cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Mission Talk with Aman!

Mission Exist because worship doesn't . Mission is the means while worship is ultimate Goal of God. Pastor John piper.

Більше
Рекламні дописи
467
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
+230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ለጫራ የሕዝብ ክፍል እንጸልይ! በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡— መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፡ አላቸው። ማቴዎስ 9፡ 37 - 38 ሰላም  የሚሽን ሞቢላይዜሽን ኢትዮጵያ ቤተሰቦች! ዛሬ አርብ ምሽት ከ3:30 ጀምሮ በቴልግራም ላይቭ ለጫራ የሕዝብ ክፍል በህብረት የምንፀልይበት ጊዜ ስለሚኖረን ከታች ባለዉ የቴሌግራም ቻናል ሊንክ በመግባት አብራችሁን እንድትጸልዩ እንጋብዛችኋለን። https://t.me/MobilizationEthiopia
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ተልእኳችን ማለዳ ሰኔ 14 – 2016 ወንጌል ምንድን ነው ? የመስቀሉ ወንጌል እና የመንግሥቱ ወንጌል ክፍል 5 የመጸሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 1፥14-15 "ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሓ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።" አራተኛ፣ አንድ ሰው መልካም የሚባልን ኑሮ ስለኖረ፣ በጎን ስላደረገ እና የኢየሱስን የኑሮ ተምሳሌት ስለተከተለ ብቻ ክርስቲያን እንደሆነ ልንቆጥረው አይገባም። ማንም ሰው ክርስቲያን ለመሆን፣ የመንግሥቱ በረከቶች ወራሽ ለመሆን ከሁሉ አስቀድሞ በአንዱና ብቸኛው መግቢያ በር መግባት ይኖርበታል። በዚህ በር ማለፍ የሚችለው ኅጢአተኝነቱን ተቀብሎ፣ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሠራው ምትካዊ ሞት አምኖ የኅጢአት ስርየት ሲያገኝ እና ምሕረት ሲደረግለት ብቻ ነው። የመናኝ ጉዞ የተሰኘው የጆን ቡንያን መጽሐፍ ላይ፣ ክርስቲያን በጉዞው ያገኛቸውን አቶ ሥርዐት እና አቶ ግብዝ ልናስታውስ እንችላለን። ክርስቲያን ከእነዚህ ሰዎች ጋር እያወራ ወዲያውኑ የሚረዳው እነዚህ ሰዎች በበሩ ያለፉ ሳይሆን፣ በአጥር ዘለው መግባታቸውን ነው። ዋናው መልእክቱ፦ እነዚህ ሁለት ሰዎች ምንም እንኳን በክርስቲያናዊ መንገዶች እየሄዱ ክርስቲያናዊ ምግባሮችን ቢተገብሩም፣ ክርስቲያኖች አይደሉም። ማንም ሰው የኢየሱስ ተከታይ ነኝ እያለ ወይም የመንግሥቱን ኑሮ እየኖርኩ ነው እያለ፣ በተሰቀለው ክርስቶስ አማካኝነት በሚገኝ ንስሓ እና እምነት የኅጢአት ይቅርታ ሳያገኝ ራሱን ክርስቲያን ብሎ መጥራት አይችልም፣ አይገባውምም። አጥሩን ዘሎ የገባው ሰው ምንም እንኳ ክርስቶስን የሚመስል ሕይወት ቢኖር፣ የመግቢያ በር በሆነው ንስሓ እና እምነት ሳያልፍ ወደ ኢየሱስ ሊመጣ አይችልም። ኅጢአቱን የሚያስተሰርይለት ብቸኛው የክርስቶስ የመስቀል ሥራ ነው። አምስተኛ፣ በዚህ በር አልፈው ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች የእግዚብሔርን መንግሥት ሥራ እየሰሩ እንደሆነ መቁጠር ተገቢ አይደለም። ክርስቲያን ያልሆነ ሰው ለዕርቀ-ሰላም እና ለፍትሕ መሥራቱ በጣም ተገቢ እና አስደሳች ነገር ነው፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሠራ እንደሆነ አድርገን ልንቆጥር አይገባም። በንጉሡ ስም ያልተሠራን ሥራ፣ ለመንግሥቱ እንደተሠራ አድርገን ልንቆጥር አይገባንም። ስድስተኛ፣ የትኛውም ዐይነት መልካም የሆነ የምሕረት እና የፍትሕ ተግባር፣ በአንድ ክርስቲያንም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ሲተገበር ዋነኛ ግቡ ሰዎችን ወደ መግቢያ በሩ መጠቆም ሊሆን ይገባል። ምግባረ ሰናይ ሥራዎችን በመሥራት ብቻ ወንጌልን እንደሰበክን ልናስብ አይገባም። ድሆችን ስንረዳ፣ ለፍትሕ ስንሟገት፣ የተጨቆኑትን ነፃ ስናወጣ፣ ሁልጊዜ የክርስቶስን የመስቀል ላይ ሥራ በመናገር ከኅጢአት ስርየት የሚገኝበትን ብቸኛ በር ልንጠቁማቸው ያስፈልጋል። ያንን ሳናደርግ፣ መልካምን ስለሠራን ብቻ ወንጌልን እንደሰበክን መቁጠር ትክክል አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደምድር የመጣው ክፉ ሰዎችን መልካም ለማድረግ ሳይሆን ሙታንን ወደ ሕይወት ሊያመጣ ነው። ስለዚህ አዎ፣ ክርስቲያን በምድር ሲኖር ክርስቶስን ሊመስል እና መልካምን ሁሉ ሊያደርግ ይገባዋል፤ ነገር ግን ይህንን በማድረጉ ብቻ ደኅንነት የሚገኝበትን ወንጌል እንደሰበከ አድርጎ ራሱን ሊቆጥር አይገባም። ሰባተኛ፣ ከላይ እንደገለጽኩት በዚህ ዘመን ያሉ እጅግ በጣም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት፣ ምንም እንኳ ወንጌሉ አስገራሚ እና አስደናቂ ነው ቢሉም፣ የሚያስደንቀው እና የሚያስገርመው ነገር በርግጥ ምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ስተዋል ብዬ አምናለሁ። ኢየሱስ ንጉሥ መሆኑ እና በምድር ላይ የፍቅር እና የርኅራኄ መንግሥት መመሥረቱ ለአይሁዶች ያን ያህል የሚደንቅ ነገር አልነበረም። ሁሉም አይሁድ አንድ ቀን ያ እንደሚሆን ያውቅ ነበር። ሲጠብቁት የነበረውም ቀን ነበር። እጅግ በጣም አስደናቂው ነገር፣ ይህ መሲሕ (ንጉሥ) ሕዝቡን ለማዳን በመስቀል መሞቱ ነበር። እጅግ በጣም ለማመን የሚከብደው ዜና በትንቢተ ዳንኤል የተገለጸው አምላካዊው የሰው ልጅ፣ በዳዊት የተነገረው መሲሕ፣ በኢሳይያስ የተተነበየው ሥቁይ አገልጋይ፣ ሁሉም አንድ ሰው መሆናቸው ነው! በስተ መጨረሻም፣ የመንግሥቱን ወንጌል እና የመስቀሉን ወንጌል አንድ ላይ የምናስተሳስራቸው በዚህ መልኩ ነው። ኢየሱስ ንጉሥ ብቻ አይደለም፤ የተሰቀለ ንጉሥ ነው። ይህን እውነት ከተመለከትን በኋላ፣ አሁን ላይ የመጡት አብየተ ክርስቲያናት አስደማሚ አድርገው የሚሰብኩት ወንጌል እምብዛም የሚደንቅ እንዳልሆነ እንመለከታለን፤ እንደውም ይሰለቻል። ስምንተኛ፣ እስካሁን ያየነው ሙግት ሁሉ የሚመራን ወደ መስቀሉ ወንጌል አስፈላጊነት ነው። በዚህ ዘመን ያሉት ሁሉም የወንጌል ተልዕኮዎች፣ ምስክርነቶች፣ እና ስብከቶች ትኩረታቸው ሊሆን የሚገባው መግቢያ በር የሆነው መስቀሉ ነው። ምክንያቱም፣ ሌላው የመንግሥቱ ተስፋ እና በረከት በሙሉ በመስቀሉ መግቢያ በኩል ባላለፉ ሰዎች ሊገታ የማይችል ነው! ያለ መስቀሉ መልእክት መልካሙ ዜና ሁሉ ክፉ ዜና ይሆናል። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ከአዲስ ኪዳን ጅማሮ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ የእግዚአብሔር መልእክት ለሰው ልጆች ሁሉ፣ ለዚህም ዘመን ሰዎች ሁሉ፣ “ንስሓ ግቡ፣ በክርስቶስ እመኑ” ነው። በወንጌሉ መልእክት የተሰጠው ትዕዛዝ አንድ ብቻ ነው፦ “ንስሓ ግቡ፣ በክርስቶስ እመኑ!” ሰዎች ሁሉ ለመዳን ሊያደርጉት የሚገባው ዋነኛ ግዴታ ይህ ነውና፤ ዋነኛ መልዕክታችን እና ልመናቸን ይህ ሊሆን ይገባል። በግሬግ ጊልበርት የተጻፈ ከ https://wongelu.com/ ድህረገጽ የተወሰደ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቀን 4 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 ለጫራ ሕዝብ ክፍል በቃሉ ላይ ተደግፈን እንጸልይ! የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏼“ሁሉን የሚችል አምላክም የጫራ ሕዝብ ለብዙዎች ጉባኤ እንዲሆኑ ባርካቸው፥ እንዲያፈሩ፥ እንዲበዙ ይባርካቸው፤”   — ዘፍጥረት 28፥3 👉🏼 በህዝቡ መካከል ታላቅ መንፈሳዊ ጉብኝት እንዲሆን እና  “ጫራዎች ለንስሐ የሚገባ ፍሬ እንዲያፈሩ፤” ማቴዎስ 3፥8 👉🏼አምላክ እግዚአብሔር የጫራ ሕዝብ ይደረሱ ዘንድ መስዕዋት እስከመሆን፣ በመስጠት እና በመጸለይ ለመላክ የሚቆረሱ ክርስትያኖችን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ፥ የኢየሱስንም ትምህርት ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማሯቸው ደቀ መዛሙርት የሚደርጉትን እንዲልክ እንማልድ! — ማቴዎስ 28፥19
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ተልእኳችን ማለዳ ሰኔ 13 – 2016 ወንጌል ምንድን ነው ? የመስቀሉ ወንጌል እና የመንግሥቱ ወንጌል ክፍል 4 የመጸሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሐዋሪያት ሥራ 13፥32-34 "እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምሥራቹን ለእናንተ እንሰብካለን… እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል።" የመንግሥቱ ወንጌል እና