en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

የአገልጋይ ብርሃኑ ገጽ

የአገልጋይ ብርሃኑ ገጽ

Open in Telegram

ይህ የአገልጋይ ብርሃኑ ገፅ ነው። 👉መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶች 👉የጽሞና መልእክቶች 👉መዝሙር 👉የጥያቄ መልሶች በዚህ ገጽ ይቀርባሉ። በማንበብና ሼር በማድረግ ከአገልግሎቴ ጎን ይቁሙ።

Show more
1 529
Subscribers
-224 hours
-27 days
No data30 days

Loading data

Attracting Subscribers
Oct '26
October '26
+1 055
in 0 channels
September '260
in 0 channels
Get PRO
August '260
in 0 channels
Get PRO
July '260
in 1 channels
Get PRO
June '260
in 2 channels
Get PRO
May '260
in 0 channels
Get PRO
April '260
in 0 channels
Get PRO
March '260
in 1 channels
Get PRO
February '260
in 0 channels
Get PRO
January '260
in 0 channels
Get PRO
December '250
in 0 channels
Get PRO
November '250
in 0 channels
Get PRO
October '250
in 0 channels
Get PRO
September '250
in 0 channels
Get PRO
August '250
in 0 channels
Get PRO
July '250
in 0 channels
Get PRO
June '250
in 1 channels
Get PRO
May '250
in 0 channels
Get PRO
April '250
in 0 channels
Get PRO
March '250
in 0 channels
Get PRO
February '250
in 0 channels
Get PRO
January '250
in 0 channels
Get PRO
December '240
in 0 channels
Get PRO
November '240
in 0 channels
Get PRO
October '240
in 0 channels
Get PRO
September '24
+14
in 0 channels
Get PRO
August '24
+35
in 0 channels
Get PRO
July '24
+9
in 0 channels
Get PRO
June '24
+3
in 0 channels
Get PRO
May '240
in 0 channels
Get PRO
April '24
+5
in 0 channels
Get PRO
March '24
+11
in 0 channels
Get PRO
February '24
+8
in 0 channels
Get PRO
January '24
+8
in 0 channels
Get PRO
December '23
+8
in 0 channels
Get PRO
November '23
+6
in 0 channels
Get PRO
October '23
+1
in 0 channels
Get PRO
September '23
+4
in 0 channels
Get PRO
August '23
+6
in 0 channels
Get PRO
July '23
+2
in 0 channels
Get PRO
June '23
+4
in 0 channels
Get PRO
May '23
+16
in 0 channels
Get PRO
April '23
+2
in 0 channels
Get PRO
March '23
+5
in 0 channels
Get PRO
February '23
+6
in 0 channels
Get PRO
January '23
+4
in 0 channels
Get PRO
December '22
+8
in 0 channels
Get PRO
November '22
+3
in 0 channels
Get PRO
October '22
+3
in 0 channels
Get PRO
September '22
+2
in 0 channels
Get PRO
August '22
+9
in 0 channels
Get PRO
July '22
+3
in 0 channels
Get PRO
June '22
+4
in 0 channels
Get PRO
