0 каналах
Get PRO
вересень '250
в 0 каналах
Get PRO
серпень '250
в 0 каналах
Get PRO
липень '250
в 0 каналах
Get PRO
червень '250
в 1 каналах
Get PRO
травень '250
в 0 каналах
Get PRO
квітень '250
в 0 каналах
Get PRO
березень '250
в 0 каналах
Get PRO
лютий '250
в 0 каналах
Get PRO
січень '250
в 0 каналах
Get PRO
грудень '240
в 0 каналах
Get PRO
листопад '240
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '240
в 0 каналах
Get PRO
вересень '24
+14
в 0 каналах
Get PRO
серпень '24
+35
в 0 каналах
Get PRO
липень '24
+9
в 0 каналах
Get PRO
червень '24
+3
в 0 каналах
Get PRO
травень '240
в 0 каналах
Get PRO
квітень '24
+5
в 0 каналах
Get PRO
березень '24
+11
в 0 каналах
Get PRO
лютий '24
+8
в 0 каналах
Get PRO
січень '24
+8
в 0 каналах
Get PRO
грудень '23
+8
в 0 каналах
Get PRO
листопад '23
+6
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '23
+1
в 0 каналах
Get PRO
вересень '23
+4
в 0 каналах
Get PRO
серпень '23
+6
в 0 каналах
Get PRO
липень '23
+2
в 0 каналах
Get PRO
червень '23
+4
в 0 каналах
Get PRO
травень '23
+16
в 0 каналах
Get PRO
квітень '23
+2
в 0 каналах
Get PRO
березень '23
+5
в 0 каналах
Get PRO
лютий '23
+6
в 0 каналах
Get PRO
січень '23
+4
в 0 каналах
Get PRO
грудень '22
+8
в 0 каналах
Get PRO
листопад '22
+3
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '22
+3
в 0 каналах
Get PRO
вересень '22
+2
в 0 каналах
Get PRO
серпень '22
+9
в 0 каналах
Get PRO
липень '22
+3
в 0 каналах
Get PRO
червень '22
+4
в 0 каналах
Get PRO
травень '22
+12
в 0 каналах
Get PRO
квітень '22
+10
в 0 каналах
Get PRO
березень '22
+10
в 0 каналах
Get PRO
лютий '22
+13
в 0 каналах
Get PRO
січень '22
+9
в 0 каналах
Get PRO
грудень '21
+12
в 0 каналах
Get PRO
листопад '21
+14
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '21
+20
в 0 каналах
Get PRO
вересень '21
+23
в 0 каналах
Get PRO
серпень '21
+18
в 0 каналах
Get PRO
липень '21
+10
в 0 каналах
Get PRO
червень '21
+19
в 0 каналах
Get PRO
травень '21
+4
в 0 каналах
Get PRO
квітень '21
+3
в 0 каналах
Get PRO
березень '21
+5
в 0 каналах
Get PRO
лютий '21
+17
в 0 каналах
Get PRO
січень '21
+6
в 0 каналах
Get PRO
грудень '20
+585
в 0 каналах
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 23 жовтня | 0 | |||
| 22 жовтня | +3 | |||
| 21 жовтня | +1 | |||
| 20 жовтня | +2 | |||
| 19 жовтня | 0 | |||
| 18 жовтня | 0 | |||
| 17 жовтня | +1 | |||
| 16 жовтня | +1 | |||
| 15 жовтня | +1 | |||
| 14 жовтня | 0 | |||
| 13 жовтня | 0 | |||
| 12 жовтня | 0 | |||
| 11 жовтня | 0 | |||
| 10 жовтня | +2 |
Дописи каналу
| 2 | If milk gets bad, it becomes yoghurt. Yoghurt is more valuable than milk. If it gets even worse, it turns to cheese. Cheese is more valuable than both yoghurt and milk.
And if grape juice turns sour, it transforms into wine, which is even more expensive than grape juice. You are not bad because you made mistakes. Mistakes are the experiences that make you more valuable as a person.
Christopher Columbus made a navigational error that made him discover America. Alexander Fleming’s mistake led him to invent Penicillin. Don’t let your mistakes get you down.
It is not practice that makes perfect. It is mistakes we learn from that makes perfect !