የመስቀሉ ወንጌል እንዴት ነው የሚገናኙት? የመንግሥቱ ወንጌል ሰፊ በመሆኑ፣ ሁልጊዜ በውስጡ የመስቀሉን ወንጌል እንደሚያጠቃልል አስቀድሜ አቅርቤ ነበር። አሁን ደግሞ በተለየ አትኩሮት መጠየቅ የምፈልገው የመስቀሉ ወንጌል የሚባለው የመንግሥቱ ወንጌል አካል ብቻ ነው ወይስ ከዚያ ያለፈ ትርጉም አለው? በመንግሥቱ ወንጌል ውስጥ ያለው የመስቀሉ ወንጌል የትኛውን ቦታ ይይዛል? መካከለኛ ነው? ወይስ ዳር ላይ ነው? ወይስ ሌላ ቦታ ይይዛል? ይሄ ከተነሣ ደግሞ፣ የወንጌላት ጸሐፊዎች ወንጌል የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ የሚጠቀሙበት ዐውድ በክርስቶስ በማመን ስለሚገኘው የኅጢአት ስርየት ተስፋ እንጂ፣ በሰፊው የወንጌል ትርጓሜ ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ቃልኪዳኖች የማያጠቃልሉት ለምንድን ነው? ለምሳሌ፣ ለምንድን ነው ጳውሎስ በየትኛውም መልእክቱ ላይ “ወንጌል ማለት ሰዎች እርስ በእርስ ይቅር መባባል የሚችሉበት መልካም ዜና ነው” ሲል የማናገኘው? ለእነዚህ ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ የምናገኘው፣ የመስቀሉ ወንጌል ከሌሎቹ የመንግሥቱ ወንጌል ተስፋዎች መካከል እንደ አንዱ ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ነው። እንደውም፣ የመስቀሉ ወንጌል ወደ መንግሥቱ ወንጌል የምንገባበት ዋናው በር፣ የፏፏቴው ምንጭ፣ እና መነሻው ዘር ነው። ሙሉ አዲስ ኪዳንን ስታነቡ የምታገኙት ተደጋጋሚ ሐሳብ ይህ ነው። ማንም ሰው የመንግሥቱን ወንጌል ተስፋዎች ለማግኘት የሚችልበት ብቸኛ መንገድ በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራ በሚገኘው የኅጢአት ስርየት በማመን ነው። የመስቀሉ በር ወደ መንግሥቱ ቃል ኪዳኖች የመግቢያው ብቸኛው በር ነው። ሌሎቹ የሚፈስሱት ከዚህ ምንጭ ነው። በዚህም ምክንያት የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ወንጌል የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ፣ “ጠባቡን” የወንጌል ትርጉም ብቻ ባማከለ መልኩ መጠቀማቸው ፍጹም ትክክል ነው። የተቀረውን የወንጌሉን በረከቶች ወንጌል ብለው አለመጥራታቸው ረስተው ወይም ተሳስተው እንዳልሆነ መረዳት ይኖርብናል። አንድ ሰው የመንግሥቱን ወንጌል ተስፋዎች ሊያገኝ የሚችለበት ብቸኛው መንገድ የመስቀሉ ወንጌል በመሆኑ የሰዎችን እርስ በርስ መታረቅ፣ የአዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር መምጣት፣ ወዘተ ወንጌል ብለን ልንጠራ አይገባም። በወንጌሉ የምናገኛቸውን በረከቶች ከወንጌሉ መልእክት ለይተን መመልከት ይኖርብናል። ወንጌል ማለት በክርስቶስ የስርየት ሥራ የሚገኘው የኅጢአት ይቅርታ ሲሆን ሌሎቹ በረከቶች ሁሉ ከዚህ ምንጭ የሚቀዱ ናቸው። መደምደሚያ ሐሳቦች እስካሁን ካየናቸው ሐሳቦች የሚወሰዱ አንኳር ነጥቦች አሉ። በመጀመሪያ፣ ወንጌል