May '22
+12
in 0 channels
Get PRO
April '22
+10
in 0 channels
Get PRO
March '22
+10
in 0 channels
Get PRO
February '22
+13
in 0 channels
Get PRO
January '22
+9
in 0 channels
Get PRO
December '21
+12
in 0 channels
Get PRO
November '21
+14
in 0 channels
Get PRO
October '21
+20
in 0 channels
Get PRO
September '21
+23
in 0 channels
Get PRO
August '21
+18
in 0 channels
Get PRO
July '21
+10
in 0 channels
Get PRO
June '21
+19
in 0 channels
Get PRO
May '21
+4
in 0 channels
Get PRO
April '21
+3
in 0 channels
Get PRO
March '21
+5
in 0 channels
Get PRO
February '21
+17
in 0 channels
Get PRO
January '21
+6
in 0 channels
Get PRO
December '20
+585
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
24 October0
23 October0
22 October+3
21 October+1
20 October+2
19 October0
18 October0
17 October+1
16 October+1
15 October+1
14 October0
13 October0
12 October0
11 October0
10 October+2
Channel Posts
በሰዎችስ ፊት ልክ ነኝ ሰው እንደሚያይ በማታየው ጌታዬ ኾይ እባክህ በአንተ ፊት ልክ ልኹን🙏😇

2
ጥቅምት 14 ርዕስ፦ ከቅናት አደገኛነት ራስን መጠበቅ የዕለቱ ጥቅስ፦ “ቍጣ ምሕረት የሌለው ነው፥ መዓትም እንደ ጎርፍ ነው፤ በቅንዓት ፊት ግን ማን ይቆማል?”— ምሳሌ 27፥4 የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 37:11-20፤ 1 ሳሙኤል 18:6-11፤ ያዕቆብ 3:14-16 የዮሴፍ ወንድሞች በዮሴፍ የከፍታ ሕልምና አባቱ በሰጠው የተለየ ፍቅር በመቅናት በልባቸው ውስጥ አደገኛን ጥላቻ አሳደጉ። ቅናት የሰውን ልጅ አእምሮ የሚጋርድና እስከ መግደል የሚያደርስ አጥፊ ስሜት ነው። የዮሴፍ ወንድሞች አስቀድመው ያሰቡት የገዛ ወንድማቸውን መግደል ነበር፤ በኋላም ሐሳባቸውን ቀይረው በባርነት ሸጡት። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደሚያሳየን፣ ቅናት በገባበት ስፍራ ኹሉ ጥፋትና ሞት አለ። ንጉሡ ሳኦል በዳዊት ስኬትና ሞገስ በመቅናቱ ምክንያት ሊገድለው ረጅም ዘመን አሳደደው፤ የሃይማኖት መምህራንም በኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራትና ተቀባይነት ማግኘት በመቅናታቸው በሐሰት ከስሰው ለሞት አሳልፈው ሰጡት። ጠቢቡ ሰሎሞን “በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?” ብሎ እንደጻፈው፣ ቅናት በሰው ልብ ውስጥ ሥር ከሰደደ መልካሙን ነገር ኹሉ ያጠፋል። በሌሎች ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ከፍታ፣ በረከትና ስኬት ልንቀና አይገባም። ቅናት የእግዚአብሔርን ስጦታና አሠራር ከመቃወም የሚመጣ የመንፈስ ድካም ነው። ይልቁንም የሌሎች ከፍታ ሲመጣ አብሮ ደስ ሊለንና ጌታን ልናመሰግን ይገባል። በሌሎች ከመቅናት መንፈስ ራሳችንን ከመጠበቃችንም በላይ፣ በቅናት ከሚነሱና በጎነታችንን ከሚያጠፉ ሰዎች ጋር በምናደርገው ግንኙነት ኹሉ ጥበበኞችና በጥንቃቄ የምንመላለስ ልንኾን ይገባል። 😇 የጥሞና ጥያቄ፦ የሌሎችን ሰዎች ስኬት፣ እድገት ወይም በረከት ሳይ በልቤ ውስጥ የሚፈጠረው ስሜት የደስታ ነው ወይስ የቅናት? ልቤን ከቅናት መንፈስ በማንጻት የሌሎችን ከፍታ በፍቅር ለመደገፍና ራሴንም ከቅናት አደጋ በጥበብ ለመጠበቅ ዛሬ ምን ላደርግ ይገባኛል? 🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦ ቅዱስ አምላኬ ኾይ፣ ልቤን ከቅናት፣ ከጥላቻና ከምቀኝነት መንፈስ ኹሉ አጥራልኝ። በወንድሞቼና በእኅቶቼ ከፍታና በረከት ደስ የሚለው ሰፊና ፍቅራዊ ልብ ስጠኝ። ራሴን በሌሎች ከመቅናት እንድጠብቅ፣ እንዲሁም በቅናት ከሚነሱብኝ ፈተናዎች ኹሉ በክንፎችህ ጥላ ሥር እንድትሸፍነኝ በኢየሱስ ስም እለምንኻለሁ። አሜን። ✍ አገልጋይ ብርሃኑ https://t.me/preac
149
3
አቤቱ ጌታዬ😔 ሲደክመኝ እንዳላቋርጥ አርፎ መቀጠልን አስተምረኝ🙏
168
4
If milk gets bad, it becomes yoghurt. Yoghurt is more valuable than milk. If it gets even worse, it turns to cheese. Cheese is more valuable than both yoghurt and milk. And if grape juice turns sour, it transforms into wine, which is even more expensive than grape juice. You are not bad because you made mistakes. Mistakes are the experiences that make you more valuable as a person. Christopher Columbus made a navigational error that made him discover America. Alexander Fleming’s mistake led him to invent Penicillin. Don’t let your mistakes get you down. It is not practice that makes perfect. It is mistakes we learn from that makes perfect ! ©Psych master https://t.me/preac
210
5
ጥቅምት 13 ርዕስ፦ የእግዚአብሔር አብሮነት የዕለቱ ጥቅስ፦ “እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ። ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።” ዘፍጥረት 39:2-3 የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 39:1-6፤ ኢሳይያስ 41:10፤ ዕብራውያን 13:5-6 ዮሴፍ በባዕድ አገር በግብፅ ውስጥ በነበረበት ወቅት የሚታመነው ዘመድ፣ የሚረዳው ወገን ወይም ከጎኑ የሚቆም “የእኔ” የሚለው አንድም ሰው አልነበረውም። በሰው ዐይን ሲታይ ሙሉ በሙሉ ባዶውን የቀረና ብቸኛ የነበረ ሰው ነው። ነገር ግን የዮሴፍ ትልቁ ስኬት፣ ሀብቱና ዋስትናው ከሰው የተገኘ ሳይኾን የእግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መኾን ነበረ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በመኾኑ ምክንያት ባርነት ሳይገድበው መከናወንን፣ ሞገስንና ታላቅ በረከትን አገኘ። ይልቁንም የእግዚአብሔር አብሮነት በዮሴፍ ሕይወት ላይ ስለተገለጠ፣ በእርሱ ምክንያት የጲጥፋራ ቤትና እርሻ ሳይቀር የእግዚአብሔር በረከት አረፈበት። ዛሬም በሕይወታችን ውስጥ ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገን የሰዎች ስብስብ፣ የሀብት ብዛት ወይም የዘመድ ድጋፍ ሳይኾን የእግዚአብሔር አብሮነት ነው። ሰው ሊርቀን፣ የጀርባ አጥንት የኾኑን ሰዎች ሊለዩን ወይም በአስቸጋሪና በብቸኝነት ሁኔታዎች ውስጥ ልናልፍ እንችላለን፤ እግዚአብሔር ግን ከእኛ ጋር ከኾነ ጉዟችን ወደ ውድቀት ሳይኾን ወደ ከፍታና ወደ መከናወን ያመራል። የእግዚአብሔር አብሮነት በሕይወታችን ውስጥ ካለ፣ እኛ ብቻ ሳንኾን በዙሪያችን ያሉ ሰዎችና የምንሠራው ሥራ ሁሉ በበረከት ይሞላል። እውነተኛ ስኬት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መኾኑ ነው። 