©Psych master
https://t.me/preac | 147 |
| 3 | ጥቅምት 13
ርዕስ፦ የእግዚአብሔር አብሮነት
የዕለቱ ጥቅስ፦
“እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ። ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።” ዘፍጥረት 39:2-3
የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 39:1-6፤ ኢሳይያስ 41:10፤ ዕብራውያን 13:5-6
ዮሴፍ በባዕድ አገር በግብፅ ውስጥ በነበረበት ወቅት የሚታመነው ዘመድ፣ የሚረዳው ወገን ወይም ከጎኑ የሚቆም “የእኔ” የሚለው አንድም ሰው አልነበረውም። በሰው ዐይን ሲታይ ሙሉ በሙሉ ባዶውን የቀረና ብቸኛ የነበረ ሰው ነው። ነገር ግን የዮሴፍ ትልቁ ስኬት፣ ሀብቱና ዋስትናው ከሰው የተገኘ ሳይኾን የእግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መኾን ነበረ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በመኾኑ ምክንያት ባርነት ሳይገድበው መከናወንን፣ ሞገስንና ታላቅ በረከትን አገኘ። ይልቁንም የእግዚአብሔር አብሮነት በዮሴፍ ሕይወት ላይ ስለተገለጠ፣ በእርሱ ምክንያት የጲጥፋራ ቤትና እርሻ ሳይቀር የእግዚአብሔር በረከት አረፈበት።
ዛሬም በሕይወታችን ውስጥ ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገን የሰዎች ስብስብ፣ የሀብት ብዛት ወይም የዘመድ ድጋፍ ሳይኾን የእግዚአብሔር አብሮነት ነው። ሰው ሊርቀን፣ የጀርባ አጥንት የኾኑን ሰዎች ሊለዩን ወይም በአስቸጋሪና በብቸኝነት ሁኔታዎች ውስጥ ልናልፍ እንችላለን፤ እግዚአብሔር ግን ከእኛ ጋር ከኾነ ጉዟችን ወደ ውድቀት ሳይኾን ወደ ከፍታና ወደ መከናወን ያመራል። የእግዚአብሔር አብሮነት በሕይወታችን ውስጥ ካለ፣ እኛ ብቻ ሳንኾን በዙሪያችን ያሉ ሰዎችና የምንሠራው ሥራ ሁሉ በበረከት ይሞላል። እውነተኛ ስኬት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መኾኑ ነው።
😇 የጥሞና ጥያቄ፦
በሕይወቴ በሚገጥመኝ ፈተናዎችና የብቸኝነት ስሜት ጊዜ በሰው መደገፍን ነው ወይስ የእግዚአብሔርን አብሮነት በመፈለግ ነው የምታመነው? በየዕለት እንቅስቃሴዬ፣ በሥራዬና በትምህርቴ ውስጥ የእግዚአብሔር አብሮነትና ሞገስ እንዲቀድም በመንፈሳዊ ሕይወቴ ለመትጋት ዛሬ ምን እርምጃ ልውሰድ?
🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦
አማኑኤል አምላኬ ኾይ፣ በሕይወቴ ከምንም ነገር በላይ የአንተ አብሮነት ታላቅ ሀብቴና ስኬቴ እንደኾነ አምናለሁ። በባዕድ ምድርና በከባድ ኹኔታዎች ውስጥ እንኳ ሳይቀር አብረኸኝ ስለምትኾን አመሰግንሃለሁ። በምኼድበትና በምሠራው ነገር ኹሉ ያንተ ሞገስና በረከት እንዲከተለኝ፣ በእኔም ምክንያት በዙሪያዬ ያሉ ኹሉ እንዲባረኩ አብሮነትህ አይለየኝ። በኢየሱስ ስም አሜን።
✍ አገልጋይ ብርሃኑ
https://t.me/preac | 188 |
| 4 | የጥቅምት 11 2019 ዓ/ም የረቡዕ አገልግሎት ትውስታዎች፣ ከእናት ቤተክርስቲያን ሳርቤት (3/3) | 183 |
| 5 | ጥቅምት 12
ርዕስ፦ የታማኝነት ዋጋና በረከት
የዕለቱ ጥቅስ፦
“ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ፤ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ።” — ዘፍጥረት 39፥6
የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 39:1-20፤ ምሳሌ 28:20፤ ማቴዎስ 25:21