መስበክ ማለት የእግዚብሔርን መንግሥት መምጣት ብቻ መስበክ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች ተሳስተዋል ማለት እንችላለን። ወንጌሉ የመንግሥቱን መምጣት የሚያበስረን ብቻ አይደለም፤ የመንግሥቱን መምጣት እና ወደዚህ መንግሥት የመግቢያ መንገዱንም የሚነግረን መልእክት ነው። በሁለተኛነት፣ የመስቀሉ ወንጌል ለብቻው ያልተሟላ ወንጌል አይደለም። መስቀሉን ብቻ መስበክ በሆነ መልኩ እንዳልተሟላ ወይም ያላለቀ ግማሽ ወንጌል እንደሆነ እድርጎ መቁጠር ስሕተት ነው። ጥያቄው “ሰው ለመዳን ማመን ያለበት መልእክት ምንድን ነው?” እስከሆነ ድረስ፣ ማመን የሚጠበቅበት ብቸኛ ወንጌል የመስቀሉን ወንጌል ነው። ይህንን ደግሞ ሐዋርያዎቹ ጳውሎስ እና ጴጥሮስ ደጋግመው አስተምረዋል። ኢየሱስ የመስቀሉን ወንጌል በተደጋጋሚ ሲሰብክ እናገኛለን። ማርቆስ 10፥45ን ለምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። ሆኖም “ወንጌል” የሚለውን ቃል በቃል ሲጠቀም ላናገኘው እንችላለን። ምንም እንኳ የቃል ጥናት መሥራት በርካታ ጠቀሜታዎች ቢኖሩትም፣ ወንጌል የሚለው ቃሉ ራሱ የግድ መገኘት አለበት ማለት አይደለም። እንደዛ አጥብቀን ከፈለግን ዮሐንስ በሙሉ መልእክቱ ውስጥ ቃሉን ስላልተጠቀመ ስለወንጌል አልጻፈም ልንል ነው። ሦስተኛ፣ የመንግሥቱን ወንጌል በትክክለኛው የወንጌል መልእክት ላይ እንደ ተጨማሪ ወንጌል መቁጠር ወይም ከትክክለኛው ወንጌል የሚያስት እንደሆነ አድርጎ መቁጠርም ስሕተት ነው። ጥያቄው “የክርስትና እምነት ጠቅላላው መልካሙ ዜና ምንድን ነው?” እስከሆነ ድረስ፣ የመንግሥቱ ወንጌል ተስፋዎች እና በረከቶች ትርፍ ወይም አላስፈላጊ ዝርዝሮች አይደሉም፤ ወንጌሉ ናቸው። ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ፣ እና ጳውሎስም ብለዋልና። በግሬግ ጊልበርት የተጻፈ ከ https://wongelu.com/ ድህረገጽ የተወሰደ ክፍል 5 ይቀጥላል. . .
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቀን 3 ጫራ የሕዝብ ክፍል 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 ባህላዊ እምነቶች ማህበረሰቡ "ከፈጣሪ" ጋር የእምነት ስርዓት የፈጠሩበት የሀይማኖት ክፍል ነው: : በተጨማሪም የተለያዩ የክርስትናብ እምነት ክፍሎችን ይከተላሉ: :  የጸሎት ርዕሶች 🤲🏾 👉🏾በዚህ ምድር ላይ የሰለጠነ ከእግዚአብሄር መንፈስ ውጪ የሆነ ሌላ ነገር ህዝቡን፣ ምድራቸውን፣ ጤናቸውን እና በረከታቸውን ለቆ እንዲወጣ አጥብቀን እንጸልይ!  👉🏾የመብዛዛት ሃይል! አሁን የሚገኙትን የጫራ ቤተ-ክርስስቲያናት በጸጋው እንዲያጠነክሩ እና ደቀመዝሙር የሆኑ አዳዲስ ደቀመዝሙሮችን እንድያፈሩ እንጸልይ! 👉🏾 ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔ ልጁ እንደሆነና  አዳኝነቱ እንዲረዱት በድንቅና በተአምራት፣ ደግሞም በህልምና በራዕይ እንዲገናኛቸው እንጸልይ!
Показати все...