😇 የጥሞና ጥያቄ፦ በሕይወቴ በሚገጥመኝ ፈተናዎችና የብቸኝነት ስሜት ጊዜ በሰው መደገፍን ነው ወይስ የእግዚአብሔርን አብሮነት በመፈለግ ነው የምታመነው? በየዕለት እንቅስቃሴዬ፣ በሥራዬና በትምህርቴ ውስጥ የእግዚአብሔር አብሮነትና ሞገስ እንዲቀድም በመንፈሳዊ ሕይወቴ ለመትጋት ዛሬ ምን እርምጃ ልውሰድ? 🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦ አማኑኤል አምላኬ ኾይ፣ በሕይወቴ ከምንም ነገር በላይ የአንተ አብሮነት ታላቅ ሀብቴና ስኬቴ እንደኾነ አምናለሁ። በባዕድ ምድርና በከባድ ኹኔታዎች ውስጥ እንኳ ሳይቀር አብረኸኝ ስለምትኾን አመሰግንሃለሁ። በምኼድበትና በምሠራው ነገር ኹሉ ያንተ ሞገስና በረከት እንዲከተለኝ፣ በእኔም ምክንያት በዙሪያዬ ያሉ ኹሉ እንዲባረኩ አብሮነትህ አይለየኝ። በኢየሱስ ስም አሜን። ✍ አገልጋይ ብርሃኑ https://t.me/preac
236
6
የጥቅምት 11 2019 ዓ/ም የረቡዕ አገልግሎት ትውስታዎች፣ ከእናት ቤተክርስቲያን ሳርቤት (3/3)+9
የጥቅምት 11 2019 ዓ/ም የረቡዕ አገልግሎት ትውስታዎች፣ ከእናት ቤተክርስቲያን ሳርቤት (3/3)
203
7
ጥቅምት 12 ርዕስ፦ የታማኝነት ዋጋና በረከት የዕለቱ ጥቅስ፦ “ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ፤ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ።” — ዘፍጥረት 39፥6 የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 39:1-20፤ ምሳሌ 28:20፤ ማቴዎስ 25:21 ዮሴፍ ወደ ግብፅ በባርነት ተሸጦ በወረደበት የጲጥፋራ ቤት ታላቅ የታማኝነት ሕይወት አሳይቷል። በባዕድ አገር፣ ማንም የማያውቀውና ቤተሰቡ በሌሉበት ኹኔታ ውስጥ እንኳ ሳይቀር አምላኩንና ጌታውን በቅንነት አገለገለ። ታማኝነቱን ያየው ጲጥፋራ ከሚበላው እንጀራ በቀር እስካያስብ ድረስ በቤቱና በንብረቱ ኹሉ ላይ ሙሉ ኃላፊነት ሰጥቶ ሾመው። የዮሴፍ ታማኝነት የጸናው በሥራው ላይ ብቻ አልነበረም፤ የጲጥፋራ ሚስት በኃጢአት ልታታልለውና ልታስተው በሞከረች ጊዜ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ይኽን ታላቅ ኃጢአት አደርጋለሁ? በእግዚአብሔርም ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?” በማለት ለጌታውና ለእግዚአብሔር ያለው ታማኝነት የማይናወጥ መኾኑን አሳዬ። ታማኝነት የእግዚአብሔር ታላቅ ባሕርይ ነው፤ እግዚአብሔር በቃሉና በአሠራሩ ኹሉ የታመነ አምላክ ነው። እኛም የእርሱ ልጆች እንደ መኾናችን መጠን በሥራ ቦታችን፣ በቤታችን፣ በትዳራችንና በምናቀርበው አገልግሎት ኹሉ ታማኞች ልንኾን ይገባል። ታማኝነት አጭር መንገድ ወይም ጊዜያዊ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የሚተውት ሳይኾን፣ የክርስቲያናዊ ሕይወታችን መለያ ሊኾን የሚገባው የጽድቅ ፍሬ ነው። በሰው ዘንድ ለመወደድ ብለን ሳይኾን፣ ማንም በማያየን ስውር ቦታ እንኳ ሳይቀር በቅንነትና በታማኝነት ስንመላለስ እግዚአብሔር ያየናል፤ የታመነ ሰውንም በጊዜው ያከብረዋል፣ ዋጋውንም ይከፍለዋል። ታማኝ እንኹን። 😇 የጥሞና ጥያቄ፦ በሥራዬ፣ በአገልግሎቴ ወይም በግል ሕይወቴ ማንም በማያያየኝ ቦታ ላይ እንኳ ለቃሌና ለኃላፊነቴ ታማኝ ነኝን? የዮሴፍን ዓይነት የታማኝነት ሕይወት በመከተል፣ በሥራ ቦታዬና በየዕለት እንቅስቃሴዬ ኹሉ የእግዚአብሔርን ስም የሚያስከብር ታማኝነትን ለማሳየት ዛሬ ለመወሰን ምን ያኽል ቁርጠኛ ነኝ? 🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦ ታማኝና ጻድቅ አምላኬ ኾይ፣ በሕይወቴና በአገልግሎቴ ኹሉ እንደ አንተ ታማኝ ሆኜ እንድመላለስ እርዳኝ። ሰው ቢያየኝም ባያየኝም፣ በማንኛውም ኹኔታ ውስጥ ለአንተና ለቃልህ ታማኝ እንድኾን የልብ ቅንነትንና መንፈሳዊ ጥንካሬን ስጠኝ። በትንሹና በትልቁ የታመነ አገልጋይ አድርገህ እንድታቆመኝ በኢየሱስ ስም እለምንኻለሁ። አሜን። ✍ አገልጋይ ብርሃኑ https://t.me/preac
249
8
🔥 መንፈሳዊ ዕድገት 🔥 የትምህርት እና የአምልኮ ጊዜ 📆 ዘወትር ረቡዕ፣ 12:00 ሰአት 📍ዘጸአት እናት ቤተክርስቲያን፣ ሳርቤት ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!! 🙏