ዮሴፍ ወደ ግብፅ በባርነት ተሸጦ በወረደበት የጲጥፋራ ቤት ታላቅ የታማኝነት ሕይወት አሳይቷል። በባዕድ አገር፣ ማንም የማያውቀውና ቤተሰቡ በሌሉበት ኹኔታ ውስጥ እንኳ ሳይቀር አምላኩንና ጌታውን በቅንነት አገለገለ። ታማኝነቱን ያየው ጲጥፋራ ከሚበላው እንጀራ በቀር እስካያስብ ድረስ በቤቱና በንብረቱ ኹሉ ላይ ሙሉ ኃላፊነት ሰጥቶ ሾመው። የዮሴፍ ታማኝነት የጸናው በሥራው ላይ ብቻ አልነበረም፤ የጲጥፋራ ሚስት በኃጢአት ልታታልለውና ልታስተው በሞከረች ጊዜ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ይኽን ታላቅ ኃጢአት አደርጋለሁ? በእግዚአብሔርም ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?” በማለት ለጌታውና ለእግዚአብሔር ያለው ታማኝነት የማይናወጥ መኾኑን አሳዬ።
ታማኝነት የእግዚአብሔር ታላቅ ባሕርይ ነው፤ እግዚአብሔር በቃሉና በአሠራሩ ኹሉ የታመነ አምላክ ነው። እኛም የእርሱ ልጆች እንደ መኾናችን መጠን በሥራ ቦታችን፣ በቤታችን፣ በትዳራችንና በምናቀርበው አገልግሎት ኹሉ ታማኞች ልንኾን ይገባል። ታማኝነት አጭር መንገድ ወይም ጊዜያዊ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የሚተውት ሳይኾን፣ የክርስቲያናዊ ሕይወታችን መለያ ሊኾን የሚገባው የጽድቅ ፍሬ ነው። በሰው ዘንድ ለመወደድ ብለን ሳይኾን፣ ማንም በማያየን ስውር ቦታ እንኳ ሳይቀር በቅንነትና በታማኝነት ስንመላለስ እግዚአብሔር ያየናል፤ የታመነ ሰውንም በጊዜው ያከብረዋል፣ ዋጋውንም ይከፍለዋል። ታማኝ እንኹን።
😇 የጥሞና ጥያቄ፦
በሥራዬ፣ በአገልግሎቴ ወይም በግል ሕይወቴ ማንም በማያያየኝ ቦታ ላይ እንኳ ለቃሌና ለኃላፊነቴ ታማኝ ነኝን? የዮሴፍን ዓይነት የታማኝነት ሕይወት በመከተል፣ በሥራ ቦታዬና በየዕለት እንቅስቃሴዬ ኹሉ የእግዚአብሔርን ስም የሚያስከብር ታማኝነትን ለማሳየት ዛሬ ለመወሰን ምን ያኽል ቁርጠኛ ነኝ?
🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦
ታማኝና ጻድቅ አምላኬ ኾይ፣ በሕይወቴና በአገልግሎቴ ኹሉ እንደ አንተ ታማኝ ሆኜ እንድመላለስ እርዳኝ። ሰው ቢያየኝም ባያየኝም፣ በማንኛውም ኹኔታ ውስጥ ለአንተና ለቃልህ ታማኝ እንድኾን የልብ ቅንነትንና መንፈሳዊ ጥንካሬን ስጠኝ። በትንሹና በትልቁ የታመነ አገልጋይ አድርገህ እንድታቆመኝ በኢየሱስ ስም እለምንኻለሁ። አሜን።
✍ አገልጋይ ብርሃኑ
https://t.me/preac | 231 |
| 6 | 🔥 መንፈሳዊ ዕድገት 🔥
የትምህርት እና የአምልኮ ጊዜ
📆 ዘወትር ረቡዕ፣ 12:00 ሰአት
📍ዘጸአት እናት ቤተክርስቲያን፣ ሳርቤት
ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!! 🙏 | 185 |
| 7 | 🔥 መንፈሳዊ ዕድገት 🔥
የትምህርት እና የአምልኮ ጊዜ
📆 ጥቅምት 11፣ 2019 ዓ/ም 12:00
📍ዘጸአት እናት ቤተክርስቲያን፣ ሳርቤት
ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!! 🙏 | 174 |
| 8 | ጥቅምት 11
ርዕስ፦ ኹሉም ነገር ለበጎ ነው
የዕለቱ ጥቅስ፦
“እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” — ሮሜ 8:28
የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 45:1-8፤ ዘፍጥረት 50:15-21