ተልእኳችን ማለዳ ሰኔ 12 – 2016 ወንጌል ምንድን ነው ? ክፍል 3 የመጸሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ ወንጌል 4፡ 17 - 19 "የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።" ሉቃስ 4፥17-19፦ 3. ሉቃስ 4፥17-19፦ "የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።" ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎቱን የጀመረበት የብሉይ ኪዳን ክፍል ይህ ነው። በትንቢተ ኢሳይያስ 61 ላይ የምናገኘው “መልካም ዜና” የሚለው ሐሳብ የሚወክለው የእግዚአብሔር መንግሥት እና አገዛዝ መውረዱን እንደሆነ እንመለከታለን። 4. ሐዋሪያት ሥራ 13፥32-34፦ "እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምሥራቹን ለእናንተ እንሰብካለን… እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል።" ጳውሎስ ያመጣላቸው መልካም ዜና በክርስቶስ በኩል የሚገኝ የኅጢአት ስርየት መሆኑን ቁጥር 38 ላይ ብናነብም፣ ቁጥር 32 ላይ የምሥራቹ ለአባቶች የተሰጠው የተስፋ ቃል እንደሆነም ይናገራል። ከእነዚህ ምንባባት የምንረዳው፣ “ወንጌል” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሁለት መልኩ እንደተቀመጠ ነው። አንደኛው አተረጓጎም ሰፊው አተረጓጎም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጠባቡ አተረጓጎም ነው። በክርስቶስ ሥራ የተገቡልን ቃል ኪዳኖች በሙሉ በሰፊው ውስጥ ይጠቃለላሉ። የኅጢአት ስርየት ብቻ ሳይሆን የሙታን ትንሣኤ፣ ከሰዎች እና ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ፣ መቀደስ፣ መክበር፣ መጪው መንግሥት፣ አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር፣ ወዘተ በሰፊው አተረጓጎም ውስጥ ተካተዋል። በማቴዎስ 4፣ ማርቆስ 1፣ ሉቃስ 4 እና ሐዋሪያት ሥራ 13 ላይ በምናየው የ’ወንጌል’ አጠቃቀም መሠረት፣ ወንጌል ማለት በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራ የተደረገልን እና ያገኘውን፣ እንዲሁም እግዚአብሔር የገባልንን ቃል ኪዳን ሁሉ ያጠቃልላል። ይህንን “ሰፊው የመንግሥቱ ወንጌል ትርጉም” ብለን ልንጠራው እንችላለን። ሌሎች ምንባባት ላይ ደግሞ ቃሉ በጠባቡ (አንድ ነገር ላይ ባነጣጠረ መልኩ) ሲገባ እንመለከታለን። ሐዋርያት ሥራ 10፣ ሙሉ የሮሜ መልእክት፣ 1ኛ ቆሮንጦስ 1 እና 15 ላይ በተቀመጠው መሠረት “ወንጌል” ማለት የኢየሱስ ክርሰቶስ ሞት እና ትንሣኤ፣ በዚያም የሚገኘውን የኅጢአት ስርየት ሲሆን ሰዎችን ሁሉ ወደ ንስሓ እና እምነት የሚጠራ መልካም ዜና ነው። ይህንን ደግሞ “ጠባቡ የመስቀሉ ወንጌል ትርጉም” ብለን እንሰይመው። አሁን ሁለት ነገሮችን ግልጽ እናድርግ። አንደኛ፣ ወንጌልን በሰፊው አተረጓጎሙ ስንወስድ ጠባቡን አተረጓጎም ባጓደለ መልኩ ሊሆን አይገባም። በሌላ አገላለጽ፣ ስለ መንግሥቱ ወንጌል ያለን መረዳት የመስቀሉን ወንጌል ሊያጠቃልል እንጂ ሊዘነጋ አይገባም። ማቴዎስ እና ማርቆስ ወንጌል ላይ ያየናቸውን ሁለት ምሳሌዎች ተመልከቱ። አንዳንዶች እንደሚሉት፣ ኢየሱስ የሚያበሥራቸው የአዲሱን መንግሥት መምጣት ብቻ ሳይሆን ወደ አዲሱ መንግሥት የሚገቡበትንም መንገድ ጭምር ነው። “መንግሥተ ሰማይ ቀርባለች እና ንስሓ ግቡ” በማለት የአዲሲቷን መንግሥት መምጣት እና የመግቢያውን መንገድ በአንድ ላይ እንደሰበከ እንመለከታለን። ይህንን ልዩነት መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው። የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረስ የሚቻልበት ብቸኛ መንገድ ከኅጢአት ንስሓ በመግባት እና