🔥 መንፈሳዊ ዕድገት 🔥 የትምህርት እና የአምልኮ ጊዜ 📆 ዘወትር ረቡዕ፣ 12:00 ሰአት 📍ዘጸአት እናት ቤተክርስቲያን፣ ሳርቤት ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!! 🙏
199
9
🔥 መንፈሳዊ ዕድገት 🔥 የትምህርት እና የአምልኮ ጊዜ 📆 ጥቅምት 11፣ 2019 ዓ/ም 12:00 📍ዘጸአት እናት ቤተክርስቲያን፣ ሳርቤት ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!! 🙏
🔥 መንፈሳዊ ዕድገት 🔥 የትምህርት እና የአምልኮ ጊዜ 📆 ጥቅምት 11፣ 2019 ዓ/ም 12:00 📍ዘጸአት እናት ቤተክርስቲያን፣ ሳርቤት ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!! 🙏
182
10
ጥቅምት 11 ርዕስ፦ ኹሉም ነገር ለበጎ ነው የዕለቱ ጥቅስ፦ “እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” — ሮሜ 8:28 የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 45:1-8፤ ዘፍጥረት 50:15-21 የዮሴፍ ሕይወት እግዚአብሔር የመከራን ሰንሰለት ወደ በረከት ድልድይ እንዴት እንደሚለውጠው የሚያሳይ ድንቅ ማሳያ ነው። በዮሴፍ ሕይወት የኾነውና የተከሰተው ነገር ኹሉ አንዱ ከአንዱ ጋር ተያይዞ ለታላቅ በጎ ነገር የተደረገ ነበር። ወንድሞቹ በቅናት ባይሸጡት ኖሮ፣ ግብፅ አይወርድም ነበር፤ ግብፅ ባይወርድ ኖሮ፣ የጲጥፋራ ቤት አይገባም ነበር፤ የጲጥፋራ ቤት ባይገባ ኖሮ፣ የጲጥፋራ ሚስት በሐሰት አታስወንጅለውምና አይታሰርም ነበር፤ ባይታሰር ደግሞ የንጉሡን ጠጅ አሳላፊ በእስር ቤት አያገኘውም ነበር፤ ጠጅ አሳላፊው ባይናገርለትና ባያስታውሰው ደግሞ፣ በፈርዖን ፊት ቀርቦ ሕልሙን አይፈታም፣ ለግብፅም ንጉሥ አይኾንም ነበር። ዮሴፍ ባይነግሥና ባይሾም ኖሮ ደግሞ፣ ቤተሰቡንና መላውን ዓለም ከረሃብ አያድንም ነበር! ሰው ክፉ አሰብኩ ብሎ ሲነሣ፣ እግዚአብሔር ግን ያንን ክፉ ዐሳብ ወደ ታላቅ መልካምነት ይለውጠዋል። ዮሴፍ በኋላ ላይ ለወንድሞቹ “እናንተ ለክፉ አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን... ለበጎ አሰበው” እንዳላቸው፣ በእኛም ሕይወት የሚገጥሙን አላስፈላጊ የሚመስሉ መከራዎች፣ ውድቀቶችና ግፎች ኹሉ በስተጀርባ እግዚአብሔር የሚሠራው ትልቅ መልካም ዓላማ አለ። ዛሬ በሕይወታችሁ የምታልፉበት ፈተና፣ እንግልትና ፍትሕ ማጣት መጨረሻችሁ አይደለም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር ወዳዘጋጀላችሁ የከፍታ ቦታና የበረከት ምዕራፍ የሚያደርሳችሁ የስውር እጁ መንገድ ነው። 😇 የጥሞና ጥያቄ፦ አሁን በሕይወቴ ከባድና አላስፈላጊ ይመስል የሚያስጨንቀኝን ፈተና በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድና እቅድ ስር አድርጌ ለማየት ዝግጁ ነኝን? እግዚአብሔር የመከራዬን ሰንሰለት ተጠቅሞ ለታላቅ መልካምነት እንደሚያበቃኝ አምኜ፣ በማልፍበት ኹኔታ ኹሉ አምላኬን ለማመስገንና በጸጥታ ለመጠበቅ ዛሬ ምን ላደርገው የሚገባኝ ነገር ምንድን ነው? 🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦ ነገርን ኹሉ ለበጎ የምትለውጥ ታማኝ አምላኬ ኾይ፣ በሕይወቴ የሚገጥሙኝን ፈተናዎችና መከራዎች ኹሉ ለበረከቴና ለከፍታዬ መንገድ የምታደርግ አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ። ባልረዳውና መስመሩ ባይገባኝ እንኳ የስውር እጅህን አሠራር አምኜ እንድጸና እምነትንና ትዕግሥትን ስጠኝ። በሕይወቴ ያለው ነገር ኹሉ ለስምህ ክብርና ለሕይወቴ በጎነት እንዲኾን አምናለሁ። በኢየሱስ ስም አሜን። ✍ አገልጋይ ብርሃኑ https://t.me/preac
243
11
Dear……………… One day you will be living the life, you prayed for.