የዮሴፍ ሕይወት እግዚአብሔር የመከራን ሰንሰለት ወደ በረከት ድልድይ እንዴት እንደሚለውጠው የሚያሳይ ድንቅ ማሳያ ነው። በዮሴፍ ሕይወት የኾነውና የተከሰተው ነገር ኹሉ አንዱ ከአንዱ ጋር ተያይዞ ለታላቅ በጎ ነገር የተደረገ ነበር። ወንድሞቹ በቅናት ባይሸጡት ኖሮ፣ ግብፅ አይወርድም ነበር፤ ግብፅ ባይወርድ ኖሮ፣ የጲጥፋራ ቤት አይገባም ነበር፤ የጲጥፋራ ቤት ባይገባ ኖሮ፣ የጲጥፋራ ሚስት በሐሰት አታስወንጅለውምና አይታሰርም ነበር፤ ባይታሰር ደግሞ የንጉሡን ጠጅ አሳላፊ በእስር ቤት አያገኘውም ነበር፤ ጠጅ አሳላፊው ባይናገርለትና ባያስታውሰው ደግሞ፣ በፈርዖን ፊት ቀርቦ ሕልሙን አይፈታም፣ ለግብፅም ንጉሥ አይኾንም ነበር። ዮሴፍ ባይነግሥና ባይሾም ኖሮ ደግሞ፣ ቤተሰቡንና መላውን ዓለም ከረሃብ አያድንም ነበር!
ሰው ክፉ አሰብኩ ብሎ ሲነሣ፣ እግዚአብሔር ግን ያንን ክፉ ዐሳብ ወደ ታላቅ መልካምነት ይለውጠዋል። ዮሴፍ በኋላ ላይ ለወንድሞቹ “እናንተ ለክፉ አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን... ለበጎ አሰበው” እንዳላቸው፣ በእኛም ሕይወት የሚገጥሙን አላስፈላጊ የሚመስሉ መከራዎች፣ ውድቀቶችና ግፎች ኹሉ በስተጀርባ እግዚአብሔር የሚሠራው ትልቅ መልካም ዓላማ አለ። ዛሬ በሕይወታችሁ የምታልፉበት ፈተና፣ እንግልትና ፍትሕ ማጣት መጨረሻችሁ አይደለም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር ወዳዘጋጀላችሁ የከፍታ ቦታና የበረከት ምዕራፍ የሚያደርሳችሁ የስውር እጁ መንገድ ነው።
😇 የጥሞና ጥያቄ፦
አሁን በሕይወቴ ከባድና አላስፈላጊ ይመስል የሚያስጨንቀኝን ፈተና በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድና እቅድ ስር አድርጌ ለማየት ዝግጁ ነኝን? እግዚአብሔር የመከራዬን ሰንሰለት ተጠቅሞ ለታላቅ መልካምነት እንደሚያበቃኝ አምኜ፣ በማልፍበት ኹኔታ ኹሉ አምላኬን ለማመስገንና በጸጥታ ለመጠበቅ ዛሬ ምን ላደርገው የሚገባኝ ነገር ምንድን ነው?
🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦
ነገርን ኹሉ ለበጎ የምትለውጥ ታማኝ አምላኬ ኾይ፣ በሕይወቴ የሚገጥሙኝን ፈተናዎችና መከራዎች ኹሉ ለበረከቴና ለከፍታዬ መንገድ የምታደርግ አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ። ባልረዳውና መስመሩ ባይገባኝ እንኳ የስውር እጅህን አሠራር አምኜ እንድጸና እምነትንና ትዕግሥትን ስጠኝ። በሕይወቴ ያለው ነገር ኹሉ ለስምህ ክብርና ለሕይወቴ በጎነት እንዲኾን አምናለሁ። በኢየሱስ ስም አሜን።
✍ አገልጋይ ብርሃኑ
https://t.me/preac | 230 |
| 9 | Dear………………
One day you will be living the life, you prayed for. | 226 |
| 10 | ዛሬ በነበረን የቆሮንቶስ መልእክት ጥናት መግቢያውን በተወሰነ መልኩ ለማየት ሞክረናል።
አንደኛ ቆሮንቶስ ሰፊ ይዘት ካላቸው የጳውሎስ ሦስት መልእክታት አንዱ ነው። የተቀሩት ኹለቱ መልእክታት ሮሜና 2ኛ ቆሮንቶስ ናቸው።
አንደኛ ቆሮንቶስ በይዘቱ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ተግባራዊ መመሪያን የያዘ መጽሐፍ ነው። የኤፌሶን መልእክት ዓለም አቀፋዊቷን ቤተክርስቲያን ሲያብራራ፣ አንደኛ ቆሮንቶስ ደግሞ አጥቢያዊ መልኳን ያሳያል። በዓለም አቀፏ ቤተክርስቲያንና በአጥቢያ ቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ልዩነትና አንድነት በዛሬው ጥናታችን ተመልክተናል።
በተጨማሪም በዛሬው ጥናታችን፦
👉 አንዲትን ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የሚያስብሏት መለያ ነጥቦች ምንድን ናቸው?