በክርስቶስ ጌትነት በማመን መሆኑ ሳይሰበክ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት መምጣትና በዚያ ውስጥ ስላሉት በረከቶች እና ቃል ኪዳኖች መስበክ ወንጌልን መስበክ ሊባል አይችልም። እንዲያውም ከወንጌል የራቀ መልእክት ሲሆን ለአድማጩም ክፉ ዜና ነው። ሰዎች የምትመጣዋ መንግሥት አባላት ሊሆኑ የሚችሉበትን ብቸኛ መንገድ ባለመናገራችን፣ ዜናችን የምሥራችነቱ ቀርቶ መጥፎ ዜና ወይም መርዶ ይሆናል። የመንግሥቱን ወንጌል መስበክ ማለት የእግዚአብሔርን መንግሥት መቅረብ መናገር ብቻ አይደለም። የመንግሥቱ ወንጌልን በተገቢው መንገድ ሰብከናል የሚባለው፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መቅረብ ስናበስር እና ሰዎች ሊገቡበት የሚችሉበት ብቸኛ መንገድ በክርስቶስ በማመን በሚገኝ የኅጢአት ይቅርታ እንደሆነ ስናስረዳ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ማስተዋል ያለብን እውነታ አለ። ይህም ቀደም ብለን ጠባቡ ብለን ያስቀመጥነውን የወንጌል ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ “ወንጌል” ብሎ እንደሚጠራው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱንም አተረጓጎሞች ወንጌል ብሎ ይጠራቸዋል። አንዳንድ ሰዎች፣ “ወንጌልን ሙሉ በሙሉ ለመስበክ የወንጌሉን በረከቶች፣ ተስፋዎች እና የእግዚአብሔርን ዓለምን የማደስ ዓላማ አብረን መስበክ አለብን፤ ካልሆነ ወንጌሉ አልተሰበከም” ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ይህ ትክክል አይደለም። ከላይ የተመለከትናቸውን ሁለት ሐዋርያት፣ ማለትም ጴጥሮስ እና ጳውሎስን ብቻ እንኳ ብንመለከት፣ በክርስቶስ ምትካዊ ሞት እና ትንሣኤ በኩል የሚገኘውን የኅጢአት ስርየት እና ይቅርታ ብቻ ከሰበኩ ሙሉ ወንጌሉን እንደሰበኩ ይቆጥሩ ነበር። ታዲያ አዲስ ኪዳናችን “ወንጌል” የሚለውን ቃል በሁለቱም ማለትም ሰፊ እና ጠባብ አተረጓጎም ከተጠቀመ፣ በእነዚህ ሁለት ትርጉሞች መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት እንረዳ? የመስቀሉ ወንጌል እና የመንግሥቱ ወንጌል እንዴት ነው የሚገናኙት? ይህንን ጥያቄ መመለስ ከቻልን፣ በመቀጠል የሚነሡ ወሳኝ ጥያቄዎችን መመለስ እንችላለን። በግሬግ ጊልበርት የተጻፈ ከ https://wongelu.com/ ድህረገጽ የተወሰደ ክፍል 4 ይቀጥላል. . .
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቀን 2 ጫራ የሕዝብ ክፍል 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 አብዛኛው የጫራ ማህበረሰብ በእርሻ ስራ የሚተዳደሩ ናቸው: : በወንጌል ተልእኮ ከመደረስ አንጻር በመካከላቸውም በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ ጥቂት ክርስታያኖች እንዳሉ መረጃዎች አሉ፤ ሆኖም አብዛኛው ህዝብ አሁንም የኢሱስን ክርስቶስ የቤዥዎት ስራ ለመስማት እየጠበቀ ይገኛል። የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏾 እግዚአብሔርን ስለዚህ ህዝብ፣ በሚሰሩት ስራ በበረከቱ እንዲጎበኛቸው ጥበቃው እንዲሆንላቸው እንጸልይ! 👉🏾ለጫራ ሕዝብ በራሳቸው ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን የመተርጎም ስራ ተጀምሯል፣ በዚህ ስራ የተጠመዱ ባለሙያዎች እና አገልጋዮችን በመንፈስ ቅዱስ እንዲረዳቸውና በሃይሉ እንዲሸፍናቸው እንጸልይ! 👉🏾 በዚህ ህዝብ መካከል ጥቂት ክርስትያኖች እንደሚኖሩ ይታወቃል፤ አማኞች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ፥ ከኢየሱስ ጋር ባላቸው ግንኙነት እንዲያድጉ እንጸልይ!
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.