238
12
ዛሬ በነበረን የቆሮንቶስ መልእክት ጥናት መግቢያውን በተወሰነ መልኩ ለማየት ሞክረናል። አንደኛ ቆሮንቶስ ሰፊ ይዘት ካላቸው የጳውሎስ ሦስት መልእክታት አንዱ ነው። የተቀሩት ኹለቱ መልእክታት ሮሜና 2ኛ ቆሮንቶስ ናቸው። አንደኛ ቆሮንቶስ በይዘቱ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ተግባራዊ መመሪያን የያዘ መጽሐፍ ነው። የኤፌሶን መልእክት ዓለም አቀፋዊቷን ቤተክርስቲያን ሲያብራራ፣ አንደኛ ቆሮንቶስ ደግሞ አጥቢያዊ መልኳን ያሳያል። በዓለም አቀፏ ቤተክርስቲያንና በአጥቢያ ቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ልዩነትና አንድነት በዛሬው ጥናታችን ተመልክተናል። በተጨማሪም በዛሬው ጥናታችን፦ 👉 አንዲትን ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የሚያስብሏት መለያ ነጥቦች ምንድን ናቸው? 👉 የጸጋ ስጦታዎች ስለተገለጡብን በጌታ ፊት ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ መኾናችንን ያሳያል ወይ? 👉 እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የየራሱ ፈተናና ተግዳሮት የሚገጥምበት ምክንያቱ 👉 ግጭቶች ሲፈጠሩ በምን መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ እንደሚያስተምር ስለ ቆሮንቶስ መልእክት በጥቂቱ ዐይተናል። ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደን ያየነው ስለ ቆሮንቶስ ከተማ ባህል፣ ሃይማኖት፣ ፍልስፍና፣ ማኅበራዊ ሕይወት፣ ሴቶች፣ ኗሪዎች ወዘተ በተመለከተ ነው። ነገም መግቢያችን ይቀጥላል ጌታ ቢፈቅድ ነገ ጠዋት 12:30 በቲክቶክ Berhanu Jesus ብላቹህ ፈልጋቹ ብትመጡና ብትቀላቀሉን ትጠቀማላችሁ። መልካም ጊዜ! https://t.me/preac
262
13
ጥቅምት 10 ርዕስ፦ የጸጥታና የማስተዋል ሕይወት የዕለቱ ጥቅስ፦ “ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እነርሱም እንደ ገና በብዙ ጠሉት።” — ዘፍጥረት 37፥5 የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 37:5-24፤ ምሳሌ 11:13፤ ምሳሌ 13:3 ዮሴፍ ከእግዚአብሔር የከፍታና የታላቅነትን ራዕይ በሕልም አየ። ነገር ግን በወጣትነት ቅንነቱና ባለማስተዋሉ ሕልሙንና የምኞቱን ከፍታ ለቤተሰቡና ለወንድሞቹ አካፈለ። ይኽንን የከፍታ ሕልም የሰሙት ወንድሞቹ በቅናት ተቃጠሉ፤ ይልቁንም “በእውነት በእኛ ላይ ልትነግሥብን ነውን?” በማለት አብዝተው ጠሉት። ይኽ ቅናት አድጎም ለሞት እስከ ማጨት፣ ውሃ በሌለው ባዶ ጉድጓድ ውስጥ እስከ መጣልና መጨረሻም ለአስማኤላውያን ነጋዴዎች በባርነት እስከ መሸጥ አደረሰው። ዮሴፍ ሕልሙን በጸጥታ ይዞት ቢኾን ኖሮ፣ ያንን ኹሉ የመከራና የእንግልት መንገድ ባልተጓዘ ነበር። ይኽ የታሪክ ክፍል በሕይወታችን ውስጥ በጸጥታና በማስተዋል የመኖርን ታላቅ ጥበብ ያሳየናል። እግዚአብሔር በሕይወታችን የሰጠንን ራዕይ፣ የሥራ አቅድ፣ ወይም የመጪው ዘመን ስኬት ለምናገኘው ሰው ኹሉ ማውራት አይገባንም። ኹሉም ሰው በአንተ ስኬትና ዕድገት ደስተኛ አይኾንም፤ አንዳንዶች በቅናትና በተንኮል ተነሥተው ራዕይህን ለማክሸፍና መንገድህን ለማደናቀፍ ይሞክራሉ። ጥበበኛ ሰው የሚሠራውን ሥራ፣ የምኞቱን ከፍታና የእግዚአብሔርን ተስፋ በልቡ ይዞ በጸጥታ ይተጋል። ስኬትህና ፍሬህ ራሱ ጮክ ብሎ እንዲናገር እንጂ፣ አስቀድመህ የምታወራው ወሬ ጠላትን አብዝቶ ለፈተና ያጋልጥሃል። 