👉 የጸጋ ስጦታዎች ስለተገለጡብን በጌታ ፊት ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ መኾናችንን ያሳያል ወይ?
👉 እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የየራሱ ፈተናና ተግዳሮት የሚገጥምበት ምክንያቱ
👉 ግጭቶች ሲፈጠሩ በምን መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ እንደሚያስተምር ስለ ቆሮንቶስ መልእክት በጥቂቱ ዐይተናል።
ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደን ያየነው ስለ ቆሮንቶስ ከተማ ባህል፣ ሃይማኖት፣ ፍልስፍና፣ ማኅበራዊ ሕይወት፣ ሴቶች፣ ኗሪዎች ወዘተ በተመለከተ ነው።
ነገም መግቢያችን ይቀጥላል
ጌታ ቢፈቅድ ነገ ጠዋት 12:30 በቲክቶክ Berhanu Jesus ብላቹህ ፈልጋቹ ብትመጡና ብትቀላቀሉን ትጠቀማላችሁ።
መልካም ጊዜ!
https://t.me/preac | 246 |
| 11 | ጥቅምት 10
ርዕስ፦ የጸጥታና የማስተዋል ሕይወት
የዕለቱ ጥቅስ፦
“ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እነርሱም እንደ ገና በብዙ ጠሉት።” — ዘፍጥረት 37፥5
የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 37:5-24፤ ምሳሌ 11:13፤ ምሳሌ 13:3
ዮሴፍ ከእግዚአብሔር የከፍታና የታላቅነትን ራዕይ በሕልም አየ። ነገር ግን በወጣትነት ቅንነቱና ባለማስተዋሉ ሕልሙንና የምኞቱን ከፍታ ለቤተሰቡና ለወንድሞቹ አካፈለ። ይኽንን የከፍታ ሕልም የሰሙት ወንድሞቹ በቅናት ተቃጠሉ፤ ይልቁንም “በእውነት በእኛ ላይ ልትነግሥብን ነውን?” በማለት አብዝተው ጠሉት። ይኽ ቅናት አድጎም ለሞት እስከ ማጨት፣ ውሃ በሌለው ባዶ ጉድጓድ ውስጥ እስከ መጣልና መጨረሻም ለአስማኤላውያን ነጋዴዎች በባርነት እስከ መሸጥ አደረሰው። ዮሴፍ ሕልሙን በጸጥታ ይዞት ቢኾን ኖሮ፣ ያንን ኹሉ የመከራና የእንግልት መንገድ ባልተጓዘ ነበር።
ይኽ የታሪክ ክፍል በሕይወታችን ውስጥ በጸጥታና በማስተዋል የመኖርን ታላቅ ጥበብ ያሳየናል። እግዚአብሔር በሕይወታችን የሰጠንን ራዕይ፣ የሥራ አቅድ፣ ወይም የመጪው ዘመን ስኬት ለምናገኘው ሰው ኹሉ ማውራት አይገባንም። ኹሉም ሰው በአንተ ስኬትና ዕድገት ደስተኛ አይኾንም፤ አንዳንዶች በቅናትና በተንኮል ተነሥተው ራዕይህን ለማክሸፍና መንገድህን ለማደናቀፍ ይሞክራሉ። ጥበበኛ ሰው የሚሠራውን ሥራ፣ የምኞቱን ከፍታና የእግዚአብሔርን ተስፋ በልቡ ይዞ በጸጥታ ይተጋል። ስኬትህና ፍሬህ ራሱ ጮክ ብሎ እንዲናገር እንጂ፣ አስቀድመህ የምታወራው ወሬ ጠላትን አብዝቶ ለፈተና ያጋልጥሃል።
😇 የጥሞና ጥያቄ፦
በሕይወቴ፣ በሥራዬ ወይም በምስጢራዊ እቅዴ ላይ ያለ ማስተዋል አስቀድሜ ለሰዎች በመናገሬ ምክንያት የገጠመኝ ፈተና ወይም እንቅፋት ነበርን? እግዚአብሔር የሰጠኝን ራዕይና እቅድ በጸጥታ፣ በጥበብና በማስተዋል ይዤ በሥራ ላይ ብቻ ለመትጋት ዛሬ ምን ላድርግ?
🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦
በጥበብና በማስተዋል የምትመራኝ አምላኬ ኾይ፣ አንተ በልቤ ያስቀመጥከውን ራዕይና ተስፋ በጥበብ እንድይዝ የማስተዋልን መንፈስ ስጠኝ። አንደበቴን እንድገታ፣ አቅዴንና ሥራዬን በጸጥታና በትጋት እንድከውን እርዳኝ። ከሰው ቅናትና አላስፈላጊ ጠብ እንድጠበቅ፣ ውጤቴና ፍሬዬ ለስምህ ክብር እንዲበቃ ጥበቃህ አይለየኝ። በኢየሱስ ስም አሜን።
✍ አገልጋይ ብርሃኑ
https://t.me/preac | 244 |
| 12 | ሰላም ቅዱሳን
ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር
ከነገ ጀምሮ አንደኛ ቆሮንቶስን መጽሐፍ ማጥናት ልንጀምር ነው።
በምን፦ በቲክቶክ Live
ሰዓት፦ ጠዋት 12:30-2:00
ርዕስ፦ 1ኛ ቆሮንቶስ፦ «የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተግባራዊ መመሪያ»
if U are interested pls join us
https://www.tiktok.com/@berhanu_jesus1?_r=1&_t=ZS-9AgWAD0dRXY | 251 |
| 13 | Be kind.
Every person survives and struggles something they never speak about. | 234 |
| 14 | ጥቅምት 9
ርዕስ፦ የተሳሳተ የልጅ አስተዳደግ
የዕለቱ ጥቅስ፦
“እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ኹሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፤ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት። ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ኹሉ ይልቅ እንዲወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም።” ዘፍጥረት 37:3-4
የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 37:1-11፤ ኤፌሶን 6:4
ያዕቆብ በራሱ ያደገበት ቤተሰብ ውስጥ የአድልዎና የልዩነት ፍቅር ያስከተለውን መራራ ፍሬ (በእርሱና በወንድሙ በዔሳው መካከል የኾነውን ጥላቻ) በሚገባ ያውቃል፤ ነገር ግን በሚያሳዝን ኹኔታ ከወላጆቹ ስሕተት ሳይማር ቀረ። ያዕቆብ በሽምግልናው ዘመን የወለደውን ዮሴፍን ከሌሎች ልጆቹ አብልጦ በመውደድና የተለየ የኅብረ ቀለም ልብስ በማልበስ የወላጅነት አድልዎ ፈጸመ። ይኽ የተለየ ፍቅር በወንድማማቾች መካከል ጽኑ ቅናትንና ጥላቻን ዘራ፤ መጨረሻውም ወንድማማቾቹ ዮሴፍን እስከ መሸጥና አባታቸውን በሐዘን እስከ መስበር ያደረሰ አደጋን አስከተለ።
ይኽ ታሪክ ዛሬ ለወላጆችና ወደፊት ወላጅ ለመኾን ለሚዘጋጁ ኹሉ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው፤ በልጆች መካከል የሚደረግ ልዩነት፣ አድልዎና የተለየ ትኩረት በወንድማማቾች መካከል የቅናትና የጠብ ዘርን ይዘራል። ሳናስተውለው የወላጆቻችንን የአስተዳደግ ስሕተት ልንደግም ስለምንችል፣ በንቃትና በማስተዋል ኾነን ልንጠነቀቅ ይገባል። እያንዳንዱ ልጅ በባህሪው፣ በስጦታውና በዕድሜው የተለያየ ቢኾንም፣ የእኛ ፍቅር፣ ትኩረትና እንክብካቤ ግን ለኹሉም በእኩልነት ሊደርስ ይገባል። ልጆችን በእኩል ፍቅር፣ በፍጹም ቅንነትና በአንድነት መንፈስ ማሳደግ በቤታችን ውስጥ ሰላምንና እውነተኛ ወንድማማችነትን ይገነባል።
😇 የጥሞና ጥያቄ፦
በቤተሰቤ ወይም ባለኝ ኃላፊነት ውስጥ ሳላስበው የአድልዎና የልዩነት ስሜት የማሳይበት ኹኔታ አለ? ከቀደሙ ስሕተቶች በመማር፣ ልጆችንና በሥራዬ ያሉትን ኹሉ በእኩል ፍቅርና ትኩረት ለማስተናገድና በቤቴ የሰላም አየር እንዲነግሥ ለማድረግ ዛሬ ምን ላደርግ ይገባኛል?
🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦
ቅዱስና ጻድቅ አምላኬ ኾይ፣ በቤቴና በቤተሰቤ ውስጥ ያለ ምንም አድልዎ በፍቅርና በእኩልነት እንድመራ የመንፈስ ቅዱስን ጥበብና አስተዋይነት ስጠኝ። የቀደሙ ስህተቶችን ሳልደግም ልጆቼንና በዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ በእኩል ፍቅርና ትኩረት እንድከባከብ እርዳኝ። በቤታችን ውስጥ የወንድማማችነት ፍቅርና ሰላም እንዲበዛ አቅም ኹነኝ። በኢየሱስ ስም አሜን።
✍ አገልጋይ ብርሃኑ
https://t.me/preac | 297 |
| 15 | “…ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ ልውደቅ
በሰው እጅ ግን አልውደቅ…።”
— 1 ዜና 21፥13 | 272 |
| 16 | ጥቅምት 8
ርዕስ፦ የፍቅር ኀይል
የዕለቱ ጥቅስ፦
“ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ኾነለት።”— ዘፍጥረት 29፥20
የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 29:15-30፤ 1 ዮሐንስ 5:1-3፤ ማቴዎስ 22:36-40
ያዕቆብ የሚወዳታን ራሔል ለማግባት ሲል ለላባ ለ14 ዓመታት በጽኑ ድካምና በባርነት ተገዛ። በዚያ ዘመን ያሳለፈው የፀሐይ ሐሩርና የሌሊት ቁር እጅግ ከባድ ቢኾንም፣ ስለ ፍቅሯ ሲል ያ ኹሉ ረጅም ዘመን በርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ኾነለት፤ ጊዜውም እንዴት እንደ ነጎደ አልታወቀውም። ፍቅር ኃያል ነው! ድካምን ወደ ደስታ፣ ረጅሙን ዘመን ደግሞ ወደ ጥቂት ቅፅበት የመለወጥ ታላቅ ጉልበት አለው። ያዕቆብን ያንን ኹሉ ዋጋ ያስከፈለው የሕግ ግዴታ ሳይኾን፣ በልቡ ውስጥ የነበረው ጥልቅ ፍቅር ነበረ።
ይኽ የታሪክ ክፍል አምላካችን እግዚአብሔርን የመታዘዝን ታላቅ ምስጢር ያበራልናል። ጌታ ኢየሱስ “ትልቁና ፊተኛው ትእዛዝ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ዐሳብህም ውደድ የሚለው ነው” ብሎ እንደ አስተማረን፣ የእኛም መንፈሳዊ ሕይወት መሠረት ፍቅር ነው። እግዚአብሔርን በእውነት ስንወደው፣ ለእርሱ መገዛትና ትእዛዙን መጠበቅ ከባድ ሸክም አይኾንብንም፤ ይልቁንም በደስታና በፍላጎት የምናደርገው የፍቅር አገልግሎት ይኾናል። ሐዋርያው ዮሐንስ “ትእዛዛቱም ከባድ አይደሉም” ያለው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ፍቅር ሲኖር መታዘዝ ሸክም ሳይኾን ደስታ ይኾናል። ቀጥሎም ባልንጀራችንን እንደ ነፍሳችን እንድንወድ የተሰጠን ትእዛዝ፣ ይኽ የፍቅር ኀይል በሰዎች መካከልም ድል አድራጊና አሸናፊ መኾኑን ያሳየናል።
😇 የጥሞና ጥያቄ፦
የእግዚአብሔርን ቃል ለመጠበቅና ለእርሱ ለመታዘዝ የማደርገው ጥረት በግዴታና በሕግ ስሜት ነው ወይስ በልቤ ውስጥ ባለው በፍጹም ፍቅር? የፍቅርን አሸናፊነትና ኀያልነት በመረዳት፣ ለአምላኬና በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች በፍቅር የተሞላ ታዛዥነትንና አገልግሎትን ለመስጠት ዛሬ ምን ላድርግ?
🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦
ፍቅር የኾነከው ቅዱስ አምላኬ ኾይ፣ ለአንተ ያለኝ ፍቅር በልቤ ውስጥ እንዲበዛና እንዲያድግ የመንፈስ ቅዱስን ቅባት ስጠኝ። ትእዛዛትህን መጠበቅና ለአንተ መገዛት በደስታና በፍቅር የተሞላ እንጂ ከባድ ሸክም እንዳይኾንብኝ ልቤን አድስ። ባልንጀራዬንም እንደ ነፍሴ እንድወድና በሕይወቴ ኹሉ የፍቅርህ አሸናፊነት እንዲገለጥ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም አሜን።
✍ አገልጋይ ብርሃኑ
https://t.me/preac | 348 |
| 17 | Немає тексту... | 291 |
| 18 | Немає тексту... | 369 |
| 19 | Never stop learning, because
Life never stop teaching. | 266 |
| 20 | ጥቅምት 7
ርዕስ፦ የእምነት ጽናትና የበረከት ትግል
የዕለቱ ጥቅስ፦
“እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው።”— ዘፍጥረት 32፥26
የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 32:22-30፤ ሆሴዕ 12:3-4
ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው ጋር ሊገናኝ ሲቃረብ ፍርሃትና ጭንቀት ከብቦት ነበር። በያቦቅ ማዶ ቤተሰቡንና ንብረቱን ካሻገረ በኋላ በዚያች ሌሊት ብቻውን ቀረ። በዚያም ሌሊት አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ከእርሱ ጋር ሲታገል አደረ። ያዕቆብ ከማን ጋር እንደሚታገል ባወቀ ጊዜ፣ ሊለቀው አልፈለገም። የጭኑን ሹልዳ ነክቶት አቅሙ ቢደክምም፣ ርሱን አጥብቆ በመያዝ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም!” ሲል የጽናትና የእምነት ድምፁን አሰማ። እግዚአብሔርም ይህንን የያዕቆብን አጥብቆ መፈለግና የእምነት ጥረት አይቶ ባረከው፤ ስሙንም ወደ “እስራኤል” ለወጠው።
ይኽ የታሪክ ክፍል እግዚአብሔርን አጥብቆ የመፈለግና በጸሎት የመጽናት ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል። “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” ማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ በግድ የመጫን እልህ ሳይኾን፣ ያለ ርሱ በረከትና አብሮነት ሕይወት ትርጉም እንደሌለው መረዳት ነው። ዛሬ በሕይወታችን ፈተናና ጭንቅ ሲበዛብን፣ ተስፋ ቆርጠን እጃችንን መስጠት የለብንም። ይልቁንም በጸሎታችንና በእምነታችን እግዚአብሔርን አጥብቀን ልንይዘው፣ በጸጋው ዙፋን ፊትም በትግዕሥት ልንቆይ ይገባል። እግዚአብሔር በጽናትና በረሃብ ወደ እርሱ የሚመጡትን፣ በረከቱን ሳይሰጣቸው ባዶአቸውን አይመልሳቸውም።
😇 የጥሞና ጥያቄ፦
በሕይወቴ ውስጥ በጸሎት አጥብቄ እግዚአብሔርን ልይዝበትና የበረከቱ ፍጻሜ እስኪመጣ ልጸናበት የሚገባ ነገር አለ? በፈተናና በጭንቅ ጊዜ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ፣ በጽናትና በእምነት በእግዚአብሔር ፊት ለመቆየትና “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” በሚል መንፈስ ለመጸለይ ያለኝ ቁርጠኝነት ምን ይመስላል?
🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦
በረከቴና ሕይወቴ የኾንክ ቅዱስ አምላኬ ኾይ፣ ያለ አንተ አብሮነትና በረከት ምንም ማድረግ እንደማልችል አምናለሁ። በሕይወቴ በሚገጥሙኝ የጭንቅና የፈተና ሌሊቶች ውስጥ ተስፋ ሳልቆርጥ በጸሎት አጥብቄ እንድይዝህ የጽናት መንፈስ ስጠኝ። ባዶዬን እንዳልመለስ በጸጋህና በበረከትህ ጎብኘኝ። በኢየሱስ ስም አሜን።
✍ አገልጋይ ብርሃኑ
https://t.me/preac | 329 |