😇 የጥሞና ጥያቄ፦ በሕይወቴ፣ በሥራዬ ወይም በምስጢራዊ እቅዴ ላይ ያለ ማስተዋል አስቀድሜ ለሰዎች በመናገሬ ምክንያት የገጠመኝ ፈተና ወይም እንቅፋት ነበርን? እግዚአብሔር የሰጠኝን ራዕይና እቅድ በጸጥታ፣ በጥበብና በማስተዋል ይዤ በሥራ ላይ ብቻ ለመትጋት ዛሬ ምን ላድርግ? 🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦ በጥበብና በማስተዋል የምትመራኝ አምላኬ ኾይ፣ አንተ በልቤ ያስቀመጥከውን ራዕይና ተስፋ በጥበብ እንድይዝ የማስተዋልን መንፈስ ስጠኝ። አንደበቴን እንድገታ፣ አቅዴንና ሥራዬን በጸጥታና በትጋት እንድከውን እርዳኝ። ከሰው ቅናትና አላስፈላጊ ጠብ እንድጠበቅ፣ ውጤቴና ፍሬዬ ለስምህ ክብር እንዲበቃ ጥበቃህ አይለየኝ። በኢየሱስ ስም አሜን። ✍ አገልጋይ ብርሃኑ https://t.me/preac
252
14
ሰላም ቅዱሳን ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ከነገ ጀምሮ አንደኛ ቆሮንቶስን መጽሐፍ ማጥናት ልንጀምር ነው። በምን፦ በቲክቶክ Live ሰዓት፦ ጠዋት 12:30-2:00 ርዕስ፦ 1ኛ ቆሮንቶስ፦ «የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተግባራዊ መመሪያ» if U are interested pls join us https://www.tiktok.com/@berhanu_jesus1?_r=1&_t=ZS-9AgWAD0dRXY
262
15
Be kind. Every person survives and struggles something they never speak about.
243
16
ጥቅምት 9 ርዕስ፦ የተሳሳተ የልጅ አስተዳደግ የዕለቱ ጥቅስ፦ “እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ኹሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፤ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት። ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ኹሉ ይልቅ እንዲወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም።” ዘፍጥረት 37:3-4 የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 37:1-11፤ ኤፌሶን 6:4 ያዕቆብ በራሱ ያደገበት ቤተሰብ ውስጥ የአድልዎና የልዩነት ፍቅር ያስከተለውን መራራ ፍሬ (በእርሱና በወንድሙ በዔሳው መካከል የኾነውን ጥላቻ) በሚገባ ያውቃል፤ ነገር ግን በሚያሳዝን ኹኔታ ከወላጆቹ ስሕተት ሳይማር ቀረ። ያዕቆብ በሽምግልናው ዘመን የወለደውን ዮሴፍን ከሌሎች ልጆቹ አብልጦ በመውደድና የተለየ የኅብረ ቀለም ልብስ በማልበስ የወላጅነት አድልዎ ፈጸመ። ይኽ የተለየ ፍቅር በወንድማማቾች መካከል ጽኑ ቅናትንና ጥላቻን ዘራ፤ መጨረሻውም ወንድማማቾቹ ዮሴፍን እስከ መሸጥና አባታቸውን በሐዘን እስከ መስበር ያደረሰ አደጋን አስከተለ። ይኽ ታሪክ ዛሬ ለወላጆችና ወደፊት ወላጅ ለመኾን ለሚዘጋጁ ኹሉ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው፤ በልጆች መካከል የሚደረግ ልዩነት፣ አድልዎና የተለየ ትኩረት በወንድማማቾች መካከል የቅናትና የጠብ ዘርን ይዘራል። ሳናስተውለው የወላጆቻችንን የአስተዳደግ ስሕተት ልንደግም ስለምንችል፣ በንቃትና በማስተዋል ኾነን ልንጠነቀቅ ይገባል። እያንዳንዱ ልጅ በባህሪው፣ በስጦታውና በዕድሜው የተለያየ ቢኾንም፣ የእኛ ፍቅር፣ ትኩረትና እንክብካቤ ግን ለኹሉም በእኩልነት ሊደርስ ይገባል። ልጆችን በእኩል ፍቅር፣ በፍጹም ቅንነትና በአንድነት መንፈስ ማሳደግ በቤታችን ውስጥ ሰላምንና እውነተኛ ወንድማማችነትን ይገነባል። 😇 የጥሞና ጥያቄ፦ በቤተሰቤ ወይም ባለኝ ኃላፊነት ውስጥ ሳላስበው የአድልዎና የልዩነት ስሜት የማሳይበት ኹኔታ አለ? ከቀደሙ ስሕተቶች በመማር፣ ልጆችንና በሥራዬ ያሉትን ኹሉ በእኩል ፍቅርና ትኩረት ለማስተናገድና በቤቴ የሰላም አየር እንዲነግሥ ለማድረግ ዛሬ ምን ላደርግ ይገባኛል? 🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦ ቅዱስና ጻድቅ አምላኬ ኾይ፣ በቤቴና በቤተሰቤ ውስጥ ያለ ምንም አድልዎ በፍቅርና በእኩልነት እንድመራ የመንፈስ ቅዱስን ጥበብና አስተዋይነት ስጠኝ። የቀደሙ ስህተቶችን ሳልደግም ልጆቼንና በዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ በእኩል ፍቅርና ትኩረት እንድከባከብ እርዳኝ። በቤታችን ውስጥ የወንድማማችነት ፍቅርና ሰላም እንዲበዛ አቅም ኹነኝ። በኢየሱስ ስም አሜን። ✍ አገልጋይ ብርሃኑ https://t.me/preac
306
17
“…ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ ልውደቅ በሰው እጅ ግን አልውደቅ…።” — 1 ዜና 21፥13
281
18
ጥቅምት 8 ርዕስ፦ የፍቅር ኀይል የዕለቱ ጥቅስ፦ “ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ኾነለት።”— ዘፍጥረት 29፥20 የዕለቱ የንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 29:15-30፤ 1 ዮሐንስ 5:1-3፤ ማቴዎስ 22:36-40 ያዕቆብ የሚወዳታን ራሔል ለማግባት ሲል ለላባ ለ14 ዓመታት በጽኑ ድካምና በባርነት ተገዛ። በዚያ ዘመን ያሳለፈው የፀሐይ ሐሩርና የሌሊት ቁር እጅግ ከባድ ቢኾንም፣ ስለ ፍቅሯ ሲል ያ ኹሉ ረጅም ዘመን በርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ኾነለት፤ ጊዜውም እንዴት እንደ ነጎደ አልታወቀውም። ፍቅር ኃያል ነው! ድካምን ወደ ደስታ፣ ረጅሙን ዘመን ደግሞ ወደ ጥቂት ቅፅበት የመለወጥ ታላቅ ጉልበት አለው። ያዕቆብን ያንን ኹሉ ዋጋ ያስከፈለው የሕግ ግዴታ ሳይኾን፣ በልቡ ውስጥ የነበረው ጥልቅ ፍቅር ነበረ። ይኽ የታሪክ ክፍል አምላካችን እግዚአብሔርን የመታዘዝን ታላቅ ምስጢር ያበራልናል። ጌታ ኢየሱስ “ትልቁና ፊተኛው ትእዛዝ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ዐሳብህም ውደድ የሚለው ነው” ብሎ እንደ አስተማረን፣ የእኛም መንፈሳዊ ሕይወት መሠረት ፍቅር ነው። እግዚአብሔርን በእውነት ስንወደው፣ ለእርሱ መገዛትና ትእዛዙን መጠበቅ ከባድ ሸክም አይኾንብንም፤ ይልቁንም በደስታና በፍላጎት የምናደርገው የፍቅር አገልግሎት ይኾናል። ሐዋርያው ዮሐንስ “ትእዛዛቱም ከባድ አይደሉም” ያለው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ፍቅር ሲኖር መታዘዝ ሸክም ሳይኾን ደስታ ይኾናል። ቀጥሎም ባልንጀራችንን እንደ ነፍሳችን እንድንወድ የተሰጠን ትእዛዝ፣ ይኽ የፍቅር ኀይል በሰዎች መካከልም ድል አድራጊና አሸናፊ መኾኑን ያሳየናል። 😇 የጥሞና ጥያቄ፦ የእግዚአብሔርን ቃል ለመጠበቅና ለእርሱ ለመታዘዝ የማደርገው ጥረት በግዴታና በሕግ ስሜት ነው ወይስ በልቤ ውስጥ ባለው በፍጹም ፍቅር? የፍቅርን አሸናፊነትና ኀያልነት በመረዳት፣ ለአምላኬና በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች በፍቅር የተሞላ ታዛዥነትንና አገልግሎትን ለመስጠት ዛሬ ምን ላድርግ? 🙏 ተንሥኡ ለጸሎት፦ ፍቅር የኾነከው ቅዱስ አምላኬ ኾይ፣ ለአንተ ያለኝ ፍቅር በልቤ ውስጥ እንዲበዛና እንዲያድግ የመንፈስ ቅዱስን ቅባት ስጠኝ። ትእዛዛትህን መጠበቅና ለአንተ መገዛት በደስታና በፍቅር የተሞላ እንጂ ከባድ ሸክም እንዳይኾንብኝ ልቤን አድስ። ባልንጀራዬንም እንደ ነፍሴ እንድወድና በሕይወቴ ኹሉ የፍቅርህ አሸናፊነት እንዲገለጥ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም አሜን። ✍ አገልጋይ ብርሃኑ https://t.me/preac
357
19
No text...
301
20
+9
No text...
395